TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ከክልሉ ሰላም ግንባታና ፀጥታ ቢሮ የተገኘው መረጃ፦

- 13 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

- ሁለቱ በግድያ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ንብረት በመዝረፍ የተጠረጠሩ ናቸው።

- በግድያ ከተጠረጠሩት ውስጥ አንደኛው ከአንድ የእጅ ቦምብ ጋር ነው የተያዘው።

- ቀሪ ዘጠኝ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እየተሰራ ነው።

- አሁን ላይ የመከላከያ ሠራዊት አባላት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች እና የአካባቢው የጸጥታ አካላት ሕዝቡን እያረጋጉ እንደሆነና ከተጎጅዎች ጋርም ውይይት እየተደረገ ነው።

[AMMA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ኢትዮጵያ ታለንት ፓዎር ሲሪየስ' ሀዋሳ...

ዳሸን ባንክ ‘የኢትዮጵያ ታለንት ፓወር ሲሪየስ’ የተሰኘውን ፕሮጀክት ጅማሮ በሃዋሳና አካባቢዋ ለሚገኙ ነዋሪዎች ይፋ ማድረጉን አስታውቋል ፡፡

የባንኩ የገበያና የደንበኞች ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስቻለው ታምሩ እንደገለጹት ባንኩ “መንግስት የቀየሰውን የስራ አጥ ቅነሳና የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ለማገዝ አዲስ አበባን ጨምሮ ስድስት ክልሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።

ፕሮጀክቱ በተለየ ሁኔታ የስራ ፈጠራ ስልጠና፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት አቅም ግንባታ፣ የከፍተኛ ትምህርት የፋይናንስ ድጋፍ፣ የቢዝነስ ክለብ ምስረታና የገበያ ትስስር ላይ ያተኮሩ ስልጠናዎችንም ይሰጣል።

[ENA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀዋሳው ፕሮግራም ላይ የተገኙት የንግድ  ሃሳቦች አማካሪው ዶክተር አቡሽ አያሌው የተናገሩት፦

"በኢትዮጵያ 19 በመቶ የሚጠጋ ስራ ፈላጊ አለ። መሰል ስልጠናዎች ሰዎች የራሳቸው ቀጣሪ እንዲሆኑ ከማስቻሉም በላይ በአገሪቱ የወጪና የገቢ ንግድ ላይ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DashenBank

በዳሽን ባንክ 'የኢትዮጵያ ታለንት ፓዎር ሲርየስ' ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ተመዝጋቢዎች ስልጠና እንዲያገኙ እንደሚደረግ ከዳሽን ባንክ መግለጫ ለመረዳት ችለናል።

ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ የፈጸሙትንና ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ የፈጠራ ሃሳቦችን በማወዳደር ከ1ኛ እስከ 3ኛ አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች ከግማሽ ሚሊዮን እስከ አንድ መቶ ሺ ብር የሚደርስ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል።

በሃዋሳ የተጀመረው የዳሸን ባንክ የኢትዮጵያ ታለንት ፓወር ሲሪየስ ፕሮጀክት በቀጣይ፦
- በአዳማ፣
- በድሬዳዋና
- በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

[ENA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WOLLEGA

የኢትዮጵያ መንግስት በወለጋ እያኬሄድኩት ነው የሚለውን ኦፕሬሽን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ ንፁሃንም የጥቃት ሰለባ እንዳልሆኑ እንዲያረጋግጥ፣ በወለጋ የሚፈፀመው ምን እንደሆነ በግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጥ በማህበራዊ ሚዲያ ግፊት እየተደረገ እንደሚገኝ እየተመለከትን ነው። በአካባቢው ኢተርኔትና ስልክ አገልግሎት በመቋረጡ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ወለጋ ቤተሰቦች በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅና በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ለማወቅ ጥረት እያደረግን ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BringBackOurGirls
#WhereAreTheStudents
#WeWantThemBack
#WeWantAnswers
እህቶቻችን የት ናቸው?
አንተስ ብትሆን፤ አንቺስ ብትሆኚ?
ይህ የሰብዓዊነት ጉዳይ ነው!

#መራሂት #MERAHIT

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BringBackOurStudents

የኢትዮጵያ መንግስት በታገቱት ተማሪዎች ዙሪያ በቂና ዝርዝር መረጃ ለተማሪዎቹ ወላጆችና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሰጥ፣ ተማሪዎቹ በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንዲገለፅ በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል፤ ዘመቻው በመንግስት ላይ ጫና በማሳደር የተማሪዎቹን ሁኔታ እንዲያሳውቅ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ሚዳያዎች ስለታገቱት ተማሪዎች ድምፅ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመ ነው።

ከወር በላይ ታግተው የሚገኙ ተማሪዎች የት እንዳሉ አይታወቅም ፤ የመንግስት ኃላፊዎች በየጊዜው በየሚዲያው እየወጡ የሚሰጧቸው መረጃዎችም እርስ በእርሳቸው የማይጣጣሙ ናቸው። የተማሪዎቹ ደህንነት ያሰጋቸው እና ያስጨነቃቸው በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መንግስት እውነቱን እንዲያወጣ ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ።

PHOTO : Yanchi Movement
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WOLLEGA የኢትዮጵያ መንግስት በወለጋ እያኬሄድኩት ነው የሚለውን ኦፕሬሽን ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ ንፁሃንም የጥቃት ሰለባ እንዳልሆኑ እንዲያረጋግጥ፣ በወለጋ የሚፈፀመው ምን እንደሆነ በግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጥ በማህበራዊ ሚዲያ ግፊት እየተደረገ እንደሚገኝ እየተመለከትን ነው። በአካባቢው ኢተርኔትና ስልክ አገልግሎት በመቋረጡ ዝርዝር መረጃዎችን ለማግኘት አስቸጋሪ ሆኗል። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ወለጋ ቤተሰቦች…
ቲክቫህ ቤተሰቦች ቄለም ወለጋ...

ከደቂቃዎች በፊት በቄለም ወለጋ አንፊሎ/ሙጊ ከተማ ቤተሰቦቻቸው የሚኖሩ የዩዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆኑ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በስልክ ለማግኘት ችለናል። ተማሪዎቹ እንደሚሉት ከሆነ በወለጋ የሰው ህይወት እየጠፋ ነው፤ መንግስት ግልፅ መረጃ ለህዝብ እየሰጠ አይደለም፤ የኢተርኔት እና ስልክ መቋረጥ ከቤተሰቦቻቸው እንዲርቁ እንዳደረጋቸውም ተናግረዋል።

በሙጊ ከተማ በያዝነው ሳምንት የሰዎች ህወይት አልፏል፤ የንግድ እንቅስቃሴ፣ ትምህርትም ቆማል፣ በከተማይቱ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ድምፅ በየጊዜው ይሰማል፣ ከባድ መሳሪያዎችም ሲተኮሱ ይሰማል፣ ወጣቶች በነፃነት መንቀሳቀስ አልቻሉም፤ በርካታ ወጣቶች ከታጣቂዎች ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል እንግልት እየደረሰባቸው ይገኛል፤ በምሽት 1:00 በኃላ መንቀሳቀስ አይታሰብም ብለውናል።

በተጨማሪ የሀገሪቱ ሚዳያዎች ዝምታን መምረጣቸው፣ በማህበራዊ ሚዲያም ለወለጋ ህዝብ ድምፅ መነፈጉ እጅግ እንዳሳዘናቸው ተማሪዎች አስረድተዋል። ወላጆቻችን በችግር ላይ ናቸው፤ እየሆነ ያለውም ጉዳይ መንግስት ግልፅ ማብራሪያ ይስጥ፣ መንግስት በሚወስደው እርምጃ ንፁሃን ዜጎች እንግልት ውስጥ ሊገቡ አይገባም፤ ጋዜጠኞችና ሚዳያዎች ገለልተኛ ሆነው የህዝቡን ድምፅ ማሰማት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

#TikvhaFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደሴ ከተማ ወጣቶች ቅሬታ...

በደሴ ከተማ ለወጣቶች የስራ እድል እንዲፈጥሩ የተሰሩ ሸዶችና ኮንቴይነሮች ለ15 ዓመታት አለአግባብ በግለሰቦች እጅ እንዲቆዩ መደረጉ ለሌሎች ወገኖች የስራ እድል እንዳይፈጠር እንቅፋት በመሆናቸው የከተማዋ ወጣቶች ቅሬታቸውን አሰምተዋል። የከተማ አስተዳደሩ በህገ ወጥ መንገድ የተያዙትን ኮንቲነሮችና ሼዶችን በማጣራት ማስለቀቅ መጀመሩን ገልጿል።

[ENA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደሴ ወጣቶች...

የሆጤ ክፍለ ከተማ ነዋሪ ወጣት ያብባል ደጀኔ፦

"በየዓመቱ ከመመዝገብና ከመደራጀት ውጭ ስራ ማግኘት ባለመቻሌ በቤተሰብ ጥገኝነት ስር ሆኖ መኖር ተስፋ እንድቆርጥና ለአዕምሮ ጭንቀት እንድዳረግ አድርጎኛል። ምክንያቱ ደግሞ ለስራ አጥ ወጣቶች የተሰጡ የመስሪያና የመሸጫ ሼዶችና ኮንቴይነሮች የወሰዱ ሰዎች በህጉ መሰረት ለ5 ዓመታት ሰርተው ሀብት በማፍራት ለሌሎች ስራ አጥ ወጣቶች ማስተላለፍ ሲገባቸው አለአግባብ ከ15 ዓመታት በላይ እንዲጠቀሙበት በመደረጉ ነው።"

በደሴ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ልማት መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ምንይሻው በሪሁን፦

"ወጣቶቹ የሚያነሱትን ጥያቄ መሰረት በማድረግ በጥናት ላይ የተመሰረተ እርምጃ መውሰድ ተጀምሯል። ኮሚቴ ተቋቁሞ ባካሄደው ማጣራትም ኮንቲነሮችንና ሸዶችን ያከራዩ፣ መኖሪያ ቤት ያደረጉ፣ ለሌላ ያስተላለፉ፣ ዘግተዉ የጠፉና በስማቸው ለማዛወር የሚያማትሩ መኖራቸውን ተረጋግጧል። በህገ ወጥ መንግድ የተያዙ 176 ሼዶችና ኮንቴይነሮች የተገኙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 58ቱን በማስለቀቅ ለስራ አጥ ወጣቶች ለማስተላለፍ ዝግጅት እየተደረገ ነው።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጥንቃቄ መልዕክት ለወላይታ ዞን ነዋሪዎች...

በደቡብ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰተ ያለው የአንበጣ መንጋ ወደ ወላይታ ዞን እንዳይገባ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ልማት መምሪያ የተሰጠ መግለጫ፡-https://telegra.ph/ETH-01-26-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአንበጣ መንጋ ስጋት በወላይታ ዞን...

የአንበጣ መንጋ ወደ ወላይታ ዞን የመዛመት ዕድሉ ሰፊ ስለሆነ ህብረተሰቡ ቅድመ ጥንቀቃቄ እንዲያደርግ የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ልማት መምሪያ አሳስቧል፡፡

ህብረተሰቡ በአካባቢው የአንበጣ መንጋ ቢከሰት የተለያዩ ድምጽ ማስተጋባት የሚችሉ ጅራፍ፣ ሪቺት በመተኮስ፣ ጩኸት በማሰማትና የተለያዩ የመኪና ጎማና የፕላስቲክ ቁራጭ በማቃጠል ጭስ በማጬስ የአንበጣ መንጋው በአካባቢው እንዳይቀመጥ መከላከል እንደሚቻል አብራርቷል፡፡

በዞኑ የአንበጣ መንጋ ሊከሰትባቸው ከሚችሉ አካባቢዎች ደጉና ፋንጎ፣ አባላ አባያ፣ ሆቢቻ፣ ዳሞት ወይዴ፣ ሁምቦ እና ዳሞት ጋሌ ወረዳዎች የስጋት ቀጠና ሆነው ተለይተዋል፡፡

[የወላይታ ዞን እርሻና ተፈጥሮ ሀብት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
7 ሚሊዮን ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል!

በሀገሪቱ እስከ ሰኔ 2012 ዓ/ም 7 ሚሊዮን ዜጎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ብሔራዊ የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከጥር እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የድጋፍ አቅርቦት የሚያስፈልጋቸው ተረጂዎችን በጥናት መለየቱንም አስታውቋል። በጥናቱ መሰረት ለሰብዓዊ ድጋፉም 1 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በምግብ ፍላጎት ተረጂ የሆኑት 6 ሚሊዮን ሰዎች እንደሆኑና ባለፈው ዓመት ከነበረው 8 ሚሊዮን ተረጂ ጋር ሲነጻጻር ቁጥሩ መቀነስ ማሳየቱንም ተሰምቷል።

[ENA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሰሞኑን ሀዋሳ ከተማ ምንያህል ገቢ አገኘች?

የሀዋሳ ከተማ ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ካስተናገደቻቸው ክብረ በዓላት ከ68 ሚሊዮን ብር በላይ ጭማሬ ያለው ገቢ መገኘቱን የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ተናገሩ፡፡

በሀዋሳ ከተማዋ ያለው ምቹ ሁኔታ የንግድ እንቅስቃሴውን እንዳሳደገው ተናግረው የቱሪዝም፣ የኢንቨስትመንት እና የንግድ መዳረሻ በመሆን የምትታወቀው የሀዋሳ ከተማ ያሏትን ምቹ አጋጣሚዎች በመጠቀም በተለየ የኢኮኖሚ መነቃቃት ላይ እንደምትገኝ ነው ከንቲባ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ያስረዱት፡፡

ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በነበሩት ሀይማኖታዊ ክብረ በዓላት በርካታ ቁጥር ያላቸው የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ጎብኚዎች በከተማዋ ቆይታቸውን እንዳደረጉ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት መረጃ ያሳያል፡፡

[የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ SRTA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

• 56 ሰዎች ሞተዋል
• 2000 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል

ከ2,000 በላይ ሰዎችን ያጠቃው የቻይናው ኮሮና ቫይረስ (2019-nCoV) ስለመከሰቱ ምልክቶች ከመታየታቸው በፊት በብዛት መሰራጨቱን ያስታወቁት የቻይና ባለስልጣናት ይሄም ቫይረሱን የመቆጣጠር ተግባራትን ፈታኝ እንዳደረገ ገልፀዋል።

ከጡረታ ተመልሶ የቫይረሱ ህመምተኞችን ሲያክም የነበረ አንድ የ62 ዓመት ቻይናዊ ዶክተር ዛሬ ጥዋት በቫይረዱ ሲሞት፤ ሌላ አንድ ዶክተር ደግሞ በህክምና ላይ እንዳለ በልብ ህመም ህይወቱ አልፏል። በቫይረሱ ስለመያዙ ግን አልታወቀም።

[AlAin]
@tikvahethiopia @tsegabwolde
TIKVAH-ETHIOPIA
የአንበጣ መንጋ ስጋት በወላይታ ዞን... የአንበጣ መንጋ ወደ ወላይታ ዞን የመዛመት ዕድሉ ሰፊ ስለሆነ ህብረተሰቡ ቅድመ ጥንቀቃቄ እንዲያደርግ የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ልማት መምሪያ አሳስቧል፡፡ ህብረተሰቡ በአካባቢው የአንበጣ መንጋ ቢከሰት የተለያዩ ድምጽ ማስተጋባት የሚችሉ ጅራፍ፣ ሪቺት በመተኮስ፣ ጩኸት በማሰማትና የተለያዩ የመኪና ጎማና የፕላስቲክ ቁራጭ በማቃጠል ጭስ በማጬስ የአንበጣ መንጋው በአካባቢው…
#ATTENTION

በወላይታ ዞን የአንበጣ መንጋ መከሰቱን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ገልጿል። የመምሪያው ሃላፊ አቶ አሞና ቶልካ እንደገለፁት የአንበጣ መንጋው ትናንት ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በዞኑ በሚገኙ ዱጉና ፋንጎ ወረዳዎች መታየት ጀምሯል።

በተለይ ደግሞ በዞኑ ድምቱ ፣ ብላቴ ኤታና ወርቅቻ ደንዶ በሚባሉ ቀበሌያት መንጋው በስፋት መከሰቱን ተናግረዋል። የአንበጣው መሬት ላይ እንዳያርፍና ጉዳት እንዳያደርስ የተለያዩ ባህላዊ ዜዴዎች በመጠቀም ህብረተሰቡ እያባረረው መሆኑን ገልፀዋል።

የአንበጣው መንጋ እስከ አሁን ድረስ ያደረሰው ጉዳት የለም ያሉት መምሪያ ሃላፊው ህብረተሰቡ በተደራጀ መልኩ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ መልእክት አስተላልፈዋል።

[ኢዜአ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"ዘረኝነት የሚለውን ቃል ትርጉም ለመጀመሪያ ጊዜ የተረዳሁት አሁን ነው" - [ቫኔሳ ናካቴ]

ዩጋንዳዊቷ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ቫኔሳ በዳቭስ በእንግድነት በተገኘችበት የአየር ንብረት ላይ ያተኮረ ዝግጅት ከሌሎች ነጭ አጋሮቿ ጋር የተነሳችው ፎቶ ተቆርጦ መውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል።

የዜና ዘገባ በመስራት ላይ የነበረው [Associated Press] ፎቶውን ዳር ላይ የነበረችውን ቫኔሳን ቆርጦ በማውጣት የነጮቹን ብቻ በመጠቀሙ ይቅርታ ጠይቋል።

ቫኔሳ ናካቴ በትዊተር ገጿ ዘረኝነት የሚለውም ቃል ትርጉም ለመጀመሪያ ጊዜ የተረዳሁት አሁን ነው ፤ የተቆረጠው የኔ ምስል ብቻ ሳይሆን አህጉር እና ሀሳብ ነው ብላለች።

[CNN, ALAIN]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot