TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
AAU 6 ኪሎ የተማሪዎች ረብሻ ተነስቷል🤔

(ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት)

ዛሬ ቀን 7:30 ስድስት ኪሎ ዪንቨርስቲ የተማሪ ጩኸት ይሰማል። ፌዴራል ፓሊሶች አሉ። ተማሪዎች ከዶርም እንዳይወጡ ተደርገዋክ። የጊቢው በሮች ዝግ ናቸው። አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማል። ረብሻ ለማስነሳት ሙከራዎች ነበሩ ግን እውነተኛ ምክንያቱን አላውቅም ሲል አንድ ተማሪ ተናግሯል።

ይህ በጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት ፌስቡክ ገፅ ላይ የቀረበው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የቲክቫህ 6 ኪሎ ቤተሰቦች ገልፀዋል። በግቢው ውስጥ አለመረጋጋት ነበር ነገር ግን ተኩስ የሚባል ነገር አልነበረም፤ መረጃው ስህተት ነው ሊታረም ይገባዋል ብለዋል። @tikvahethiopiaBot
ጋሞ ዞን...

በጋሞ ዞን በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማይገባቸው ደረጃ ላይ ተቀምጠው በተገኙ 31 ግለሰቦች ላይ ክስ ለመመስረት የሚያስችል መረጃ ማሰባሰቡን የዞኑ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ገለፀ። የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዳበሮ ዳልጬ እንደገለፁት ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በዞን ደረጃና በስሩ በሚገኙ ወረዳዎች የ3ሺህ 238 ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራ ተከናውኗል። ከእነዚህ ዉስጥ 31 የመንግስት ሠራተኞች በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ለበርካታ ዓመታት የመንግስትን ገንዘብ ያለአግባብ ሲጠቀሙ መቆየታቸውን ተረጋግጧል፡፡

(ENA)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AAU

ጋዜጠኛ ጌትነት ተስፋዬ - ተኩስ ነበረ የተባለው #ውሸት ነበር በሚል ዳግም በፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ አስተካክሏል። በተማሪዎች ስም እኛም እናመሰግናለን!
-------
ጥቃቅ የሚመስሉ ነገር ግን ወላጆችን የሚያስጨንቁ መረጃዎች ስላሉ ጋዜጠኞችም ሚዲያዎችም ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ መረጃ ቢያቀብሉ ይመረጣል!! ትላንት ፋና ብሮድካስቲንግ በፌስቡክ ገፁ ይዞት የወጣው የተሳሳተ መረጃ በርካታ ቤተሰቦቻችን ላይ ጭንቀት ፈጥሮ ነበር።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ የነበረው ግርግር በፍጥነት ተረጋግቷል አለ!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በዩኒቨርሲቲው ተፈጠረሮ የነበረውን ችግር በፍጥነት በመቆጣጠር አሁን የተረጋጋ ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል፡፡ ግርግሩ ተማሪዎች ባነሱት ጥያቄ የተፈጠረ ቢሆንም ጥያቄው ምን እንደሆነ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡ ከደቂቃዎች በፊት በዩኒቨርሲቲው ግርግር ከተፈጠረ በኋላ የፀጥታ አካላት ሁለት ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ከዩኒቨርሲቲው ይዘዉ ሲወጡ ታይተዋል፡፡

(Tamirayehu W. Seven)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና ወ/ሮ ያለም ፀጋይ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኙ!

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወይዘሮ ያለም ፀጋይ የቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኙ። በጉብኝታቸውም በሆስፒታሉ ግቢውስጥ በቅርቡ የጤና ሚኒስቴር ያስከፈተውን የመረጃ ማዕከል እንዲሁም ህሙማንን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በተጨማሪም የሆስፒታሉን የልብ ሀክምና ማዕከል፣ የቶክሲኮሎጂ (የተመረዙ ሰዎች ህክምና) የስልክ ጥሪ ማዕከል እና የቀዶ ህክምና ማዕከልን ጎብኝተዋል። በዚህ ወቅትም በህክምና ክፍሉ የሚስተዋሉት የአቅርቦትና የግብዓት ችግሮች እንዲፈቱ የራሳቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።

(ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬም ባለፉት ቀናት በተለያዩ ጥፋቶች ላይ ተሳትፈዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን የመያዙ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲል ገልጿል፡፡ የትላንት የዩኒቨርሲቲዎች አዳርም ሰላማዊ ነበር፤ ከተደረጉ ውይይቶች በኃላ ወደ ትምህርት የተመለሱ ተማሪዎች ቁጥርም በእጅጉ እየተሻሻለ ነው ብሏል፡፡

(የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#InjibaraUniversity

የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠልና የዩኒቨርሲቲውን ሰላም ለማስጠበቅ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመጡ ተማሪዎች መካከል ስምምነት ላይ ተደረሰ!
.
.
በተለያዩ የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ የነበረውን ስጋት ለመቅረፍ ከሰኞ ማለትም ከቀን 08/02/12 ጀምሮ ምክክር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

በምክክሩ ላይ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከክልልና ከዞን የተወከሉ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር አካላት፣ መምህራንና የተማሪ ተወካዮች እንዲሁም ሁሉም ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በውይይት ሂደቱም በዋናነት በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚከሰቱት አላስፈላጊ ግጭቶች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሊንፀባረቁ እንደማይገባና ተማሪ ጥያቄ ካለው በሰለጠነ መንገድ ማቅረብ እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ከሁሉም አካባቢ የመጡ ተማሪዎች ተቻችለውና ተከባብረው ለዩኒቨርሲቲውና ለሀገር ሰላም በጋራ መቆም እንዳለባቸውም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በመጨረሻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፕ/ር ብርሃኑ በላይ እና የሀገር ሽማግሌዎች ለተማሪዎች ምክር ሰጥተው፤ ለተገኘው ሰላምና በጋራ የመቆም መንፈስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ከነገ ማለትም ከ12/03/12 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም ተማሪ በክፍል እንዲገኝም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

(Injibara University)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በእንጂባራ ዩኒቨርሲቲ ከነገ ዓርብ 12/03/12 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም ተማሪ በክፍል እንዲገኝ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከAAU ቲክቫህ ቤተሰቦች...

"አሁን አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ (AAU 6 ኪሎ) ተማሪዎችን ሰብስበው ካናገሩን በኃላ ሁሉም ነገር ተረጋግቶ ወደ ዶርም ተመልሰናል። የተወሰኑ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ከዛ ውጪ እንደሚባለው #የተጋነነ ምንም የተፈጠረ ነገር የለም። ፕሬዝዳንቱም የሚያረጋጋ ንግግር አድርገዋል። ለተፈጠረውም ነገር ተማሪዎችን ይቅርታ ጠይቀዋል። በአሁን ሰዓት ተዘግተው የነበሩት የዩኒቨርሲቲው በሮች በሙሉት ተክፍተዋል። L(Tikvah Family-AAU)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ውብ ምስል ከሸገር ደርቢ . . .

ከሸገር ደርቢ በፊት ሁለቱ የሜዳ ላይ ተፎካካሪዎች ደጋፊዎቻቸው በአንድነት ከጨዋታው በፊት አንድ መሆናቸውን በስታዲየም ዙሪያ እየተጨዋወቱ የሚያሳይ ምስል!

TIKVAH FAMILY ( LEO )

በስታዲየም መግባት ላልቻላችሁ እንዲሁም በስራ ጫና በቴሌቪዥን መከታተል ያልቻላችሁ ቤተሰቦቻችን ጨዋታውን በፅሁፍ ከቲክቫህ ስፖርት መከታተል ትችላላችሁ👇
@tikvahethsport https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
በአዳማ ከተማ ተከስቶ የነበረው ግጭት ባስከተለው ጉዳት የተጠረጠሩ 179 ግለሰቦች ለህግ ቀረቡ!

በአዳማ ከተማ ሰሞኑን በተፈጠረው ግጭት የሰው ህይወት በማጥፋትና ንብረት በማውደም የተጠረጠሩ 179 ግለሰቦች ለህግ መቅረባቸውን የከተማዋ አስተዳደርና ፀጥታ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።

የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ሁባድ ጂና እንደገለጹት ለህግ የቀረቡት ተጠርጣሪ ግለሰቦች ሰላማዊውን የወጣቶችን ተቃውሞ በመጠምዘዝ ወደ ግጭት እንዲያመራ ምክንያት የሆኑ ናቸው ብለዋል።

ጉዳዩን በማስተባበር፣በመምራትና በመሳተፍ ለሰው ህይውት መጥፋትና በንብረት ማውድም የተጠረጠሩ 179 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ተናግረዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-21-2

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል!

ውጤቱ የሲዳማ ዞንን ወደ ክልልነት የሚመራ ከሆነ ከዚህ በኋላ ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደሕዴን) ጋር ግንኙነት አይኖረንም ብለዋል፡፡

- የአዲሱ የብልፅግና ፓርቲ አባል እንሆናለን፣ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱንም በክልላችን እንከፍታለን ብለዋል፡፡

- በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የጣቢያው ውጤቶች ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ተለጥፈዋል፡፡

- ዛሬ እና ነገ አጠቃላይ ጊዜያዊ ውጤቱ ይደርሳል ተብሏል፡፡

- ምርጫ ቦርድ በ7 ቀናት ውስጥ አጠቃላይ ውጤቱን አሳውቃለሁ ብሏል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MekdelaAmbaUniversity

ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በስጋት ምክንያት ከግቢ የወጡ ተማሪዎች እስከ ህዳር 15/2012 ዓ/ም ድረስ ብቻ ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመልሰው ትምህርታቸው እንዲከታተሉ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አቀረበ። በተጠቀሰው ቀን ለማይመጡ ተማሪዎች ኃላፊነቱን አለወስድም ሲል ዩኒቨርስቲው ገልጿል። በአሁኑ ሰዓት የዩኒቨርሲቲው ሁለቱም ካምፓሶች በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛሉ፤ መደበኛው የመማር ማስተማር ስራም እየተከናወነ ይገኛል ብሏል ተቋሙ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

ዛሬ ከሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቡጁምቡራ ውስጥ ካረፈ በኋላ በሽብር ድርጊት የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የቡሩንዲ ባለስልጣናት አረጋገጡ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን አንድ ተሳፋሪ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት በሰነዘረው ማስፈራሪያ አውሮፕላኑ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ወደሚያርፉበት የቡጁምቡራ አየር ማረፊያ እንዲቆም መደረጉም ተነግሯል። አውሮፕላኑ ዛሬ በቀጥታ በረራ ከአዲስ አበባ ወደ ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ እየበረረ ሳለ ነበር ችግሩ የተከሰተው ተብሏል።

More👇
https://telegra.ph/BBC-11-21

(BBC)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
70 ክላሽንኮቭን ጨምሮ ሌሎች የጦር መሳሪያዎች በቡኖ በደሌ ዞን በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹ በተለምዶ ቦቴ ተብሎ በሚጠራው የፈሳሽ ጭነት ተሽከርካሪ ውስጥ በድብቅ ተጭነው በመጓጓዝ ላይ እያሉ በተደረገ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። በተደረገው ፍተሻም 70 ክላሽንኮቭን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኮማንደር ቶሎሳ ሙሉጌታ መናገራቸውን ኦ.ቢ.ኤን ዘግቧል።

(OBN)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰበር ዜና!

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር /ኢህአዴግ/ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ የድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የመራለትን የፓርቲውን ውህድ በሙሉ ድምጽ አፅድቋል፡፡

(EBC)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት ተከባበረው፣ ተዋደውና ተደጋግፈው የኖሩ ህዝቦች ናቸው" - የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች

የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት በሚጥሩ ሃይሎች ምክንያት የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ጠብና ጥላቻ ውስጥ እንደማይገቡ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ-ገዳዎችና የአገር ሽማግሌዎች ገለጹ። የአማራና ኦሮሚያ ክልሎችን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ የሰላም የምክክር መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

በሰላም ውይይት መድረኩ ላይ የተሳተፉት የሃይማኖት አባቶች፣ አባ-ገዳዎችና የአገር ሽማግሌዎች የአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ለረጅም ዘመናት ተከባበረው፣ ተዋደውና ተደጋግፈው የኖሩ ህዝቦች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ይሁንና በአንዳንድ የፖለቲካ ትርፍ ፈላጊዎችና በማህበራዊ የትስስር ገጾች ሳቢያ በመካከላቸው “ቁርሾ እንዳለ ተደርጎ የሚናፈሰው ወሬ ከወሬ የዘለለ አይደለም” ብለዋል። በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች መነሻን በማወቅ ችግሩን ከምንጩ መፍታት ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል።

ቤተክርስቲያንና መስጊድ ማቃጠል ከየትኛውም የሃይማኖት አስተምህሮ ውጪ መሆኑን ያነሱት ተሳታፊዎቹ፤  እንዲህ አይነት እኩይ ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች የትኛውንም ብሄርና ሃይማኖት የማይወክሉ በመሆናቸው ሊወገዙ እንደሚገባም አሳስበዋል። በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን ግንኙነት የበለጠ እንዲጠናከር የማድረግ ሃላፊነትም የእነርሱ ቢሆንም ተሳታፊዎቹ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ አለመወጣታቸውን ተናግረዋል።

(ENA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአማራና የኦሮሞ አክቲቪስቶች ምን መከሩ?

"እንዴት ነው የነበረን ድርሻ የጥላቻ ንግግር፣ የጥላቻ ፅሁፍ በቪድዮም በፅሁፍም የሚደረገው ነገር ቆሞ፤ ወደ አንድነት እና ወደ መቀራረብ ወደ ሰላም የሚያመጣ ፅሁፎች እየፃፍን ያለውን ውጥረት ማርገብ አለብን በሚለው ላይ ተስማምተን ነው 10 ነጥብ ያለው የአቋም መግለጫ ያወጣነው" አቶ ሃምዛ ቦረና (አስተባባሪ)

(BBC RADIO)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሁሉም በሀገር ነው!

ጥሩ ልብስ ለብሰን...አምሮብን ተውበን የምንታየው፤
ሰዎች እንረዳ ቢገባን ትርጉሙ...ሁሉም በሀገር ነው!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ድምጽ መስጠት ሂደት ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንደተከናወነ ይታወቃል፡፡ በድምጽ መስጫው ቀን ማምሻ ላይ ቆጠራው ተጠናቆ የህዝበ ውሳኔው ውጤት በምርጫ ጣቢያዎች ላይ ይፋ ተደርጓል፡፡

በትላንትናው እለት የሁሉም ምርጫ ጣቢያ ውጤቶች ተጠናቀው ወደ15ቱም ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቶች የገቡ ሲሆን በዛሬው እለት የዞን ማስተባበሪያ ጣቢያ ላይ ውጤቱን የማጠቃለል ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ቦርዱ ውጤት የሚያሳውቀው ነገ ቅዳሜ ህዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም በመሆኑ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በትእግስት እንዲጠብቁ ጥሪ ያስተላልፋል፡፡

(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot