TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#የካቲት11

45ኛው ዓመት ህወሓት የተመሰረተበት የየካቲት 11 በዓል የተለያዩ ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊስት ኃይሎች፣ የፌደራልና የክልል መንግስት አመራሮች፣ ነባር ታጋዮች እና ምራሁራን በተገኙበት የፓናል ውይይት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።

በሌላ መረጃ፦

45 ተኛው ዓመት የትግራይ ህዝብ የትጥቅ ትግል የጀመረበት የካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ ከጎረቤት ሀገር ሱዳን የመጡ እንግዶች ጋር የፓነል ዉይይት ተካሂዷል፡፡

#ትግራይቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ተፈታኞች ኦንላይን ይመዘገባሉ!

ዘንድሮ በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የኦንላይን [online] ምዝገባ ስርአት በመላው አገሪቱ ተግባራዊ እንደሚደረግ የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

የኤጀንሲው የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሽፋ እንዳሉት በ2010 እና 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ በሙከራ ደረጃ ተወስኖ የነበረው የኦንላይን ምዝገባ ስርአት በመላው አገሪቱ ባሉ የፈተና ጣብያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል።

የኦንላይን [online] ምዝገባው ካሁን በፊት ከእንግሊዝ ሲመጣ የነበረውን የምዝገባም ሆነ የመልስ መስጫ ወረቀት እንደሚተካ ገልፀዋል።

ይህንንም ከሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር በትምህርት ቤቶቹ ተግባራዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱ ጠቁመዋል፡፡

አንዳንድ የግብአትም ሆነ የአቅም ማነስ የሚያጋጥማቸው ጣብያዎች ካሉም በነባሩ አሰራር በወረቀት የመመዝገብ ሂደት ሊተገበር እንደሚችልም ከክልሎች ጋር መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

የኦን ላይን [online] ምዝገባውን በትክክል ለማስኬድም ባለፈው ወር ለክልል የፈተና ጉዳይ አስፈፃሚና ለአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመዋል፡፡

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት11

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ /ህወሓት/ 45ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በመቐለ ትግራይ ስታዲየም በመከበር ላይ ይገኛል። ማለዳ ላይ በዓሉን በማስመልከት በሰማዕታት ሀውልት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ነባር ታጋዮች የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

በአሁኑ ሰዓት የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በትግራይ ስታዲየም እየተከበረ ሲሆን፥ የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ነባር ታጋዮች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

#TIGRAYCOMMUNICATION #FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ከስልጤ ዞን ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ለመወያየት ወራቤ ገብተዋል፡፡

ከሁሉም የዞኑ ወረዳዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት ውይይቱ ለማድረግ በቂ ዝግጅት ተደርጓል፡፡

በውይይቱም የልማትና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ትኩረት ያገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#PMOEthiopia #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኋላ ሁለት እግር የሌለው ጥጃ ተወለደ!

በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ጺዮን ሰጓጅ ቀበሌ ክስተቱ የታየው ንብረትነቷ የአቶ አበበ ጌጡ በሆነች ላም ላይ ሲሆን ጥጃው የኋላ ሁለት እግር የሌለው ጎደሎ ሆኖ የተወለደ ሲሆን አቶ አበበም ላሟ ከሁለት ሳምንት በፊት የመቅበጥበጥና የመደበት ስሜት ያዩባትና ስትወልድም በመቸገሯ ምክኒያት እርዳታ አድረገውላት መውለዷን ጠቁመው ጠንካራና የአንድ ወር እድሜ ያለው የሚመስለው ጥጃ በእንዲህ ያለ ሁኔታ በመወለዱ ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፡-Gondar zuria communication
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መኪናችን ተይዞብናል...

ከሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ኮድ 2 ቫን መኪናዎች እየተያዙ እንደሆኑ ተሰምቷል። መኪናቸው ለተያዘባቸው የቤተሰባችን አባላት መካከል ተከታዩን መልዕክት አጋርተዋል፦

"የጉሙሩክ ሰራተኞች አ/አ መካኒሳ ኮሬ አካባቢ ቫኖችን በማስቆም በተሳሳተ ሰነድ የገባ መኪና እንዳለና የኛም መኪና መጣራት እንዳለበት አሳውቀውን ወደ ጉምሩክ 10 የሚሆኑ ቫኖችን ይዘው ሄደዋል። ሆኖም ጉምሩክ ግቢ ውስጥ ከገባን በኃላ መኪናችን እንደማይለቀቅ እና ቫን በኮድ 2 መንዳት እንደማይቻል እና ተጨማሪ ታክስ መክፈል እንዳለብን ነግረውን መኪናችንን ቀምተው መልሰውናል። ታርጋውን የሰጠን መንግስት፣ መኪናውን የሸጠልን የመኪና አስመጪ፤ እኛ በምን ጥፋታችን ነው 700,000 እና ከዛ በላይ አውጥተን የገዛነው መኪና ድጋሚ 700,000 ብር ታክስ ክፈሉ የምንባለው?"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ከአዲስ አበባ...

እጅግ በርካታ የቤተሰባችን አባላት በኮድ 2 ማሽከርከር አትችሉም በሚል መኪናቸው እንደተያዠባቸው የሚገልፁ መልዕክቶችን እያደረሱን ይገኛሉ። አንዳንድ የቤተሰባችን አባላት ይህን ጉዳይ በመስማታቸው ዛሬ መኪና ይዘው እንዳልወጡ ገልፀውልናል። በጉዳዩ ላይ ምላሽ ሰጪ ካለ ምላሹን እንድታነቡት እናደርጋለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መንግስት ንብረታችንን እየነጠቀን ነው...

መኪና የተነጠቀባቸው የቤተሰባችን አባላት፦

"መንግስት የህዝብ ንብረት መንጠቅ ተያይዞታል። ኮድ 2 ኦሮ VAN መኪኖች የሰጠን ኦሮሚያ መንገድ ትራንስፖርት ስህተት ካለበት የሰጠ አካል ነው መጠየቅ ያለበት ህዝብ ያለጥፋቱ እየተገላታ ነው። ኮድ 2 ኦሮ van መኪኖች እየቀሙ ቃሊቲ ግምሩክ መጋዘን እያስቀምጡ ነው እነሱ የሚሉት ኮድ 3 መሆን ነበረባቸው፤ ኮድ 2 የማይፈቀድ ከሆነ መጠየቅ ያለበት የሰጠ አካል የኦሮሚያ መንገድ ትራንስፖርት ነው የአንድ ሀገር ህግ እስከሆነ በመሀል ህዝብ እየተሰቃየ ነው። ኮድ 3 A.A ያላወጣነው የአ.አ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት አላስተናግዳችሁም በማለቱ ነው እንጂ በወቅቱ ጠይቀን ነበር፤ እና ለዚህ ጉዳይ ለኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን መለሰ መሰጠት ያለበት የአ.አ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን ነው"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የራይድ አሽከርካሪ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፦

የራይድ አሽከርካሪዎች የሆኑ የቤተሰባችን አባላት ህጋዊ ሆነን እየሰራን በየአካባቢው እየተደበደብን ነው ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል። በአሁን ሰዓት የራይድ አሽከርካሪ 'ተደብድቦ' የረር አለማየሁ ህንፃ ጋር በርካታ የራይድ አሽከርካሪ ተሰብስቦ ፖሊስና የሚዲያ ሰዎችን እየጠበቀ እንደሆነ ገልፀውልናል ። ህጋዊ ስራ እየሰራን መደብደብ የለብንም፣ ንብረታችን መኪናችንም መሰባበር የለበትም፣ በነፃነት መስራት አልቻልንም፣ ወከባ ይደርስብናል መንግስት ካለ ህግ ያስከብር ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ethiotelecom

