TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ170 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ!

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ170 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኦርሱላ ቮን ደር ሌይን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅትም ህብረቱ ለኢትዮጵያ ጤና፣ ምርጫ ቦርድ ማጠናከሪያ፣ የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንት የሚውል የ170 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አድርጓል።

ከዚህ ውስጥ 50 ሚሊየን ዩሮ ለጤና የሚውል ሲሆን፥ 10 ሚሊየን ዩሮው ደግሞ ለስራ እድል ፈጠራና ኢንቨስትመንት እንዲሁም 10 ሚሊየን ዩሮ ለምርጫ ቦርድ ማጠናከሪያ ይውላል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም 100 ሚሊየን ዩሮው በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ህብረት ማዕቀፍ ስምምነት መሰረት ሃገር በቀል ማሻሻያውን በቀጥታ ለማገዝ ይውላል ነው የተባለው። በተጨማሪም ድጋፉ የቀጠናውን መሰረተ ልማት ትስስር ለማሳደግ የሚውልም ይሆናል።

(ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት

የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"

ዝርዝር መረጀዎች ይኖሩናል!

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ጋሞዞን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ታላቅ አለም አቀፍ የዳዕዋ ዝግጅት በቡታጀራ ከተማ!

ከ 1 መቶ ሺህ በላይ ኢትዮጵያዋንም ጨምሮ የአለም ሀገራት የእስልምና እምነት ተከታዮችን እንግዶች ተቀብላ እያስተናገደች ነዉ። "አበሻ እጅቲማዕ" በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ይህ በሀገራችን ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄደዉን ታላቅ አለም አቀፍ የዳዕዋ ዝግጅት ነዉ። ከህንድ ፣ከሱዳን ፣ከኬንያና ከሌሎች የአለም ሀገራት የተዉጣጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች የዳዕዋዉ ተሳታፊ ናቸዉ።

ከ1 መቶ ሺህ በላይ አትዮጵያዉያን ጨምሮ የአለም ሀገራት እያስተናገደች ትገኛለች። "አበሻ እሽቲማ" ዳዕዋ ከሕዳር 26 ቀን 2012 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ማለት እስከ እሁዱ የሚቀጥል ነዉ፡፡

የከማዉ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸዉን ለእንግዶች ክፍት አድርገዉ እንግዳ የመቀበል ባህላቸዉን በከፍተኛ ሁኔታ እያንጸባረቁ ነዉ። ከተለያዩ የአለም ሃገራት ማለትም ከአፍሪካና ከአውሮፓ ሃገሮች ከ አንድ መቶ ሺህ በላይ የእስልምና የእምነቱ ተከታዮች የዳዕዋዉ ተሳታፊዎች ናቸዉ።

(Gurage Zone Administration Public Relation Office)

#SRTA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት የ"ኡቡንቱ አርባ ምንጭ" የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአሁን ሰዓት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ወጣቶች፣ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተገኙበት በሃይሌ ሪዞርት እየተካሄደ ይገኛል። "በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!" "እኛ ወንድምና…
#አርባምንጭ #ሃይሌሪዞርት #ቲክቫህ #ፒስሞዴል

የኡቡንቱ የማጠቃለያ ፕሮግራም በሀገራችን ብሔራዊ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን የጋሞ ዞን አስተዳደር ተወካይ አቶ እሸቱ አልቶ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በዚሁ ንግግራቸው ወቅት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች በሙሉ ወጣቶች መሆናቸው መርኃግብሩን ለየት እንደሚያደርገው ገልፀዋል፡፡ አቶ እሸቱ አክለውም 500,000 ቤተሰቦችን ስለ ፍቅር እና አንድነት ብቻ እየሰበከ ላሰባሰበን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የቴሌግራም ቻናል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ቀጥሎም የኃይማኖት አባቶች፣የጋሞ አባቶች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡ በተለይ ለወጣቱ ባስተላለፉት መልዕክት፦ እርስ በእርስ መከባበር እና ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን ማስቀደም እንደሚገባ አበክረው ገልፀዋል፡፡

አሁን "ስለ እርቅ ለመወያየትና ለማስታረቅ እድሜ ምክንያት ሊሆን ይችላልን?" በሚል ርዕስ ወጣቱም ስለ ዕርቅ፣ ስለ ሰላም የበኩሉን እንዲወጣ በፈጣሪ አሰፋ አማካኝነት ምክክር እየተደረገ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል

በዛሬው የውይይት ዝግጅት ላይ በስፋት ከተነሱት ሀሳቦች መካከል ሰው በሰውነቱ፡ብቻ ሊከበር እንደሚገባውና ሰላምን የሚያስቀድም ትውልድ ለመገንባት ሁሉም የበኩሉን ሊወጣ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በውይይቱ የተሳተፉ ወጣቶች ደግሞ የጋሞ አባቶች ሰላም ወዳድነት ከአንድም ሁለት ጊዜ በተግባር የተገለጠ መሆኑን ጠቅሰው እንዲህ በአንድ መድረክ ስለ ሰላም አብረው መምከራቸው ትልቅ ትምህርት እንደሚሰጣቸው አንስተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከውይይቱ በኀላ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው ስለ ሁሉም ሰው ልጆች ክብር የድርሻቸውን ለመወጣትና ይህን ለማድረግ እድሜ እንደማይገድበው በማመን የሚጠበቅባቸውን ሀላፊነት ሁሉ ለመወጣት ቃል ገብተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዛሬው መርኃ ግብራችን ላይ ታዳጊ ህጻናት እንዲህ በማለት መልዕክታቸውን አቅርበዋል፡-

"እኛ ህጻናት የእናንተው ልጆች ነን ለሀገራችንም ተምረን ተስፋ የምንሆናት ትውልዶች እኛ ነን፡፡ በፍቅር አድገን ወላጆቻችንንና ሀገራችንን ማገዝ እንመኛለን፡፡"

"እኛ ህጻናት ፍቅር ያስፈልገናል፡፡ የወደፊት የሀገራችን ተስፋዎች እኛ ነንና ታላላቆቻችን ፍቅር ልታስተምሩን ይገባል"

"መልካምነትን የምንማረው ከታላላቆቻችን ነውና እባካችሁ መልካምነትን በተግባር አስተምሩን"

"አባቶቻችን ትላንት እርጥብ ሳር ይዘው ለሰው ልጅ እንዴት ክብር መስጠት እንዳለብን አስተምረውናልና እኛ ህጻናት ከልባችን እናመሰግናቸዋለን"

ይህንን መልዕክት በኮልታፋ አንደበታቸው ካቀረቡ በኀላ በትህትና ዝቅ ብለው የአባቶችን ጉልበት ስመዋል አባቶችም ህጻናቱን መርቀው የሰላም ምልክት የሆነውን ነጭ ባንዲራ አበርክተውላቸው ልጆቻቸው በሰላም እንዲኖሩ በሙሉ አቅማቸው ለሰው ልጅ ክብርና ለሰላም እንደሚተጉ ቃል ገብተውላቸዋል፡፡

#ጋሞዞን #አርባምንጭ #ቲክቫህ #ፒስሞዴል #ሃይሌሪዞርት

@tikvahethiopia @tsegabwolde
#እናመሰግናለን!

ጥሪያችንን አክብራችሁ የተገኛችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የጋሞ አባቶች፣ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች እና የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ ላቅ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ለዚህ መርኃግብር መሳካት የድርሻችሁን ለተወጣችሁ ለመልካሙ ሀሳብ መልካምነታችሁን ለገለጻችሁ በሙሉ የዚህ ዝግጅት መሳካት ክብሩ የእናንተ ነውና ክብር ይገባችኀል፡፡

በተለይ ባስፈላጊው ነገር ሁሉ ላልተለየው ድጋፋቸው የጋሞ ዞን አስተዳደርን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ለዚህ ስራ ብዙ ድጋፍ ያደረጉ አካላትንም ሳናመሰግን አናልፍም፡፡ በተለይም ኃይሌ ሪዞርት፣ ኦሞቲክ ጀነራል ትሬዲንግና ዊዝደም አካዳሚ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

ዲዛይነሮቻችን፦
•ፌቨን ደረጀ
•በረከት መንግስቱ
•ሂሩት ታዬ
•ሄርሜላ ተሾመ
•ቅዱስ ዮሐንስ

ሳውንድ ሲስተምና ዲኮር፦
•ሙሉቀን መሉ የሳውንድ ሲስተምና ዲኮር ስራ

#ኡቡንቱ #አርባምንጭ #ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል

በቀጣይ በሌሎች የሀገራችን ከተሞች ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች (ከወጣቶች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከሃገር ሽማግሌዎች፣ ከአባ ገዳዎች ጋር ተመሳሳይ መድረኮችን እያዘጋጀን የምንመክር ይሆናል። እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች፣ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ጋር ተመሳሳይ ዝግጅቶችን ይኖሩናል።

"በምክንያት የሚያምን ሚዛናዊ በሆነ ትውልድ መካከል የሚፈጠር የሃሳብ ልዩነት የጥንካሬ ምንጭ እንጂ የጠብ መነሻ አይሆንም!"

"እኛ ወንድምና እህት ነን፤ እዚህ ምድር ላይ አብረን እንጓዛለን!"

ቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tsegabwolde @tikvahethiopia