TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.13K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፍሽክታ ደቅና ፍሽልታ ዓድና - ነፃ ሕክምና ምስንጣቕ ከንፈርን ታሕናግን

ብቑፅሪ ስልኪ፦ 0914 211212፣ 0914003465፣ 0910488892

#ሼር #share

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የሲዳማ ብሔር ህዝብ ውሳኔ ውጤት አስመልክቶ ከወላይታ ዞን አስተዳደር የተላለፈ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት!

(ወላይታ ሶዶ ህዳር 13/2012 ዓ/ም)

የሲዳማ ህዝብ የዘመናት ጥያቄ ሆኖ የቆየው ራሱን በራስ የማስተዳደር በክልል የመደራጀት ህገ-መንግስታዊ ጥያቄ ከረጅም ጊዜ ትግልና መስዋትነት በኋላ የተገኘ በመሆኑ የወላይታ ዞን አስተዳደር የተሰማውን ታላቅ ደስታ በዞኑ መንግስትና ህዝብ ስም ይገልጻል፡፡

"የወላይታና የሲዳማ ወንድም ህዝቦች" ለዘመናት አብሮ የኖሩ፣ አንድ ትውልድ በሌላው ትውልድ ስተካ በዘመናት መካከል በመከባበር ላይ የተመሰረተ አንድነት በባህላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ታሪካዊ ጉዳዮች የተሰናሰሉ ከመሆናቸው ባለፈ የደም ትስስር ጭምር የሚያገናኛቸው ህዝቦች ናቸው፡፡ በእነዚህ የአብሮነት ጊዜያት በክፉም ደጉም በጋራ በሀገር ግንባታ ሂደት የበኩላቸውን ሚና ሲወጡ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

የሀገራዊ ለውጥ ሂደት ተከትሎ በ2010 ዓ/ም ሁለቱን ወንድም ህዝቦች በማጋጨት የፖለቲካ ጥቅም ለማግኘት የፈለጉ እኩይ ዓላማ ያላቸው ሀይሎች የተለያዩ ጥረቶች ያደረጉ ቢሆንም በህዝቦች መካከል ለዘመናት የዘለቀው የጋራ እሴት እንዳይሸረሸር ሁለቱ ወንድም ህዝቦች ባደረጉት ጠንካራ ተጋድሎ ሁኔታው ወደ ነበረበት የቀድሞ ሠላማዊ ሁኔታ ተመልሷል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-23-4

(ወላይታ ዞን አስተዳደር)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE የአፋር ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ወደ ብልፅግና ፓርቲ የሚደረገውን ውህደት በመደገፍ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ጋህአዴን - የጋምቤላ ህዝቦች አንድነት ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ጋህአዴን/ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤውን ነገ #በጋምቤላ ከተማ እንደሚያካሄድ አስታወቀ። የድርጅቱ ሊቀመንብር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ እንደገለጹት የደርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለአንድ ቀን በሚካሄደው ጉባኤው የኢህአዴግና አጋር ድርጅቶች ውህደት ዙሪያ  በስፋት ይወያያል፤ ተወያይቶም ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል።

(ENA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ጊዜያዊ ውጤትን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ህዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም
(ሃዋሳ)

የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ህዳር 12 ቀን 2011 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የሲዳማ ዞን በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝብ ውሳኔ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም ተካሂዷል።

የህዝበ ወሳኔው አፈፃፀም ተአማኒ፣ ሰላማዊ እና ፍትሃዊ አንዲሆን ለማድረግ ቦርዱ እስከ ህዝብ ውሳኔው ድምጽ መስጫ እለት ድረስ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል።

ቦርዱ የህዝበ ውሳኔውን ጥያቄ የማስፈፀም ሀላፊነቱን መወጣት የጀመረው ሂደቱ ፍትሃዊ፣ ሰላማዊ እና ተአማኒ እንዲሆን እንዲሁም በሲዳማ ዞን እና በሀዋሳ ከተማ የሚኖሩ ዜጎች ያለ አድሎ ፍላጎታቸውን የሚገልፁበት አሰራር ለመዘርጋት የሚያስችል የሲዳማ ህዝብ ውሳኔ አፈፃፀም መመሪያ በማጽደቅ ነው፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-23-5

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የወላይታ ህዝብ በተመሳሳይ ሁኔታ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ራስ በራስ የማስተዳደር ህገ-መንግስታዊ ጥያቄን አንግቦ በየጊዜው ህዝቡ ጥያቄውን በተለያየ መንገድ ለመንግስት እያቀረበ የቆየ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ የኢትዮጰያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የወላይታ ክልል ሆኖ የመደራጀት ህዝበ ውሳኔ የሚያደራጅበት ሁኔታ እየተጠባበቀ ይገኛል!"

(የወላይታ ዞን አስተዳደር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE - የህወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል። የህወሃት ስራ አስፈፃሚ አሁን ባለው አገራዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ የክልሉ ቀጣይ የልማት ጉዞ እና እቅዶች ለመምከር ነው ስብሰባ የተቀመጠው።

(JB)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሲዳማ - 10ኛው ክልል!

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ለሲዳማ ህዝብ "የእንኳን ደስ አላችሁ" መልእክት አስተላልፈዋል። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፥ የሲዳማ ህዝብ ህዳር 10 2012 ዓ.ም ባካሄደው ህዝበ ውሳኔ ሲዳማ ክልል ሆኖ መደራጀት የሚያስችለውን ድምጽ ማግኘቱን ተከትሎ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
.
.
"ህዝብን የማዳመጥ ውጤት የሆነው የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደርጎ ሲዳማ 10ኛው የፌዴሬሽኑ ክልል መሆኑ እውነተኛ ህብረ ብሄራዊ የፌዴራሊዝም ስርዓት ስራ ላይ መዋል መጀመሩን ያመላክታል" - አቶ ሽመልስ አብዲሳ
.
.
"ራስን በራስ የማስተዳደር መብትን ማረጋገጥ፣ በማንም የማይገረሰስ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች #ሉአላዊነት መግለጫ ነው ብሏል!" - የትግራል ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ 

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-23-6

(ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbeba

- በአዲስ አበባ ከተማ "ለአረንጓዴ ቦታነት" ተከልለው የነበሩ ቦታዎች ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ በመሆን ፓርክ እንዲሰራባቸው ተወሰነ፡፡ በከተማዋ በተለያዩ ቦታዎች ለአረንጓዴ ቦታነት በሚል ለረጅም አመታት ተከልልው የነበሩ ቦታዎች ቢኖሩም ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ እንዳልነበረ የከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

- በተጨማሪም አካባቢዎቹ ለህገወጥ የመሬት ወረራ የተጋለጡ እና ለቆሻሻ ማከማቻነት የዋሉ ሆነዋል፡፡ ይህንን የገመገመው የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔም ቦታዎቹ ከባለሃብቶች ጋር በመሆን የተሟላና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ያማከሉ መዝናኛ ያላቸው ፓርኮች እንዲሰራባቸው ወስኗል፡፡

- ፓርኮቹ ለነዋሪዎች ተጨማሪ የመዝናኛ አማራጭ እንደሚሆኑና የከተማዋ አረንጓዴ ሽፋን ለማሳደግም የካቢኔው ውሳኔ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ የሚገኙ የህዝብ መዝናኛ ማእከሎችን ማሳደግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው፡፡

(Mayor Office AA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GDG_ADDIS

Google Developers Group Addis(GDG ADDIS) ሁለተኛውን ዓመታዊ ፕሮግራማቸውን በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው "ኤሊያና ሆቴል" እያካሄዱ ነው።

PHOTO: ELI(Tikvah Family)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የቲክቫህ ቤተሰቦች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች!

(ህዳር 13/2012 ዓ/ም)👇
https://telegra.ph/TIKVAH-11-23
እንኳን ደስ አለን!

(Ethiopian Athletics Federation)

የፌዴሬሽናችን ተ/ም/ፕሬዝዳንት ኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዓለም አትሌቲክስ እ.አ.አ. በ2019 በሴትነቷ ላበረከተችው የላቀ አስተዋፅዎ በአትሌቲክሱ እድገት በአትሌትነት፣ በአሰልጣኝነት፣ በአመራር ዘርፍ ባካሄደው ምርጫ የዓመቱ ምርጥ ሴት ብሎ ሸልሟታል። በተጨማሪም ወጣቱና የዶሃ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ5000ሜ የብር ሜዳሊስቱ አትሌት ሰለሞን ባረጋ የራይዚንግ አትሌት ሽልማትን በማሸነፋ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተሰማውን ደስታ እየገለፀ ለሁለቱም እንኳን ደስ አላችሁ።

(Ethiopian Athletics Federation)

#WorldAthleticsAwards2019
(Ethio Kickoff)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለትውስታ ከአምናው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቲክቫህ ቤተሰቦች ጉዞ...

ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተውጣጡ፤ በተለያዩ የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚማሩና በማህበራዊ ሚዲያ(ቴሌግራም) ብቻ የተሰባሰቡት የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች...

በልዩነቶቻቸው ተከባብረው፤ በሰውነታቸው ተዋደው፤ ከምንም ነገር በላይ ሰብዓዊነታቸውን አስቀድመው፤ ጥላቻን፣ ሰዎችን ማንቋሸሽ፣ ሰዎችን በማንነታቸው ማሸማቀቅን፣ መግፋትን፣ ሰዎችን በሰውነታቸው አለማክበርን #ተፀይፈው "ነጩን የሰላም ምልክት፣ባንዲራ ተሸክመው ለሀገራች ህዝቦች ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አድርገው ነበር።

ለሀገራቸው ሰላም እና ፍቅር ቀና አስበው፤ ያለ አንዳቸው የግለሰብም ሆነ የድርጅት ድጋፍ፣ የትምህርት ጊዜያቸውን ሰውተው፤ ረጃጅም ጉዞዎችን እየተንገላቱ ተጉዘው፤ ከቤተሰባቸው ከሚላክላቸው ገንዘብ ቀንሰው ለጉዞ አውለው፣ ከራሳቸው ኪስ አውጥተው ተመገበው፣ የሚስማማቸውን ምግብ ካገኙ በልተው ከሌለም ፆም አድረው፤ ለፍቅር እና ለሰላም ሲሉ ብዙ ዋጋ ከፍለዋል። እንደ አንድ #ዜጋ ከራሳቸው የሚጠበቀውን በዚህ እድሜያቸው አድርገዋል። የህሊና ተወቃሽ ከመሆንም ድነዋል። ሁሌም ለሰው ልጅ ባላቸው ቀና አመለካከት ስናከብራቸው እና ስናወድሳቸው እንኖራለን።

የአንድ እናት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
የአንድ ቤት ልጆች ነን መስመር አይለየን🇪🇹
.
.
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"
"Nuti Hunduu OBBOLEEWWANI"

#Jimma #Wollo #Haramaya #DebreBrihan #Mekelle #Woldia #ArbaMinch #Hawassa #WolitaSodo #Wachamo #Wolkite

የቲክቫህ ቤተሰቦች ትውስታ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሚመለከታችሁ አካላት!

ወደ ደሴ በሚወስደው መንግድ-ደብረ ሲና መድረሻ መንገድ ላይ - መንገዱ በወደቀ ዛፍ እና ጭቃ በመዘጋቱ በርካታ መኪኖች ማለፍ አልቻሉም። እስካሁን ድረስም የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት ከፍተኛ ርብርብ እና መኩራ እየተደረገ ቢሆንም አልተሳካም የሚመለከታችሁ አካልት መፍትሄ ትፈልጉ ዘንድ መንገደኞች ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#2

ለሚመለከታችሁ አካላት!

ከወለንጪቲ ወደ መተሃራ መውጫ - እና - ከመተሃራ ወደ ወለንጪቱ መግቢያ ላይ ሁለት ተሳቢ ተሽከርካሪዎች ተጋጭተው መንገድ ተዘግቷል። በርካታ መንገደኞችም እየተጉላሉ ነው። የሚመለከታቸው አካላት መፍትሄ ይፈልጉ። በነገራችን ላይ በግጭቱ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የለም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኦሮሚያ እና የአማራ ወጣቶች የጋራ የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው!

በኦሮሚያ እና በአማራ ባለሃብቶች ኮሚቴ አስተባባሪነት እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ መድረክ ከሁለቱ ክልሎች የተውጣጡ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች፣ በሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ግንኙነትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡

የኦሮሚያ እና የአማራ ባለሃብቶች ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ፍሬዓለም ሽባባው ውይይቱ በሁለቱ ክልል ወጣቶች መካከል ያሉ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ለመፍታት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የሁለቱ ክልሎች የሃይማኖት አባቶች፣ ፖለቲከኞች፣ ባለሃብቶችና አክቲቪስቶች ውይይት ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡

(EBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaBot
- ደብረ ሲና መዳረሻ አካባቢ የተዘጋውን መንገድ ለመክፈት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል! መንገዱ በመዘጋቱ በርካታ ተሽከርካሪዎች ቆመዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot