TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የህዝበ ውሳኔ የመራጮች ምዝገባ የሚደረግባቸው ጣቢያዎች ጎበኙ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በሲዳማ ክልል ህዝበ ውሳኔ ላይ የመራጮች ምዝገባ የሚደረግባቸውን አንዳንድ የሀዋሳ ከተማ የምርጫ ጣብያዎችን መጎብኘታቸውን ማለዳ ሚዲያ ዘግቧል። ወ/ሪት ብርቱካን እስካሁን ያለው የመራጮች ምዝገባ ሂደትም ፍጹም ሰላማዊ እና በታቀደው መልኩ እየሄደ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

(ማለዳ ሚዲያ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MEKELLE

የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች ማስታወቂያ በሚያስነግሩ ሰዎችና ድርጅቶች ከመጠን በላይ በሚለቀቅ ድምጽ መቸገራቸውን ተናገሩ። በከተማው በተሽከርካሪዎች እየዞሩ የተለያዩ ማስታወቂያዎች የሚያስነግሩ ድርጅቶች በድምጽ ማጉያ ከልክ በላይ በሚለቁት ድምጽ ሕብረተሰቡን እያወከ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
.
.
.
በመቐለ ከተማ አስተዳደር "የአካባቢ ጥበቃ ጽህፈት ቤት" አስተባባሪ አቶ ጀማል ካሕሳይ ስለ ጉዳዩ ከኢዜአ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ የህብረተሰቡ ቅሬታ አግባብ መሆኑን ተናግረዋል።

በከተማው በቀን እና በማታ የሚለቀቀው ድምጽ ከመጠን በላይ ያለፈና የከተማዋን ነዋሪዎች እያወከ መሆኑን አመልክተዋል። ህብረተሰቡ ለማስተማርም ሆነ በአጥፊዎች ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድርግ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በጽህፈት ቤቱ ያለው የሰው ኃይል አንድ ሰው ብቻ በመሆኑ መቸገራቸውን አስረድተዋል።

(ENA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አሚር አማን....

በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘው የራስ አበበ አረጋይ መኖሪያ የነበረው ቤት ይዘቱን ሳይቀይር የጤና እና ከጤና ጋር ተዛማጅ የሆኑ መረጃዎች ማከማቻ /data center/ ተደርጎ ተሰርቷል፡፡ ማዕከሉ በተጨማሪ የስልጠና ፣ የሶፍትዌር ልማት /software development/ ፣ ጤና ላይ የሚሰሩ የኤሌክትሮኒክ ሲስተም ላይ መረጃ የሚሰጥ የ24 ሰዓት የጥሪ ማዕክል እና የምርምርና የልዕቀት ማዕከል አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጎ ነው የታደሰው፡፡ ለማዕከሉ ግንባታና እድሳትም የጤና ሚኒስቴር እና አጋር ድርጅቶ ትብብር ማድረጋቸውን ከጤና ሚኒስተር ዶ/ር አሚር አማን ማህበራዊ ድረ ገፅ ላይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

(ዋልታ ቴሌቪዥን)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዋሽንግቶን ዲሲ ከንቲባ የሚመራ የልኡካን ቡድን ነገ አዲስ አበባ ይገባል!

የአሜሪካዋ ዋሽንግቶን ዲሲ ከተማ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር ከነገ ቅዳሜ ጀምሮ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ይገባሉ። ከ50 በላይ የንግድ ማህበረሰብ አባላትም ከከንቲባዋ ጋር አብረው ይመጣሉ፡፡

ከንቲባዋ በአዲስ አበባ ቆይተቸው አዲስ አበባና ዋሽንግቶን ዲሲ የእህትማማች ከተማነት ስምምነታቸውን በአዲስ መልክ ለማደስ የሚያስችላቸው ስምምነትም ያደርጋሉ፡፡

ከንቲባዋ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት ከዚህ ቀደም ኢ/ር ታከለ ኡማ በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት ባቀረቡላቸው ጥሪ መሰረት ነው፡፡ ከንቲባዋ በአዲስ አበባ ቆይታቸው በተለያዩ ተቋማት ጉብኝትና ውይይት የሚኖራቸው ይሆናል፡፡

(EPA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአንበጣ መንጋ -- በድሬዳዋ⬆️

(ድሬዳዋ-ቲክቫህ ቤተሰቦች)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትዊተር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው!

የትዊተር መሥራች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጃክ ዶርሴይ ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት የአፍሪካ ሀገራትን በዚህ የህዳር ወር እንደሚጎበኙ ተናግረዋል።

ጉብኝታቸውንም በናይጄሪያ የጀመሩ ሲሆን፥ በቀጣይ ወደ ኢትዮጵያ፣ ጋና እና ደቡብ አፍሪካ በማምራት ከሥራ ፈጣሪዎች ጋር እንደሚወያዩም በትዊተር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ ከኢትዮጵያውያኑ የቴክኖሎጂ የሥራ ፈጣሪ ወጣቶች፣ ቤተልሄም ደሴ፣ ኖኤል ዳንኤል እና ጌትነት አሰፋ ጋር ሰፊ ቆይታ እንደሚኖራቸው ነው ጃክ ዶርሴይ የገለጹት።

(ኢዜአ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

ጥቁር አንበጣ ወደ መርሳ እየገባ ነው!

አሁንም የአንበጣ መንጋ ወደ መርሳ እየገባ በመሆኑ የመርሳ ከተማ #ወጣቶች የተለመደ ትብብራችሁን በማድረግ አርሶ አደሩን ከጥፋት ታደጉት።

(መርሳ ከተማ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በተፈጠረው ጉዳይ ተቋሙ ማስታወቂያ አውጥቷል፡፡ ማስታወቂያው እንደሚለው ከሆነ ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሴት ተማሪዎች "የእርግዝና ምርመራ" በማድረግ ውጤቱን በ48 ሰዓት ውስጥ ለፕሮክተሮች እንዲያስገቡ የማያዝ ነው፡፡ (ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ - ቲክቫህ ቤተሰቦች) @tsegabwolde @tikvahethiopia
ዩኒቨርሲቲው ይቅርታ ጠየቀ!

ድሬዳዋ ዩንቨርሲቲ ሴቶች የእርግዝና ምርመራ አድርጉ ብሎ ባሰራጨው መረጃ ይቅርታ ጠየቀ። የዩንቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር መቅደስ ካሳሁን ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት ዛሬ ጠዋት በ28/02/2012 ዓ.ም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለሴት ተማሪዎች በሙሉ የወጣው ማስታወቂያ በስህተት ነው ብለዋል። ለተከሰተው ስህተትም ዩንቨርሲቲው ይቅርታ ጠይቋል፡፡

(ETHIO FM)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ...

የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነት ባለሞያ በስልክ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት ዛሬ በግቢው ውስጥ የተለጠፈው ማስታወቂያ በስህተት የተለጠፈ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ የተማሪዎች ህብረትም የተለጠፈው ማስታወቂያ በሙሉ እንዲነሳ መደረጉን ገልጾልናል። ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ዩኒቨርስቲው የሚከተለውን መልዕክት በፌስቡክ ገጹ አሰራጭቷል፦

"ዛሬ ጠዋት በ28/02/2012 ዓ.ም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለሴት ተማሪዎች በሙሉ የወጣው ማስታወቂያ በስህተት መሆኑንና ማስታወቂያው በዋናው የፌስቡክ ገጻችን እና በቴሌግራም አድራሻችን ላይ አለመውጣቱን ዩኒቨርሲቲያችን እየገለጸ ለተከሰተው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡"

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ቃጠሎው የተነሳው ከቅኔ ማህሌቱ ሳይሆን ከመቅደሱ ውስጥ ነው፡፡ ማን አስነሳው እንዴት ተነሳ ሻማ አብርቶ የወጣው ዲያቆኑ ነው ወይስ ቄሰ ገበዙ ለምን ሳያጠፉ ወጡ የሚለው ከፖሊስ ምርመራ በኋላ አብረን የምናየው ይሆናል!" - የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል
.
.
በቀን 28/02/2012ዓ.ም ጥዋት 11 ሰአት ላይ በኮምቦልቻ መንበረ ሕይወት መድሐኒዓለም ቤተ ክርስትያን በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ከደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል ለሚዲያ አካላት የተሰጠ መግለጫ፦

ትናንት በ27/02/2012ዓ.ም በመላው ቤተ ክርስያን የሚከበረው የታላቁ በአላችን መድሀኒዓለም የሰው ልጆችን ያዳነበት ነው፡፡ ይህን አስመለክቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተከበሯል፡፡

በተጨማሪም በሀገሪቱ ላይ ባለው አለመረጋጋትና መከራ ስደትና የቤተክርስትያን ቃጠሎ አስመልከቶ ቅዱስ ሲኖዶስ በሰጠው መመርያ መሰረት አጠቃላይ በኢትዮጵያ የሚገኙ ገዳማትና አድባራት አምላካችን የመጣውን መከራ እንዲያስታግስልንና ቀጣይ ደግሞ ምእመናኑ ህወታቸውን እንዲጠብቁ ጸሎተ ምህላ ከጀመርን እነሆ ዛሬ አምስተኛ ቀናችን ነው፡፡

የማታው መርሀ ግብር ከንግሱ በአል በላይ የምእመኑ ቁጥር ብዙ ነበር፡፡ በአሉ ፖሊሶችና የፀጥታ አካላት ባሉበት ከቀኑ 11 ሰአት የጀመረው ከምሽቱ 2 ሰአት በሰላም ተጠናቋል፡፡ተረኛ የቤተክርስትያን አገልጋዮች ቁልፉን ለተረኛ ጥበቃ አስረክበው ወጥተዋል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-08-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮምቦልቻ

"በአካባቢው የነበሩ የሙስሊም ማህበረሰቦች ከኛ ጋር አብረው እየጮሁ፣ እየተጨነቁ፣ አፈርና ውሀ እየተሸከሙ እሳቱን ለማጥፋት ላደረጉት ርብርብ መድሀኒዓለም ጤና እና እድሜ ይስጥልን!" የደብሩ ዋና አስተዳዳሪ መላከ ሰላም አባ ሳሙኤል

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወንጀለኞች የታገቱ ኢትዮያውያን ህጻናት ተለቀቁ!

(Ethiopian Embassy Pretoria SA)

በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና በደቡብ አፍሪካ ፖሊስና የጸጥታ አካላት በተደረገው ከፍተኛ ጥረት በጆሐንስበርግ ከተማ በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮጵያውያን ህጻናት ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ተለቀው በፕሪቶሪያ ከተማ በሠላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል፡፡

የህጻናቱ ቤተሰብ አባላት ልጆቻቸው ከወንጀለኞች እጅ በሠላም መለቀቃቸው እጅግ እንዳስደሰታቸው የገለጹ ሲሆን፣ ኤምባሲው እና የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ኤምባሲው ከህጻናቱ ቤተሰቦችና ህብረተሰቡ ጋር በጥምረት ይሰራል፡፡

በዚህ አጋጣሚ በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር እንዲሁም በዜጎቻችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀለኞችን በህግ ለመፋረድ ለሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

(Ethiopian Embassy Pretoria SA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዋሽንግቶን ከንተባ ሙሪየል ቦውሰር አዲስ አበባ ገብተዋል!

ከንቲባው አ/አ ሲደርሱ ኢ/ር ታከለ ኡማና የተለያዩ የከተማዋና የፌደራል ክፍተኛ የስራ ሀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከከንቲባዋ ጋር ከ50 በላይ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ግለስቦች አብረው አዲስ አበባ ገብተዋል።

ከንቲባዋ በቆይታቸው የተለያዩ ጉብኝቶችን የሚያደርጉ ሲሆን አዲስ አበባና ዋሽንግተን ዲሲም የእህትማማች ከተማነት ስምምነታቸውን የሚያጠናክር ስምምነት የሚፈራረሙ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የነቢዩ ሙሐመድ (ሠዓወ) የልደት በዓልን አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት።

#PMOEthiopia

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የስልጤ ዞን ምክር ቤት አቶ አሊ ከድርን የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ። ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 5ኛ አስቸኳይ ጉባኤዉን ትላንት በወራቤ ከተማ አካሂዷል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SUDAN

•የሱዳን ዩኒቨርሲቲ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ሊያስተምር ነው!

•ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ዓረብኛ ቋንቋን ይሰጣል
!

በሱዳን ካርቱም የሚገኝው ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አፍሪካ በአማርኛና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ በዲግሪ ደረጃ ለማስተማር ስምምነት ላይ መድረሱ ተገለፀ። ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲም ዓረብኛ ቋንቋን በዲግሪ ደረጃ ሊሰጥ ነው።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሂዩማኒቲስ ቋንቋዎች ጥናት ጋዜጠኝነትና ኮሙዩኒኬሽን ኮሌጅ ዲን ዶክተር አማኑኤል አለማየሁ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደተናገሩት፤ በተገባደደው በጀት ዓመት ነሐሴ ወር ላይ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ፣ ከኮተቤ ሜትሮፖሊታን እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጣ አንድ ልዑክ ቡድን ወደ ሱዳን አቅንቷል።

ልዑኩ ከሱዳኑ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ጋር ባደረገው ውይይት የአማርኛና የአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎችን በሱዳን ዩኒቨርሲቲ እንዲሰጥና የዓረብኛ ቋንቋን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ እንዲሰጥ የሁለትዮሽ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CONGRATULATIONS

በአሁን ሰዓት "ጎንደር ዩኒቨርስቲ" የህክምና ተማሪዎቹን በደማቅ ሁኔታ እያስመረቀ ይገኛል፡፡ በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተማሪ ወላጆች፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ

@tikvahethmagazine
#ደሴ

በህገ ወጥ መንገድ 19 ወጣቶችን ወደ አረብ ሀገር ለማስወጣት የሞከሩ ግለሰቦች ደሴ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። ህጻናትና ወጣቶችን ወደ የቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🕌 እጅግ የምናከብራችሁና የምንወዳችሁ ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የእስልምና እምነት ተከታዮች የሆናችሁ ቤተሰቦቻችን እንኳን 1 ሺህ 494ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በዓሉ የሰላም፣ የመረዳዳት የመደጋገፍ በዓል እንዲሆንልን እንመኛለን መልካም በዓል🕌

#TIKVAH_ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HappeningNow

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሰላማዊ መማር ማስተማርን በተመለከተ ከጅማ ከተማ ማህበረሰብ ጋር ውይይት እያካሔደ ይገኛል!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ “የ2012 ዓ.ም ሰላማዊ መማር ማስተማር ሒደትን ማረጋገጥ” በተመለከተ ከጅማ ከተማ ማህበረሰብ ጋር በግብርና እና እንሰሳት ህክምና ኮሌጅ አዳራሽ ውይይት እያካሔደ ይገኛል፡፡

በውይይቱም የዩኒቨረርሲቲው የማኔጅመንት እና የካውንስል አባላት፣ የጅማ ከተማ መስተዳድር የስራ ሐላፊዎች፣ ከአባገዳዎች፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የሐገር ሽማግሌዎች፣ ቄሮዎች እና ቃሬዎች በ2012 ዓ.ም ሠላማዊ መማር ማስተማር ሒደት ውይይት ላይ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡

ውይይቱን እየመሩ የሚገኙት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ ዩኒቨርሲቲው መደበኛ ስራውን እንዲፈጽም ሰላም ቀዳሚ መሆኑን አንስተው ሁሉም ተሳታፊዎች የበኩላቸውን እንዲወጡ አጽንኦት በመስጠት ውይይቱን እንዲያስጀምሩ ለከተማ መስተደድሩ ከንቲባ እድሉን ሰጥተዋል፡፡

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ መክዩ መሐመድ በቡኩላቸው በመላው ሐገሪቱ የሚገኙ አባቶችና እናቶች ልጆቻቸውን አስረክበውናል፤ በመሆኑም የልጆቻችን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ሐላፊነት አለብን በማለት ከቀበሌ አመረር ጀምሮ፣ የከተማው መስተዳድር፣ የሐይማኖት ተቋማት የየድርሻቸውቸን ወስደው መስራት እንዳለባቸወው በመግለጽ ውይይቱን ለተሳታፊዎቸ ክፍት አድርገዋል፡፡

(ጅማ ዩኒቨርሲቲ)

@tsegabwolde @tikvahethiopia