TIKVAH-ETHIOPIA
በጣልያን በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 197 መድረሱ ተሰምቷል። ከትላንት በስቲያ ሀሙስ ብቻ በኮሮና ቫይርስ 41 ሰዎች ሞተዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19
በነገራችን ላይ ጣሊያን ውስጥ በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በኮሮና ቫይረስ አማካኝነት የ49 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ መንግስት አሳውቋል፡፡ በጣሊያን በአንድ ቀን ይህን ያልህ ሰው በቫይረሱ ሲሞት ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የሶስት ሰው ህይወት ጠፍቷል! ቦሌ ሞርኒንግ ስታር ሞል በሚገኘው 'እናት ባንክ' የሚሰሩ ጥበቃዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የ3 ሰው ህይወት ማለፉን የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልፀዋል። ፖሊስ የማጣራት ስራ እየሰራ ይገኛል፤ በአካባቢው አምቡላንስ እየተመላለሰም እንደሆነ የቤተሰባችን አባላት አሳውቀዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፦
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሞርኒንግ ስታር ሞል በሚገኘው እናት ባንክ ዶ/ር ጀንበር ተፈራ ቦሌ ቅርንጫፍ ሲሰሩ በነበሩ ሦስት የጥበቃ ሠራተኞች መካከል በተፈጠረ ለጊዜው መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ጸብ የሦስት ሰዎች ህይወት አልፏል።
ዛሬ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓ/ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት አካባቢ በሦስቱ የጥበቃ ሠራተኞች መካከል በተፈጠረው ያለመግባባት አንደኛው የጥበቃ ሠራተኛ በያዘው ክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ሁለት የጥበቃ ጓዶቹን ህይወት አጥፍቶ የራሱንም ህይወት አጥፍቷል፡፡ ሟቾች ዕድሜያቸው ከ30 አስከ 35 ዓመት የሚገመቱ ጎልማሶች ሲሆኑ የጉዳዩን መነሻ እየተጣራ ይገኛል።
በግለሰቦች መካከል ያለመግባባት ሲፈጠር በምክክርና በንግግር ችግሩን ለመፍታት ጥረት ማድረግ የሚገባቸው ሆኖ ከአቅም በላይ ከሆነ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ጉዳዩን ማሳወቅ እንጂ ወንጀል ውስጥ መግባት ተገቢነት የሌለው ተግባር መሆኑን ኮሚሽኑ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡
[Addis Ababa Police Commission]

የኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ ትምህርት እና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ማህበር፦
ለአባል የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በዛሬው እለት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሲሰጥ ውሏል። በዚህም ስልጠና ላይ የማህበሩ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሞላ ፀጋዬ፣ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዶ/ር ኤባ ሚጀና ፣ ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጅንሲ(HERQA) የእውቅናና ፍቃድ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብይ ተገኝተው ስልጠናውን ሲሰጡ ነበር።
በዚህም መሰረት፦
-በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአገር አቀፍ የትምህርት ማሻሻያ ሚና
-እውቅና እና የእውቅና ፍቃድ እንዲሁም የግል ትምህርት ተቋማትን ከማዘመን እና የአጠቃላይ ሀገራዊ አስተዋፅኦውን ከማጠናከር በተሻለ መልኩ ማስኬድ ስለሚቻልባቸው አጠቃላይ ግንዛቤዎች
- ተቋም ተኮር ኦዲትና የባለድርሻ አካላት (የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚ/ር፣ ትምህርት ሚ/ር፣ የአግባብነትና ጥራት ኤጀንሲን ባካተተ መልኩ) ሚና እና በመሳሰሉ ጉዳዮች ሲመክር ነበር።
#TikvahFamily

