TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ለማ በVIP ተርሚናል ነው የተስተናገዱት!

(Elias Meseret)

KMN በተባለ የፌስቡክ ገፅ "የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ እና የቦሌው አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ድራማ" ብሎ የወጣው መረጃ የፈጠራ ወሬ እንደሆነ ከኤርፖርት አካባቢ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል ሲል የAssociated Press ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ገልጿል።

ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ዛሬ ጠዋት አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት አቶ ለማ በVIP ተርሚናል የተስተናገዱ ሲሆን "እንደ ክቡር ሚኒስተርነታቸው እና ለሁሉም ሚኒስትሮች እንደሚደረገው በስነስርአት ተስተናግደዋል። ከዛ ውጪ ያለው የፈጠራ ወሬ ነው።" ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የተዘነጋው የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ጉዳይ!

በኢትዮጵያ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) መቀነስ ባለበት ደረጃ እየቀነሰ አለመሆኑን ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) ስርጭት ከ1 በመቶ በላይ ከሆነ በወረርሽኝ መልኩ የሚገለጽ መሆኑን የፌደራል ኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠሪያ ጽሕፈት ቤት ይገልጻል፡፡ በዚህም መሰረት ስርጭቱ ወረርሽኝ መልክ ያልተከሰተባቸው የሶማሌ፣ የኦሮሚያና የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች ብቻ ናቸው፡፡ ቀደም ብሎ በመጣው ውጤት መርካት፣ በበሽታው የመሞት እና የአልጋ ቁራኛነት መቀነስ፣ በየእርከኑ ያሉ የአመራር አካላት ትኩረት መላላት፣ የበጀት ዕጥረት እንዲሁም በመንግስት የመዋቅር ማስተካከያዎች በቂ ትኩረት ማጣት ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ ስርጭት መጨመር በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡

(OBN)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትኩረት...

አሁንም ቢሆን በአንዳንድ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚበተኑት የማስፈራሪያ ወረቀቶች ቀጥለዋል፡፡ ይህ ጉዳይ ተማሪውን ሰላም ከሚነሱ ጉዳዮች ዋነኛውና አንዱ ቢሆንም እነዚህን ወረቀቶች በሚያዘጋጁና በተደራጀ መልኩ በመማሪያ ክፍል በመኝታ አከባቢ እየተንቀሳቀሱ ማስፈራሪያ የሚያደርጉ አካላት ላይ ትኩረት ያለመደረጉ የታሰበውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ እንዳይጀመር ያደርገዋል። በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከዚህ አካባቢ የመጣችሁ አትማሩም፣ ከዚህ ሂዱልን የሚሉ ለሀገር አደጋ የሆነ ድርጊት እየተፈፀመ ይገኛል። ይህ ጉዳይ ከወዲሁ ትኩረት ካልተሰጠው ለዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ሳይሆን ለሀገር አደጋ ነው። ተማሪዎች የሀገሪቱ ሚዲያዎች እያቀረቡት ያሉት ዘገባ እውነታውን የደበቀ እንደሆነ ገልፀዋል። ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች የሚላኩትን የስጋት መልዕክቶች እንዲሁም ጥቆማዎች እና ችግሮች ለሚመለከታቸው አካላት ለማድረስ ጥረት እያደረግን እንገኛለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ የተገነባዉ የኢፈ ቱላ ሱሮ ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታዉ ተጠናቆ ትምህርት እየሰጠ ነው!

በቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸዉ በምእራብ ጉጂ ሱሮ ባርጉዳ የተገነባዉ የኢፈ ቱላ ሱሮ ብርሀን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታዉ ተጠናቆ ትምህርት እየሰጠ እንደሚገኝ የቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት አስታወቀ፡፡ ፅ/ቤቱ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ትምህርት ቤቶችን እያስገነባ መሆኑ ይታወቃል፡፡

(EPA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ብልፅግናፓርቲ #NEBE

"ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ እስካላሸነፈ ድረስ ቀሪውን የስልጣን ዘመን መቆጣጠር አይችልም!" - አቶ ዘራይ ወልደሰንበት (የህግ ባለሞያ)
.
.
"የተለያዩ ሰዎች የፖለቲካ ፓርቲ ሲመሰርቱም ሆነ ስማቸውን ሲቀይሩ እኛ አስተያየት አንሰጥም። ይህም ጉዳይ ከዚህ የተለየ አይደለም። እኛን በቀጥታ የሚመለከተን ምዝገባ ነው። የብልፅግና ፓርቲ ለቦርዱ የምዝገባ ጥያቄ እስካሁን አላቀረበም። ጥያቄውን ካቀረቡ ልክ እንደማንኛውም አሰራር አይተን እንመዘግባለን። ለብልፅግና ፓርቲ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊት የነበሩ ፓርቲዎች ስማቸውን ሲቀይሩ፣ ሲዋሃዱ ወይም ተለያየን ሲሉ እኛ ጋር በተለያየ መልኩ የመጣ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ምንም አይነት ምላሽም ሆነ አስተያየት አንሠጥም!" - ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ (በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር)

(ቢቢሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ የመቀዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ መስራችን አነጋገሩ!

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ የመቀዶኒያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ መስራችን አቶ ብንያም በለጠን እና የስራ ባልደረቦቻቸውን በብሔራዊ ቤተ መንግስት አነጋግረዋል። ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ የተሰራውን ስራ አድንቀው የመቀዶኒያ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚቻለውን በማድረግ እንደሚደግፉ በመግለፅ የማበረታቻ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ፡- የፕሬዚዳንት ፅ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኤርትራዊው ሙዚቀኛ በአዲስ አበባ ጥቃት ደረሰበት!

''ወዲ ማማ'' በሚል የቅጽል ስም የሚታወቀው ኤርትራዊ ሙዚቀኛ፣ ተክለ ነጋሲ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በማይታወቁ ሰዎች ጥቃት እንደተፈጸመበት ተነገረ።

ድምጻዊው ባለፈው እሁድ ከሰዓት በኋላ ገርጂ በሚገኘው አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በእግሩ በሚጓዝበት ወቅት ማንነታቸውን በማያውቃቸው አምስት ሰዎች ጥቃቱ እንደተፈጸመበት ተክለ ለቢቢሲ ተናግሯል።

ጨምሮም ጥቃቱን ከፈጸሙበት ሰዎች ጋር ምንም አይነት ንግግር እንዳልነበረና አላማቸው ጉዳት ማድረስ እንደነበረ ገልጿል። "ምንም አይነት ንግግር አልተናገሩኝም፤ በቀጥታ ወደ ድብደባ ነበር የገቡት" ሲል ተናግሯል።

ድምጻዊው ተክለ ነጋሲ ሱዳን ውስጥ በነበረበት ጊዜ በደረሰበት የመኪና አደጋ እግሩ ተሰብሮ እንደነበር ጠቅሶ፤ እግሩ ላይ ብረት እንዳለውና ጥቃት ያደረሱበት ሰዎች በተደጋጋሚ በአደጋው ጉዳት የደረሰበት እግሩን ይመቱት እንደነበር ተናግሯል።

ከዚህም በመነሳት ከባድ አደጋን ለማድረስ ዕቅድ እንደነበራቸውና ጥቃቱ የታቀደና "በደንብ የሚያውቁኝ መሆን አለባቸው" በማለት ግምቱን አስቀምጧል።

ድማጻዊ ወዲ ማማ በደረሰበት ድብደባ ሳቢያ በቀኝ እጁ፣ በአፍንጫው፣ በጭንቅላቱና የግራ ኩላሊቱ ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበትም ለቢቢሲ ተናግሯል።

https://telegra.ph/BBC-12-03

(BBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"አገራችን ኢትዮጵያ እጅግ አስፈሪና አደገኛ ሁኔታ ላይ ትግኛለች!" - ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል
.
.
አገራችን ኢትዮጵያ፣ እጅግ አስፈሪና አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ ህገ መንግስትና ህብረ ብሄራዊ ፌደራሊዝም ስርዓትን የማዳን አገር አቀፍ መድረክ ላይ ለመሳተፍ ለመጡ ተሳታፊዎች የመክፈቻ ንግግር ያቀረቡት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ገለፁ፡፡

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል አገራችን ውስጥ ህገ መንግስቱ በግላጭ በሚጣስበት፣ የሰላም እጦትና የዜጎች ደህንነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ በመጣበት፣ መፈናቀልና የንብረት ውድመት የዘወትር ተግባር በሆነበትና የዜጎች ህይወት መጥፋት በተበራከተበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ካለ በሗላ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የጠቅላይነት አስተሳሰብ የተጫናችው ተግባራት በአግሪቱ እይተፈፀሙ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-03

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ ከአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ተወያየ!

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ ከአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር በዛሬው እለት ውይይት አድርጓል።

በመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ ከትናንትናው እለት ጀምሮ በአሜሪካ ጉብኝት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራውና የኢፌዴሪ ጦር ሀይሎች ኢታማዦር ሹም ጀነራል አደም መሀመድ የተካተተበት ልኡኩ በዛሬው እለትም ከአሜሪካ ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ አስታውቀዋል።

በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት ልዑክ በአሜሪካ እያደረገ ያለው ጉብኝት የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን የሁለትዮሽ የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አምባሳደር ፍጹም ገልፀዋል።

(FBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
እንኳን ደስ አለን 500,000 ደረሰናል!

ውድ ቤተሰቦቻችን ለዚህ መድረሳችን ትልቁን ድርሻ የምትወስዱት እናተ ናችሁ። ጥላቻ የምትፀየፉ፣ ስድብን የምትፀየፉ፣ ለሰው ልጆች ሁሉ የምትጨነቁ፣ ለሀገር ሰላም እንቅልፍ የምታጡ፣ ሰው የምታከብሩ፣ ስሜታዊነት የማየጠቃችሁ፣ እርቆ አሳቢ የሆናችሁ፣ መረጀዎችን አመዛዝናችሁ የምትቀበሉ፣ የተቸገሩትን የምትደግፉ፣ ሁሌም ለመልካም ስራ ቀድማችሁ የምትገኙ ውድ፣ እንቁ የሀገራችን ዜጎች ናችሁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ለናት ተነግሮ፣ ተፅፎ የማያልቅ ክብር አለን!

በያካባቢያችሁ ያሉትን ሁኔታዎች በመሳወቅ፣ መረጃዎች ሳትደብቁ የምትገልፁ፣ በመንግስት የሚፈፀሙ ተገቢ ያልሆኑ ስራዎች አፍረጥርጣችሁ የምትገልፁ፣ በዚህ ሀገር በየትኛውም ቦታ በክቡር የሰው ልጅ ላይ የሚፈፀሙ ብደሎችን ሳትፈሩ የምትጠቁሙ፣ አንደኛው ሌላኛው አከባቢ ስላለው ጉዳይ እውነቱን እንዲያውቅ በማድረግ፣

ሀሰተኛ ነገር እንዲህ በበዛበት ሰዓት በማስረጃ እያስደገፈችሁ የሚመለከታቸው ሰዎች እንዲደርሳቸው በማድረግ ትልቅ ተግባር እየፈፀማችሁ ነው።

ዛሬ በኛ መብዛት፣ በናተ ተፅኖ ፈጣሪነት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ገፁን እየተከታተሉ እንደሆነ፣ የሚተላለፉ ጥቆማዎችን እየተመለከቱ መፍትሄ ለመስጠት እየሰሩ እንደሆነ እናምናለን።

እኛ መረጀዎችን ከተለያዩ ገፆች እየሰበሰብን ስናቀርብላችሁ በተለይ በፌስቡክ ላይ የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግሮችን፣ የሰው ክብር የሚነኩ ስድቦችን፣ ማንነት ላይ የነጣጠሩ እና ሰዎችን ለግጭት ከሚገፈፉ መልዕክቶችን በጥቂቱም ቢሆን እድትርቁልን ለማድረግ እየሞከርን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የስራ እንዲሁም የትምህርት ሰዓታችሁ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳይባክን ሚዛናዊ መረጃዎችን ከተለያዩ እውቅና ካላቸው ገፆች መርጠን እዚህ እየሰበሰብንላችሁ ነው።

በተጨማሪ...

በጋዜጠኝነት ስራቸው ክብር ያገኙ፤ ሞያቸውን ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ለህዝብ አብዝተው የሚጨነቁ፣ ሚዛናዊ፣ ለሀቅ የቆሞ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች የተመረጡ መረጃዎችን እንዲያቀርቡልን በትብብር እየሰረን ነው ለምሳሌ፦ (ቅዳሜ ከምሽቱ 12:00-1:00 - ኤልያስ መሰረት ታዬ)

በቅርቡ ሌሎች ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች የቤተሰቡ አባላት መረጃ በማድረስ ከአንባቢነት ወደ ፀሃፊነት እንዲመጡ የምናደርግ ይሆናል።

ከ500,000 ለምትበልጡ ለቤተሰባችን አባላት ከፍተኛ ክብር አለን፤ ሁላችንም የዚህ ገፅ ባለቤቶች ነን! ያንተ ችግር የኔ ነው። ያንተ ደስታ የኔ ነው። አብሮነታችን ቤተሰባዊ ስሜታችን ነገም ይቀጥላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከጀርባው ያለው የሚደግፈው፣ የሚግዘው፣ ዋጋ የሚከፍልለት፣ ስለእውነት የሚቆረቆርለት አካል ዛሬ 500,000 ደርሷል!

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የግለሰብ፣ የግል ድርጅት፣ የመንግስት ወይም የሌላ አካል አይደለም የቲክቫህ ባለቤቶች 500,000 የምትልቁት ቤተሰቦቻችን ናችሁ፤ ከየትኛውም አካል ጥገኛ ሳንሆን እርስ በእርሳችን ተደጋግፈን ብሩህ ጊዜ እስኪመጠ እንሰራለን። ይህ ገፅ የግለሰቦች ፍላጎት ማንፀባረቂያ፣ የግለሠቦች እውቅና መገንቢያ፣ አንድ ሰው አመለካከት መጫኛ አይደለም 500,000 የተከበሩ ዜጎች የሚገኙበት እንዚህ ላይ የምናስተባብረው ሰዎችም እንደ አንድ የቤተሰቡ አባላይ ከማንም ባልተለየ መልኩ ድምፃችን የሚሰማበት ብቻ ነው።

ምስጋና!

•ለመላው ክቡር ሆናችሁ ቤተሰቦቻችን፣ እውነተኛ ጉዳዮች በማስረጃ አስደግፋችሁ በማሳወቅ፣ ሁሌም ለእገዛ ቀድማችሁ ለምትገኙ፣ ጥቆማዎችን የምታደርሱ፣ ሚዲያዎች ሽፋን የማይሰጧቸውን ጉዳዮችን የምታሳውቁ፣ የሚሰራጩ መረጃዎች የምታርሙ፣ የምታስተካክሉ፣ ከስሜታዊነት ርቃችሁ የምትተቹ ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ!

•በዚህ ፈታኝ ሰዓት ጥቂት ለሆናችሁ ሀቀኛ፣ እውነተኛ፣ ተማኝ፣ የሙያ ስነምግባራችሁ ጥንቅቃችሁ ለምታውቁ፣ ጊዜያችሁን ለሀገር ሰላም እየሰጣችሁ ላላችሁ ጋዜጠኞች (በተለይም የቤተሰባችን አባላት)

•ከስሜታዊነት ርቃችሁ እያመዛዘናችሁ ለሀገር ገንቢ የሆኑ ሃሳቦችን ለምታቀርቡ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል ላላችሁ ወጣቶች!

•ከድክመታችሁ ጋር ግል እና የመንግስት ሚዲያዎች የመንግስት መስሪያ ቤቶች የኮሚኒኬሽን ቢሮዎች!

•በድጋሚ ለናተ ለጨዋዎቹ፣ በሀገራችን ተስፋ እንዳንቆርጥ ለምታደርጉን ሰው አክባሪዎች 500,000 ቤተሰቦች!

ምስጋና በቅርቡ በቤተሰባችን ከአንባቢነት ወደ ፀሃፊነት ለተሸጋገሩት፦

(@tikvahethiopia የአሶሼትድ ፕሬሱ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ታዬ)

(@tikvahethsport ዓለም አቀፍ የስፖርት ጋዜጠኛ ፍሬው አስራት እንዲሁም ጢሞትዮስ ባዬ)

@tikvahethiopia @tsegabwolde
500,000 + Tikvah Family !

Pic. Elias Meseret

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ2019 የፀረ-ኤችአይቪ/ኤድስ ቀን “ማኅበረሰቡ የለውጥ አቅም ነው” በሚል መሪ ቃል በዓለምቀፍ ደረጃ እየተከበረ ነው፡፡

PHOTO:ሮይተርስ

#WAD2019

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#CocaCola

ኮካ ኮላ ኩባንያ መንግሥት ለሽያጭ ከሚያቀርባቸው የስኳር ፋብሪካዎች መካከል የተወሰኑትን ለመግዛት መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ የግዥ ፍላጎቱን ለመንግሥት በማስታወቅ የጨረታ ሒደቱ ይፋ የሚደረግበትን ጊዜ እየተጠባበቀ መሆኑ ገልጿል፡፡

(ሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
«መንግሥት ስለ ቫይረሱ አስገንዝቦ ተስፋ ያለዉ ትዉልድን ካላነፀ ማንን ሊመራ ነዉ» - ቫይረሱን ለመከላከል የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እና ግለሰቦች

አሳሳቢዉ የኤድስ ስርጭት!

በኢትዮጵያ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ዓለም አቀፍ ፀረ-ስርጭት ቀንን መጠበቅ የለብንም ሲሉ ቫይረሱን ለመከላከል የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ገለፁ።

«የኤድስ ስርጭትን ለመከላከል በየዓመቱ የፀረ ኤድስ ቀን በሚታሰብባት በኢትዮጵያ ትኩረቱ ከርዳታ ድርጅቶች በሚገኘው ገንዘብ ላይ እንጂ የኤድስን ስርጭት ለመግታት እና ግንዛቤ ማስጨበጡ ላይ አይደለም» ሲሉ አንድ ከኤድስ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ተናግረዋል። «ወጣቱን ትዉልድ መድሃኒት የሚዉጥ ተስፋ አልባ ትዉልድ ለማድረግ እየታሰበ ነዉ» ሲሉም ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

ከስድስት ሰባት ዓመታት በፊት የኤድስ ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት፤ ግንዛቤ ለመፍጠር እና በቫይረሱ የተያዙትን ለመርዳት፤ በመላ ኢትዮጵያ 430 ማኅበራት እንደነበሩ ያስታወሱት ግለሰቡ፤ በአሁኑ ወቅት ግን ግማሹ ያህል እንኳ መኖራቸዉ እጠራጠራለሁ ብለዋል። «መንግሥት ስለ ቫይረሱ አስገንዝቦ ተስፋ ያለዉ ትዉልድን ካላነፀ ማንን ሊመራ ነዉ» ሲሉም ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥበት ጠይቀዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Day1 #ኡቡንቱ #Ubuntu

አርባ ምንጭ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ - #ኡቡንቱ በሚል ርዕስ ያዘጋጀነው የግንዛቤ መፍጠሪ መድረክ የመጀመሪያ ቀን ውሎ ስኬታማ ነበር። ሁሉንም አካላት ከልብ ለማመስገን እንወዳለን! ከወጣቶች ጋር የምናደርገው ውይይት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴ እስከ ህዳር 27 ይቀጥላል።

“Ubuntu is about a community coming together to help one another.”— Paul Pierce

#TIKVAH_ETHIOPIA

#ቲክቫህኢትዮጵያ
#ፒስሞዴል
#ጋሞዞንአስተዳደር

"ኡቡንቱ" ላይ የምንሰራቸው ሀገር አቀፍ ስራዎች ላይ አስተያየታችሁ፣ ሃሳባችሁን አካፍሉ። በምን በኩል ብንሰራ ውጤት እናመጣ ይሆን? ልታግዙን ይምትችሉ አካላትም አናግሩን! @tsegabwolde
@tikvahethiopiaBot 0919743630