TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#share #ሼር

በኮሮና በሽታ ሪፖርት ወደ አደረጉ ሀገራት ሄዶ የበሽታውን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቋም ማሳወቅ ወይም ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ሪፖርት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

- 8335 [በነፃ የስልክ መስመር]

- 0118276796 [በመደበኛ የስልክ ቁጥር]

- [email protected]

- [email protected]

[የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ትላንት በፍቅር ያሸንፋል ማህበር ባዘጋጀው መድረክ ላይ ከተገኙ እንግዶች መካከል የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ትብብር (ት.ዴ.ት ) ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሔና የቀድሞ የሰራዊት አባል ብ/ጀ ካሳዬ ጨመዳ አስተያየታቸውን አካፍለውናል፡፡

ዳ/ር አረጋዊ በርሄ፡-

- ሰው ከተፋቀረ ሁሉንም ነገር ሊያሸንፍ ይችላል ካልተፋቀረ ግን እርስ በእርሱ ይጠፋፋል፡፡

- የእናት ሆድ ዥንጉር እንደሆነ ልዩነትም ቢኖር የአንድ እናት ልጆች እስከሆንን ድረስ በኢትዮጽያ ማዕቀፍ ሆነን ያሉብንን ችግሮች በፍቅር መፍታት እንችላለን ካልሆነ ግን እርስ በእርስ ልንጠፋፋ እንችላለን፡፡

ብ/ጀ ካሳዬ ጨመዳ፡-

- አባቶቻች ፍቅርን ያስቀደሙ ናቸው እንኳን ለኢትዮጵያዊ ቀርቶ ለውጪ ሰው አብልተው አጠጥተው መኝታቸውን ለቀው የሚሄዱ ነበሩ፡፡

- ብዙ ሊቃውንቶች አሉን ሙሁራኖች አሉን ጥሩ ተናጋሪዎች አሉን ከሙስሊሙም ከክርስቲያኑም ጥሩ የሃይማኖት አባቶች አሉን በዘመቻ መልክ ወጥተን ህዝባችንን እንስበከው የኢትዮጵያ ህዝብ ፈሩን ካሳየሀው ደግና የዋህ ህዝብ ነው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
• መልአከ ህይወት ቆሞስ አክሊለ ማርያም የአገልግሎት ስፍራቸው በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰንዳፋ በኬ ማርያም መሆኑን ይናገራሉ በምሥራቅ ሐረርጌ የሚገኝ መስጂድንና ቤተ ክርስቲያንንም በእኩል ቆመው ያሳንጻሉ። መልዕክታቸውን እንዲህ አስተላልፈዋል፡-

- ኢትዮጵያዊያን ድሮ የሚያስቡት ሰውን ሰው በመሆኑ ምክንያት ነው፡፡

- አሁን ያለው ነገር እንኳን በተማሩት በእኔ ባልተማርኩት፣ በኔ በታናሹ፣ በኔ በመነኩሴው ዘንድ ያሳስበኛል፡፡

- ከአማራ ክልል ወደ ኦሮሚያ ክልል ለትምህርት ሄደው የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ በጣም ያሳስበኛል፡፡ እኔ ያደኩት አሁንም ያለውት በኦሮሚያ ክልል ነው በእውነት የኦሮሞ ህዝብ ደግ ህዝብ ነው። ይህንን ስራ የሚሰሩት የፓለቲካ ትርፍ ያላቸው ናቸው፡፡

- እኔ በየዕለቱ ቅዱስ ቁርዓን አነባለሁ ቅዱስ ቁርዓን ማንበብ ከጀመርኩ በኀላ ኢትዮጵያ ብዙ እሴት ያላት ሀገር መሆኗን ነው የተረዳውት፡፡

- በአሁን ሰዓት በእምነት መኖር ሳይሆን በእምነት መሸጋገር ያስፈልጋል፡፡

🎧 11 MB [WiFi ተጠቀሙ]

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Vaayirasii Koronaa: Dursanii Ittisuuf Ergaa Fayyadu

#share
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ: አስቀድሞ ለመከላከል ጠቃሚ መልዕክት!

#share #ሼር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
#OLF

በደቡባዊ ኦሮሚያ ዞኖች እና በምዕራብና ቄለም ወለጋ አካባቢዎች የመንግስት ወታደሮች በንጹሃን ዜጎች ላይ ግድያ እየፈጸሙ ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ከሷል።

ሰዎች በጅምላ ይታሰራሉ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣም እየደረሰ ነው የሚለው ግንባሩ ፣ ክስተቱ ሆን ተብሎ በመንግስት እየተፈጸመ ያለ ነውም ብሏል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ይህን ድርጊት እየፈጸሙ ያሉት ወታደሮች የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳያውጅ የተሰማሩ የኮማንድ ፓስት አባላት ሲሆኑ ለአንድ አመት ህዝቡን እያስጨነቁ በመሆኑ ወደ ካምፓቸው እንዲመለሱ መቸየቃቸውን የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።

በዜጎች ላይ ደርሷል ያለውን ጉዳትም ገለልተኛ እና ነጻ አካል እንዲመረምረው በማለት ግንባሩ ጠይቋል። 

[DW]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማሳሰቢያ ፦

ቲክቫህ ኢትዮጵያ [TIKVAH-ETH] ምንም ዓይነት የፌስቡክም ሆነ የትዊተር ገፅ የለውም። በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ስም ተመሳስለው በተከፈቱ ሀሰኛተኛ ገፆች እንዳትደናገሩ። የሚሰራጩት መረጃዎች እኛን የሚወክሉ አይደሉም። ልብ በሉ ቲክቫህ በፌስቡክ እና በትዊተር አይገኝም!

በሌላ በኩል...

- ትክክለኛው የቲክቫህ ስፖርት የቴሌግራም ገፅ ይህ ከ56,000 በላይ የቲክቫህ ቤተሰቦች ያሉበት ነው። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ሆነው የስፖርት ወዳጅ ከሆኑ የተመረጡ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ስፖርታዊ አጫጭር መረጃዎችን በገፁ ላይ ታገኛላችሁ። መቀላቀል ይቻላል፦ https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethsport

#Kidus #Goitom #FirewAsrat #TimotiosBaye
----------- ------------- --------------- ---------
- ትክክለኛው የቲክቫህ መፅሄት ገፅ ይህ ከ119,000 በላይ አባላት ያሉት ነው። በዋናው ቻናል በስፋት የማይዳሰሱ ወይም ተሰባስበው የማይቀመጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የቴክኖሎጂ፣ የስራ ፈጠራ፣ መዝናኛና ሌሎች በርካታ መረጃዎች ማግኘት ያስችላችኃል። መቀላቀል ይቻላል https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tikvahethmagazine
#UPDATE

በቻይና ለትምህርት የሄደ አንድ ካሜሮናዊው ዜጋ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተገለጸ፡፡ የመጀመርያው አፍሪካዊ ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ነው የተገለጸው፡፡

ትምህርቱንበቻይና ዩኒቨርስቲ ዉሃን ከተማ ላይ ይከታተል የነበረው ይህ ተማሪ በበሽታው መያዙን ዩኒቨርስቲው ያወጣውን መግለጫ ቢቢሲ ዋቢ አደርጎ ዘግቧል። ዩኒቨርስቲው ለተማሪው ቤተሰቦች እንዲሁም ለኤምባሲው ማሳወቁንና ህክምናም እየተከታተለ ነው ተብሏል።

በአሁኑ ሰዓት የሰውነት ሙቀቱ እየተስካከለ እንደሆነ፣ የምግብ ፍላጎቱም መመለሱን እንዲሁም በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ዩኒቨርስቲው በመግለጫው አትቷል።

300 የሚሆኑ ካሜሮናውያን በዉሃን ከተማ የሚገኙ ሲሆን የውሃ፣ ምግብና ሌሎችም ቁሳቁሶች እጥረት በመኖሩ የተነሳ መንቀሳቀስ አይችሉም ተብሏል። በውሀን ከተማ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው አፍሪካዊያን ይገኛሉ፡፡

እነዚህ ዜጎች የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ፍጥነት መዛመቱን ተከትሎ ለመንግስቶቻቸው ከቻይና እንደያወጣቸው ቢጠይቁም እስካሁን ምንም መልስ ማግኝት አልቻሉም ተብሏል፡፡

[BBC, ETHIO FM 107.8]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም...