"የሞባይል ድምፅ እና ኢንተርኔት የተቋረጠው በቴክኒክ ችግር ነው" - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም ትላንት ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት የሞባይል ድምፅ እና ኢንተርኔት አገልግሎት ከምሽቱ 12:15 ጀምሮ ተቋርጦ እንደነበር ገልጿል።

ትላንት ከምሽቱ 1:10 ጀምሮ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም ከምሽት 4:30 ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ችግሩ ተግቶ አገልግሎቱ መቀጠሉን አሳውቋል። ተቋሙ ደንበኞች ላሳዩት ትዕግስት ምስጋና ያቀረበ ሲሆን ለተፈጠረው እንግልት ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ከሰኞ የካቲት 09 ቀን 2012 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባኤውን እያደረገ ሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በትላንትናው ውሎ 'የኦሮሚያ ቤተክህነት አደራጅ ኮሚቴ' ላይ ውሳኔ ማስተላለፉን ሐራ ዘተዋሕዶ ዘግቧል ውሳኔውም፡-

- ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን፣ አባ ገብረ ማርያም ነጋሳ፣ ዲ/ን ኀይለ ሚካኤል ታደሰ፣ ቄስ በድሳ ፥ ከዛሬ የካቲት 11 ቀን ጀምሮ እስከ ሚቀጥለው የግንቦቱ ምላዓተ ጉባኤ ድረስ በጥፋታቸው ተጸጽተው ከተግባራቸው በይቅርታ እስኪመለሱ ድረስ ሥልጣነ ክህነታቸው እንዲያዝ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ልዩነት በሌለው ድምፅ ወስኗል፤

- “የኦሮሚያ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እናዳራጃለን” በማለት በመዋቅር ላይ መዋቅር በመፍጠራቸው እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ማኅተም አስቀርፀው በመንቀሳቀሳቸው፣ በአገሪቱ ሕግ ይጠየቃሉ፤

- ያስቀረፁት ማኅተም ገቢ እንዲደረግ፤ የከፈቷቸው ጽሕፈት ቤቶች፥ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም የተከፈቱ እና ሕገ ወጥ በመኾናቸው እንዲዘጉ እንዲደረግ ወስኗል፤

- ኢሬቻንና ዋቄፈናን ከኦርቶዶክስ ክርስትና ጋራ ኾነ ብለው እያመሳሰሉ ለሚያደናግሩ፤ ቤተ ክርስቲያንን ያለስሟ ስም እየሰጡ ለሚተቹ እና በቡድኑ ድጋፍ ለታተሙ መጻሕፍት፥ የሊቃውንት ጉባኤ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ ቋንቋዎች መልስ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶሱ አዟል፡፡

#ሐራዘተዋሕዶ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መኪናቸው የተያዘባቸው ባለንብረቶች ቅሬታ፦

መኪናቸውን የተቀሙ ግለሰቦች ዛሬ ምክንትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ በሚገኙበት የከተማው መስተዳደር ደጃፍ ቅሬታ ማሰማታቸውን ፌደል ፖስት ዘግቧል።

ቅሬታ አሰሚ ባለነብረቶች እንደተናገሩት ከሆነ 600 የሚጠጉ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በአዲሰ አበባ እና በደቡብ ክልል በ2 ቁጥር ታርጋ የተሰጣቸው D4D እና ዳማስ መኪኖቻቸው ተይዞባቸዋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጎሙሩክ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የበተነው ሰርኩርላር ደብዳቤ እንደሚያሳየው መኪኖቹ በህዝብ አገልግሎት ሰበብ ገብተው በግል አገልግሎት ሲሰሩ በመገኘታቸው ነው ለግል አገልግሎት በሚቀረጥ የቀረጥ ሂሳብ እንዲከፍሉ እየተገደዱ ያሉት ብሏል።

ምንጭ፦ ፊደል ፖስት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 1,874 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 73,336 በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,874 የደረሰ ሲሆን 73,336 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 12,921 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 2,012 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 75,307

በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,012 የደረሰ ሲሆን 75,307 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 14,942 መድረሳቸውን ተመልክተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia