TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዘንድሮው የ10ኛ ክፍል(የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና) አይሰጥም!

10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከዚህ ዓመት (2012 ዓ/ም) ጀምሮ አይሰጥም። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ማረጋገጥ እንደቻለው የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከወዲሁ ቅድም ዝግጅት ጀምሯል። በአዲሱ የትምህርት እና ስልጠና ፍኖተ ካርታ መሰረት ቀደም ብሎ በ10ኛ ክፍል ይሰጥ የነበረው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከ2012 ዓ/ም ጀምሮ በ12ኛ ክፍል እንዲሰጥ ምክረ ሃሳብ መቅረቡ ይታወቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጣይ ሳምንታት ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ያደርሳችኃል።

@tikvahethiopia @tsegabwolde
"በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ የዚካ ቫይረስ ስጋት የለም" - የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት!

በአሁን ጊዜ በኢትዮጵያ የዚካ ቫይረስ ስጋት አለመኖሩን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል። የእንግሊዝ መንግስት ባለፈው ሰኞ በኢትዮጵያ የዚካ ቫይረስ ስጋት በመኖሩ በተለይ ነፍሰጡር እናቶች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የዚካ ቫይረስ ስጋት አለመኖሩን አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች ቅኝትና ምላሽ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ መስፍን ወሰን አንዳስታወቁት የዚካ ቫይረስ አምጪ ትንሽ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሁሉም የዓለም አገራት ትገኛለች። ይሁንና “ትንኟ አለች ማለት በሽታው ተከስቷል” ማለት አለመሆኑን ገልጸው፤ በአሁኑ ጊዜ በየትኛውም የአገሪቷ አካባቢ  በትንኟ አማካኝነት በቫይረሱ የተያዘ ሰው የለም ብለዋል። የእንግሊዝ መንግስት ለዜጎቹ ያሰራጨው መረጃ ከምን ተነስቶ እንደሆነም ግልጽ አለመሆኑን ተናግረዋል።

የዚካ ቫይረስ ‘ኤደስ’ በምትባል የወባ  ዝርያ የሆነች ትንኝ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው በደም ልገሳ፣ ከእናት ወደ ልጅ እንዲሁም በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ የመተላለፍ ዕድል አለው።

(ኢዜአ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደኢህዴን የብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል ወሰነ!

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) የብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል በሙሉ ድምጽ ወሰነ። ደኢህዴን በዛሬው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ባካሄደው አስቸኳይና ልዩ ጠቅላላ ጉባኤ ነው የብልጽግና ፓርቲን ለመቀላቀል በሙሉ ድምጽ የወሰነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኦነግ ስለ ኦሮሚያ ባለስልጣናት ግድያ...

በምዕራብ ኦሮሚያ በባለስልጣናት ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ በመንግስት የውስጥ አሻጥር የሚፈጸም ነው ብሎ እንደሚያምን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) በተለይ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ገለጸ። ኦነግ በግድያዎቹ “እጁ እንደሌለበት፤ የሚያዘውም ሰራዊት እንደሌለው” አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈጸሙ ስላሉ ግድያዎች በጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጥያቄ የቀረበላቸው የኦነግ ቃል አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ “በእኛ ግምት እና በአንዳንድ ምልክቶች፤ የውስጥ አሻጥር የሚመስል ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። “ከመንግስት የውስጥ መዋቅር በተለይም ከመከላከያው እና ጸጥታ ክፍሉ ውስጥ ሆን ብለው አሻጥር (ሳቦታጅ) የሚሰሩ ይኖራሉ” ብለዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-28-2

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ~ DW)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መጠቀም የሚያስችል የኤቲኤም አገልግሎት ተጀመረ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል የኤቲኤም (ATM) ማሽን በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ማድረጉን አስታወቀ።

አዲስ የATM የገንዘብ ገቢ ማድረግና የውጭ ምንዛሬ መመንዘር የሚያስችል የATM ማሽን አገልግሎት በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፍንፍኔ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ንጉሴ ለማ አስታውቀዋል።

እንደ አቶ ንጉሴ ገለፃ ቀደም ሲል አገልግሎት ላይ ከዋለው የገንዘብ መክፈያ የATM ማሽን በተጨማሪ አዲሱ ማሽን ወጪ ብቻ ሳይሆን ደንበኞች ገንዘብ ወደ ሂሳባቸው ገቢ ማድረግ እና የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚችሉበት ነው።

ይህ አገልግሎት ለመጀመርያ ጊዜ በስራ ላይ የዋለው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆኑ የጠቆሙት ስራ አስኪያጁ ፤ ማሽኑ በአሁኑ ሰኣት በሙከራ ደረጃ በፍንፍኔ ቅርንጫፍ አገልግሎቱ መጀመሩን ተናግረዋል።

ይህ ማሽን ስራ ከማቀላጠፍና ከማቃለል በተጨማሪ በተለይ ባንኮች ክፍት በማይሆኑበት ዕለታት ደንበኞች የእለተ እለት ስራቸውን ለማቀላጠፍ እንዲችሉ ታሳቢ ተደርጎ እየተዘጋጀ መሆኑን አቶ ንጉሴ ጠቁመዋል።

https://telegra.ph/ETH-11-28-3

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ሃሙስ በመላዋ ዩናይትድ ስቴትስ፤ የምሥጋና ቀን እየተከበረ ነው!

የሕዳር ወር በገባ አራተኛው ሃሙስ በየዓመቱ በዚህ ዕለት ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመድ ጓደኛ ተሰባስቦ የሚያከብሩው የምሥጋና ቀን በዓል እየተከበረ ነው። ይህ ቪድዬ በደቡባዊ ካሊፎርንያ የሚኖሩ አሜሪካውያን ዓመታዊውን የምስጋና ቀን ለማክበር ትናንት ዕሮብ ዕለት ወደ የቤተሰቦቻቸው ጉዞ ሲያደርጉ ያሳያል፡፡ በዚሁ ዓመታዊ ክብረ በዓል ወደ 55 ሚሊዬን የሚጠጉ አሜሪካውያን ወደ ቤተሰቦቻቸው፣ ዘመድና ወዳጆቻቸው የሚጓጓዙ ሲሆን ከአለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የዘንድሮ ቀጥር ጨምሯል፡፡ በዚህ ዓመታዊ በዓል ዩናይትድ ስቴትስ አውራ ጎዳናዎችና የአውሮፕላን ማረፍያዎች በተጓዦች ይጨናነቃሉ።

(የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 7ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ጉባኤ ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያካሂዳል ተብሏል፡፡ በፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ ከዛሬ ጀምሮ በሚካሄደው መደበኛ ጉባኤ ተደጋጋሚ የህዝብ ጥያቄዎች የሚነሱባቸውን አራት ተቋማት ማለትም ትምህርት ቢሮ፣ የቤቶችና ኮንስራክሽን ቢሮ፤ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እንዲሁም የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ሪፖርታቸውን ለምክር ቤቱ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

(አዲስ ሚድያ ኔትወርክ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ኢጋድ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) 13ኛው የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ተበተነ!

ፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት ከምርጫ ቦርድ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ውይይት በተፈጠረ አለመግባባት ተበተነ። የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የስነምግባር አዋጅ መፅደቁ ይታወሳል። የፀደቀው አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ ላይ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ለማድረግ በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ቢሰባሰቡም መግባባት ላይ ባለመድረሳቸው ውይይቱ ተበትኗል።

(AhaduTV)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይጠበቅ አፍጋኒስታን ሄዱ!

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አፍጋኒስታን የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮችን ጎበኙ። ትራምፕ ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ሳያሳውቁ፤ 'ቴንክስጊቪንግ' የተባለውን በዓል አስታከው ወደ አፍጋኒስታን በማቅናት ከወታደሮች ጋር ተገናኝተዋል።

በ 'ባግሪም ኤርፊልድ' የተገኙት ፕሬዘዳንቱ፤ አሜሪካ ከታሊባን ጋር እየተወያየች መሆኑን፣ ታሊባኖች "ስምምነት እንደሚፈልጉም" ለወታደሮቹ ተናገረዋል። ትራምፕ ወደ አፍጋኒስታን ሲሄዱ ይህ የመጀመሪያቸው ሲሆን፤ ከአፍጋኒስታን ፕሬዘዳንት አሽራፍ ጋኒ ጋርም ተገናኛተዋል።

ከታሊባን ጋር ወደ ሰላማዊ ስምምነት ለመመለስ ሲባል፤ የእስረኞች ልውውጥ መካሄዱን ተከትሎ ነው ትራምፕ ወደ አፍጋኒስታን የሄዱት። አሜሪካ ወታደሮቿን "በእጅጉ እየቀነሰች ነው" ሲሉም ተደምጠዋል። አሜሪካ እአአ የደረሰውን የመስከረም 11 ጥቃት ተከትሎ፤ በአፍጋኒስታን ጣልቃ ከገባች 18 ዓመት የሞላ ሲሆን፤ አሁን በአፍጋኒስታን 13,000 ወታደሮች ይቀሯታል።

ትራምፕ ጉብኝታቸውን ያካሄዱት፤ ታሊባን ለአራት ዓመታት ታግተው የነበሩ ሁለት ምዕራባውያን ምሁራንን ነፃ ከለቀቁ በኋላ ነው። በምላሹም ሦስት ታጣቂዎች ነፃ ተደርገዋል። "ከታሊባን ጋር ስንነጋገር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ፈልገን ነበር። እነሱ ግን አልፈለጉም፤ አሁን ግን የተኩስ አቁም ስምምነት ማድረግ ፈልገዋል" ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል። ውይይቱ ምን ያህል መስመር እንደያዘ የታወቀ ነገር የለም።

(BBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#GamoZone #EmbassyOfItaly

የጋሞ ዞን ከጣሊያን ኢምባሲ ጋር በመተባበር Italian Trade Agency (ICE) ከተባለ ድርጅት ጋር በአትክልትና ፍራፍሬ ምርት አቅርቦትና ማቀነባበር ዙሪያ ውይይት እየተካደ ነው፡፡ በውይይቱ ላይ በአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበር የሚታወቁ ሶስት የጣሊያን ኩባንያዎች (Tropical Food Machinery, CERMAC,MACFIRUT) የተባሉ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን የአከባቢውን ምርት ማቀነባበር እና በቀላሉ ለአለም ገበያ ማድረስi በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከዞኑ አመራር፣ ከኢንቨስተሮች እና ህብረት ሥራ ማህበራትና ዩኒየኖች ጋር ተወያይተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ተበተነ! ፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው ዕለት ከምርጫ ቦርድ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ውይይት በተፈጠረ አለመግባባት ተበተነ። የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባና የስነምግባር አዋጅ መፅደቁ ይታወሳል። የፀደቀው አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ ላይ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውይይት ለማድረግ በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ቢሰባሰቡም መግባባት ላይ ባለመድረሳቸው ውይይቱ ተበትኗል። (AhaduTV) …
የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ መበተን...

ውይይቱ ሊቋረጥ የቻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አዋጅ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት ረቂቁ ላይ የሰጡት አስተያየት ግብዓት ሆኖ አላገለገለም የሚል ሃሳብ ስላላቸው እንደሆነ ተገልጿል።

”በመሆኑም የኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አዋጅ ለማስፈጸም በወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ ከመወያየታችን በፊት በአዋጁ ላይ ያነሳነው ጥያቄ ሊመለስልን ይገባል” ሲሉ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀ በመሆኑ ከዚህ በኋላ ቦርዱን የሚመለከት ጉዳይ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።

በመሆኑም እንደተቋም የአዋጁን ማስፈጸሚያ ደንብ ማውጣትና መተግበር ስለሚያስፈልግ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደባለድርሻ አካላት በረቂቁ ላይ ሃሳብ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

ነገር ግን የፖለቲካ ፓርቲዎቹ አባላት ”ከዚህ በፊት  በአዋጁ ረቂቅ ላይ የሰጠነው ሃሳብ ግብዓት ሆኖ ባለማገልገሉ አሁን በዚህ ደንብ ላይ የምንሰጠው አስተያየት ግብዓት ይሆናል የሚል እምነት የለንም” ብለዋል።

በዚህ የተነሳም ለግማሽ ቀን ተጠርቶ የነበረው መድረክ ካለስምምነት ተበትኗል። የምርጫ ቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱኳን ሚደቅሳና ሌሎች የቦርዱ አባላት የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በሌላ ጊዜ ለውይይት ተዘጋጅተው እንዲመጡ አሳስበው፤ ያላቸውን ጥያቄ በጽሁፍ ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ጠይቀዋል።

ረቂቅ ደንቡ ፓርቲዎቹ ተወያዩበትም አልተወያዩበትም መጽደቁ ስለማይቀር ለፖለቲካ ሂደቱ ስኬት ሲባል ቢወያዩበት የሚመረጥ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከላይ የምትመለከቱት በድሬ ትዩብ (DireTube) የፌስቡክ ገፅ ላይ ከቀረበው ዜና ጋር የተያያዘው ፎቶ ሀሰተኛ ነው። መረጃው እና ፎቶው ምንም አይነት ግንኙነት የላቸውም።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ በትላንትናው እለት ሁለት ሰዎች ውሀ ውስጥ ገብተው መሞታቸው ተገለጸ!

የአዲስ አበባ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳስታወቀው በትላንትናው እለት ሁለት ሰዎች ውሃ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው አልፏል ብላል፡፡ የመጀመርያው የሞት አደጋ የደረሰው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ እድሜው 40 አመት የሆነ ጎልማስ ወንዝ ውስጥ ገብቶ ህይወቱ አልፏል ተብሏል፡፡

ሁለተኛው የሞት አደጋ የደረሰው ደግሞ በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ዮሴፍ ቄስ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ እድሜው 50 አመት የሆነ ጎልማሳ ህይወቱ እንዳለፈ ነው ኮሚሽኑ ያስታወቀው፡፡

በአዲስ አበባ ከቀርብ ጊዜ ወዲህ ጉድጓድ እና ወንዝ ውስጥ ገብተው የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን በያዝነው ዓመት ብቻ 25 ሰዎች ውሃ ውስጥ ገብተው ሞተዋል፡፡ በከተማዋ ለተለያዩ አገልግሎት ተብለው የሚቀፈሩ ጉድጓዶች በተለይም ለግንባታ እና ለቆሻሻ ማጠራቀምያ እና ለውሀ ማጠራቀሚያ ተብለው የሚቆፈሩ ጉድጓዶች ከፍተኛ አደጋ እያደረሱ እንደሆነ የአዲስ አበባ የእሳትና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያው አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ተናግረዋል፡፡

(ETHIO FM 107.8)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የእንጦጦ የሳተላይት መረጃ መቀበያ አንቴና ግንባታ ተጠናቀቀ!

በእንጦጦ ኦብዘረቫቶሪና ምርምር ማዕከል የሚካሄደው የሳተላይት መረጃ መቀበያ አንቴና ግንባታ ተጠናቀቀ፡፡ በማዕከሉ የተገነባው የመረጃ መቀበያ አንቴና ኢትዮጵያ በቅርቡ የምታመጥቃትን ሳተላይት ጨምሮ ለሳተላይት መቆጣጠሪያ እና መረጃ መቀበያ አገልግሎት የሚውል መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

(የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሰምንታት በፊት በአዳማ ከተማ ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመመለስ የከተማው አስተዳደርና ህብረተሰቡ በጋራ በመሆን በአዳማ ከተማ የእርቅ ስነ ስርዓት በትላንትናው ዕለት ተካሂዷል፡፡

የከተማዋ ከንቲባ አቶ አሰግድ ጌታቸው እንደተናገሩት ከባህላችን ውጪ በሆነ መንገድ የተፈጠረው ነገር ማንም የተጠቀመ የለም ያሉ ሲሆን የከተማዋን ፀጥታ ለማደፍረስ የሚሰሩትን ከዚህ በኀላ ዝም ብለን አንመለከትም ብለዋል፡፡ አቶ አሰግድ አክለውም ከሁሉም ብሔሮች ጋር ተከባብረን ተደጋግፈን ለሀገራችን ለውጥ በአንድነት መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶችም የአዳማ ህዝብና የኦሮሞ ህዝብ አቃፊና የሰላም ምሳሌ እንደሆነ ገልጸው በሰላም መኖር ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ብልፅግና ፓርቲና የ‹ባለ አደራ መንግሥት›...

ሕወሓት፤ ብልፅግና ፓርቲ በ2012 ዓ/ም እንደሚደረግ ከሚጠበቀው አገር ዐቀፍ ምርጫ በፊት ከተመሰረተ ኢትዮጵያ በባለ አደራ መንግሥት መመራት አለባት አለ፡፡ ከቀናት በፊት ሊቀመንበሩ ደብረፂዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ብልፅግና ፓርቲን መመስረቱም ሆነ ኢሕአዴግን የማፍረሱ ሒደት ሕጋዊ መንገዱን አልተከተለም በሚል ኢትዮጵያ ከምርጫ በፊት በባለ አደራ ልትመራ ትገደዳለች ማለታቸው ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ ኅዳር 18 ምሽት በትግራይ ቴሌቪዥን ቆይታ የነበራቸው የሕወሓት እና ኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ጌታቸው ረዳ ይህንኑ ሀሳብ ደግመውታል፡፡
ኢሕአዴግ አራቱን ብሔራዊ ድርጅቶች የማፍረስ ስልጣን አልተሰጠውም የሚሉት ጌታቸው፤ በሐዋሳው ጉባኤ ሀላፊነቱ ተሰጥቶታል የሚባለው #ውሸት ነው ሲሉ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

‹‹ብልፅግና ፓርቲ ውኅድ ሳይሆን አዲስ ፓርቲ ነው በማለትም›› ብልፅግናን መስርተው አሁን ባለው የመንግሥትነት ቦታ እንቀጥላለን ካሉ፤ ያን ጊዜ ሕግ የሚፈታው ጉዳይ ይሆናልም ብለዋል፡፡ በመሆኑም ብልፅግና ፓርቲ ኢህአዴግን መውረስ አይችልም፤ የብልፅግና ፓርቲ እየሄደበት ያለው ሂደትም ጨፍላቂ ነው ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል፡፡ በአንጻሩ ብልፅግና ፓርቲ ሕጋዊ ሂደቶችን ተከትሎና ኢሕአዴግን አዋኅዶ እየተፈጠረ መሆኑን በተደጋጋሚ የሚናገሩት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ዐቢይ አሕመድ፤ አዲሱ ውህድ ፓርቲ እውነተኛ ፌደራሊዝምን የሚተገብር እንጂ ጨፍላቂ አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ፡፡

(አሃዱ ቴሌቪዥን)

@tikvahethiopia @tikvahethipiaBpt
"የሀዋሳ ጉባኤ ውህደቱን እንዲያስፈፅም ለኢህአዴግ ምክር ቤት ውክልና ሰጥቶታል የሚባለው፣ ንፁህ ውሸት ነው!"- አቶ ጌታቸው ረዳ

"ኢህአዴግን ለማፍረስ የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ ቢንስ ሶስቱ የግምባሩ ድርጅቶች ሌላ ነገር ነው የምንፈልገው ብለው ቢያንስ አቋማቸው ስለገለፁ ፣ ቢያንስ በአመራር ደረጃ ማለት ነው፤ ስለዚህ ኢህአዴግን ለማፍረስ የሚያስችሉ መስፈርቶች ይነስም ይብዛም የተሟሉ ነው የሚመስለው፡፡ ፖለቲካሊ ማለቴ ነው፡፡ በፖለቲካ ደረጃ የኢአዴግ አባል ድርጅቶች ፍላጎት ሲኖራቸው ነው ኢህአዴግ ሊኖር የሚችለው፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ እንደ ግምባር ሊቀጥል የሚችልበት እድል አባል ድርጅቶቹ እንዲቀጥል ሲፈልጉ ነው፡፡ ስለዚህ እንዲቀጥል አንፈልግም የሚል እምነት የሚያረጋግጥ የሚመስል ውሳኔዎች ቢያንስ በአመራሮቹ ደረጃ ወስነዋል። ቢሆንም ኢህአዴግን የማፍረስ ሂደት በህግ ማለቅ የሚኖሩባቸውን ጉዳዮች እስኪማሉ ድረስ ቴክኒካሊ ፈርሰዋል ለማለት ግን አይቻልም፡፡ ያው ፍቺ ሲፈርስ የጋራ ሀብት፣ ንብረት የመከፈል ጉዳይ ስለሚኖር።

More👇
https://telegra.ph/TPLF-11-29

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Ethiopian Airlines 🛫 ደምቢ ዶሎ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከታህሳስ 7 ጀምሮ በሳምንት ሁለት ቀን ወደ ምዕራብ ኦሮሚያ ደምቢ ዶሎ የበረራ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል።

(የኢትዮጵያ አየር መንገድ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ለሦስት የመንግስት የስራ ኃላፊነት ቦታዎች ሹመት ሰጡ!

ጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት ለኢቲቪ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው፦

1. አቶ አህመድ ቱሣ የብረታ ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣

2. ዶ/ር አለሙ ስሜ በሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማእከል ዘርፍ አስተባባሪ፣

3. አቶ አወሉ አብዲ በሚንስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማእከል የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ላይ ተመድበዋል፡፡

ተሿሚዎቹ ከህዳር 18 ቀን 2012 ጀምሮ በተጠቀሱት የስራ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ተመድበዋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸውን ሊለቁ ነው!

ጸረ-መንግሥት ተቃውሞ በናጣት ኢራቅ ጠቅላይ ሚንሥትር አደል አብደል ማኅዲ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ ዛሬ ዐስታወቁ። ጠቅላይ ሚንሥትሩ በጽሑፍ ባሰራጩት መግለጫ ለሀገሪቱ ምክር ቤት የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን በይፋ እንደሚያስገቡ ገልጠዋል። የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄው ኢራቅ ውስጥ የጸጥታ ኃይላት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ተኩሰው ቢያንስ ዐርባ ሰዎችን በገደሉ ማግስት ነው። የሀገሪቱ የሺዓ እምነት ከፍተኛ ባለሥልጣን ዓሊ ኧል ሲስታኒ ለመንግሥት የሚያደርጉት ድጋፍን «እንደሚያጤኑበት» ለምክር ቤቱ ዛሬ ቀደም ብለው ዐስታውቀው ነበር። ጠቅላይ ሚንሥትር አደል አብደል ማኅዲ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ በመግለጣቸው በርካታ ተቃዋሚዎች መዲናዪቱ ባግዳድ ወደ ሚገኘው ታኅሪር አደባባይ በብዛት በመሰባሰብ ደስታቸውን ገልጠዋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopia @tsegabwolde