"የተማሪዎቹ ዕገታ እንደ አገር ከገጠሙን ችግሮች አንዱ ነው" - አቶ ደመቀ መኮንን [የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር]
ሁለት ወር ለሚጠጋ ጊዜ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ታግተው የሚገኙ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመው ዕገታ በአሁኑ ወቅት እንደ አገር ካገጠሙ ችግሮች ውስጥ አንዱ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ።
ይህንን የተማሪዎች ዕገታ ጉዳይ "በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ የተጨበጠ ውጤት ላይ ለማድረስ መንግሥት ሙሉ ኃይሉን አሰባስቦ እየተረባረበ" መሆኑንም አመልክተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት በሰባት ቤት የአገው ፈረሰኞች ማኅበር 80ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በእንጅባራ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው።
More https://telegra.ph/BBC-02-01
[BBC]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

አጫጭር መረጃዎች ለቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፦
- "የኛ ጊዜ ልጅነት" በሚል ወላጆች የልጅነት ጊዜያቸውን ለልጆች የሚያሳዩበት ልዩ ፕሮግራም መዘጋጀቱን አዘጋጆቹ ለቲክቫህ ገልፀዋል። ፕሮግራሙ የካቲት 01/2012 ዓ/ም በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማሰልጠኛ ተቋም እንደሚካሄድም ተገልጾልናል። እንደአዘጋጆቹ ገለፃ የፕሮግራሙ መግቢያ 100 ብር እንደሆነና ለዝርዝር መረጃም በዚህ ቁጥር እንደሚገኙ ገልፀዋል፦ 0944160928
- "ለሚጥል ህመም እንራመድ" በሚል የካቲት 8/2012 ዓ/ም የእግር ጉዞ እንደሚደረግ ከኬርኢፕሊፕሲ ኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሁሉም አካላት በ5ተኛው የሚጥል ህመም ሳምንት የእግር ጉዞ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል። የአንድ ቲሸርት ዋጋም 250 መሆኑ ተገልፆልናል። ዝርዝር መረጃዎችንም በ0913052292 እና በ0116694455 ላይ ማግኘት እንደሚቻልም ተጠቁሟል።
- ከሰሞኑን ሁለት አዳዲስ ድረገፆች ተከፍተው ለህዝብ መረጃዎችን የማቅረብ ስራዎችን እየሰሩ እንደሆነ ተመልክተናል። የመጀመሪያው ድረገፅ የአውሎ ሚዲያ [ awlomediatv.com ] ነው። አውሎ ሚዲያ በቅርቡ በማህበራዊ ሚዲያው ብቅ ያለ ነገር ግን በአጭር ጊዜ ታማኝነትንና እውቅና ያተረፈ ሚዲያ ነው። በተለይም ፌስቡክና ዩትዩብ ላይ በስፋት ይንቀሳቀሳሉ። ሁለተኛው ከሰሞኑን ወደስራ የገባው ድረገፅ ደግሞ በጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት የሚመራው Fidelpost.com ነው። ጋዜጠኛ ተስፋዬ የረጅም ዓመታት የጋዜጠኝነት ልምድ ያለውና በገለልተኛነቱም የሚታወቅ ነው።
More https://telegra.ph/TIKVAH-02-01

የጥላቻ ንግግር...
በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተበራከተ የመጣው የጥላቻ ንግግርና ሀሰተኛ መረጃ በዜጎች ደህንነት ላይ ስጋት ደቅኗል። በቅርቡም በአንዳንድ አካባቢዎች የዜጎች መፈናቀል፣ የንብረት ውድመት፣ ባስ ሲልም የሰው ሕይወት እስከመጥፋት ያደረሰ አደጋ ሲከሰት ተስተውሏል።
እንደ አውሮጳዊያኑ አቆጣጠር 1994 በሩዋንዳ፤ በ20ኛ ክፍለ ዘመን አጋማሽ በጀርመንና በአውሮጳ የደረሰው አሰቃቂ የዜጎች እልቂት የጥላቻ ንግግር በጊዜ ካልተገታ የሚያመጣው ጥፋት ከባድ መሆኑን አመላካች ነው።
ይህን አይነቱ ችግር በኢትዮጵያ እንዳይከሰት ለመከላከል መንግሥት የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ አዋጅ ለማፅደቅ በሂደት ላይ ይገኛል።
ረቂቅ አዋጁ ዜጎች ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ሲጠቀሙ ግጭት ወይም ሁከት የሚቀሰቅስ፣ ብሄር፣ ኃይማኖት፣ ዘር፣ ጾታ፣ አካል ጉዳተኝነት፣ ግለሰብ ወይንም ቡድኖች ላይ ጥላቻ የሚያስነሱ ንግግሮችን መጠቀምን ይከለክላል። የተቀመጠውን ክልከላ ተላልፈው የተገኙ ዜጎች እንደ ጥፋቱ ደረጃ ከአንድ እስከ አምስት ዓመት እስር ሊፈረድባቸው፤ ከ50 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ሊጣልባቸው እንደሚችልም ይደነግጋል።
More https://telegra.ph/ENA-02-01
[ኢዜአ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

የእንቦጭ አረም ወደ ጫሞ ሃይል ተስፋፍቷል...
በጋሞ ዞን በአባያ ሀይቅ ላይ ተከስቶ የነበረው የእንቦጭ አረም ወደ ጫሞ ሀይቅ በመስፋፋቱ አሳሰቢ ደረጃ መድረሱን የዞኑ አካባቢ ጥበቃና ደን ልማት ጽህፈት ቤት ገለጸ።
በጽህፈት ቤቱ የብዝሃ ህይወት ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ጋንቡራ ጋንታ እንዳሉት በጫሞ ሀይቅ ላይ ከ10 ሄክታር በላይ የሚሸፍን የውሃው ክፍል በአረሙ ተወሯል፡፡
ይህም ቀደም ሲል በአባያ ሀይቅ ላይ ከ2ሺህ ሄካታር በላይ የሸፈነው የእንቦጭ አረም በሚፈጠረው ማዕበልና ከኩልፎ ወንዝ ተፋሰስ በመታገዝ ተስፋፍቶ የመጣ መሆኑን አስረድተዋል።
[ENA]

#UPDATE
ኮሮና ቫይረስ የዓለም ስጋት መሆኑ ቀጥሎ ፊሊፒንስ ውስጥ አንድ ግለሰብ በቫይረሱ ህይወቱ ማለፏ ተረጋግጧል። ከቻይና ውጪ በቫይረሱ ሰው ሲሞት ይህ የመጀመሪያው ነው።
የ44 ዓመቱ ቻይናዊ ግለሰብ በሁቤ ግዛት በምትገኘው ዉሃን ከተባለችው ከተማ የመጣ ሲሆን ቫይረሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘውም በዚችው ከተማ ነበር። የዓለምአቀፉ ጤና ድርጅት እንዳስታወቀው ግለሰቡ ፊሊፒንስ ከመድረሱ በፊት በቫይረሱ ተይዞ ነበር።

የፊሊፒንስ ዜጎች እንዲረጋጉ ጥሪ ተላልፎላቸዋል...
ከቻይና ተጉዞ ፊሊፒንስ ውስጥ ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ ከእሱ በተጨማሪ አብራው የነበረችው የ38 ዓመቷ ቻይናዊ ባለቤቱ በቫይረሱ እንደተያዘች ማረጋገጣቸውን የሀገሪቱ የጤና ኃላፊዎች አስታውቀዋል።
በፊሊፒንስ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ የሆኑት ራቢንድራ አቤያሲንግ ዜጎች እንዲረጋጉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ''ከቻይና ውጪ በቫይረሱ ሰው ሲሞት ይህ የመጀመሪያው ነው። መርሳት የሌለብን ግን ግለሰቡ በሽታውን ከቻይና ይዞት መምጣቱን ነው'' ብለዋል።

በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 305 ደርሷል። 14,559 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መጠቃታቸው ተሰምቷል። #nCoV
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

- የአሜሪካ
- የአውስትራሊያ
- የኬንያ
- የሩዋንዳ
- የማዳጋስካር
- የሞሪሸስ እና የሞሮኮ አየር መንገዶች ወደ ቻይናና ከቻይና ያደርጓቸው የነበሩትን ሁሉንም ጉዞዎች ለጊዜው አቁመዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁንም የኮሮና ቫይረስ ባስፋት ባልተስፋፋባቸው የቻይና ከተሞች ሻንጋይ፣ ቤጂንግ ፣ ጉዋንዡ፣ ቼንግዱ በከፍተኛ ጥንቃቄ በረራዬን ቀጥያለሁ ማለቱ ይታወቃል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
- የአሜሪካ
- የአውስትራሊያ
- የኬንያ
- የሩዋንዳ
- የማዳጋስካር
- የሞሪሸስ እና የሞሮኮ አየር መንገዶች ወደ ቻይናና ከቻይና ያደርጓቸው የነበሩትን ሁሉንም ጉዞዎች ለጊዜው አቁመዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁንም የኮሮና ቫይረስ ባስፋት ባልተስፋፋባቸው የቻይና ከተሞች ሻንጋይ፣ ቤጂንግ ፣ ጉዋንዡ፣ ቼንግዱ በከፍተኛ ጥንቃቄ በረራዬን ቀጥያለሁ ማለቱ ይታወቃል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
“ሴቶችን ማገት ሀገር ማገት ነው”
ሰለታገቱት ተማሪዎች በጎንደርና በሌሎች ከተሞች ሰልፍ ተካሂዷል። በደምቢዶሎ ዪንቨርስቲ ይማሩ የነበሩ እና ከሁለት ወር በፊት ወደቤት ሲመለሱ እስከአሁነ ማንነታቸው ባልታወቀ ቡድኖች ስለተጋቱት 17 የአማራ ክልል ተማሪዎች መንግስት ከእገታው እንዲያስለቅቃቸው ለማድረግ ዛሬ ጥር 24 ከጠዋት አንድ አሰአት ጀምሮ በጎንደር ፣በደብረ ታቦር ፣ በዋግኅምራ እና በሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው። ሴቶችን ማገት ሀገር ማገት ነው፣ ሴቶቻችን ይለቀቁ ፣ሴቶች ሚኒስትሮች የት አላቹ? የሚሉ መፈክሮች በሰላሚዊ ሰልፉ ላይ ታይተዋል።
ከታዳጊ ተማሪዎች አንስቶ ወጣቶች ፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አዛውንቶች እና ጎልማሶች በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተሳትፈዋል።ከቀናት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት በተሰጠ መግለጫ የታገቱት ተማሪዎች በሕይወት እንዳሉ ቢገለፅም ለጥንቃቄ ሲባል የት እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ የተነገረ ነገር የለም።
[ፊደል ፓስት፣ PHOTO :AMMA]

TIKVAH-ETHIOPIA
#JawarMohammed #Election2012 የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] አቶ ጃዋር መሃመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ተጠይቋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በፃፈው ደብዳቤ መሰረት የቀረበ እንደሆነ ነው የተረጋገጠው። ኦፌኮ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት የደብዳቤው ኮፒ ለአቶ ጃዋር መሃመድ ልኮለታል። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የተናገሩት፦ "መንግስት…
#Election2012 #JawarMohammed
"አቶ ጃዋር የኢትዮጵያ ዜጋ ሆነዋል" - ጠበቃ ገመቹ ጉተማ
በታኅሳስ ወር የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስን [ኦፌኮ] መቀላቀላቸውን ያስታወቁት ጃዋር መሐመድ ረቡዕ ጥር 13/2012 ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና የወሳኝ ኩነት የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸውን ጠበቃቸው ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግረዋል።
የጃዋር መሐመድ ጠበቃ የሆኑት ገመቹ ጉተማ፤ ጃዋር በዜግነት አዋጁ የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላታቸውን እና በዚህም መሰረት ለሚመለከተው አካል ማስገባታቸውን ገልፀዋል። ‹‹በሕጉ መሰረት ዜግነትን መልሶ ለማግኘት የምንጠብቀው ምንም ዓይነት መልስ የለም። አስፈላጊ ሰነዶችን ግን አስገብተናል›› ሲሉ ተናግረዋል።
[አዲስ ማለዳ ጋዜጣ]

#JawarMohammed
ትላንት አዲስ ስታንዳርድ በእንግሊዘኛ ቋንቋ መረጃዎች የሚያሰራጭ ድረ ገፁ አቶ ጃዋር መሃመድ ለኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዜግነቱ እንዲመለስለት ያስገባባትን ሁለት ገፅ ማመልከቻ ይዞ ወጥቷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiabot

የህዳሴው ግድብ 71℅ ደርሷል ተብሏል...
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በ2015 ዓ/ም መጨረሻ ለማጠናቀቅ ግብ ተይዞ እየተሰራ ሲሆን አሁን ላይ የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 71% ደርሷል። ይህ የተገለፀው በትላንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታን በ2015 ዓ/ም መጨረሻ ለማጠናቀቅ ግብ ተይዞ እየተሰራ ሲሆን አሁን ላይ የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ 71% ደርሷል። ይህ የተገለፀው በትላንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም ተዘዋውረው በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
ቲክቫህ ቤተሰቦች ቄለም ወለጋ... ከደቂቃዎች በፊት በቄለም ወለጋ አንፊሎ/ሙጊ ከተማ ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩ የዩዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በስልክ ለማግኘት ችለናል። ተማሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ በወለጋ የሰው ህይወት እየጠፋ ነው፤ መንግስት ግልፅ መረጃ ለህዝብ እየሰጠ አይደለም፤ የኢተርኔት እና ስልክ መቋረጥ ከቤተሰቦቻቸው እንዲርቁ እንዳደረጋቸውም ተናግረዋል። በሙጊ ከተማ በያዝነው…
ከቲክቫህ ቤተሰብ አባላት፦
ከዚህ ቀደም በወለጋ ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በአካባቢው ኢንተርኔት እና በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ስልክ በመቋረጡ ሳቢያ ከቤተሰቦቻቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ ቅሬታቸውን ሲያቀርቡ ነበር።
ዛሬም በርካታ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ሰሚ አጥተናል መንግስት በአካባቢው ፈፅመዋለሁ ስለሚለው ኦፕሬሽን ግልፅ መረጃ ይስጠን በማለት እየጠየቁ ነው።
እኚሁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት መንግስት እየወሰደ ባለው እርምጃ ንፁሃን እየተጎዱ ነው፤ ይህንንም አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ቢገልፁም የትኛውም የሀገር ውስጥ ሚዳያ አይዘግብም የቤተሰቦቻችን ድምፅ ታፍኗል ብለዋል።
በመንግስት በሚወስደው እርምጃ ንፁሃን እንዳይጎዱ ስለሚደረገው ስራ በቂና ዝርዝር መረጃ መንግስት ለህዝብ ሊሰጥ ይገባል፤ ወላጆቻችን ምን ሆኑ በሚል ተማሪዎች በአግባቡ ሊማሩ አልቻሉም ሲሉ ገልፀዋል። የሚዲያዎች ዝምታና ትኩረት መንፈግም እጅግ እንዳሳዘናቸውም ተናግረዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምዕራብ ወለጋ የፀጥታ ስጋት...
“ሰብዓዊ መብትትን የሚጥሱ ሰዎች ላይ ለምን እርምጃ ተወሰደ? የሚል ተቃውሞ ማሰማት እጅግ አሳዛኝ ነው” - አቶ ታዬ ደንዳአ [የኦሮሚያ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ]
"የታጠቁ አካሎች እንዳሉ እናውቃለን፤ አካባቢው ላይ የፀጥታ ችግር አለ፤ ግን እነዚህ ሰዎች ላይ እና የታጠቁ ኃይሎች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሰላማዊ መንገድ፤ ሀሳባቸውን ከኃይል በራቀ መልኩ የሚገልፁና የሚችሉ ሰዎች እነሱ ላይ ማተኮር የለበትም። ታጥቀው ችግሩን የሚፈጥሩትን ሰዎች ለይቶ ነው እርምጃ መወሰድ ያለበት። ያየናቸው እስሮች ብዙዎቹ የከተማ ሰዎች ናቸው። እንደዛም ሆኖ በወንጀል ተሳትፈው ሊሆን ይችላል ያ ማለት ግን የህግ ከለላ ሊያገኙ አይገባም ማለት አይደለም። በ48 ሰዓት ፍርድ ቤት መቅረብ አለባቸው፣ የታሰሩበት ምክንያትና የተያዙበት ምክንያት በግልፅ ሊነገራቸው ይገባል፣ ምርመራውም ተጠናዉ ቶሎ መቅረብ አለባቸው።" - አቶ ፍስሃ ተክሌ [የአምነስቲ የአፍሪካ ቀንድ ተመራማሪ]
📹9 MB [WiFi ተጠቀሙ]
[ዘገባው ከJanuary 31 የተወሰደ ነው]

"የመንግስት ጦር ሁለት የአክስቴን ልጆች ገድሏል፤ እንዳይቀበሩም ጭምር ከልክሏል" - አቶ በቀለ ገርባ [የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር]
የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ በቀለ ገርባ በግል የፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ የመንግስት ጦር በትላንትናው እለት በምዕራብ ወለጋ ነጆ ወርዳ በቡያ ቦሊቲ ቀበሌ የአክስቴን ልጆች ታምሩ ታደሰን እና ጆቴ ታደሰ ገድሏል፤ መግደል ብቻ አይደለም እንዳይቀበሩም ከልክሏል ሲሉ ገልፀዋል አክለውም ሁለቱም ያልታጠቁ አርሶ አደሮች ነበሩ" ብለዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኦሮሞ ፌደራሊስ ኮንግረስ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ በቀለ ገርባ በግል የፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ የመንግስት ጦር በትላንትናው እለት በምዕራብ ወለጋ ነጆ ወርዳ በቡያ ቦሊቲ ቀበሌ የአክስቴን ልጆች ታምሩ ታደሰን እና ጆቴ ታደሰ ገድሏል፤ መግደል ብቻ አይደለም እንዳይቀበሩም ከልክሏል ሲሉ ገልፀዋል አክለውም ሁለቱም ያልታጠቁ አርሶ አደሮች ነበሩ" ብለዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኮሮና ቫይረስና ማህበራዊ ሚዲያ!
ኮሮና ቫይረስን በተመለከተ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የሚወሩና የሚጋሩ ሳይንሳዊ መሰረት የሌላቸው ወሬዎች ሰዎችን ጭንቀት ውስጥ እየጣሉ፣ ቻይናውያንን ደግሞ ለከፍተኛ መገለልና የዘረኝነት ስድቦች እየዳረጉ ነው ተብሏል።
ኮሮና ቫይረስን የፅዳት ኬሚካሎችን ወይም ማቅለሚያዎችን በልኩ በመውሰድ መዳን ይቻላል የሚል ብዙዎች የተመለከቱት የፌስቡክ ፖስት እና ሌሎች የዩትዩብ ቪዲዮዎችን ለአብነት አንስቷል- ብሉምበርግ። የቻይናውያንን አመጋገብና ባህል የሚነቅፉና፣ የናንተ ቫይረስ ነው፣ እዚያው በጠበላችሁ የሚሉ የዘረኝነት ፅሁፎችን በቻይና ሬስቶራንቶች ማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ላይ ተፅፈውም ታይተዋል።
ትዊተር፣ ፌስቡክና ጉግል በሚቻል መጠን የተሳሳቱ የኮሮና ቫይረስ መረጃዎችን ከየገፆቻቸው ላይ ለመቀነስና ሰዎችንም ተዓማኒ ወደሆኑ ገፆች ለመምራት ጥረት እያደረጉ መሆኑን አስታውቋል።
በኢትዮጵያ በኩል የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአንፃራዊነት ጥሩና ፈጣን ሊባል የሚችል መረጃን በየማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻቸውና የፕሬስ መግለጫዎች እየሰጡ ይገኛሉ። ስለቫይረሱ መረጃ ለማግኘት የእነዚህን ተቋማት ፌስቡክና ትዊተር ገፆች መመልከት መልካም ነው።
[ሃሽታግ- አዲስፕላስ፣ ኤልያስ መሰረት]

#UPDATE - የአሜሪካ - የአውስትራሊያ - የኬንያ - የሩዋንዳ - የማዳጋስካር - የሞሪሸስ እና የሞሮኮ አየር መንገዶች ወደ ቻይናና ከቻይና ያደርጓቸው የነበሩትን ሁሉንም ጉዞዎች ለጊዜው አቁመዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ? የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁንም የኮሮና ቫይረስ ባስፋት ባልተስፋፋባቸው የቻይና ከተሞች ሻንጋይ፣ ቤጂንግ ፣ ጉዋንዡ፣ ቼንግዱ በከፍተኛ ጥንቃቄ በረራዬን ቀጥያለሁ…
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የማደርገውን በረራ አላቋረጥኩም፤ በረራውን የማደርገውም በጥንቃቄ ነው ቢልም የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ እየተመለከትን ነው። በማህበራዊ ሚዲያዎች ዞር ዞር ስንል ይህንን አስተያየት አገኘን፦
"ለቻይና እንኳን የከበደ በሽታ ግባልን ብሎ በር መክፈት ምን ይሉት ማን አለብኝነት ነው? ሞተን አላልቅ አልን ወይ? የኢትዮጲያ አየር መንገድ በረራዬን ወደ ቻይና አላቆምም ማለቱ ምንን ተስፋ አድርጎ ነው? Temperature ለክቼ አሳልፋለሁ አለ? screening ከተባለ ፣ ሲጀመር virus Incubation period ሁለት ሳምንት አለው ፣ ሰውየው ምንም ምልክት ሳያሳይ ለሁለት ሳምንት በሽታውን ለሌሎች ማስተላለፍ ይችላል። ስለዚህ ሰውየው ትኩሳት ስለማይኖረው እቺን "screening" አለፋት ማለት ነው። ነው ወይስ ጤና ጥበቃ አቋቋምኩት ያለውን ድንኳን ተስፋ አድርጎ ነው? ድንኳኑ እሺ ይሁን ግን Corona virus ለማከም በትንሹ መተንፈሻ ማሽን (mechanical ventilators) ያስፈልጋል! ኢትዮጲያ ውስጥ ያሉት በሙሉ መተንፈሻ ማሽኖች ቢቆጠሩ 100 መሙላታቸውን እንጃ። አንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ከገባ በሽታውን ማኔጅ የምናረግበት አቅም የለንም ፣ ደሞ በዚ ላይ አኗኗራችን ለቫይረሱ መስፋፋት ምቹ ነው ፤ ኧረ ስማ በለው!!" - ዶ/ር ነፃነት መንገሻ

ዶ/ር ኤልያስ ገብሩ ምን ይላሉ፦
"ይሄ አንዲት በቻይና ዉሃን ከተማ የምትሰራ ነርስ እጅ ነው። የኮሮና በሽታ ሲከሰት በሆስፒታሉ ህጻናትን የምትከታተል ባለሙያ ነበረች። ባከመች፣ በነካች፣ በወጣችና በገባች ቁጥር እጆቿን በፀረ-ጀርም (Anti-septic) ማጽ ዳትና ጓንት መቀየር ነበረባት። ታድያ ካለእረፍት የሰራችበት እጇ እንደዚህ ተላልጧል። ክብር ይገባታል። በሽታው ግን ቀላል አይደለም። ብዙ ዋጋ ያስከፍላል። ጓንት እንኳን በቅጡ የማናሟላ አገር ሆነን ሳለን በረራ አናቆምም ማለት ትልቅ ቀልድ ነው። ለሚመጣው ችግር በሙሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጠያቂነቱን እንደሚወስድ ከወዲሁ ማወቅ አለበት። የሳንባ ምች (Pneomonia) እና ቲቢ እስካሁን ብዙዎችን በሚገድሉበት አገር ኮሮና ቢገባ የሚከሰተውን እልቂት ማሰብ ይዘገንናል። #StopFlyingToChina"

#UPDATE በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 305 ደርሷል። 14,559 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ መጠቃታቸው ተሰምቷል። #nCoV @tikvahethiopia @tikvahethiopia
#UPDATE
በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 14,631 ደርሷል። ጥዋት በሰጠናችሁ መረጃ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 14,559 እንደነበር ታስታውሳላችሁ። በሰዓታት ልዩነት 72 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃጣቸው ተሰምቷል።