TIKVAH-ETHIOPIA
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል። "በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!" "እኛ ወንድምና…
#አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት #ቲክቫህ #ፒስሞዴል
የኡቡንቱ የማጠቃለያ ፕሮግራም በሀገራችን ብሔራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የጋሞ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ እሸቱ አልቶ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
በዚሁ ንግግራቸው ወቅት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሙሉ ወጣቶች መሆናቸው መርኃግብሩን ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡ አቶ እሸቱ አክለውም 500,000 ቤተሰቦችን ስለ ፍቅር እና አንድነት ብቻ እየሰበከ ላሰባሰበን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ቀጥሎም የኃይማኖት አባቶች፣የጋሞ አባቶች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ በተለይ ለወጣቱ ባስተላለፉት መልዕክት፦ እርስ በእርስ መከባበር እና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ማስቀደም እንደሚገባ አበክረው ገልፀዋል፡፡
አሁን "ስለ እርቅ ለመወያየትና ለማስታረቅ እድሜ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?" በሚል ርዕስ ወጣቱም ስለ ዕርቅ፣ ስለ ሰላም የበኩሉን እንዲወጣ በፈጣሪ አሰፋ አማካኝነት ምክክር እየተደረገ ይገኛል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል
በዛሬው የውይይት ዝግጅት ላይ በስፋት ከተነሱት ሀሳቦች መካከል ሰው በሰውነቱ፡ብቻ ሊከበር እንደሚገባውና ሰላምን የሚያስቀድም ትውልድ ለመገንባት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ ወጣቶች ደግሞ የጋሞ አባቶች ሰላም ወዳድነት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተግባር የተገለጠ መሆኑን ጠቅሰው እንዲህ በአንድ መድረክ ስለ ሰላም አብረው መምከራቸው ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጣቸው አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከውይይቱ በኀላ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው ስለ ሁሉም ሰው ልጆች ክብር የድርሻቸውን ለመወጣትና ይህን ለማድረግ እድሜ እንደማይገድበው በማመን የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሁሉ ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

በዛሬው መርኃ ግብራችን ላይ ታዳጊ ህጻናት እንዲህ በማለት መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡-
"እኛ ህጻናት የእናንተው ልጆች ነን ለሀገራችንም ተምረን ተስፋ የምንሆናት ትውልዶች እኛ ነን፡፡ በፍቅር አድገን ወላጆቻችንንና ሀገራችንን ማገዝ እንመኛለን፡፡"
"እኛ ህጻናት ፍቅር ያስፈልገናል፡፡ የወደፊት የሀገራችን ተስፋዎች እኛ ነንና ታላላቆቻችን ፍቅር ልታስተምሩን ይገባል"
"መልካምነትን የምንማረው ከታላላቆቻችን ነውና እባካችሁ መልካምነትን በተግባር አስተምሩን"
"አባቶቻችን ትላንት እርጥብ ሳር ይዘው ለሰው ልጅ እንዴት ክብር መስጠት እንዳለብን አስተምረውናልና እኛ ህጻናት ከልባችን እናመሰግናቸዋለን"
ይህንን መልዕክት በኮልታፋ አንደበታቸው ካቀረቡ በኀላ በትህትና ዝቅ ብለው የአባቶችን ጉልበት ስመዋል አባቶችም ህጻናቱን መርቀው የሰላም ምልክት የሆነውን ነጭ ባንዲራ አበርክተውላቸው ልጆቻቸው በሰላም እንዲኖሩ በሙሉ አቅማቸው ለሰው ልጅ ክብርና ለሰላም እንደሚተጉ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡
#ጋሞዞን #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል #ሃይሌሪዞርት
@tikvahethiopia @tsegabwolde

#እናመሰግናለን!
ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እና የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ለዚህ መርኃግብር መሳካት የድርሻችሁን ለተወጣችሁ ለመልካሙ ሀሳብ መልካምነታችሁን ለገለጻችሁ በሙሉ የዚህ ዝግጅት መሳካት ክብሩ የእናንተ ነውና ክብር ይገባችኀል፡፡
በተለይ ባስፈላጊው ነገር ሁሉ ላልተለየው ድጋፋቸው የጋሞ ዞን አስተዳደርን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ለዚህ ስራ ብዙ ድጋፍ ያደረጉ አካላትንም ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ በተለይም ኃይሌ ሪዞርት፣ ኦሞቲክ ጀነራል ትሬዲንግና ዊዝደም አካዳሚ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
ዲዛይነሮቻችን፦
•ፌቨን ደረጀ
•በረከት መንግስቱ
•ሂሩት ታዬ
•ሄርሜላ ተሾመ
•ቅዱስ ዮሐንስ
ሳውንድ ሲስተምና ዲኮር፦
•ሙሉቀን መሉ የሳውንድ ሲስተምና ዲኮር ስራ
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል
በቀጣይ በሌሎች የሀገራችን ከተሞች ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች (ከወጣቶች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ከአባ ገዳዎች ጋር ተመሳሳይ መድረኮችን እያዘጋጀን የምንመክር ይሆናል። እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ጋር ተመሳሳይ ዝግጅቶችን ይኖሩናል።
"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"
"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"
ቲክቫህ ቤተሰቦች!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

"አብሮነት ከጋሞ እስከ ጎንደር" የተሰኘ የጉዞ ፕሮግራምን በተመለከተ እና " የኢትዮጵያ የሀገር ሸማግሌዎች ሕብረት" ምስረታን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ በአርባ ምንጭ ተሰጠ!
የግንዛቤ ማስጨበጫውን ያዘጋጀው ሕብረመንጎል ቲቪ መልቲ ሚዲያ የተባለ የግል ድርጅት ሲሆን እስካሁን በመንግስትም ሆነ በሌሎች አካላቶች እየተሰሩ ያሉትን የሠላም እና የእርቅ ሥራዎችን ለማገዝ እና የበኩሉን አስተዋፅኦ ትውልዱ ላይ ለማሳረፍ ፣እንዲሁም ሃላፊነቱን ለመወጣት ይቅርታ፣ ፍቅርን ፣ መቻቻልን እና መከባበርን ፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትና አንድነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
More👇
https://telegra.ph/eth-12-08-3
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

የጉበት በሽታ በኢትዮጵያ!
የኢትዮጵያ ጉበት ጤና በጎ አድራጎት ድርጅት ምስረታ ጉባኤ በአዲስ አበባ አካሂዷል። ድርጅቱ በጉበት በሽታ ሐኪሞች፣ የህመሙ ተጠቂዎችና ሌሎች ጉዳዩ በሚመለከታቸው በጎ ፈቃደኞች እነደተመሰረተ ተገልጿል። በወቅቱ እንደተገለጸው በኢትዮጵያ የጉበት በሽታ ወይም ሄፓታይተስ በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል።
በዚህም ምክንያት የበሽታውን ተጎጂዎች ለመደገፍ እና በበሽታው መካለከል ዙሪያ ስራዎችን ለመስራት የኢትዮጵያ ጉበት ጤና በጎ አድራጎት ድርጅት ተመስርቷል።
በዓለማችን ከ325 ሚሊዮን ዜጎች በጉበት በሽታ የተጠቁ ሲሆን በኢትዮጵያ ደግሞ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በጉበት በሽታ መጠቃታቸው ተገልጿል። የጉበት በሽታ በተለይም ንጽህናውን ባልጠበቀ ምግብና ውሃ የሚተላለፍ ገዳይ በሽታ ሲሆን ከሄፓታይተስ ቢ ውጪ ሌሎቹ የጉበት በሽታዎች በወቅቱ ህክምና ካገኙ መዳን ይቻላል።
የሕክምና ባለሙያዎች አራት አይነት የጉበት በሽታዎች ያሉ ሲሆን ሄፓ ታይተስ A,B,C,D,E በሚል ያስቀምጧቸዋል። በጤና ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት አንጻር ደግሞ ሄፓታይተስ A እና E የጉበት በሽታ ተጠቂዎች በወቅቱ ህክምና ካገኙ በቀላሉ ከበሽታው መዳን የሚቻል ሲሆን ሄፓታይተስ ቢ እና ሲ የበሽታው ምልክቶች ሳይታዩ ከ20 አስከ 30 ዓመት ተደብቀው ሊቆዩ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ካሉ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን የበሽታው ተጠቂዎች ውስጥ የሄፓታይተስ ሲ የጉበት በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር እስከ 230 ሺህ የሚደርስ ሲሆን እስከ 110 ሺህ የሚሆኑት ደግሞ የሄፓታይተስ ቢ ጉበት በሽታ ተጠቂዎች ናቸው ተብሏል።
https://telegra.ph/ETH-12-08-4
(ETHIO FM 107.8)

‹‹የፀረ ሽብር ህጉ ሠለባዎች›› ጥያቄያቸውን በዝርዝር ለመንግስት አቀረቡ!
•በአንድነት ፓርክ ውስጥ የመታሰቢያ ሃውልት እንዲቆምላቸውም ጠይቀዋል!
ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑት በፖለቲካ እስር ምክንያት የፀረ ሽብር ህጉ ሠለባዎች የነበሩ ግለሰቦች ከመንግስት የሚፈልጉትን በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን፤ መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣቸው ዘንድ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ጫና እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡
ባለፈው አመት ጥር ወር ከአዲስ አበባ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ጋር ስለደረሰባቸው ጉዳትና መንግስት ሊያደርግላቸው ስላቀደው ድጋፍ የተነጋገሩ ቢሆንም እስከዛሬ አለመፈፀሙን የጠቆሙት የፀረ ሽብር ህጉ ሠለባዎች፤ መንግስት አሁንም አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጣቸው ከሆነ ኢትዮጵያ የፈረመቻቸውን የሰብአዊ መብት ጥበቃ ድንጋጌዎችን መነሻ በማድረግ፤ በአለማቀፍ ህግ መንግስትን ለመክሰስ መዘጋጀታቸውንም አስታውቀዋል፡፡
ባለፉት አመታት በፀረ ሽብር ህጉ ምርመራ ሲደረግባቸው በሃይልና በአስገዳጅነት የሠጡት ቃል፣ አሻራና የመሳሰሉት ሰነዶች በይፋ እንዲሠረዙላቸው፤ መንግስት ይቅርታ በጠየቀው መሠረት ለተፈፀመባቸው ግፍ በግልጽና በሠነድ እውቅና እንዲሰጣቸውና ያለፉት ማህደሮች መምከናቸውን እንዲያረጋግጥላቸውም ጠይቀዋል፡፡
በተጨማሪም በወቅቱ ንብረት ሃብታቸውን አጥተው ቤተሰባቸው ተበትኖ ለከፍተኛ ችግርና እንግልት ተዳርገው እንደነበር በማመልከትም መጠለያ እንዲሠጣቸውም ጠይቀዋል፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-12-08-2
(Addis Admas)