ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ!
በትላንትናው ዕለት በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የጽዳት ዘመቻ ለሰላም እና አብሮነት በሚል መሪ- ቃል ተካሂዷል፡፡ የጽዳት ዘመቻው በዩኒቨርርሲቲው ማኅበረሰብ እና ተማሪዎች መካከል ያለውን የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የመተሳሰብ እሴት ለማዳበር ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሁሉም የአስተዳደር ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የጸጥታ አካላት እና ተማሪዎች ተሳተፈዋል፡፡ ከጽዳት ዘመቻው በኋላም ተማሪዎችን የሚያዝናኑ ልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎች በዋልያ የባህልና የኪነ-ጥበብ ቡድን ቀርበው ነበር።
(ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ቤጉህዴፓ አስቸኳይ የመሸጋገሪያ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው!
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) ወደ ሀገራዊ ብልጽግና ፓርቲ የሚያደርገውን ውህደት ለማስፈጸም አስቸኳይ የሽግግር ጉባኤውን ሊያካድ ነው፡፡
የቤጉህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይስሀቅ አብዱልቃድር እንዳስታወቁት ኢህአዴግ ወደ ውህድ ፓርቲ ለመሸጋር መወሰኑን ተከትሎ ቤጉህዴፓ በመጪው ሕዳር 15 እና16 ቀን 2012 ዓ.ም አስቸኳይ የሽግግር ጉባኤውን ያካሂዳል፡፡
ወደሀገራዊ ፓርቲ የሚደረገውን ውህደት ለማስፈጸም ለሚካሄደው የሽግግር ጉባኤ ከወዲሁ ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሠራ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
(ENA)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ በድርጊቱ “እጃቸው አለበት” በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው!
በባህርዳርና አዲስ አበባ ከአማራ ክልል አመራሮችና ከእነ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ግድያ ጋር በተያያዘ በወንጀል ድርጊቱ “እጃቸው አለበት” በሚል የተጠረጠሩ 13 ግለሰቦች ዛሬ ክስ ተመሰረተባቸው። የጀነራል ሰዓረ ጥበቃ የነበረው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡን ጨምሮ 13ቱም ተከሳሾች ዛሬ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ እየተነበበላቸው ነው።
ተጠርጣሪ ተከሳሽ አስር አለቃ መሳፍንት ችሎቱ የሚጠይቀውን ምላሽ መስጠት እንዳልቻለና “እሺ” እና “አዎ” የሚሉ ምላሾችን ብቻ እንደሚሰጥ ኢቢሲ ከችሎቱ ቦታ ዘግቧል።ችሎቱ “መናገር ካልቻልክ ሀሳብህን በፅሁፍ ግለፅ” ቢለውም ተከሳሹ ይህንንም አለመቻሉ ተመልክቷል።
ከሰኔ 15ቱ ወንጀል ጋር በተያያዘ ባህርዳር ላይ የአማራ ክልል አመራሮች አቶ አምባቸው መኮንን፣ አቶ ምግባሩ ከበደና አቶ እዘዝ ዋሴ ሲገደሉ እንዲሁም አዲስ አበባ ላይ ደግሞ የኢፌዴሪ መከላከያ ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ መገደላቸው ይታወሳል።
ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ከተመሰረተባቸው ተጠርጣሪዎች መካከል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለ ይገኙበታል። ዓቃቤ ህግ በተከሳሾቹ ላይ " ህገ መንግስትን በኃይል ለመናድ" በሚል ነው ክሱ የመሰረተባቸው።
(EBC)

Audio
ህወሓት የአዲሱ ፓርቲ ውህደት አባል አልሆንም...
ኢህአዴግ ባለፈው ቅድሜ ሕዳር 6/ 2012 ዓ/ም ባካሄደው ስብሰባ የፓርቲው የውህደት ሃሳብና ውሳኔ አስመልክቶ ህወሓት በስብሰባው ወቅት ያነሳቸው ጥያቄዎችና እንዲሁም ውህደቱን የተቃወመበት ምክንያት የህወሓትና የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አባልና የህወሓት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኢህአዴግ ባለፈው ቅድሜ ሕዳር 6/ 2012 ዓ/ም ባካሄደው ስብሰባ የፓርቲው የውህደት ሃሳብና ውሳኔ አስመልክቶ ህወሓት በስብሰባው ወቅት ያነሳቸው ጥያቄዎችና እንዲሁም ውህደቱን የተቃወመበት ምክንያት የህወሓትና የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ አባልና የህወሓት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ የተናገሩት!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE
ኢትዮጵያ በመጪው ታህሳስ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ወደ ህዋ ታመጥቃለች። ቻይና የተሰራችውና 72 ኪሎ ግራም የምትመዝነው ሳተላይት በአካባቢ ጥበቃ፣ በግብርና እና በአየር ሁኔታ መረጃ ትሰጣለች። ታህሳስ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ከቻይና ቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትወነጨፈው የኢትዮጵያ ሳተላይት ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቃ ትቀመጣለች ነው የተባለው።

በሶስት ቀናት ዉስጥ 487 ጥይትና 9 የቱርክ ሽጉጥ ተያዘ!
ሰሞኑን የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች ባደርጉት ፍተሻ በቀን 09/03/2012 በአዋሽ ጉ/ቅ/ፅ/ቤት አለበረከቴ ኬላ በተደረገ ፍተሻ በሶላር ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር የነበረ 218 ጥይት 126 የብሬን ና 92 የክላሽ ጥይቶች ከአራት ከተጠርጣሪዎች ጋርታርጋ ቁጥር ኮድ 3-62743 ኦሮ የህዝብ መመላለሻ መኪና ዉስጥ ተይዘዋል፡፡
በተመሳሳይ በቀን 09/03/2012 ዓ.ም በሞያሌ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ሞያሌ መ /ጣቢያ ኬላ በተደረገ ፍተሻ 9 የቱርክ ሹጉጥ 96 ጥይት የህዝብ ማመላለሻ FSR ታርጋ ቁጥር ኮድ-3 47008 ኦሮ ከኮንሶ ወደ ሞያሌ ከተማ ስገባ ተይዟል፡፡
በቀን 10/03/12 አ/ም ማታ 5 ሰዓት አከባቢ በአርበረከቴ ጉ/መቆ/ጣቢያ የሰ/ቁጥር ኮድ 3 67409 ኦሮ ሚንባስ ዉስጥ 173 የክላሽ ጥይት የረዳት መቀመጫ ኩርስ ዉስጥ በድብቅ አስቀምጦት በፍተሻ ተይዛል። ባጠቃላይም 487 ጥይትና 9 የቱርክ ሽጉጥ በሶስት ቀናት ዉስጥ መያዛቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
(የገቢዎች ሚኒስቴር)

የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ተጠናቀቀ!
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቋል፡፡ በሁለተኛ ቀን ውሎው ዛሬ የአዲሱ ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ ላይ በጥልቀት ከመከረ በኋላ የተገኙት አባላት በሙሉ ድምጽ ማፅደቃቸው ነው የተነገረው፡፡ በመጀመሪያ ቀን ውሎው ምክር ቤቱ የፓርቲውን ውህደትና ፓርቲው ወደ ፊት የሚመራበት ፕሮግራም ላይ በመምከር አጽድቋል፡፡
(EPRDF)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር (ኢህአዴግ) ምክር ቤት ለሁለት ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቋል፡፡ በሁለተኛ ቀን ውሎው ዛሬ የአዲሱ ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ ላይ በጥልቀት ከመከረ በኋላ የተገኙት አባላት በሙሉ ድምጽ ማፅደቃቸው ነው የተነገረው፡፡ በመጀመሪያ ቀን ውሎው ምክር ቤቱ የፓርቲውን ውህደትና ፓርቲው ወደ ፊት የሚመራበት ፕሮግራም ላይ በመምከር አጽድቋል፡፡
(EPRDF)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እርቀ ሠላም እየፈጸሙ ነው!
"የደብረ ታቦር በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች" የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የአንድነት መርሐግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመካከላችን ዳግም ክፍተትን አንፈጥርም ብለዋል ተማሪዎቹ።
(ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"የደብረ ታቦር በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች" የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የአንድነት መርሐግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል። በመካከላችን ዳግም ክፍተትን አንፈጥርም ብለዋል ተማሪዎቹ።
(ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ቲክቫህኢትዮጵያ 💐 የመጨረሻ ተስፋችን እናተ ናችሁና ሰላም ስትሆኑልን ውስጣችን ሰላም ይሆናል፤ ሰላም ስታወርዱ ውስጣችን በደስታ ይሞላል፣ ስትወዳዱልን ልትጠፋ የደበዘዘችው #ተስፋች እንዳዲስ ብቅ ትላለች፣ እናተ አበባዎቻችን ናችሁ፤ የመጨረሻዎቹ የሀገራችን ተስፋ ናችሁና በአጭሩ እንድትቀጠፉብን በፍፁም አንፈልግም።
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"
"Nuti Hunduu OBBOLEEWWANI"
የቲክቫህ ቤተሰቦች!!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"
"Nuti Hunduu OBBOLEEWWANI"
የቲክቫህ ቤተሰቦች!!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ታርቀናል!!
የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰቦች "ታርቀናል፤ ሰላም እና እርቅ ወርዷል!" ሲሉ የተለያዩ ፎቶዎችን እያጋሩን ነው!!
PHOTO: HENA(Tikvah Family)

ከDTU ተማሪዎች #ETHIOPIA #ኢትዮጵያ
ውድ የሀገራችን ወጣቶች፤ ሀገራችን ያለናተ ማንም የላትም፤ ብቸኛ የኢትዮጵያ ተስፋ እናተ ናችሁና ተዋደዱ፣ ተከባበሩ፣ ተፋቀሩ!
እናመሰግናለን!
"ሁላችንም ወንድማማቾች ነን!"
"ሁላችንም እህትማማቾች ነን!"
"Nuti Hunduu OBBOLEEWWANI"
@tikvahethiopia @tsegabwolde

ወሎ ዩኒቨርስቲ (ደሴ ካምፓስ) በተማሪዎች መካከል እርቀ ሰላም ወርዷል፤ ተማሪዎችም ሰላማቸውን በጋራ ለመጠበቅ ቃል ገብተዋል!
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የደሴ ግቢ ተማሪዎች የአቋም መግለጫ፦
አገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ምድረ ቀደምት ከሚባሉት ጥቂት ሃገራት አንዷ መሆኗ አሌ የማይባል ሃቅ ነው፡፡ በየዘመናቱ የመጡ ወራሪዎችን መክታና አሳፍራ በመመለሷ ከአፍሪካ በቅኝ ግዛት ካልተገዙ ሁለት ሃገራት አንዷ ነች፡፡ የዚህ ዋናው ሚስጢሩ የጥንት አባቶቻችንና እናቶቻችን በዘር፣ በጐጥ፣ በሃይማኖትና ሌሎች ልዩነቶች ሳይከፋፍሉ በአንድነት በመንቀሳቀሳቸው ነው፡፡ ነገር ግን ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ጀምሮ ለኢትዮጵያ ሃገራችን እድገትና ብልጽግና ፀር የሆኑ አካላት የውስጥ ጥቅመኞችንና ሆድ አደሮችን በመያዝ አገራችንን የትርምስ ቀጠና ለማድረግ ሌት ከቀን መስራት ከጀመሩ ውለው አድረዋል:: በዚህ መጥፎ ተግባር ህይወታቸውን እያጡ ላሉ ወገኖቻችን ነብስ ይማር እያልን ይህ መጥፎ ተግባር በአስቸኳይ ይቆም ዘንድ የሚከተለውን ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል፡፡
1. ዩኒቨርሲቲዎች የዕውቀት ማዕድ የሚቀርብባቸው የምርምርና የቴክኖሎጂ ፈጠራ ማዕከላት በመሆናቸው የብጥብጥ ቀጠና ለማድረግ የሚደረገውን እንቅስቃሴ
አጥብቀን እናወግዛለን፣
2. እኛ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዓለም ዓቀፍ እውቀታችን እንዲጐለብትና እንዲሰፋ በአዕምሮ ልማት ላይ የማይነጥፍ ድጋፍን እንጅ በብሔር ፣ በሃይማኖትና በፖለቲካ ልዩነት እርስ በርስ ሊያፋጁን የሚጥሩትን መንግስት ከጐናችን ሆኖ እርምጃ እንዲወሰድልን እንጠይቃለን፡፡
More👇
https://telegra.ph/ETH-11-22

አሳዛኝ ዜና!
ህዳር 12 ቀን 2012 ዓ/ም በግምት ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ ሌሾ ማዞሪያ ከተማ አንድ አይሱዙ ኤፍ ኤስ አር/ ISUZU FSR/ የጭነት መኪና ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ/ ባጃጅ/ በመግጨቱ በደረሰው አደጋ በባጃጁ ውስጥ የነበሩት ተሳፋሪዎች ሕይወታቸው አልፏል። የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር በዚህ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ለሞቱት ወገኖች የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፤ ለዘመዶቻቸው፥ ለቤተሰቦቻቸው እንዲሁም ለመላው የዞኑ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝቷል።
(የዞኑ ሕዝብ ግንኙነት ጽ/ቤት)

#አዳባ
በዛሬው ዕለት አዳባ ከኬላው አለፍ ብሎ በአንድ ዶልፊን እየተባለ በሚጠራ መኪና ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የሰው ህይወት አልፏል፣ ከባድ እና ቀላል ጉዳትም ተከስቷል ሲል በስፍራው የነበረ የቤተሰባችን አባል አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በዛሬው ዕለት አዳባ ከኬላው አለፍ ብሎ በአንድ ዶልፊን እየተባለ በሚጠራ መኪና ላይ በደረሰ የመገልበጥ አደጋ የሰው ህይወት አልፏል፣ ከባድ እና ቀላል ጉዳትም ተከስቷል ሲል በስፍራው የነበረ የቤተሰባችን አባል አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በቦሌ ኤርፖርት የዓለም አቀፍ መንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል አንድ መንገደኛ በትናንትናው ዕለት 86,350 ዩሮ እና 89,090 የስዊዝ ፍራንክ ከአዲስ አበባ ወደ ውጭ ሀገር ሊያስወጣ ሲል በወጪ መንገደኞች የጉምሩክ ፈታሾች በቁጥጥር ስር ውሏል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ASTU
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ(ASTU) ዛሬ ለሶስተኛ ጊዜ ባወጣው ማስታወቂያ የመማር ማስተማ መርሃ ግብር መቆራረጡ እንደቀጠለ እንደሆነ ገልጿል። ከሰኞ ጀምሮ ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ እንዲገኙ በጥብቅ አሳስቧል። ይህ ሆኖ ባይገኝ ግን በትምህርት ገበታው ላይ ያልተገኘ ተማሪ በራሱ ፍቃድ ትምህርት እንዳቋረጠ ተቆጥሮ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው ይህን ቢልም...
መልዕክቶቻቸው "ለቲክቫህ ኢትዮጵያ" የላኩ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ተማሪዎች የሆኑ የቤተሰባችን ዓባላት በግቢው ውስጥ በበራሪ ወረቀት እየተሰራጩ የሚገኙ እንዲሁም በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እየተላለፉ ያሉ የማስፈራሪያ መልዕክቶች ትምህርታችንን በአግባቡ እንዳንከታተል እንቅፋት ሆኖብናል ብለዋል።

"ተማሪዎች እንዳይረጋጉና ምዝገባ አከናዉነዉ ወደ ትምህርት እንዳይመለሱ በማህበራዊ ሚዲያ የማስፈራርያ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ሙከራ የሚያደርጉ አካላት መኖራቸዉ ተደርሶበታል!" - ጅማ ዩኒቨርሲቲ
.
.
ዛሬ አርብ ህዳር 12/2012 ዓ.ም. በጅማ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ካምፓሶች የዩኒቨርሲቲዉ ሴኔት ባስተላለፈዉ ዉሳኔ መሰረት ምዝገባ ተካሂዷል፡፡ ምዝገባዉ ነገ ቅዳሜ ህዳር 13/2012 እና እሁድ ህዳር 14/2012 ዓ.ም. ቀጥሎ የሚከናወን ሲሆን፣ በታቀደዉ መሰረት ሰኞ ህዳር 15/2012 ዓ.ም. የመማር-ማስተማር ሂደቱ ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ ይቀጥላል፡፡
ይሁን እንጂ ተማሪዎች እንዳይረጋጉና ምዝገባ አከናዉነዉ ወደ ትምህርት እንዳይመለሱ በማህበራዊ ሚዲያ የማስፈራርያ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ሙከራ የሚያደርጉ አካላት መኖራቸዉ ተደርሶበታል፡፡ ይህን የሚያደርጉ አካላት ላይ ዩኒቨርሲቲዉ ጥብቅ ክትትል እያደረገ ሲሆን በግቢ ዉስጥ የተጠናከረ የጸጥታና ህግ-ማስከበር ስራ በተጠናከረ መልኩ እየተካሄደ መሆኑን እናሳዉቃለን፡፡
በመሆኑም፣ ዉድ ተማሪዎቻችን አስተማማኝ የጸጥታና ደህንነት ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን አዉቃችሁ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሳሳች መልእክቶች አብዛኛዉን ትምህርት ፈላጊ ተማሪዎችን ለማደናገር የሚደረጉ ሙከራዎች መሆናቸዉን በመገንዘብ ዩኒቨርሲቲዉ ቀደም ብሎ ባወጣዉ ማስታወቂያ መሰረት ተመዝግባችሁ ትምህርታችሁን እንድትቀጥሉ እናሳስባለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሰላምና መረጋገት ሰፍኖ ትምህርት እንዲጀመር ጉልህ ሚና እያበረከታችሁ ለምትገኙ የግቢ ዉስጥና ዉጭ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናችንን ለማቅረብ እንወዳለን፡፡
(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)