TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 1,526 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 67,110 በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,526 የደረሰ ሲሆን 67,110 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 8,365 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
- የሟቾች ቁጥር 1,669 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 69,275
በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1,669 የደረሰ ሲሆን 69,275 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 9,695 መድረሳቸውን ተመልክተናል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#የካቲት11
45ኛው ዓመት የየካቲት 11 በዓል በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እመከበሩን ቀጥሏል። ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ተከታትለን እናጋራለን።
[PHOTO : TPLF]

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስራ ጉብኝት ዛሬ ይጠናቀቃል!
- በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውንን ህጋዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
- ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት የጉዞ ሰነድ በማጣት እና በከፋ ችግር ውስጥ ሆነው ከሀገር እንዳይወጡ ለዓመታት ተከልክለው የቆዩ 135 ኢትዮጵያውያንን ከጠይቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውንን ህጋዊ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
- ከሀገሪቱ መንግስት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት የጉዞ ሰነድ በማጣት እና በከፋ ችግር ውስጥ ሆነው ከሀገር እንዳይወጡ ለዓመታት ተከልክለው የቆዩ 135 ኢትዮጵያውያንን ከጠይቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው!
የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች እውነተኛ ፌደራሊዝምን ለመተግበር እየሰራ ያለውን ብልፅግናን እንደገፍላን በማለት ዛሬ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከተለያዩ የከተማዋና አካባቢዋ ቀበሌዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በሰልፉ ላይ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
[ኢቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች እውነተኛ ፌደራሊዝምን ለመተግበር እየሰራ ያለውን ብልፅግናን እንደገፍላን በማለት ዛሬ የድጋፍ ሰልፍ እያካሄዱ ነው። በድጋፍ ሰልፉ ላይ ከተለያዩ የከተማዋና አካባቢዋ ቀበሌዎች የተውጣጡ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል። በሰልፉ ላይ የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
[ኢቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012
ጋዴፓ መድረክን በይፋ ተቀላቀለ!
የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ጋዴፓ/ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ [መድረክ] አባል መሆኑን ይፋ አደረገ፡፡
ጋዴፓ የመድረክ ግንባር አባል መሆኑን ይፋ ያደረገው ትናንት በአርባ ምንጭ ከተማ ባካሔደው አንደኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔው ላይ ነው።
የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ጋዴፓ/ በተሻሻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ መሰረት ህዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ክልላዊ ፓርቲ ሆኖ ህጋዊ ሰውነት አግኝቶ እየሠራ እንደሚገኝ በጉባኤው ተገልጿል።
#ENA

የሞተር አልባ ትራንስፖርት በአዲስ አበባ... የፊታችን እሁድ ወደ ስራ አንደሚገባ የተነገረው ከጀሞ እስከ ለቡ ያለው የብስክሌት ሞተር አልባ ትራንስፖርት መስመር አገልግሎቱ በአዲስ መልክ ከሚጀመርባቸው መንገዶች አንዱ ሲሆን በአስር አመት ውስጥ ሊተገበር ከታሰበው የ100 ኪሎሜትር እቅድ አካል ነው። መንገዱ የተመረጠው በአካባቢው በተከታታይ ‹‹እንደመንገድ ለሰው› ያሉ ከመኪና ነጻ ሁነቶች የተከናወኑበት፣…
#UPDATE
በአዲስ አበባ ከለቡ እስከ ጀሞ 1 የተገነባው የብስክሌት ትራንስፖርት መንገድ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡ ኘሮጀክቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢ/ር እንዳወቅ አብጤ መርቀው ከፍተዋል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከለቡ እስከ ጀሞ 1 የተገነባው የብስክሌት ትራንስፖርት መንገድ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡ ኘሮጀክቱን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢ/ር እንዳወቅ አብጤ መርቀው ከፍተዋል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦፌኮ ሁለተኛ ዙር ስብሰባዎችን በኦሮሚያ ያካሂዳል!
ባለፉት ሁለት ወራት ከሕዝብ ጋር የመተዋወቅ አላማ ያለው ሕዝባዊ ስብሰባ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ሲያደርግ የቆየው ኦፌኮ ፤ የዚህ ቀጣይ የሆነውን ተመሳሳይ ፕሮግራም ወደ ደቡብና ምዕራብ ኦሮሚያ ከቀጣዩ ሳምንት ጀምሮ ያደርጋል ተብሏል፡፡
‹‹እያደረግሁ ያለሁት ሕዝባዊ ስብሰባ እንጂ ፖሊሲዬን የማስተዋወቅ የምርጫ ቅስቀሳ አይደለም›› ያለው ኦፌኮ፤ ብልጽግና ግን የምርጫ ቅስቀሳ እያደረገ ነው ሲል ወቅሷል፡፡
ጠ/ሚኒስትሩ ከአዲስ አበባ ሴቶች ጋር ያደረጉትን ስብሰባ የምርጫ ቅስቀሳ ነው በማለት ለአብነት የጠቀሰው ኦፌኮ፤ በጅማ ከተማ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ አቅዶ ቀደም ብሎ በደብዳቤ ፈቃድ ቢጠይቅም፤ ሕጋዊ መሰረት የሌለው ክልከላ እንዳጋጠመው አስረድቷል፡፡
ይሁን እንጂ በሁለተኛ ዙር ሕዝባዊ ስብሰባ ዘመቻው ኦፌኮ ፣ በጅማ በቀጣይ ሳምንት ተመሳሳይ ሕዝባዊ ስብሰባ ለማድረግ ማቀዱንና ከሕዝቡም ተደጋጋሚ ጥሪ እየቀረበለት መሆኑን የፓርቲው ም/ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ ገልፀዋል፡፡ ቀጣዩ የሕዝባዊ ስብሰባ ዘመቻው ኢሉባቡር፣ ጅማና ወለጋ አካባቢዎችን እንደሚያካልልም ም/ሊቀመንበሩ አስረድተዋል፡፡
[አዲስ አድማስ ጋዜጣ]

#BURAYUU ዛሬ ማምሻውን በቡራዩ በነበረ የሆቴል ምርቃ ላይ የተገኙ ሰዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል ተብሏል። በፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ከተፈፀመባቸው ሰዎች መካከል እውቋ አርቲስት ሀዊ ቀነኒ እና ሌሎች ይገኙበታል። አርቲስት ሀዊ በተፈፀመባት ድብደባ ሆስፒታል ገብታ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ነው። የፀጥታ ኃይሎች ድምፃዊ ደሳለኝ ቤከማ እና አርቲስት ልጅ ያሬድን በቁጥጥር…
#BURAYUU
የቡራዩ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብደላ ጤቤሶ ለFBC የተናገሩት፦
ትናንት [የካቲት 7/2012 ዓ/ም] በከተማዋ የአንድ ሆቴል ምረቃት ላይ የነበረው ግጭት መንስኤ ስነ ስርዓቱን ለማድመቅ የተጋበዙ አርቲስቶች መካከል የዘፈን ምርጫን በተመለከተ የነበረ አለመግባባት ነው።
ያንንም አለመግባባት በመያዝ ምረቃው ተከናውኖ ምሽት ላይ ከውስጥም ከውጭም የነበሩ ልዩነቱን ይዘው ወደ መጣላት እና ግጭት አምርተዋል፤ በዚህም ወቅት በሁለት አርቲስቶች ላይ መጠነኛ ጉዳት ድርሷል።
በሰዓቱም ፖሊስ በስፍራው በመድረስ ግጭቱን በማሰቆም ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ አድርጓል። ጉዳቱን ማን እንዳደረሰ የፖሊስ ቡድን ተዋቅሮ እየመረመረ ነው።
ከዚህ ውጭ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለ ጉዳቱ፣ ሰዎች ታስረዋል እና ፖሊስ ጉዳት አደረሰ ተብሎ የሚወራው ሀሰት መሆኑን እና የታሰረ ሰው እንደሌለ፤ የፖሊስም ሚና ግጭቱን የማስቆም እና ጉዳት እንዳይደርስ የማድረግ ብቻ ነበር። አሁን ላይ ከተማዋ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

በመድረክ ስብስብ ደረጃ በቀጣይ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በትግራይ መቐለ እና አዲግራት ከተሞች እንዲሁም በአዲስ አበባ፣ ሃዋሳ ፣ አርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ ላይ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚካሄዱ ተሰምቷል።
[ADDIS ADMAS, PHOTO : FILE]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመድረክ ስብስብ ደረጃ በቀጣይ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በትግራይ መቐለ እና አዲግራት ከተሞች እንዲሁም በአዲስ አበባ፣ ሃዋሳ ፣ አርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ ላይ ህዝባዊ ስብሰባዎች እንደሚካሄዱ ተሰምቷል።
[ADDIS ADMAS, PHOTO : FILE]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012
በባህር ዳር ከተማ ህዝባዊ ውይይት ያደረጉት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ አመራሮች ትላንት አመሻሹን ጎንደር ከተማ ገብተዋል፤ ጎንደር ሲደርሱም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፤ ከደቂቃዎች በኃላ ከጎንደር ነዋሪዎች ጋር ህዝባዊ ውይይት እንደሚደረግም ሰምተናል።
PHOTO : SINTAYEHU CHEKOL

#ነፃነት_እና_እኩልነት_ፓርቲ
ፓርቲ እና መንግስት ይለዩ!!
ነጻነት እና እኩልነት ፓርቲ ገዥው ፓርቲ ድርጅታዊ ስራዎቹን ከመንግስት መዋቅር ውጪ እንዲያካሂድና ከባለሀብቶች ገንዘብ ለመሰብሰብ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ከመንግስት መዋቅር ውጪ በፓርቲው አደረጃጀት ስር ብቻ እና ብቻ እንዲያካሂድ ጥሪ አቀረበ፡፡
በተመሳሳይ ፓርቲው በፌደራል እና በክልል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከሚሰሩ አባላቱ የሚሰበስበውን የአባልነት መዋጮ ከመንግስት መዋቅር ውጪ በፓርቲው ጽ/ቤቶች እና አደረጃጀት እንዲያከናውን አሳስቧል።
የመንግስት መዋቅርን በመጠቀም የሚደረግ እንቅስቃሴ የፖለቲካ ሜዳውን ያልተስተካከለ የሚያደርግ እና የተፎካካሪ ፓርቲዎችን የፖለቲካ እንቅስቃሴ አሉታዊ በሆነ መንገድ የሚጎዳ መሆኑን አመልክቷል፡፡

ህወሓት የተመሰረተበት 45ኛው ዓመት የካቲት 11 በዓል ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት 08/06/12 ዓ/ም ከተለያዩ የሀገሪቱ ህብረተሰብ ክፍሎችና አደረጃጀቶች የነፃነት ችቦ የተለኮሰባትን ደደቢት መጎብኘታቸውን ህወሓት በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ገልጿል።
በጉብኝቱ የፌደራሊስት ሓይሎች ተወካዮች ፣ የምሁራን ፎረም ፣ የወጣቶች ፎረም ፣ ያገር ሽማግሌዎች፣ እንዲሁም ከ 9 የአገራችን ክልሎች የተውጣጡ የማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም የኢህአዴግ ነባር አመራሮች በድምር ከ300 ሰው በላይ ላይ ተሳትፈዋል።

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል...
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የዲያሊሲስ ሕክምና ማዕከልንና አዲሱን የእናቶችና የሕጻናት ሆስፒታል ጎበኙ፡፡
ሙፍቲ ሐጂ ዑመር የሕክምና ክፍሎችን ተዘዋውረው ያዩ ሲሆን ሕሙማንንም አነጋግረዋል፡፡ በተለይ የገንዘብ ችግር ላለባቸው ለዲያሊሲስ ሕሙማንን ሕብረተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

#Congratulations
በዛሬው ዕለት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 221 የህክምና ዶክተሮችና ስፔሻሊስቶችን አስመርቋል። ከተመራቂዎቹ መካከል 192 የህክምና ዶክተሮች ሲሆኑ 29 ስፔሻሊስት ዶክተሮች ናቸው። ከዛሬዎቹ 221 ተመራቂዎች ውስጥ 22 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውንም ተጠቁሟል።