የነዳጅ ስለፍ...
የነዳጅ ሰልፍ ምን ባህር ዳር እና ሀዋሳ ከተሞች ብቻ እዚሁ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥም አለ፤ ስራ አቁመን ለነዳጅ የምንሰለፍበት ቀን ብዙ ነው ሲሉ የቲክቫህ አ/አ ቤተሰቦች ሪፖርት አድርገዋል።
የአርባ ምንጭ፣ ዲላ ቲክቫህ ቤተሰቦችም ለነዳጅ መሰልፍ እየተደጋገመ መሆኑ አስገንዝበዋል። በዚህም በከፍተኛ ደረጃ የስራ ሰዓታቸውን እየተሻማ እንደሚገኝ አሳውቀዋል።
አንድ የባጃጅ ሹፌር የሆነ የኮምቦልቻ ቤተሰባችን ደግሞ እሱ ባለበት ከተማ ይሄ ነገር በተደጋጋሚ እንደሚከሰት ገልጿል።
'ስሜቱን አውቀዋለሁ ሰልፋ በጣም ስለሚያስጠላኝና የስራ ሰአቴን ስለሚሻማኝ ሌሊት 10:00 ሰአት እንቅልፌን አሸንፌ እነሳለሁ ነዳጅ ለመቅዳት፤ እሚገርመው ነገር ግን በዚያ ሌሊት ሄጄ እንኳን ሰልፉ እንዳለ ነው እና ይሄ ነገር መፍትሄ ቢሰጠው ባይ ነኝ' ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

#ET302 መጋቢት 1/2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737-800 ማክስ አውሮፕላን ተከስክሶ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች የፊታችን ማክሰኞ እዚሁ ሀገራችን ላይ በሚደረግ የመታሰቢያ መርሐ-ግብር ለመታደም ይሰባሰባሉ ተብሏል። #EsheteBekele @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
ከአንድ ዓመት በፊት የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን አደጋ ምክንያት የአውሮፕላኑ የዲዛይን ችግር እንደሆነ መርማሪዎች ለአሜሪካ መንግሥት መስሪያ ቤቶች ያዘጋጁት የአደጋው ረቂቅ ሪፖርት አመለከተ።
ሮይተርስ እንደዘገበው የአሜሪካ ብሔራዊ የትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ በረቂቅ ሪፖርቱ ላይ ቅሬታ ወይም እንዲለወጥ የሚያቀርበው ሃሳብ ካለው ዕድል እንደተሰጠው፤ ሪፖርቱ ይፋ ስላልተደረገ ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ ሰዎች ተናግረዋል።
የቦርዱ ቃል አቀባይ ኤሪክ ዌይስ ጊዜያዊው ረቂቅ ሪፖርትን እንደተቀበሉ ቢገልጹም ድርጅታቸው ለውጥ እንዲደረግ ይጠቅ እንደሆነ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። ቦይንግ ሪፖርቱን በተመለከተ ምላሹ ምን እንደሆነ በሮይተርስ ቢጠየቅም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።
ረቂቅ ሪፖርቱን ቀድሞ ይፋ ያደረገው ብሉምበርግ ኒውስ እንዳለው የሪፖርቱ ማጠቃለያ ስለኢትዮጵያ አየር መንገድም ሆነ የበረራ ሰራተኞቹ አሰራርን በተመለከተ ውስን ወይም ምንም ነገር ባለማለቱ በምርመራው ላይ በተሳተፉ አንዳንድ ሰዎች ዘንድ ጥያቄን አስነስቷል።
ምንጭ፦ BBC

የ2 ሰው ህይወት የቀጠፈው የነቀምቴው እሳት አደጋ!
በነቀምቴ ከተማ በኬጀሞ በተባለ መንደር ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተከስቶ በነበረ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሌሎች ሁለት ሰዎች ደግሞ ከባድ የቃጠሎ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ማርቆስ ዋጋሪ ለኤፍ ቢ ሲ ከተናገሩት፦
- የእሳት አደጋው ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ30 ላይ ነው የደረሰው። ፖሊስ የእሳት አደጋው መነሻ ምናልባትም የኤሌከትሪክ መቀጣጠል ሊሆን እንደሚችል መገመቱን እና ነገር ግን በቤት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ቤንዚን ቃጠሎውን አባብሶታል።
- በአደጋው አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ህይወታቸው አልፏል፤ የአካባቢው ነዋሪ እሳቱን ለማጥፋት ባደረገው ርብርብ የሁለት ሰዎችን ህይወት መታደግ ተችሏል። እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በነቀምቴ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ።
ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት

#DrTedrosAdhanom
የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ቫይረስ በሽታ [COVID-19] መስፋፋት “በእጅጉ ያሳስባል” ያሉ ሲሆን ሁሉም ሀገራት ለበሽታው ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
#BBC

ፖላንድ ትላንት ምሽት ብቻ 4 በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ ግለሰቦች በሀገሯ መኖራቸውን አረጋግጣለች። ይህም በፖላንድ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎችን ቁጥር ወደ 6 ከፍ አድርጎታል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦
• ደቡብ አፍሪካ ሁለተኛውን የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ዛሬ ይፋ አድርጋለች።
• ማልታ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ በሀገሯ መኖሩን ይፋ አድርጋለች።
• ትላንት በኔዘርላንድ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሞት ተመዝግቧል።

በጣሊያን የሴሪ አ እግር ኳስ ግጥሚያዎችን ጨምሮ ሁሉም የስፖርት ውድድሮች ለአንድ ወር ያህል ለተመልካች ዝግ ሆነው እንደሚካሄዱ ተገልጿል። በተጨማሪም መንግሥት በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን ይህንን በሽታ ለመግታት ሲል ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለ10 ቀናት እንዲዘጉ አዟል።

#ETHIOPIA
ከአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በተጨማሪ በ30 የየብስ ትራንስፖርት መዳረሻ የድንበር ኬላዎች ላይ በሽታውን [COVID-19] ለመከላከል የሚያስችል የቁጥጥር ሥራ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡
የውጭ ሀገራት ተጓዦች ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡባቸው ይችላሉ በሚባሉ 30 የየብስ ትራንስፖርት መዳረሻዎች እና የድንበር አካባቢዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ የሙቀት ልየታ ቁጥጥር እየተካሄደ ይገኛል። የድንበር ቁጥጥሮቹ በዋነኛነት በክልሎች የሚከናወን ሲሆን፣ በፌደራል ደረጃ የድጋፍ ሥራ እየተከናወነ ነው።
#አዲስዘመን

#COVID19 እንደ GulfNews.com ዘገባ በትላንትናው እለት በUAE 15 አዲስ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ግለሰቦች መገኘታቸውን የአገሪቱ ጤና ጥበቃ እና በሽታ መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል። በቫይረሱ እንደተጠቁ የተነገረላቸው የተለያየ ሀገራት ዜጎች ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል ተብሏል። በአሁን ሰዓት በUAE በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 45 መድረሱም ተገልጿል። …
በኮሮና ቫይረስ የተጠቁት 2ቱ ኢትዮጵያውያን ከየት ተነስተው ወደ UAE እንደገቡ አልታወቀም!
በUAE በትናንትናው ዕለት የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 15 ሰዎች መካከል 2 ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የአገሪቱ ጤና ጥበቃ እና በሽታ መከላከያ ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወቃል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳለው ቫይረሱ የተገኘባቸው 15 ሰዎች በሙሉ ከሌላ አገር ወደ UAE የተጓዙ ናቸው።
ኢትዮጵያውያኑም ሆነ ሌሎች ተሕዋሲው የተገኘባቸው ሰዎች ከየት ተነስተው ወደ አገሪቱ እንደተጓዙ የተባለ ነገር የለም።
የኢትዮጵያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ድዔታ ዶክተር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ መንግስት መረጃው እንደደረሰው አረጋግጠው ከUAE ባለሥልጣናት ጋር ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር ሊያ የኢትዮጵያውያኑን «የምርመራ ውጤቶች፤ ከየት ወደ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እንደተጓዙ እየመረመርን ነው» ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።
#DW #GULFNEWS

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በሴቶች ብቻ የሚመራ ታሪካዊ በረራ ለ6ኛ ግዜ በአለም አቀፍ የሴቶች ቀን ከሀገራችን መዲና አዲስ አበባ ወደ ዋሺንግተን ዲሲ ይበራል።

ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ በረራው ይካሄዳል...
ዛሬ በሴቶች ብቻ ለሚመራው በረራ የሽኝት ፕሮግራም በስካይ ላይት ሆቴል ተካሂዷል። ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው በረራ ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ይካሄዳል።
መልካም ጉዞ እንመኛለን! #TikvahFamily

ጠ/ሚ ዐቢይ ጂንካ ከተማ ይገኛሉ!
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለህዝባዊ ውይይት ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ከሰዓታት በፊት ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጂንካ ከተማ ሲገቡ የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ርስቱ የርዳውና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች አንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በመቀጠልም ከአካባቢው የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የክልልና ሌሎች የፌዴራል የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ጂንካ ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትናንትናው ዕለት በኮንታ ልዩ ወረዳ ከኮይሻ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።
#ENA

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ ስታድየም ደርሰዋል። የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝም በጂንካ ስታዲየም ተገኝተዋል። የአገር ሽማግሌዎች ኘሮግራሙን በምርቃት ጀምረዋል። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስታዲየሙ ለተገኘው ህዝብ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ይጠበቃል።
#SRTA