TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኛ የመጨረሻ ተስፋችን እናተ ናችሁ😢

በፌደራል መንግስት በሚተዳደሩት የሀገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ደህነታቸው በእጅጉ ሊጠበቅ ይገባል።

በሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ለነገ የሀገር ተስፋ የሆኑ ተማሪዎች ማንነታቸው ላይ ተገን ተደርጎ የሚፈፀመው ተገቢ ያልሆነ፣ አፀያፊ ድርጊት በዚሁ በቃ ካልተባለ ሀገሪቱን አሁን ካለችበት ችግር ወደ ማያባራ እልቂት ውስጥ ይከታታልና መንግስት ሳይውል ሳያድር እርምጃ ሊወስድ ይገባል።

መንግስት ለተማሪዎች ሞት ተጠያቂ የሆኑትን በመለየት እርምጃ ከመውሰድ አንስቶ የሌሎች ተማሪዎችን ደህንነት ከመጠበቅ አንፃር ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅበታል። የሁሉም ዩኒቨርሲቲ ደህንነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠበቅ ሊል ይገባል።

እየደረሰባቸው ባለው ማስፈራሪያ፣ እየተለጠፉ ባሉ ፅሁፎች፣ በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጩ ዛቻዎች ምክንያት በሁሉም ቦታ ለሚንገላቱ ምስኪን ተማሪዎች ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። በየቤተ እምነቱ የተጠለሉ ምስኪን ተማሪዎችም ደህንነታቸው ተጠብቆ ትምህርታቸውን የሚቀጥሉበት አልያም ወደየቤታቸው የሚሸኙበት መንገድ ሊፈለግ ይገባል፤ የሰው አእምሮ ሰላም ሲሆን ብቻ ነውና ለትምህርት ዝግጁ የሚሆነው።

ውድ ወጣቶች በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ያላችሁ እባካችሁ ወንድሞቻችሁን አትግፉ፣ ተዋደዱ፣ ተከባበሩ፣ ለህይወታቸው ሰግተው ግቢያቸውን ጥለው የወጡትንም አቅፋችሁ መልሱ፣ ተደጋገፉ፣ የአንዱን ወንጀል ለአንዱ አትስጡ። ወንጀል ፈፃሚ የሚወክለው እራሱን ነውና።

የኛ የመጨረሻ ተስፋ እናተ ወጣቶች ናችሁ። ሰላም ስትሆኑ ደስ ብሎን እናድራለን፣ ስትዋደዱ ጭንቀታችን ይጠፋል፣ ከቂም ከበቀል ስትርቁ ነገን ለማየት እንጓጓለን፣ ስትከባበሩ ጤናችን ይመለሳል!! በእናተ መቼም ተስፋ አንቆርጥም!!

ቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tikvahethiopiaBot👈ሀሳብ መቀበያ
#FakeNewsAlert

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ "ሁለት ተማሪዎች ሞቱ" ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃ ውሸት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ምንም የሞተ ተማሪ የለም፤ በውሸት መረጃም እንዳትሸበሩ ሲል ዩኒቨርሲቲው መልዕክቱን አስተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዩኒቨርሲቲያችን የሞተ ተማሪ የለም!

(ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ)


በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ረብሻ ተነስቶ ሁለት ተማሪዎች ሞቱ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚሽከረከረው መረጃ ውሸት መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ በዩኒቨርሲቲያችን ምንም የሞተ ተማሪ የሌለ በመሆኑ በውሸት መረጃ እንዳትሸበሩ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

(ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ)

Universiti Haramaya keessatti
jeeqqumsii ka'ee barataan akka midhamee fi du'ee marsaaneeti irratti naanna'uu sobbaa fi kan dhugaa irraa faggattedha.

Universiti Haramaya keessatti barataan lubbun isaa darbittee akka hin jiree hubbatanii akka tasgabooftan ergaa keenya dabarsu barbaannaa.

(Universiti Haramaya)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Freweini Mebrahtu

ፍረወይኒ መብራህቱ ላለፉት 13 ዓመታት በኢትዮጵያ በሴቶች ወር አበባ ላይ ያለው የተሳሳተ አመለካከት ለማረም የሚያግዙ ስራዎች ሲከውኑ ቆይተዋል። የራሳቸው የፈጠራ ውጤት የሆነ እየታጠበ በተደጋጋሚ አገልግሎት መስጠት የሚችል የሴቶች ንፅሕና መጠበቂያ ሰርተው ለተጠቃሚዎች አቅርበዋል። የንፅሕና መጠበቂያውን በገጠሩ የኢትዮጵያ ክፍል ለሚኖሩ አንድ ሚሊዮን ገደማ ልጃገረዶች ከሌሎች በጎ አድራጊ ተቋማት ጋር በመተባበርም በነፃ እንዲያገኙ አድርገዋል። 

የCNN ቴሌቪዥን ጣቢያ የ2019 የአለማችን 10 ጀግኖች ብሎ ከመረጣቸው መካከል ፍረወይኒ አንዷ ናቸው። የፍረወይኒ የፈጠራ ውጤት የሆኑት የሴቶች ንፅሕና መጠበቅያ ምርቶች የሚመረቱት መቐለ በሚገኘው ማርያም ሳባ ተብሎ የሚታወቅ ማምረቻ ተቋም ውስጥ ነው። ከዚያ ተነስተው በትግራይ ክልል ባሉ ሌሎች አካባቢዎች፣ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና አፋር ክልሎች ለሚገኙ ሴቶች ይደርሳሉ። በዚህም ሴት ተማሪዎች በወር አበባ ጊዜ ከትምህርት ገበታ ሲቀሩበት የነበረው ችግር እና ሌሎችም ተዛማጅ ችግሮች መቀነሳቸው በጥናት ተረጋግጧል።

Vote for the CNN Hero of the Year!
https://www.cnn.com/SPECIALS/cnn.heroes/vote/10/?source=instagram

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#attention #DireDawa

"ሰላም መምህር S ከድሬዳዋ #TIKVAH ቤተሰብ ከእሁድ ጀምሮ በአንዳንድ ሰፈሮች ላይ በተፈጠሩ ግርግሮች ዛሬ የትምህርት የፕሮግራሞችን አቋርጠናል። መንግስት ፀጥታውን በማረጋገጥ ትምህርቱን ማስቀጠል ብንችል መልካም ነው። ተማሪዎች መውስድ የነባረባቸውን Mid exam በሁለቱም የግርግር ወቅቶች እያራዝምን በአግባቡ ማስተማር አልቻልንም። ተፅዕኖውም ተማሪዎች ላይ በግልፅ ይታያል።"

በሌላ በኩል ምስራቅ ሃረርጌ ኢርና እና አካባቢው አለመረጋጋት መፈጠሩን የቤተሰባችን አባላት እየገለፁ ይገኛሉ፤ መንግስት ትኩረት እንዲያደርግ እናሳስባለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያሉበት ሁኔታን የሚመለከታቸውን ክፍል አነጋግሮ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተከታዩን ዘገባ ሰርቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TimotiyosBaye #TikvahSportFamily

ታዋቂው የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወኪል በፊፋ ፍቃድ ያገኘው የቲኪቫህ ስፖርት ቤተሰብ ጢሞቴዎስ ባዬ በይፋ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ለተከበራችሁ ቤተሰቦቻችን ጥልቅ የሆኑ የሀገር ውስጥ እና የአውሮፓ ጨዋታዎች ላይ በሜዳ ላይ ስለሚኖሩ ታክቲካዊ እይታዎችን ባማረ አቀራረብ የሚያጋራን ይሆናል ::

ከዚህም በተጨማሪ ከሀገር ውስጥ ክለቦች ያልተሰሙ አዳዲስ መረጃዎች ጎን ለጎን ያልተሰሙ ቃለ መጠይቆችን ከጢሞቴዎስ ባዬ በቲኪቫህ ስፖርት በቀጥታ የምናደርስዎ ይሆናል።

Join 👉 @tikvahethsport
በምስረታ ላይ ያሉት የዘምዘም፣ የሂጅራ፣ የዛድና የነጃሺ እስላማዊ ባንኮች የአክሲዮን ሽያጭም ሆነ የሚሰጡት አገልግሎት ለሁሉም ዜጋ ክፍት መሆኑ ተገለጸ።

የባንኮቹ የሥራ ኃላፊዎች ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ባንኮቹ የሚሰጧቸው አገልግሎቶች የሸሪያን ህግ መሰረት ያደረጉ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በባንኮች በመስኮት ደረጃ የሚሰጡትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችንና ከወለድ ነፃ አገልግሎቶችን ያካተቱ ናቸው።

ባንኮቹ ወለድን ከመቀበልና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚጎዱ አልኮል ለማምረት፣ ለቁማርና ለጦር መሳሪያዎች ከሚውል ብድርና አገልግሎት ውጭ ሌሎች አገልግሎቶችን በሙሉ ይሰጣሉ ያሉት ኃላፊዎቹ፣ በባንኮቹ የእስልምና ተከታዮች ብቻ ሳይሆን የተለያየ እምነት ተከታይ ማህበረሰቦችም የሚገለገሉበት ነው ብለዋል።

(EPA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

እየተሻሻለ በሚገኘው የፀረ ሽብር ህግ በደህንነት መስሪያ ቤት ብቻ በሚቀርብ መረጃ ተጠርጣሪዎችን ለብይን የሚዳርገው አሰራር እንዲቀር መደረጉ ተገልጿል!

https://telegra.ph/ETH-11-13-2

(ኤፍ ቢ ሲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

#Live
animation.gif
17.2 KB
#ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ(ASTU) የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠል እየሰራ መሆኑን ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ለሚ ጉታ ዛሬ ለኢዜአ እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማረጋገጥ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው። በዚህም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመቀናጀት ተማሪዎች ትምህርታቸውን ለማስቀጠል እየተሰራ ነው ብለዋል።

ተማሪዎች ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ወደ  ተቋሙ የመጡበትን ዓላማ እንዲተዉ የሚገፋፏቸውን አካላት የፖለቲካ አጀንዳ ማስፈጸሚያ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊነቱን ጠብቆ ለማካሄድ በከተማዋ ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ጋር በመሆን የተማሪዎችን ደህንነት  በመጠበቅ  ላይ እንደሚገኝ ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።

(ኢዜአ)

በሌላ በኩል ከቲክቫህ ቤተሰቦች...

በASTU፣ ሀረማያ፣ ጅማ(JiT)፣ መደወላቡ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መቱ ዩንቨርስቲዎች ውስጥ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ ተማሪዎች ያደረባቸውን ስጋት ዛሬም እየገለፁ ይገኛሉ። ለህይወታችን ሰግተናል ያሉ ተማሪዎች በቤተ እምነት ውስጥ ተጠለልው እንደሚገኙ ገልጸዋል። መልዕክት የላኩት ተማሪዎች ጉዳዩ ይሄ ያህል እስኪከር ድረስ ምንም መፍትሄ ባለመሰጠቱ የፌደራል መንግስቱን ወቅሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከደቂቃዎች በኋላ መግለጫ ይሰጣል። ከሰሞኑ በተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፀጥታ ችግር አጋጥሟል፤ የተማሪዎች ሕይወትም አልፏል፡፡ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ የሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በእነዚህ የፀጥታ ችግሮችና መፍትሔዎች ላይ ያተኮረ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines #CNN

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአለም አቀፉ መገናኛ ብዙሃን CNN ለማስታወቂያ 60 ሺ የአሜሪካ ዶላር መድቤያለሁ ማለቱን ሸገር ሰምቷል፡፡ CNN አየር መንገዱን እና ኢትዮጵያን በአለም ለማስተዋወቅ ተመርጧል ተብሏል፡፡

በ60 ሺህ ዶላርም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ በአሜሪካ በሚገኘው እውቁ የቴሌቪዥን ቻናል Cable News Network (CNN) ይተዋወቃል ብለው ለሸገር ኤፍ ኤም የተናገሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ናቸው፡፡

በCNN የቴሌቪዥን ቻናልም ስለ ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚነገር ማስታወቂያ ለ2 ወር በየቀኑ 3 እና 4 ጊዜ ይተዋወቃል ተብሏል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከCNN ጋር በማስታወቂያው ጉዳይ እንዳልተፈራረመ ነገር ግን በሂደት ላይ እንዳለ አቶ ተወልደ ተናግረዋል፡፡

(SHEGER FM)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ላይ ሰኔ 15 ከተፈፀመው ጥቃት ጋር በተያያዘ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከሰጠው መግለጫ፦

•ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ 70 ተጠርጣሪዎች መያዣ ወጥቶባቸው 31ዱ በቁጥጥር ስር ውለዋል

•የ147 ሰዎችን ቃል መቀበል ተችሏል

•የ22 ተጠርጣሪዎች የባንክ ሂሳብ ታግዷል

•ወንጀሉን ከሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ጀምሮ ለመፈፀም ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል

•ጥቃቱ በብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ መሪነት የተፈጸመ ነው

•ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ማጣራት ተደርጎ ከተጠርጣሪዎቹ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች፣ በርካታ ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ የውጭና የሃገር ውስጥ ገንዘብ፣ 5 ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ በርካታ ቁሳቁሶች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል

•በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ 4 ጠባቂዎችን ጨምሮ 8 አጃቢዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል!

(FBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE የጄኔራል ሰዓረ መኮንን ገዳይ የተባለው አስር ዓለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ትዕዛዝ የተቀበለው በብርጋዴየር አሳምነው ጽጌ የተመለመለ ጎንደር ድረስ ሔዶ ካገኛቸው እና ስሙ ካልተገለጸ ግለሰብ መሆኑን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ተናግረዋል። አቶ ብርሐኑ እንዳሉት ከባለሥልጣናቱ ግድያ ጋር በተያያዘ በባሕር ዳር 277 በአዲስ አበባ 140 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ነበር። በባህሕር ዳር 55 በአዲስ አበባ በ13 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ይመሰረታል።

(እሸት በቀለ-ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ የደህንነት ስጋት ያደረባቸውና በጅማ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የተጠለሉ ተማሪዎች ከሃይማኖት አባቶች፣ ከአባ ገዳዎች፣ ከተማሪ ተወካዮች፣ ጋር እየተወያዩ ነው። በነገራችን ላይ በየመስጊዱም የተጠለሉ ተማሪዎች እንዳሉ የቲክቫህ ቤተሰቦች ጠቁመዋል። በውይይቱ ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ የሚለውን ቆየት ብለን እናቀርባለን።

(ቲክቫህ ቤተሰቦች)

@tsegawolde @tikvahethiopia