#Day3 #አርባምንጭ #ዊዝደምአካዳሚ
"የነገ ተስፋችሁ እኛነንና ፍቅርን አስተምሩን"
ዛሬ ከሰዓት በኃላ በነበረን መርኃግብር "በዊዝደም አካዳሚ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት" ተማሪዎች ጋር ጥሩ ጊዜ አሳልፈናል። ተማሪዎቹ ልዩ ልዩ የባህል ፕሮግራሞችን አዘጋጅተው የጠበቁን ሲሆን በህጻናት ግጥሞች ቀርበዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ አባቶች ተገኝተው ልጆቹን የመረቁ ሲሆን የአርባ ምንጭ የህክምና ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ጋሞዞን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ተስፋችሁ እኛ ነን፤ ፍቅር አስተምሩን!
አርባ ምንጭ❤️ዊዝደም አካዳሚ❤️
እነዚህ ትንንሽ የነገ ሀገር ተረካቢዎች ስናይ ተስፋችን ተሟጦ እንዳላለቀ በደንብ እንገነዘባለን። ለተተኪው ትውልዱ ከቂም፣ ከክፋት፣ ከተንኮል፣ከመገፋፋት፣ ከጥላቻነፃ የሆነች ሀገር የማስረከብ ግዴታ አለብን። ለነዚህ ሀገር ተረካቢ ልጆች ፍቅር፣ መዋደድን፣ መተባበርን፣ መደጋገፍን የማስተማር ግዴታ አለበን።
#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፒስሞዴል #ኡቡንቱ #Day3
ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛው አይነት ሃሳብ፣ አስተያየት እና መልዕክት ካላችሁ በ @tsegabwolde ወይም በ @tikvahethiopiaBot ላይ ማድረስ ትችላላችሁ!
@tikvahethiopia

የኢትዮጵያና የአሜሪካ የጦር አዛዦች ተገናኙ!
የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታ ማዦር ሹም ጄነራል አደም መሐመድ ማህሙዴና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር ኃይሎች ምክትል ኤታ ማዦር ሹም ጄነራል ጆን ሃይተን ትላንት ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ ተገናኝተዋል፡፡
የኢታ ማዦር ሹም ፅህፈት ቤቱ ቃል አቀባይ ሻለቃ ትሪሻ ጉይቦ ዛሬ ባወጡት ፅሁፍ ነው የሁለቱን የጦሮች አዛዦች ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ላይ ተገናኝቶ መወያየት ያሳወቁት፡፡
ለአካባቢያዊ መረጋጋት ኢትዮጵያ ስላላት አስተዋፅዖና ቁርጠኛነት፣ በመላ አፍሪካ ላለው የተባበሩት መንግሥታት ሰላም የማስከበር ተልዕኮዎች ስላላቸው ድጋፍም ጄነራል ሃይተን ለጄነራል አደም ምሥጋና አቅርበዋል፡፡ አዛዦቹ ወታደራዊ ትብብሮቻቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው መንገዶች ላይም ተወያይተዋል፡፡
በዩናይትድ ስቴትስና በኢትዮጵያ መካከል ያለው አጋርነት ለምሥራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋር እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን የቃል አቀባይዋ የሻለቃ ጊዮቦ የፅሁፍ መግለጫ አመልክቷል፡፡
(ቪኦኤ)

አሜሪካ ጉብኝት እያደረጉ ላሉት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ የአሜሪካ ጦር የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥ ፕሮግራም አዘጋጅቷል!
ፕሮግራሙ የተከናወነው ቪርጂንያ፣ አርሊንግተን በሚገኘው "ያልታወቀው ወታደር መቃብር" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ሲሆን የአሜሪካ ጦር ብርጋዲየር ጀነራል ኦማር ጆንስ አዘጋጁ ነበሩ።
Photo: U.S. Army Photography
(Elias Meseret)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሮግራሙ የተከናወነው ቪርጂንያ፣ አርሊንግተን በሚገኘው "ያልታወቀው ወታደር መቃብር" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ሲሆን የአሜሪካ ጦር ብርጋዲየር ጀነራል ኦማር ጆንስ አዘጋጁ ነበሩ።
Photo: U.S. Army Photography
(Elias Meseret)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመከላከያ ሚ/ር አቶ ለማ መገርሳ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ቲቦር ናጅ ጋር ተወያዩ!
የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ቲቦር ናጅ ጋር በአፍሪካ ቀንድ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በዋሽንግተን ዲሲ ተወያይተዋል።
በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በሶማልያ የተሰማራው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ለቀጣናው ገንቢ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሆነ በውይይቱ ወቅት መገለፁን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል ።
በአቶ ለማ መገርሳ የሚመራው የልዑካን ቡድን ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በአሜሪካ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
(ኢቢሲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

የትግራይ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን 87 ሚሊዮን ብር የመንግስት ገንዘብ እንዲመለስ አደረገ!
የትግራይ ክልል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በተያዘው ሩብ ዓመት ብቻ በተለያየ ምክንያት ተጭበርብሮ የቆየ ከ87 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንግስት ገቢ እንዲሆን ማድረጉን አስታወቀ። የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በዓል በክልል ደረጃ ለ14ኛ ጊዜ በተለያዩ ዝግጅቶች በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ እንደሚከበር ተገልፇል።
የክልሉ ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ብርሃነ ተክሉ እንደገለጹት ከመንግስት ካዝና ያለ አግባብ ለግለሰቦች ተከፍሎ የነበረ የመንግስት ገንዘብ ተመላሽ እንዲሆን ተደርገዋል። የክልሉ ውሀ ስራዎች ኮንስራክሽን ኢንተርፕራይዝ ያለ አግባብ ከአንድ ግለሰብ ጋር በተጋነነ ዋጋ ያደረገውን የስራ ስምምነት እንዲሰረዝ በማድረግ 83 ሚሊዮን ብር ለመንግስት እንዲመለስ መደረጉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
ቀሪው ደግሞ በመቀሌና ዓድዋ ከተሞች ለሁለት አመታት ያህል ለመንግስት መከፈል የነበረበት የከተማ መሬት የሊዝ ውዝፍ ክፍያ መሆኑን አስረድተዋል። ከማጭበርበር ስራው ጋር ግንኝነት የነበራቸው የመንግስት ተቋማትና ግለሰቦችም በህግ እንዲጠየቁ ይደረጋል ብለዋል።
(ኢዜአ)

የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ የቀላል ባቡር ድጎማን አልከፍልም አለ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የቀላል ባቡር ሥራ ከጀመረበት 2008 ዓ.ም እስክ ጥር 18 ቀን 2011 ዓ.ም ያለውን ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ የድጎማ ማካካሻ ክፍያ ለፌዴራል መንግሥት እንደማይከፍል ውሳኔ አሳለፈ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽህፈት ቤት ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ በጻፈው ደብዳቤ ከጥር 18 ቀን 2011 ዓ.ም በፊት ለቀላል ባቡር አገልግሎት የቀረበውን የድጎማ ማካካሻ እንደማይከፈል ካቢኔው በዘጠነኛው መደበኛ ስብሰባው ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል።
ለካቢኔው ውሳኔ መነሻ የሆነው የቀድሞው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የአሁኑ የገንዘብ ሚኒስቴር በታህሳስ 10 ቀን 2010 ለከተማው የመንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የድጎማ ማካካሻ ገንዘብ እንዲከፍል መጠየቁ ነው። ሚኒስቴሩ በጻፈው ደብዳቤ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት ወጪን ከተሳፋሪዎች የሚገኘው ገቢ ስለማይሸፍን የድጎማ ማካካሻ በከተማ አስተዳደር በኩል እንዲሸፈን ጠይቋል።
(ኢፕድ)

"በመንገድ ትራፊክ አደጋ በየቀኑ 12 ሰዎች ይሞታሉ" — የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን
የመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች ማስታወሻ ቀን “ሕይወት የተሽከርካሪ አካል አይደለም መለዋወጫ የለውም” በሚል መሪ ሃሳብ ሲታሰብ፤ በኢትዮጵያ በትራፊክ አደጋ በየቀኑ 12 ሰዎች ሕይወታቸውን ያጣሉ ተባለ።
14ኛው የዓለም የመንገድ ትራፊክ አደጋ ተጎጂዎች ማስታወሻ ቀን በኢትዮጵያ ለ12ኛ ጊዜ “ሕይወት የተሽከርካሪ አካል አይደለም መለዋወጫ የለውም” በሚል መሪ ሃሳብ በአቤት ሆስፒታል አዘጋጅነት ትላንት በአዲስ አበባ ታስቦ ውሏል።
የመንገድ ትራፊክ አደጋ አስከፊነት በተለይም ባላደጉ አገራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። የአደጋው ሰለባ ከሆኑት አገራት ጋር በምትመደበው ኢትዮጵያም በ2011 ዓ.ም ብቻ 4 ሺህ 597 ዜጎቿ በመንገድ ትራፊክ አደጋ ለሕልፈት ተዳርገዋል።
ባለፉት ሶስት ወራትም በርካታ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋዎች ደርሰው በአዲስ አበባ ብቻ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች መጎዳታቸውን የጤና ተቋማት መረጃዎች ያሳያሉ።
የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ምትኩ አስማረ አገሪቷ ካላት የተሽከርካሪ ቁጥር አንጻር እየደረሰ ያለው አደጋ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል። የ2010 ዓ.ም የትራፊክ አደጋ ከ2011 ዓ.ም ጋር ሲነጻጸር የቀነሰ ቢሆንም አሁንም በየቀኑ የ12 ሰዎች ሕይወት እየጠፋ ነው ብለዋል።
(ENA)

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በስልጣን ላይ ስለመቆየት እና የሀገሪቱን ህዝብ ስለማገልገል ... #DrAbiyAhemed
ቪድዮ: ፋይል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቪድዮ: ፋይል
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በገብረ ጉራቻ በአራት ጸጥታ አስከባሪዎች ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ!
በገብረ ጉራቻ ከተማ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ አራት የመንግሥት ጸጥታ አስከባሪ አባላት ላይ ጉዳት ደረሰ። ትናንት (ሃሙስ) ምሽት 2፡30 ገደማ በሰሜን ሸዋ ዞን ኩዩ ወረዳ ገብረ ጉራቻ ከተማ የተፈጸመው ጥቃት ፖሊስ ጣቢያ ፊት ለፊት መሆኑን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ ደንደዓ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጥቃቱ የመንግሥት የጸጥታ አስከባሪ አካላትን ለመግደል ያለመ መሆኑን አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
የግድያ ሙከራው ኢላማ ከነበሩት መካከል የኩዩ ወረዳ ፖሊስ ኃላፊ ዋና ሳጅን አዱኛ ደቀባ እና አብረዋቸው የነበሩ ሌላ የወረዳው ፖሊስ አባል እንደሚገኙበት አስተዳዳሪው ይናገራሉ።
ጥቃቱ የተፈጸመው የፖሊስ አባላቱ እራት በልተው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ግቢ እየገቡ ሳለ እንደነበር የሚናገሩት የኩዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደረጄ፤ በፖሊስ አባላቱ ላይ በሁለት አቅጣጫ ተኩስ እንደተከፈተባቸው ያስረዳሉ።
"ዋና ሳጅን አዱኛ እግራቸውን ነው የተመቱት። አብሯቸው የነበረው የፖሊስ አባል ደግሞ እጁን ነው የተመታው" የሚሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ የተኩስ ድምጽ ሰምተው ወደ በስፍራው የተገኙ ሌሎች ሁለት የቀበሌ ሚሊሻዎች ላይም ተኩስ ተከፍቶ ጉዳት ደርሶባቸዋል" በማለት ትናንት ምሽት በገብረ ጉራቻ ከተማ የተፈጠረውን ክስተት ያስረዳሉ።
አቶ ደረጄ በአራቱም የጸጥታ አስከባሪ አካላት ላይ የደረሰው ጉዳት ለህይወት የሚያስጋ አለመሆኑን የተናገሩ ሲሆን፤ ሶስቱ እግራቸው ላይ አንዱ ደግሞ እጁ ላይ ጉዳት ማጋጠሙን አስረድተዋል።
More👇
https://telegra.ph/BBC-12-06

#ኡቡንቱ #Ubuntu #አርባምንጭዩኒቨርሲቲ
(ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ) የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ በዩኒቨርሲቲው ስላለው ሰላም እንዲሁም አጠቃላይ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተከታዩን መልዕክት አስተላልፈዋል፦
"በከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች የአዕምሮ ሥራ የሚሰሩ ተማሪዎች ናቸው፡፡ በዩኒቨርሲቲው የሚቆዩበት ጊዜም አጭር በመሆኑ ባላቸው ጊዜ አዕምሯቸውን ሙሉ ለሙሉ በሳይንሱ ሥራ ላይ ቢያተኩሩ ወደፊት ለሀገራቸውም ሆነ ለራሳቸው ሙሉ የሆነ የዕውቀትና የክህሎት አስተሳሰብ ታጥቀው ይወጣሉ፡፡ ይህ ባልሆነበት ግን በሌሎች ሀሳብና አስተሳሰብ ጊዜን ማባከን በተሟላ መልኩ ሊያገኙት የሚችሉትን ነገሮችን ያጓድላል፡፡ እኛም እንደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አሁን ላይ ትኩረት አድርገን እየሰራን የምንገኘው ጊዜን መሻማት ላይ ነው፡፡ በዚህም የትምህርት ዘመኑ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲቀጥል እየሰራን እንገኛለን፡፡ ሌሎች ግቢዎች ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች እኛንም እኩል የሚያሙን ጉዳዮች ናቸው፡፡ ያሉ ችግሮች ተቀርፈው ጊዜን በአግባቡ መጠቀም እንዲቻል ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይጠበቅበታል፡፡"

#Setaweet
#አለኝታ
#orangetheworld
#16DaysOfActivism
#GenerationEquality
ጾታዊ እኩልነት ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት እና ጾታዊ ጥቃትን ለመቀነስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገው የ16 ቀን ንቅናቄ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ሴታዊት የተሰኘው ድርጅትም በማህበራዊ ድረ፟ ገጾች ላይ ፎቶግራፎችን፣ ምስሎችን፣ የተለያዩ የውይይት ርእሶችን በመፍጠር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ቪድዮውን ሼር ያድርጉት!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#አለኝታ
#orangetheworld
#16DaysOfActivism
#GenerationEquality
ጾታዊ እኩልነት ላይ የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት እና ጾታዊ ጥቃትን ለመቀነስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረገው የ16 ቀን ንቅናቄ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ሴታዊት የተሰኘው ድርጅትም በማህበራዊ ድረ፟ ገጾች ላይ ፎቶግራፎችን፣ ምስሎችን፣ የተለያዩ የውይይት ርእሶችን በመፍጠር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ቪድዮውን ሼር ያድርጉት!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#FakeNewsAlert
"የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የስራ መልቀቂያ አላስገቡም!"-የመከላከያ ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ክፍል
አቶ ለማ መገርሳ የስራ መልቀቂያ አስገብተዋል ተብሎ እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሐሰት መሆኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ። የመከላከያ ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ክፍል ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ እንዳስታወቀው ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳ መልቀቂያ አላስገቡም ብሏል።
አቶ ለማ በአሜሪካ ስራቸውን በማከናወን ላይ ናቸው የስራ መልቀቂያ አስገቡ ተብሎ እየተናፈሰ ያለው መረጃ ከአውነት የራቀ መሆኑን አስታውቋል። የኮሚንኬሽን ክፍሉ ለሬድዮ ጣቢያው እንደገለፀው በተቋም ደረጃ እንደዚህ አይነት መረጃ የለም ውሸት ነው ሲል የተናገረ ሲሆን ከዛ ውጪ የሚናፈሰው ወሬ የፖለቲከኞች እንጂ በተቋም ደረጃ ስለዚህ ጉዳይ የተነሳ ነገር የለም ብሏል፡፡
(ETHIO FM 107.8)

በድጋሚ ለሀገራችን መንግስት ጥሪ እናቀርባለን!
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎችን በንቃት ሲከታተል ቆይቷል። ተማሪዎች የሚያቀርቡትን ቅሬታዎች፣ ጥያቄዎች፣ የሚደርሱባቸው ችግሮችን በገፁ አማካኝነት ለሚመለከታቸው ሲያቀርብ ነበር። ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት የነበረው እንቅስቃሴ እና በዚህ ዓመት የተመለከትናቸው ፈፅሞ የሚገናኙ አይደሉም። መረጃዎች ሁሉ መልካቸውን የሚቀይሩበት፣ ነገሮች የሚቀጣጠሉበት ሁኔታም ከዚህ በፊት ገጥሞን አያውቅም።
ከዚህ ቀደም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በጋር ሆነው ችግሮቻቸው እንዲፈቱላቸው ሲተገሉ፣ ሢጠይቁ፣ ድምፃቸውን በጋራ ሲያሰሙ ነው የምናውቀው አሁን ግን እየተመለከትነው ያለነው ነገር እጅግ ተቃራኒው ነው። ይህ ጉዳይ ነገ ሳይሆን ዛሬ እልባት ካልተሰጠው ሀገሪቷን ከባድ ፈተና ውስጥ ይከታታል። በየዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከህግ በላይ የሆኑ አካላት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴዎች በዝምታ እየታለፈ፣ በሚዲያዎች እየቀርቡ የተዛቡ እና የተሳሳቱ መረጃዎች መስጠት ተማሪዎችን እና የተማሪ ወላጆችን እያስቆጣ ነው።
ውድ ቤተሰበቦቻችን ዛሬም የሚሰማን የመንግስት አካል ካለ እንጮሃለን፤ የት የት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተለይተው እንዳይማሩ እየተደረገ እንደሆነ፣ የት የት ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንደተቋረጠ፣ የትኞቹ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ተማሪዎች ማስፈራሪያ እንደሚደርሳቸው፣ በየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የማስጠንቀቂያ ወረቀቶች እንደልብ እንደሚሰራጩ፣ ከየትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በስጋት ምክንያት በርካታ ተማሪዎች ግቢ ለቀው እንደወጡ፣ በየትኛው ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሚደርሳቸውን ማስፈራሪያ ምክንያት ሰግተው አዳራሽ ውስጥ እንዳሉ መንግስትና የዩኒቨርሲቲ አስተዳደሮች ጠንቅቀው እንደሚያውቁ እናምናለን።
ተጨማሪ አንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-12-06

840 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ተመለሱ!
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳኡዲ አረቢያ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በሳኡዲ እስር ቤቶች ከአምስት እስከ ስምንት አመት ተፈርዶባቸው የነበሩ 840 ኢትዮጵያዊያን በፈቃዳቻው ዛሬ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ኢትዮጵያዊያኑ ቀይ ባህርን አቋርጠው የሳኡዲን ድንበር ሲሻገሩ የተያዙ እና በሳኡዲ አረቢያ በጂዳ እና ጂዛን ግዛት በሚገኙ እስር ቤቶች ይኖሩ የነበሩ ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸው ተጠቅሷል። ተመላሾቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማሪፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ዮሃንስ ሾዴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።