TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ATAYE

በአጣዬ ከተማ አንድ ኮንቲነር ልባሽ ጨርቅና ሺሻ በሐሰተኛ ሰነድ በተሽከርካሪ ጭኖ ሲያጓጉዙ የነበረ ግለሰብ በተጠርጣሪነት መያዙን በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አስታወቀ።

በቅርንጫፉ የህግ ተገዥነት ተወካይ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ እንድሪስ መሃመድ እንደገለጹት ግለሰቡ የተያዘው ጥቅምት 21/2012ዓ.ም. ነው።

የተያዘው ተጠርጣሪው ግለሰብ ኮድ 3-25275 ኢት የሆነ የጭነት ተሽከርካሪ ህገ ወጥ የሆነው እቃ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ ሲያጓጉዝ ነበር ሾፌር መሆኑን አመልክተዋል።

የአካባቢው ህብረተሰብ በሰጠው ጥቆማ ተሽከርካሪ ሲፈተሽ ኮንቲነሩ ሙሉውን ልባሽ ጨርቅና የሚጨሰው ሺሻ ጭኖ መገኘቱን አስረድተዋል።

ሾፌሩ በፖሊስ ተይዞ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ያመለከቱት አቶ እንድሪስ “በኮምቦልቻ ደረቅ ወደብ ስም የተዘጋጀ ሐሰተኛ የይለፍ ሰነድም ይዞ ተገኝቷል “ብለዋል፡፡

የእቃው ብዛትና ግምት ቆጠራው ሲጠናቀቅ እንደሚገጽና ህብረተሰቡ ህገ ወጦችን ለመከላከል የሚያደርገው ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ከሳምንት በፊትም 340 ሺህ ብር ግምት ያለው ህገ ወጥ የግንባታ እቃ መያዙም ተመልክቷል፡፡

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-SPORT
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋልያዎቹ ፕሮግራም . . . . . .

የኢትዮጵያ ብሔራ ቡድን ከፊታችን ላለበት የ 2021 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ የምድቡ ሁለት ከባድ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ልምምዳቸውን በመቀሌ የሚያካሂዱ ይሆናል ፡፡

በዚህም መሰረት በኢንስትራከተር አብርሀም መብርሀቱ የሚሰለጥኑት ዋልያዎቹ ፕሮግራማቸው የሚከተለውን ይመስላል ፡፡

ጥቅምት 24 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ መቀሌ በማቅናት በዚሁ ዕለት ልምምዳቸውን ማምሻውን የሚያደርጉ ይሆናል ፡፡

ህዳር 1 - ልምምዳቸውን በማድረግ ከቆዩ በኋላ ዋልያዎቹ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱ ይሆናል ፡፡

ህዳር 2 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዕለተ ማክሰኞ የመጀመሪያ ተጋጣሚው ወደ ሆነው ማዳጋስካር አንታናናሪቮ የሚጓዝ ይሆናል ፡፡

ህዳር 6 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ የ 2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታውን ከሜዳው ውጪ ከማዳጋስጋር ጋር የሚያደርግ ይሆናል ፡፡

ህዳር 7 - ዋልያዎቹ የመክፈቻ ጨዋታቸውን ባደረጉ ማግስት በዕለተ እሁድ ወደ አዲስ አበባ የሚመለሱ ይሆናል ፡፡

ህዳር 8 - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን ሁለተኛውን ወሳኝ ጨዋታ ለማድረግ ወደ መቀሌ ለዝግጅት በረራውን ያደርጋል ፡፡

ህዳር 9 - ዋልያዎቹ የምእራብ አፍሪካዋን ከባዷን ኮትዲቯር የምድቡ ሁለተኛ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል ፡፡

Via #FirewAsrat

@tikvahethsport @kidusyoftahe @GoitomH
ጋዜጠኛ እና የአዲስ አበባ ባለደራ ምክር ቤት ሰብሳቢ የሆነው እስክንድር ነጋ ትላንት በበርካታ ወጣቶች ተከቦ እንደነበር ለቢቢሲ አረጋግጧል!

"ትናንት ቅዳሜ ምሽት 1፡00 አካባቢ፤ ፒያሳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ከሚገኘው ቢሯችን ስብሰባ ጨርሰን ስንወጣ ነው የተወሰኑ ወጣቶች ናቸው የከበቡን" ይላል እስክንድር። እስክንድር ቁጥራቸው ከ10 በላይ ይሆናል ያላቸው ሰብሰብ ያሉ ወጣቶች ከቢሮው ውጪ ደጃፍ ላይ ጠብቀው እርሱንና አራት የባልደራስ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን እንደከበቧቸው ያስረዳል። «አልፈናቸው ስንሄድ በከበባ መልክ ተከትለውናል። እንቅስቃሴያቸው አስጊ ስለነበር ወደ ኋላ ተመልሰን ፖሊስ ይዞ እንዲጠይቅልን ሙከራ አድርገናል። ቢሆንም አንዱ ብቻ ነው በፖሊስ ቁጥጥር ሥራ መዋል የቻለው።

More👇
https://telegra.ph/BBC-11-03-2

Via BBC አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር 12ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ኮንፈረንስ መካሄድ የጀመረው ሰሞኑን በተከሰተው የጸጥታ መጓደል ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ ነው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የደቡብ ኢትዮጵያ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት አብርሀም ፍቃዱ እንደገለጸው ማህበሩ በከተማዋ ለሚገኙ የደቡብ ተወላጆች ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የሚያችሉ ተግባራትን ሲየከናውን ቆይቷል፡፡ ለአብነትም በጌዲኦና ጎፋ ዞኖች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመርዳት ከ500 ሺህ ብር በላይ እንዲሁም በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ የወጣት ማዕከላትን በቁሳቁስ ለማደራጀት ግምቱ ከ700 ሺህ ብር በላይ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-03-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት በሁሉም የኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ከተሞች የሰላም ኮንፍረንስ ተካሂዷል። የሰላም ኮንፍረንሱ ላይም የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች፣ መምህራን እንዲሁም የመንግስት መስሪያ ቤት ሰራተኞች መካፈላቸው ተገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ArbaMinch

የጋሞ ዞን አስተዳደር ከአ/ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂዷል። ውይይቱ የከተማዋ ሰላም÷ ለልማት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር። በውይይቱ ማጠቃለያም የነበረውን የከተማን ሰላም ማስቀጠል÷ ልሜቷን መማፋጠን እና የአካባቢውን መረጋጋት የማይፈልጉ የግል ጥቅም ፈላጊዎች በማህበራዊ ሚድያ ከሚያሰራጩት ከሀሰት ወሬዎች እንዲቆጠቡ ማድረግ እንደሚገባ ተገልጿል። የከተማዋም መገለጫ የራሱን ሰላም የሚያስጠብቅ ህብረ-ብሔራዊ ህዝብ ያላት መሆኑ÷ ድንቅ አፈጣጠሯ እና ሰላማዊ ከተማ መሆኗ የሚያኮራ መሆኑን የዞኑ አስተዳዳሪ ገልፀዋል።

Via ብርሽ ዘውዴ(TIKVAH FAMILY)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል!

አንድ ወደፊት ስንሄድ ሁለት ወደኋላ የሚመልሱንን ሀይሎች ማስቆም እንደሚገባ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ አሳሰቡ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዛሬው እለት ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በመግለጫቸውም ከሰሞኑ በተከሰተው ግጭት የ86 ሰዎች ህይወት አልፏል ያሉ ሲሆን፥ ከሟቾች መካከል 82 ወንድ፣ 4 ሴቶች መሆናቸውምን አስታውቅዋል።

በብሄር ደግሞ 50 ኦሮሞ፣ 20 አማራ፣ 8 ጋሞ፣ 2 ስልጤ፣ 1 ጉራጌ፣ 2 ሀዲያ እና አንድ አርጎባ ሲሆኑ፥ የአንዱ ሟች ብሄር እንዳልታወቀም አስታውቀዋል። በሀይማኖት ደግሞ ከሟቾቹ መካከልም 40 ክርስቲያን ሲሆኑ፥ 34 ሙስሊም እና 12 የሌላ እምነት ተከታዮች መሆናቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በመግለጫቸው ያስታወቁት። ከሟቾቹ መካከል 76 ሰዎች በእርስ በእርስ ግጭት፤ 10 ሰዎች ደግሞ በፀጥታ ሀይሎች ህይወታቸው ማለፉንም ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በመግለጫው፥ ይህ ክፉ ክስተት በኢትዮጵያ የግጭት እሳት ሲነሳ አንዱን ክፍል አቃጥሎ ሌላውን አሙቆ የሚያልፍ እንዳልሆነ ያሳየ ነው ብለዋል። መንግስት የፖለቲካ እና የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በማሰብ ሆደ ሰፊነቱን አብዝቶ ሲያስታምም ከርሟል ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-11-03-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሰሞኑን በተከሰተው ግጭት የሟቾች ቁጥር 86 ደርሷል!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከሰሞኑ በተከሰተው ግጭት የ86 ሰዎች ህይወት አልፏል ብለዋል። ያከሟቾች መካከል 82 ወንድ፣ 4 ሴቶች መሆናቸውምን አስታውቅዋል። በብሄር ደግሞ 50 ኦሮሞ፣ 20 አማራ፣ 8 ጋሞ፣ 2 ስልጤ፣ 1 ጉራጌ፣ 2 ሀዲያ እና አንድ አርጎባ ሲሆኑ፥ የአንዱ ሟች ብሄር እንዳልታወቀም አስታውቀዋል። በሀይማኖት ደግሞ ከሟቾቹ መካከልም 40 ክርስቲያን ሲሆኑ፥ 34 ሙስሊም እና 12 የሌላ እምነት ተከታዮች መሆናቸውንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በመግለጫቸው አስታውቀዋል። ከሟቾቹ መካከል 76 ሰዎች በእርስ በእርስ ግጭት፤ 10 ሰዎች ደግሞ በፀጥታ ