#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በሴቶች ብቻ የሚመራ ታሪካዊ በረራ ለ6ኛ ግዜ በአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ከሀገራችን መዲና አዲስ አበባ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ይበራል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በረራው ይካሄዳል...
ዛሬ በሴቶች ብቻ ለሚመራው በረራ የሽኝት ፕሮግራም በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል። ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው በረራ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ይካሄዳል።
መልካም ጉዞ እንመኛለን! #TikvahFamily

ጠ/ሚ ዐቢይ ጂንካ ከተማ ይገኛሉ!
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለህዝባዊ ውይይት ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ከሰዓታት በፊት ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጂንካ ከተማ ሲገቡ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርስቱ የርዳውና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች አንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በመቀጠልም ከአካባቢው የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የክልልና ሌሎች የፌዴራል የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ጂንካ ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትናንትናው ዕለት በኮንታ ልዩ ወረዳ ከኮይሻ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።
#ENA

#UPDATE
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ስታድየም ደርሰዋል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝም በጂንካ ስታዲየም ተገኝተዋል። የአገር ሽማግሌዎች ኘሮግራሙን በምርቃት ጀምረዋል። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስታዲየሙ ለተገኘው ህዝብ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።
#SRTA

TIKVAH-ETHIOPIA
በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት 2ቱ ኢትዮጵያውያን ከየት ተነስተው ወደ UAE እንደገቡ አልታወቀም! በUAE በትናንትናው ዕለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 15 ሰዎች መካከል 2 ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የአገሪቱ ጤና ጥበቃ እና በሽታ መከላከያ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወቃል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳለው ቫይረሱ የተገኘባቸው 15 ሰዎች በሙሉ ከሌላ አገር ወደ UAE የተጓዙ ናቸው። ኢትዮጵያውያኑም ሆነ…
#UPDATE
ሰሞኑን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች [UAE] የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተገኘባቸው ሁለት ኢትዮጵያውን በሀገሪቱ ለሁለት ዓመታት የኖሩ እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ያረጉት ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ እንደሌላቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰሞኑን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች [UAE] የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተገኘባቸው ሁለት ኢትዮጵያውን በሀገሪቱ ለሁለት ዓመታት የኖሩ እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ያረጉት ምንም ዓይነት የጉዞ ታሪክ እንደሌላቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዶክተር ሊያ ታደሰ፦
"የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች [UAE] ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን የኤምሬትስ ነዋሪ ሲሆኑ በዛ ሀገር ለአመታት የኖሩ እና በቅርቡም ጉዞ ያላደረጉ መሆኑን አረጋግጠናል"
#EliasMeseret

#COVID19
ኢትዮጵያዊው የAP ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረትን ጨምሮ 25 የሚሆኑ ከ25 ሀገራት የተውጣጡ ጋዜጠኞች ከነገ ጀምሮ በአሜሪካ 3 ግዛቶች በመገኘት የሀገሪቱን ምርጫን እንዲዘግቡ ፕሮግራም ተይዞ የነበረ ቢሆንም "ለጥንቃቄ" ሲባል ፕሮግራሙ በስድስት ወር እንደተራዘመ ተሰምቷል።

#EthiopianAirlines ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በረራው ይካሄዳል... ዛሬ በሴቶች ብቻ ለሚመራው በረራ የሽኝት ፕሮግራም በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል። ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው በረራ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ይካሄዳል። መልካም ጉዞ እንመኛለን! #TikvahFamily @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደብሊን የተደረገ አቀባበል!
በሴቶች ብቻ የተመራው የበረራ ቡድን ደብሊን ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል። የበረራ ቡድኑ በአሁን ሰዓት ወደ USA ዋሺንግተን ዲሲ በረራውን ቀጥሏል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየርመንገድ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

የኢትዮጵያ መንትዮች ማህበር ምስረታ!
በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ መንትዮች ማህበር ምስረታ በማግኖሊያ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦችን በስፍራው ተገኝተናል፤ ተጨማሪ መረጃዎችንም እንሰጣችኃለን።
#TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአሁን ሰዓት የኢትዮጵያ መንትዮች ማህበር ምስረታ በማግኖሊያ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦችን በስፍራው ተገኝተናል፤ ተጨማሪ መረጃዎችንም እንሰጣችኃለን።
#TikvahFamily
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19
በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በሰሜናዊ ጣሊያን 16 ሚሊየን ሰዎች በልየታ (በኳራንቲን) እንዲቀመጡ መደረጉ ተገለጸ፡፡
ጣሊያን የኮሮረና ቫይረስ ወረርሽኝ በሀገሯ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ በሽታውን ለመቆጣጠርና ስርጭቱን ለመቀነስ የተለያዩ እርምጃዎች በመውሰድ ላይ ትገኛለች፡፡
ለዚህም በሰሜናዊ ጣሊያን16 ሚሊዮን ሰዎችን በ14 አውራጃዎች እስከ ሚያዝያ ወር መጀመሪያ ድረስ ተለይተው እንዲቀመጡ መደረጉ ተገልጿል፡፡
በእነዚህ አካባቢዎች ከአደጋ ጊዜ በስተቀር መውጣትም ሆነ መግባት እንደማይቻል ነው የተገለጸው፡፡ ከዚህ ባለፈም ጂሞችን ፣ የመዋኛ ገንዳዎችን ፣ ሙዚየሞች እና የበረዶ ላይ መዝናኛዎችም ይዘጋሉ ነው የተባለው፡፡
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉዩሴፔ ኮንቴ ÷እነዚህ አይነት እርምጃዎችአንዳንድ ጊዜ ትናንሽ እና አንዳንዴ ደግሞ ትልቅ መስዋትነትን ሊያስከፍሉ ይችላሉ ነገር ግን ለዜጎቻችን ጤና ዋስትና መስጠት እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
#BBC #FBC

የተጋረደው ጀግንነት!
"የተጋረደው ጀግንነት" በሚል ርዕስ በአቶ ውብሸት አማረ የተጻፈው መጽሐፍ ትላንት በዋቤ ሸበሌ ሆቴል ተመርቋል።
መጽሐፉ በዶ/ር ሲሳይ መንግሥቱና በረ/ፕ ሲሳይ አውጋቸው የተገመገመ ሲሆን አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ፓለቲከኞችና ሙሁራን ንግግር አድርገዋል።

ተምኔታዊ ደሴት!
በአብዱልጀሊል ዐሊ ካሳ የተፃፈው 'ተምኔታዊት ደሴት' የተሰኘ መፅሐፍ ዛሬ በአምባሳደር ትያትር አዳራሽ ተመርቋል። ምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ታዋቂ ሰዎች፣ ምሁራን እና በርካታ እንግዶች ተገኝተው ነበር።

የሆቴል ህንፃ ተደርምሶ 4 ሰዎች ሞቱ!
በቻይና የኮሮና ቫይረስ ለይቶ ማከሚያ የነበረ ሆቴል ህንጻ በመደርመሱ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉና 29 ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አለመታወቁ ተነግሯል። ሆቴሉ በትላንትናው ዕለት የተደረመሰ ሲሆን፤ የአደጋው መንስኤ አለመታወቁም ተገልጿል።
ቢቢሲ እንደዘገበው በሆቴሉ ውስጥ ከነበሩት 71 ሰዎች 38ቱን ማውጣት መቻሉን የአገሪቱ አደጋ መከላከል አስተዳደር ሚኒስትር አስታውቋል።
በዘገባው እንደተመለከተው በቻይና ጓንዡ ከተማ የሚገኘው ሆቴሉ የኮሮና ቫይረስ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል ሆኖ ሲያገለግል የቆየ ሲሆን በከተማው 47 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ተመዝግበዋል።
የቻይና የመንግስት መገናኛ ብዙሃን እንዳስታወቀው ሆቴሉ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ህመምተኞች ጋር ቅርብ ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች ላይ ክትትል የሚደረግበት ማዕከል ነበር።
#BBC

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በምዕራብ ኦሮሚያ ወለጋ ዞኖች እየተወሰደ ያለውን እርምጃ አስመልክቶ ትላንት በምክትል ኮሚሽነር ግርማ ገላን መግለጫ ሰጥቶ ነበር።
ዋና ዋና ነጥቦች የነበሩት፦
• መንግስት ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ የተደራጀ የህግ የበላይነት ማስከበርን ያለመ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል።
• የኦነግ ሸኔ አባላት በአካባቢው ላይ በንፁሃን ዜጎች፣ በፖሊስ አባላት እና በውጭ ሀገራት ዜጎች ላይ ግድያ ፈፅመዋል። ከዚህ ባለፈም አባላቱ እያደረሱት ባለው ጥፋት በርካታ ንፁሃን ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።
• በሴቶች ላይ አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ በርከት ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችንም በመፈፀም ላይ ይገኛሉ።
• ፖሊስ እስካሁን እየወሰደ ያለው እርምጃ አባላቱ ከፈፀሙት ድርጊት ጋር ተመጣጣኝ ያልሆነ ዝቅተኛ መሆኑን ነው። አሁን ላይ የህግ የበላይነትን ለማስከበር የክልሉ ፖሊስ ከአካባቢው ህብረተሰብ ፣ ከፌደራል ፖሊስ እና ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን በቅንጅት የተጠናከረ እና የተደራጀ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል።
• የኦነግ ሸኔ አባላትን በሎጀስቲክ እና በሌላ መልኩ ድጋፍ እየደረጉ ያሉ ግለሰቦች እና ቡድኖች መኖራቸውን በመግለፅም እነዚህ አካላትን በተመለከተ ፖሊስ ጥናት እያደረገ መሆኑንና የጥናቱን ውጤት ለህዝብ ይፋ ያደርጋል።
#ኤፍቢሲ

ዛሬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፣ አርቲስት ደበበ እሸቱ፣ ተጋባዥ እንግዶችና የመንትዮች ማህበር አባላት በተገኙበት በማንጎልያ ሆቴል የመንትዮች ማህበር ምስረታ ተካሂዷል፡፡
በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ልጅ ወልዶ ማሳደግ ትልቅ ኃላፊነት ነው መንታ ልጅ ወልዶ ማሳደግ ደግሞ ድርብ ኃላፊነት ነው ያሉ ሲሆን ማህበሩ ሌሎችም እንደ እናንተ ወጤታማ እንዲሆኑ የምታስችሉበት እንደሚሆን ተስፋ አለኝ ሲሉ ገልጸዋል፡፡