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ወደ ቻይና በሚደረጉ ጉዞዎች ላይ እገዳ መጣል ተገቢ አለመሆኑን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ገለፁ።

በቻይና የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ሀገራት ወደ ሀገሪቱ የሚደረጉ ጉዞዎችን እያገዱ፣ የንግድ ግንኙነቶችን እያቋረጡ እና አየር መንገዶችም ጉዞ እየሰረዙ መሆኑ ይታወቃል። ዋና ዳይሬክተሩ ግን፥ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እንዲህ አይነት ውሳኔ ማሳለፋቸው ተገቢ አይደለም ሲሉ ተችተዋል።

ሁሉም ሀገራት በመረጃ ላይ የተመሰረተ እና ተገቢ የሆነ ውሳኔ እንዲያሳልፉም ጥሪ አቅርበዋል። በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ድንበር መዝጋት ስርጭቱን ከመቆጣጠር ይልቅ ሊያባብሰው ይችላል ብለዋል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች በህገ ወጥ መንገድ ከገቡ ቫይረሱ ሳይታይ ሊሰራጭ እንደሚችል በማንሳት።

የቻይና ባለስልጣናትም የዓለም ጤና ድርጅት ምክረ ሀሳብን በመውሰድ ሌሎች ሀገራት እያሳለፉ ያለውን ውሳኔ ተቃውመዋል። በስዊዘርላንድ ጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤት የቻይና አምባሳደር ሊ ሶንግም፥ ሀገራት እየወሰዱት ያለው እርምጃ የዓለም ጤና ድርጅት ካወጣው ምክረ ሀሳብ ጋር የተቃረነ ነው ሲሉም ወቅሰዋል።

[ኤፍ ቢ ሲ፣ ሮይተርስ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#DESSIE

በደሴ ከተማ አስተዳደር በከተሞች ምግብ ዋስትና እና ሥራ እድል ፈጠራ ፕሮግራም አንድ ሺህ የጎዳና ተዳዳሪዎችን ከጎዳና የማንሳት ስራ መጀመሩን የከተማው ምክትል ከንቲባ አስታውቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

በአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሰጎ እና የሲሌ ወንዝ በመሙላቱ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቆላ ሸሌ፣ ሸሌ ሜላ እና ኤልጎ ቀበሌዎች በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

ጥር 25 ለሊት11 ፡00 በጣለው ዝናብ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ የሰጎ እና ሲሌ ወንዝ በመሙላቱ ቆላ ሸሌ ቤሌ ንኡስ ፣ሸሌ ሜላ እና ኤልጎ ቀበሌዎች ላይ የተፈጥሮ አደጋ ተከስቷል።

በተፈጠረው የጎርፍ አደጋ አብዛኛው ቤቶች በውሀ ተውጠዋል።የቤት ንብረት ወድሟል ፣በማሣ ላይ ያለ ቋሚ ሰብል እና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በዞኑ አስተዳዳረ ተወካይ አቶ ደርሶ በላይ የተመራ የዞንና የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ከፍተኛ አመራሮችም በስፍራው በመገኘት የደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል።

2012 ዓ.ም የሰጎ እና የሲሌ ወንዝ ሞልቶ በአካባቢው ተደጋጋሚ ጉዳት ያደርሳል። የሲሌ ወንዝ ሙላት ገለዳ ቀጠና አንድ እና ጨፌ ላይ ጉዳት አድርሷል። ሰብአዊ እርዳታ በአፋጣኝ በሚደርስበት ዙሪያም እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

[የጋሞ ዞን አስተዳደር]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ...

በአሁኑ ሰዓት 30 አባወራ፣ በቁጥር አንድ እማወራ እንዲሁም በቤተሰብ ደረጃ 170 ወገኖች ሙሉ ለሙሉ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በትምህርት ቤት ተጠልለው ይገኛሉ። በቀጣይም የተፈናቃዮች ቁጥር 510 ሊደርስ ይችላል ተብሏል፡፡

እስካሁን ለተፈናቃዮችም 17 ኩይንታል በቆሎ፣ 60 ሊትር ዘይት እና 3 ኩይንታል ጥራጥሬ በተጨማሪ ድጋፍ ተደርጓል።

በቀጣይ ተፈናቃዮችን በዘላቂነት ለማቋቋም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ በመገንዘብ በተለይ በዞኑ ከፍታማ ቦታዎች እና ለጎርፍ ተጋላጭ በሆኑ አከባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

[ጋሞ ዞን አስተዳደር]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE 254 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የገናሌ ዳዋ ሶስት የውሃ ሀይል ማመንጫ በሚቀጥለው ማክሰኞ እንደሚመረቅ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

9 ዓመታት ለዘለቀውና 451 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የፈሰሰበት የበዳዋ ወንዝ ተፋሰስ ላይ የተገነባው የገናሌ ዳዋ ቁጥር 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ዛሬ ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ተመርቋል።

አጭር መረጃ፦

- የገናሌ ዳዋ ቁጥር 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ የተጀመረው በ2003 ዓ.ም ነበር።

- ፕሮጀክቱ የተከናወነው በቻይናው ጌዙባ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ (CGGC) ነው።

- የኃይል ማመንጫው ሦስት ጀኔነሬተሮች አሉት። እያንዳንዳቸውም 84.7 ሜጋ ዋት በድምሩ 254 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም አላቸው።

[ስታንቴክ፣ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 427 - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ብዛት 20,636 በኮሮና ቫይረስ [nCoV] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 427 ደርሷል፤ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ወደ 20,636 ከፍ ብሏል። @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 20,708 ደርሷል። የሟቾች ቁጥር ጥዋት ከተገለፀው 427 ውጭ እስካሁኗ ደቂቃ በቫይረሱ የሞተ ሰው የለም። 781 ሰዎች ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል ወጥተዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethioiaBot
#UPDATE

በአዲስ አበባ ከተማ የካቲት 1 እና 2 ቀን 2012 ዓ.ም ለሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ 45 የአባል አገሮች መሪዎች እንደሚሳተፉ ማረጋገጫ መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። እስከ ትናንት ድረስ በኀብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ 8 ሺህ 700 ሰዎች ተመዝግበዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኢህአዴግ በተግባር ፈርሷል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢህአዴግን ንብረት አስመልክቶ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ወስኗል፦

1. ብልጽግና እና ህወሃት የኢህአዴግ ንብረትና ሂሳብ የሚያጣራ አጣሪ በጋራ እንዲሰይሙ

2. በኢህአዴግ ስም ያለ ማናቸውም እዳ ተጣርቶ እንዲከፈል

3. ከእዳ ክፍያ ቀሪ የሆነ ሃብት 3/4ተኛው ለብልጽግና ፓርቲ (የሶስቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውህደት በመሆኑ) ¼ተኛ ደግሞ ለህወሃት ድርሻ መሆኑ ታውቆ በዚያ መሰረት ክፍፍል እንዲያጠናቅቁ

4. ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራት በህጉ መሰረት በ6 ወር ውስጥ ለቦርዱ እንዲያሳውቁ ተወስኗል፡፡ ውሳኔው በጽሁፍ የሚደርሳቸው ይሆናል።

More https://telegra.ph/TIKVAH-02-04

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
መፍትሄ ያልተገኘለት የቴፒ ከተማ ችግር... በቴፒ ከተማ ለበርካታ ጊዚያት ካለው የፀጥታ ስጋት ሳቢያ ከተማዋን ከሚዛን ፣ ከጅማና ከማሻ ከተሞች የሚያገናኘው መደበኛ የትራንስፖርት አገልግሎት ከተቋረጠ ወራቶችን አስቆጥረዋል። በከተማው የንግድ እንቅስቃሴ ከተቀዛቀዘ ቆይቷል፤ የነዋሪዎች ደህንነት አደጋ ላይ ከወደቀ ቆይቷል፣ አገልግሎት ሰጪዎች ስራ መስራት አልቻሉም፣ በከተማ ውስጥ የሚደረግ እንቅስቃሴ ስጋት…
#ATTENTION

ላለፉት በርካታት ሳምንታት ከመደበኛ በእንቅስቃሴዋ ተገታ የቆየችው ቴፒ ከተማ በዛሬው ዕለት ወደ እንቅስቃሴ የመመለስ አዝማሚያ አሳይታ ነበር።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቴፒ ቤተሰቦች እንደተናገሩት ከሆነ ዛሬ ከቀኑ 10:00 ገደማ በተፈጠረ አለመረጋጋት በከተማይቱ የሰው ህይወት አልፏል፤ በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። በሰው ህይወት ላይ ጉዳት የደረሰው በፀጥታ አስከባሪዎች በተኮሱት ጥይቶች እንደሆነም ነው የገለፁልን።

በሌላ በኩል ዛሬ በከተማይቱ በተፈጠረው አለመረጋጋት በፀጥታ አስከባሪዎች ላይም ጉዳት እንደደረሰ ተገልጾልናል። ዝርዝር መረጃዎች እያጣራን ሲሆን በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

ዛሬም በቴፒ ከተማ የሰዎች ደም መፍሰስ አላቆመም፤ የነዋሪዎች፣ የተጎጂ ቤተሰቦች ሀዘን አላቆመም፤ ከተማይቱ ዘላቂ መፍትሄ ሳይፈለግላት፤ ሰላሟም ሳይመለስ ዓመታት አልፈዋል። ነዋሪዎቹ አሁንም የከተማውን ጉዳይ መፍታት የሚችል አካል ካለ እንዲፈታ የዜጎች ስቃይም እንዲያበቃ እየጠየቁ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

ቻይና በአገሯ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊንን ከኮሮና ቫይረስ [nCoV] ለመጠበቅ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን አስታወቀች። አገሪቱ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር ሙሉ አቅም እንዳላትም አስታውቃለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር ረዳት ሚኒስትር ከሆኑት ቼን ሽያዶነግ በአዲስ አበባ ተወያይተዋል።

[ETHIO FM 107.8]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በሚዲያዎች የተረሳችው ቴፒ፤ ዛሬም መፍትሄ ትሻለች...

ማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ዋና ዋና የመገናኛ ብዙሃን የዘነጓት ቴፒ ከተማ ዛሬም መረጋጋት ተስኗት የሰው ህይወት እየጠፋባት ነው። የሀገር ጉዳይ የሚያሳስበው ሰው፤ የዜጎች ስቃይ እንዲቆም የሚጠይቅ ሰው፤ በአንዱ አካባቢ የሚፈጠርን ችግር ብቻ ሳይሆን የሌላውን ወገኖቹን ድምፅ ሊያሰማ ይገባል።

የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬም ከችግር ውስጥ ሊወጡ አልቻሉም፤ ከተማይቱ መፍትሄ አልተገኘላትም፤ ነገሮች በየጊዜው መልካቸው እየቀያየሩ የዜጎችን ህይወት እየቀጠፉ ነው። የማህበራዊ ሚዲያዎች ፣ የዋና ዋና መገናኛ ብዙሃን አሳፋሪ ዝምታ፤ በአንድ ሀገር እየተኖረ ይህን ያህል የአያገባኝም ስሜት መኖሩ እጅግ የሚያሳዝን ነው።

መንግስት ሰላም ያምጣልን! ስቃይ፣ የተኩስ እሩምታ፣ መሳቀቅ ሰለቸን፤ ደከመን፤ መቼ ነው ሰርተን የምናድገው? መቼ ነው ልጆቻችን በሰላም የምናሳድገው? መቼ ነው ከዚህ መከራ የምንወጣው?? መንግስት ብቻ ሳይሆን በየዕለቱ አጀንዳዎች ሲፈጠሩ የሚያሰራጩና የሚያራግቡ የማህበራዊ ሚዲያዎችም ጭምር እንደ ዜጋ አልቆጠሩንም ይህ አሳዛኝ ነው። የሚዲያዎች ወገንተኝነት የሚያሳዝን ነው።

እየመረጡ ማዘን፣እየመረጡ መጮህ፣እየመረጡ ማልቀስ፣ እየመረጡ ስለሰብዓዊነት መለፈፍ፣ ህዝብ እወዳለሁ እያሉ ማስመሰል፣ የሰው ልጅ ህይወት ያሳስበኛል እያሉ በሀሰት መሸንገል፣ የኔ ወገን ካልሆን ምን አገባኝ የሚል አመለካከት እጅግ የሚያስተዛዝብ ነው፤የአንድ ሀገር ዜጎች ሆነን ይህን የለየለት ቸልተኝነትና ወገንተኝነት ማየት ልብ ይሰብራል።

- ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን
- ለዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች
- ለሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች

[የቲክቫህ ቤተሰቦች ከቴፒ ከተማ]

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ATTENTION

- 22 ማዞሪያ እና ቀበሌ 24 አካባቢ የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ከለሊት 6:00 ጀምሮ እየሰሙት ባለው ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እረፍት ማድረግ እንዳልቻሉ እየገለፁ ነው።

- በዚህ ለሊት ምን ተፈጠረ? ብለን የጠየቅናቸው በርካታ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የተለያዩ ምክንያቶችን ገልፀውልናል፤ ፖሊስ ተደጋጋሚ ተኩስ እየተኮሰ እንደሆነና የበርካታ ሰዎች ጩኸትም እንደሚሰማ ነገረውናል።

- የቲክቫህ ቤተሰቦች ሁኔታው ትኩረት ይፈልጋል፤ ህብረተሰቡ በዚህ ለሊት እረፍት ማድርግ አልቻለም፤ አለመረጋጋቱ ለሰዎች መጎዳት መንስኤ ሊሆን ይችላል ጥንቃቄና ትኩረት እንዲሁም መፍትሄ ይሻል ብለዋል። መፍትሄ የሚሰጥ አካል ካለ መፍትሄ ይፈልግ ሲሉም አሳስበዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot