TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TIKVAHFAMILY #HATRICKSPORT

የሀገር ውስጥ የእግር ኳስ እንቅስቃሴዎችን ፤ ቁጥራዊ መረጃዎችን ፤ የወሩ ምርጥ ሽልማቶችን ባማረ አቀራረብ ወደ እናንተ ቤተሰቦቻችን ለማድረስ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ የሚገኘው ቲክቫህ ስፖርት ከዛሬ ጀምሮ በይፋ ከተባባሪ አጋራችን ሀትሪክ ስፖርት ድህረ-ገፅ ጋር በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰናል።

www.Hatricksport.net

በዚህም መሰረት ያልተሰሙ የሀገር ውስጥ መረጃዎችን ፤ የተጫዋቾች ዝውውሮች ፤ ቁጥራዊ መረጃዎች ፤ ቃለ መጠይቆች እንዲሁም ሌሎች አበይት ጉዳዮች ወደ እናንተ ቤተሰቦቻችን በጋራ የምናደርስ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ኮሮና ቫይስ የቤት እንስሳትን ባለቤት አልባ እያደረገ ነው!

በጎ አድራጊዎች በቻይና በኮሮናቫይስ ምክያት የሚጣሉ የቤት እንስሳትን መሰብሰብ ከአቅማችን በላይ ሆነ እያሉ ነው። በቫይረሱ የተያዙ እና በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሰዎች የቤት እንስሳት በተለይም ውሾች እየተጣሉ ይገኛሉ።

ከዚህ በተጨማሪ ሰዎች ከመኖሪያ ቤታቸው እንዲወጡ ስለማይፈቀድላቸው የእንስሳት ምግብ መግዛት አልቻሉም። በዚህም የቤት እንስሳቱ እየተጣሉ ይገኛሉ። በኮሮና የሞቱ ሰዎች ባለቤት የነበሩ እንስሳትም የሚደርሳቸው እጣ ተመሳሳይ መሆኑ ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ኮሮና ቫይረስ ሶስት ተጫዋቾችን ይዟል !

በጣልያን እግር ኳስ ልይ ትልቅ ጫናን እያሳደረ የሚገኘው ይህ ቫይረስ ሶስት ተጫዋቾች መያዛቸው ይፋ ተደርጓል ::

የሦስተኛ ደረጃ የጣሊያን እግር ኳስ ክለብ የሆነው ፒያኔሱ ክለብ ሶስት ተጫዋቾችን በኮሮና ቫይረስ በሽታ መያዛቸውን በትላንትናው ዕለት አረጋግጠዋል ፡፡

@tikvahethsport @kidusyoftahe @GoitomH
#ATTENTION

በቅርቡ በሰሜን ሜጫ ወረዳ ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ከትናት በስቲያ ጀምሮ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን አቸፈር ወረዳ 8 ቀበሌዎች ማለትም በእስቱሚት፣ በቁንዝላ፣ ለግዲ፣ ጉግ፣ አንበሸን ወንበሪያ እየሱስ እና ቆንገሪ ቀበሌዎች ላይ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል፡፡

መንጋው በስቱሚትና በቁንዝላ ቀበሌዎች ባልደረሱ ሰብሎች ላይ በጓያ እና በአትክልትና ፍራፍሪዎች ላይ ቀላል ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ ሁሉም የወረዳው የህብረተሰብ ክፍል ወደ ሌሎች ቀበሌዎች ከመዛመቱ በፊት ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADWA

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የዐድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን በተመለከተ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላለፉት መልዕክት!

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

አውረስትራሊያ ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ምክንያት ሰው እምደሞተባት አሳውቃለች። ግለሰቡ በዳይመንድ ፕሪንሰስ መርከብ ውስጥ የነበረ የ78 ዓመት አዛውንት ነው ተብሏል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ትላንት በአሜሪካ የሞተው ግለሰብ በ50ዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኝና ሌሎች በሽታዎች ያሉበት ሰው ነው። የአሜሪካ ባለሥልጣናት ሟቹ የቫይረሱ ስጋት ወዳለበት አካባቢ አልተጓዘም ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ የዋሽንግተን አገረ-ገዥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል። ካሊፎርኒያ፣ ኦሬጎን እና ዋሽንግተን ግዛቶች ውስጥ የቫይረሱ ስጋት ያለባቸው ቦታዎች ያልሄዱ ሰዎች የበሽታውን ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ ስጋት አድሯል።

ዋሽንግተን ውስጥ በሚገኝ አንድ የአዛውንቶች መንከባከቢያ ክበብ ሁለት ሰዎች የቫይረሱን ምልክት አሳይተው ወደ ጤና ጣብያ ተወስደዋል። ሌሎች በርካታ የክበቡ አባላት ምርመራ እየተደረገላቸው ነው።

ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት በሰጡት መግለጫ ላይ ምንም እንኳ ቫይረሱ አገራቸው ቢገባም 'የሚያስደነግጥ ነገር የለም' የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ፕሬዝደንት ማይክ ፔንስ ደግሞ ኢራን ላይ ተጥሎ የነበረው የጉዞ እግድ እንደሚቀጥልና ባለፉት 14 ቀናት ኢራንን የጎበኘ ማንኛውም የውጭ ዜጋ ወደ አገራቸው እንደማይገባ አሳውቀዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KFO #OFC #ADAMA

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] በአዳማ ሊያደርግ የነበረው ህዝባዊ ውይይት በፀጥታ ኃይሎች መከልከሉን የአዳማ ቲክቫህ ቤተሰቦች አሳውቀውናል።

ውይይቱ ለምን? በማን? ሊከለከል እንደቻለ ግን የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ቤተሰቦቻችን ተናገረዋል። ውይይቱ ለመካፈል መጥተው የነበሩ የፓርቲው ደጋፊዎች ተቃውሞ ማሰማታቸውም ተገልጾልናል።

PHOTO : SOCIAL MEDIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ADWA124

የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ 124ኛውን የዓድዋ በአል አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ “ከ124 አመታት በፊት በሩቁ፣ በአሻጋሪ ተመልክተው በጨለማ የምንኖር ደካሞች አድርገው ለቆጠሩን በኅብረት፣ በእውቀት ብርሃን የምንኖር ፅኑ መሆናችንን በአድዋ አስተምረናል” ብለዋል።

ዓድዋ የፍቅር ፣ የመተባበር ፣ በጋራ የማደግ፣ የለጋስነት ፣ ጎረቤትን እንደራስ የመውደድ ትምህርት ኢትዮጵያውያን ሁሌም የሚያስተምሩት የእውነት መንገድ መሆኑንም ነው ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የገለፁት።

ም/ከንቲባው “የሀሰት፣ የትዕቢት፣ የመጠቃት ደንገርጋራ መንገድን ኢትዮጵያውያን እንጠላለን፣ ጠልተንም በአድዋ መንገድ እንድንፃረረው ሆነን አድገናል” ማለታቸውን የከንቲባ ፅ/ቤት አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KFO #AWADAY #OFC

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሐረርጌ ዞን አወዳይ ከተማ ላይ ተፈጽሟል ያለውን ኢ ሰብዓዊ ድርጊት የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አጣርቶ ውሳኔ እንዲያስተላልፍበት ኦፌኮ ጠይቋል።

የኦፌኮ ለፓርላማው በጻፈው የአቤቱታ ደብዳቤው የካቲት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ለማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውና ዜጎች እየተቀባበሉ ስለተመለከቱት በአወዳይ ከተማ ማህበረሰብ ላይ የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ሲፈጽሙት የሚታየውን ጭካኔ የተሞላበት ደብደባና ግድያ ጉዳይ እንዲጣራ ነው የጠየቀው፡፡

በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የነበረው የድምጽ ምስል መረጃ በቀላሉ የምንመለከተው አይደለም ያለው ኦፌኮ ድርጊቱም እጅግ አሳዝኖኛል ብሏል፡፡

ከዚህ ቀደም ሐምሌ 30/2008 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ የፀጥታ ሀይሎች በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ሲፈጽሙ ከሚታየው ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን የጠቀሰው ኦፌኮ ም/ቤቱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቋል፡፡

በአወዳይ ከተማ ተፈጽሟል የተባለውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊትም ፓርላማ አስቸኳይ ምርመራ አድርጎ እንዲወያይበትና ውሳኔ እንዲሰጥበት ኦፌኮ ጠይቋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ አድማስ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Mekelle

የስላሴ ጨለቖት ዘውድ ትላንት በመቐለ ራስ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ የተደረገው ደማቅ አቀባበል።

PHOTO : ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቀነኒሳ የሞ ፋራህን የግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰበረ !

በለንደን ከተማ በተካሄደው የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን፤ ቀነኒሳ በቀለ ክብረ-ወሰን በመስበር አሸንፏል።

የ5 ሺህ እና 10 ሺህ ሜትር ውድድሮች የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤቱ ቀነኒሳ በዚህ ውድድር ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው።
1:00:22 በሆነ ሰዓት የገባው ቀነኒሳ፤ በእንግሊዛዊው ሯጭ ሞ ፋራህ የተያዘውን የቫይታሊቲ ቢግ ግማሽ ማራቶን ክብረ-ወሰን ሰብሯል።

ከቀነኒሳ ጋር ይፋጠጣል ተብሎ የተጠበቀው ሞ ፋራህ ከጥቂት ቀናት በፊት በህመም ምክንያት እንዳይማሰተፍ ማሳወቁ አይዘነጋ።

Join @tikvahethsport

@tikvahethsport @tikvahethiopia
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የኢትዮጵያ መንግሥት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን የተመለከተ ሰነድ አዘጋጅቶ ለድርድር እንደሚያቀርብ ሪፖርተር ጋዜጣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ ገለፁልኝ ብሎ ዘግባል።

በአሜሪካ እና በዓለም ባንክ አመቻችነት የግድቡን የውኃ አሞላል እና አለቃቀቅን በተመለከተ ሲደረግ የቆየው ድርድር ውጤት የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዳ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን የአገሪቱን ሉዓላዊነትና ጥቅም የሚያስከብር የድርድር ሰነድ እንዲያዘጋጅ በመንግሥት ታዞ ሰነዱን በማዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ከተደራዳሪ ቡድኑ በተጨማሪ የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የዓለም አቀፍ ሕግ ስምምነት ባለሙያዎች፣ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ ከተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ ዩኒቨርስቲዎች የተወጣጡ ኢትዮጵያዊያን ባለሙያዎች ሰነዱን በማዘጋጀት ሒደት ላይ ሌት ተቀን እየሠሩ እንደሚገኙ ማረጋገጥ ተችሏል።

More https://telegra.ph/reporter-03-01

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ታላቁ የህዳሴ ግድብ የእኔ ነው!

የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ መላው ኢትዮጵያውያን ከጉድለታቸው በመቆጠብ በጥረታቸው እና በላባቸው ዕውን ያደረጉት ነው።

አንድ የሃይማኖት አባት በግድቡ መጀመር ሰሞን ይህን ብለው ነበር፦ “በማህጸን ካለ ሕፃንና በመቃብር ካለ አስክሬን ውጪ” ሁሉም ኢትዮጵያውያን የቆሙለትና የደገፉት ታሪካዊ ፕሮጀክት ነው።

#ኢትዮጵያፕሬስድርጅት
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ወቅታዊ መግለጫ፦

የኢፌዴሪ የሚነስትሮች ምክር ቤት በትላንትና ውሎው አዲስ የቋንቋ ፖሊሲ ማፅደቁን ተናግሯል። በዚህ አዲሱ የቋንቋ ፖሊሲ በአፋን ኦሮሞና ሌሎች ቋንቋዎች የፌደራሉ መንግስት የስራ ቋንቋ መሆን የሚያስችል ነው ተብሎ ተናግሯል። ይህ የቋንቋ አጀንዳ በርካታ ጊዜያት ተነስቶ መልሶ የጠፋ፣ የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ ሲንከባለል ዛሬን ደርሷል። አሁንም ይህ ውሳኔ በስራ ስለሚተረጎበት ሁኔታ የሚታወቅ ነገር የለውም።

ስለሆነም ኦነግ የዚህ ውሳኔ ስራ ላይ መዋል በጥርጣሬ አይን ያያል። ይህ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተረጋገጠው ውሳኔ ስራ ላይ እንዲውል፦

1. ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንዲፀድቅ እንጠይቃለን።

2. የፊንፊኔና ድሬዳዋ በህግ አግባብ፣ በታሪክ እንዲሁም መሬቱ የኦሮሞ ህዝብ ሀብትና የኦሮሚያ አካል ስለሆኑ የነዚህ የሁለቱ የኦሮሚያ ከተሞች ጉዳይ በአስቸኳይ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ፍትሃዊ ውሳኔ እንዲያገኝ እንጠይቃለን።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ItsMyDam #ItsOurDam #GERD

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ ያወጣው መግለጫ፦ https://telegra.ph/NAMA-03-01

ኢዜማ የታላቁ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ፦ https://telegra.ph/EZEMA-03-01

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot