TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ጥር 14 ቀን 2012 ዓ.ም ያካሂዳል። በስብሰባውም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።  

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JAWARMOHAMMED #OFC

[በዋዜማ ሬድዮ]

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ በቅርቡ ፓርቲውን የተቀላቀለው ጃዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ደብዳቤ እንደፃፈለት ተሰምቷል።

የቀድሞው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሲሆን የውጪ ዜግነቱን መልሶ የኢትዮጵያ ዜግነት ለመውስድ እየሞከረ እንደነበር ከወራት በፊት ገልጿል። ይሁንና የዜግነቱ ጉዳይ እልባት ሳያገኝ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲን ተቀላቅሎ መታወቂያም ወስዷል።

ጉዳዩን በተመለከት ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ለኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ድብዳቤ ፅፎ ማስረጃ የጠየቀ ሲሆን ፓርቲው በበኩሉ ጃዋር ማስረጃ እንዲያቀርብ በደብዳቤ አሳስቧል። የፓርቲው ሊቀመንበር መረራ ጉዲና ይህን መረጃ አረጋግጠዋል። “የኛ አባል ሲሆን ለምን ይህ ጥያቄ እንደተነሳ ባይገባኝም እኛ ደብዳቤ ፅፈንለታል” ብለዋል ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና።

እንዴት ለዜግነቱ ማረጋገጫ ሳያቀርብ በህግ ባልተፈቀደ መልኩ ጃዋር መሀመድ ፓርቲውን እንዲቀላቀልና መታወቂያ እንዲወስድ እንደተፈቀደለት ለተነሳላቸው ጥያቄ መረራ ጉዲና ሲመልሱ ” እኛ የምናውቀው ኢትዮጵያዊ መሆኑን ነው፣ የሀገሩን ቋንቋ ይናገራል፣ ፊቱም ኢትዮጵያዊ ይመስላል፤ መንግስትም ይህን ያውቃል” ሲሉ ቀልድ አዘል ምላሽ ስጥተዋል።

በጃዋር ዜግነት ላይ ከመንግስት የሚነሳው ጥያቄ ፖለቲካዊ ፍላጎትንም ያካተተ ሊሆን ይችላል ያሉት መረራ ጉዲና ጃዋር በቅርብ ዜግነቱን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ እንደሚመጣ ተስፋ እንደሚያደርጉና ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድም በጊዜው ምላሽ እንደሚሰጡ ተናግረዋል።

[ዋዜማ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወጣት ሃኪሞች የስራ ፈጣሪነት ስልጠና...

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አመታዊ የህክምና ጉባኤውንና የጤና ኢግዚቢሽን በሚቀጥለው ወር ያካሂዳል፡፡ ጉባኤው የሚካሄደው ለ56ኛ ጊዜ ሲሆን በህክምናው ዘርፍ የተሰሩ አዳዲስ የጥናት ግኝቶች ይቀርባሉ፡፡

ወጣት ዶክተሮችን በማብቃት የጤናውን ዘርፍ ማጎልበት በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ጉባኤ ህንድና ታይዋንን ጨምሮ በጤና ቱሪዝም ላይ የተሰማሩ አለም አቀፍ ተሳታፊዎች ይገኙበታል፡፡

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ወ/ሮ ትእግስት መኮንን እንደተናገሩት በተለይም ካለፈው አመት ጀምሮ በህክምና ትምህርት ተመርቀው የስራ እድል ያላገኙ ወጣት ሃኪሞችን ወደ ስራ ፈጣሪነት ለማምጣት የሚያስችል የስራ ፈጣሪነት፣ ስራ አመራርና ስነ-ምግባር ስልጠና ይሰጣቸዋል፡፡

ለመመዝገብ www.emaconference2020.org

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"መንግስት ለተጎጂዎች ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል" - አቶ ኦርዲን በድሪ [የሀረሪ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር]

ከጥምቀት በዓል አከባበር [ጥር 10 እና ጥር 11] ጋር ተያይዞ በሀረር ከተማ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለደረሰው ጉዳት መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የሀረሪ ክልል ርዕሰ-መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ አስታወቁ።

ርዕሰ-መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት ለበዓሉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር አስፈላጊው ዝግጅት ቢደረግም ግጭት የመፍጠር ተልዕኮን ባነገቡ አካላት በተፈጸመ ተግባር በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል። በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን የገለጹት ርዕሰ-መስተዳደሩ፣ መንግስት ለተጎጂዎች ተገቢውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም አሳውቀዋል።

በቀጣይም በድርጊቱ የተሳተፉ፣ በተለያየ መንገድ ሲመሩና ሲደግፉ የነበሩ አካላትን የክልሉ የፀጥታና ፍትህ አካላት በአፋጣኝ አጣርተው ለፍርድ በማቅረብ የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ በትኩረት እንደሚከናወን ገልፀዋል።

ሕብረተሰቡ ላሳየው ትዕግስት እና ከጸጥታ አካላት ላደረገው ትብብር በራሳቸው እና በሀረሪ ክልል መንግስት ስም ምስጋናቸውን ያቀረቡት አቶ ኦርዲን በድሪ በቀጣይም ከመንግስት ጎን በመቆም አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ ትብብሩን እንዲያጠናክር ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

[ENA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#LONDON

የኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅትና ትግበራ ተሞክሮበት ለንደን ከተማ እየተካሄደ ባለው የትምህርት አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ቀረበ፡፡ ኘሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የሚመራ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጣ የኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ልኡካን ቡድን ለንደን ከተማ “One Generation: What does it take to transform education?” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው የትምህርት አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡

[EPA]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#LONDON የኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ ዝግጅትና ትግበራ ተሞክሮበት ለንደን ከተማ እየተካሄደ ባለው የትምህርት አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ቀረበ፡፡ ኘሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የሚመራ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጣ የኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ልኡካን ቡድን ለንደን ከተማ “One Generation: What…
የትምህርት አለም አቀፍ ጉባኤ 2020፦

- ጉባኤው በየአመቱ በጥር ወር ላይ በለንደን የሚካሄድ ነው። በጉባኤው ከፍተኛ የሆኑ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ይሳተፉበታል፡፡

- በዘንድሮው ጉባኤ ላይ የ130 ሀገሮች ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ የትምህርት ኃላፊዎች፣ በትምህርት ላይ የሚሰሩ አለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ትምህርትን የሚደግፉ ድርጅቶች፣ በትምህርትና ሥልጠና ላይ ምርምር የሚያካሂዱ ታዋቂ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት እና ሌሎችም የተውጣጡ በጠቅላላ ከ800 በላይ ተሳታፊዎች የተሳተፉበት ነው፡፡

- በዚህ ጉባኤ ላይ በየአመቱ ምርጥ ተሞክሮዎች ያላቸው ሀገሮች የሚመረጡና ተሞክሮዎቻቸውን ለሌላው ዓለም የሚያጋሩ ሲሆን ኢትዮጵያም የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ - ካርታ ዝግጅትና ትግበራ አካሄዷን እንድታቀርብ ተመርጣለች፡፡

- ኘሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም የኢትዮጵያን የትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ-ካርታ ተሞክሮ በመድረኩ ለታዳሚዎች አጋርተዋው በመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ የወረዳነት ጥያቄ... የአካባቢው ነዋሪዎች ኮሚቴ ወኪል አቶ ደሱ ፀጋየ፦ - ጥያቄያችን ወረዳችን ይመለስልን የሚል ነው፤ ህንጣሎ ውጀራት ወረዳ ነበረች። ወጀራት ተመለሰች ነገር ግን ህንጣሎ ተሰጠች። - ይህንን ጥያቄያችንን ማቅረብ ከጀመርን ስድስት ወራት ተቆጥረዋል። ቅሬታችንን ለማቅረብ ያልሄድንበት ፤ ያልደረስንበት ቦታ የለም። በወረዳ እና በዞን የሚገኙ የፍትሕም ሆነ የፀጥታ…
• “ሽፍታ በሚመስል መንገድ ችግር እየፈጠሩ ያሉት ጥቂት ግለሰቦች ናቸው” - አቶ ጌታቸው ረዳ

• “ጥያቄው የጥቂቶች ሳይሆን የሕዝብ ነው” - የአካባቢው ነዋሪዎች

ሕንጣሎ ወረዳ ወደሒዋነ መቀላቀል የለበትም ‹‹ወረዳችን ይመለስልን›› በማለት መንገድ ዘግተው የሽፍታ በሚመስል መንገድ ችግር እየፈጠሩ ያሉት ጥቂት ግለሰቦች ናቸው ሲሉ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል፡፡

አቶ ጌታቸው በአካባቢው ለተነሳው ጥያቄ መልስ የሚሰጠው ወረዳው መሆኑን አመልክተዋል፡፡ አንድ ቀበሌ ውስጥ ያሉ ጥቂት ሰዎች ይህንን ጉዳይ ለእኛ ሲባል መመለስ አለበት ማለት አይችሉም ጥያቄው በሕዝቡ ውሳኔ ይፈታል፤ ለዚህም ሲባል የሕዝብ ተወካዮች ወደቦታው ተልከዋል ሲሉ አመልክተዋል፡፡

More https://telegra.ph/EPA-01-22

[አዲስ ዘመን ጋዜጣ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እስር...

የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ አብዱል ሰላም ሸንግል እና የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ አሶሳ ውስጥ ታስረዋል።

የቤኒሻንል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ የሕዝብ ግንኘነት ኃላፊ አቶ መሀመድ እስማኤል ሁለቱ የፖለቲካ የድርጀት መሪዎች በፖሊስ የታሰሩት ሰኞ መኾኑን ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

ሁለቱ ደርጅቶች ባለፈው ሳምንት የጋራ ጉባኤ አዘጋጅተው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ግንባር የሚል ጥምረት መመስረታቸውንም አቶ መሐመድ ገልጸዋል።

ከጋራ ጉባኤው በፊት ግን ሁለቱ ፓርቲዎች ላይ ቀደም ሲል ተደጋጋሚ ዛቻዎች ይደርሱባቸው እንደነበርም አክለው ተናግረዋል። የክልሉ ባለሥልጣናት ፖለቲከኞቹ የታሰሩት በወንጀል ተጠርጥረው ነው ብለዋል።  

[የጀርመን ድምፅ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#JAWARMOHAMMED #OFC [በዋዜማ ሬድዮ] የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ በቅርቡ ፓርቲውን የተቀላቀለው ጃዋር መሀመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ደብዳቤ እንደፃፈለት ተሰምቷል። የቀድሞው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ የአሜሪካ ዜግነት ያለው ሲሆን የውጪ ዜግነቱን መልሶ የኢትዮጵያ ዜግነት ለመውስድ እየሞከረ እንደነበር ከወራት…
#JawarMohammed #Election2012

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] አቶ ጃዋር መሃመድ ኢትዮጵያዊ ዜግነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲያቀርብ ተጠይቋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በፃፈው ደብዳቤ መሰረት የቀረበ እንደሆነ ነው የተረጋገጠው። ኦፌኮ በጉዳዩ ላይ ምላሽ እንዲሰጥበት የደብዳቤው ኮፒ ለአቶ ጃዋር መሃመድ ልኮለታል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የተናገሩት፦

"መንግስት ግቡና አግዙን ባለው መሰረት ወደሀገር ቤት የገባን፣ በፓርቲ አመራርነት ያልተቀመጠንና በምርጫ ገና ያልተወዳደረን አካል እንዲህ ማለቱ ግራ የሚያጋባ ነው። ስሙም፣ መልኩም ኢትዮጵያዊ ነው።"

ምንጭ፦ አል-ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ሶስት የሚኒስትርነት ሹመቶችን ሰጡ፦

- ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ [የትምህርት ሚኒስትር]

- አቶ መላኩ አለበል [የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር]

- ዶ/ር አብርሃም በላይ [የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር]

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
NOVEL CORONAVIRUS... የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በቻይና ከተከሰተው አዲስ ቫይረስ ጋር በተያያዘ አስቸኳይ የኮሚቴ ስብሰባ ለነገ ረቡዕ ጠሩ። ኮሚቴው ካይረሡ ዓለም አቀፍ ስጋት ነው አይደለም የሚለውን ጨምሮ በምን መልኩ ለመቆጣጠር እንደሚቻል ምክረ ሃሳብን እንደሚያስቀምጥ ዶ/ር ቴድሮስ አስታውቀዋል። ሰዎችን የገደለው አዲሱ ኮሮናቫይረስ 223 ሰዎችን ማጥቃትና…
#UPDATE

- 2019-nCoV ቫይረስ በቻይና በርካታ ግዛቶች ተከስቷል
- እስካሁን ዘጠኝ (9) ሰዎች ሞተዋል
- 440 የቫይረሱ ተጠቂዎች አሉ
- ቫይረሱ በአሜሪካ፣ ታይላንድና ደቡብ ኮሪያ ተስፋፍቷል

2019 ኤን ሲ ኦ ቪ፦

ይህ ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን የሚያጠቃ ሲሆን አሁን ካለበት በላይ ሊስፋፋ እንደሚችል ማስጠንቀቂያዎች እየተላለፉ ነው። ቫይረሱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳየው መስፋፋት በቀጣይ በርካታ አካባቢዎችን ያዳርሳል የሚል ስጋትን አጭሯል።

2019 ኤንሲኦቪ ቫይረስ ከዚህ ቀደም በሰዎች ላይ ያልታየ መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ገልጸዋል። የመተንፈሻ አካል ችግር፣ ከፍተኛ ትኩሳት፣ መተንፈስ አለመቻል፣ ሳል እና የትንፋሽ መቆራረጥ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች የሚያሳዩት ምልክት ነው።

[ቢቢሲ፣ ኤፍ ቢ ሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NEBE #Election2012

በቅርቡ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእውቅና ሰርተፍኬት እና ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የሰጣቸው ፓርቲዎች የሚከተሉት ናቸው፦

1. ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ
2. አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
3. አማራ ጊዮናዊ ንቅናቄ
4. እናት ፓርቲ

- አገው ብሔራዊ ሸንጎ እና
- ብልጽግና ፓርቲ የምዝገባ ፈቃድ ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡

ጊዜያዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት ምንድነው ?

ጊዜያዊ የምዝገባ ሰርተፍኬት በአዋጅ 1162 አንቀጽ 66 ንኡስ አንቀጽ 3- 5 ድረስ ባለው የህግ አግባብ መሰረት የሚሰጥ ሲሆን ጊዜያዊ ሰርተፍኬተ ለማግኘት፦

- ማመልከቻ
- በጽሁፍ የሚቀርብ የምዝገባ ጥያቄ
- ለአገር አቀፍ ቢያንስ 200፣ ለክልላዊ ፓርቲ ቢያንስ 100 አመልካቾች የፈረሙበት የስብሰባ ቃለ ጉባኤ
- የሚመሰረተው የፓለቲካ ፓርቲ ጊዜያዊ ስም
- የምርጫ ህጉንና ተያያዥ ህጎችን የሚያከብሩ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እና ቦርዱ የሚወስነውን የአገልግሎት ክፍያ

ፍቃዱ የሚያገለግለው፦

- ለሶስት ወራት ብቻ (አመልካቾች በቂ ምክንያት አቅርበው የጠየቁ እንደሆነ ለተጨማሪ 3 ወር ሊራዘም ይችላል)

[የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ አስተዳደር ሹምሽር...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዚህ ሳምንት ውስጥ የካቢኔ ሹምሽር እንደሚያደርግ የሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። በምክትል ከንቲባነት አስተዳደሩን እየመሩ የሚገኙት ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) በዚህ ሳምንት የሚያደርጉትን ሹምሽር ለከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት አቅርበው እንደሚያፀድቁ ተሰምቷል።

ይነሳሉ ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ ምክትል ከንቲባና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊውን ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር) ጨምሮ የመሬት አስተዳደር፣ እንዲሁም የከተማው ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኃላፊዎችና ሌሎችም መሆናቸው ታውቋል። በተጨማሪም የትምህርት ቢሮ ኃላፊው፣ የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊውና የፍትሕ ቢሮ ኃላፊውም እንደሚነሱ ተገልጿል።

በመሬት አስተዳደር ላይ የሚደረገው ሹምሽር መጠነ ሰፊ እንደሚሆን የተሰማ ሲሆን፣ ከቢሮ ኃላፊው እስከ ወረዳ ድረስ የሚገኙ የመሬት አስተዳደር ኃላፊዎች በሙሉ ይነሳሉ። የዚህ ምክንያቱ ደግሞ በከተማዋ በተለያዩ ጊዜያት የሚከናወኑ የመሬት ወረራዎች፣ እንዲሁም በመሬት አስተዳደር ውስጥ ያለውን ችግር ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት ታስቦ እንደሆነ ነው የተሰማው።

ከሰሞኑ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ሹምሽር የሚነሱትን ኃላፊዎች በመተካት የአፋር፣ የሶማሌና የሐረሪ ተወላጆች የካቢኔ አባል ሆነው ይሾማሉ ተብሏል። በአዲሱ ካቢኔ የሚካተቱት አብዛኞቹ አዲስ አበባ የተወለዱና የኖሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ ሹምሽሩ በቀናት ውስጥ እንደሚካሄድና ለዚህም ሲባል የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ስብሰባ እንደሚጠራ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደህንነት ካሜራ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ...

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስጀመር በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ ተቋሙ አስቀድሞ ለመስራት ከአቀዳቸው ስራዎች መካከል የተማሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የደህንነት ካሜራ በግቢው ውስጥ መግጠም እንደሆነ ገልጿል፡፡

በዚሁ መሰረት የደህንነት ካሜራ በግቢው ውስጥ ተገጥሞ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ ይከሰት የነበረውን ህገ ወጥ ድርጊቶች ለመቆጣጠር ያስችላል ተብሎ ተገምቷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ወደ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ የሚገባ ማንኛውም ሰው ተማሪ ወይም ሠራተኛ መሆኑን የሚለይ ሲስተም በዩኒቨርሲቲው መምህራን አማካኝነት ተሰርቶ አገልግሎት ላይ መዋሉን አሳውቋል።

[ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚዓብሔር ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ካቢኔ መሰናበታቸውን የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

ከአንድ አመት በላይ የኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር የነበሩት ፈትለወርቅ ገብረእግዚዓብሔር ተሽረዉ በአቶ መላኩ አለበል ተተክተዋል። አቶ መላኩ አለበል የቀድሞው የንግድ ሚኒስቴር፣ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር ከመዋሐዱ በፊት የንግድ ሚኒስትር ነበሩ።

የአማራ ክልል የንግድ እና የኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ሆነው በመስራት ላይ የነበሩት አቶ መላኩ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በባሕር ዳር ከተማ ከተፈጸመው የከፍተኛ ባለሥልጣናት ግድያ ከተረፉት ባለስልጣናት አንዱ ናቸው።

[የጀርመን ድምፅ ሬድዮ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia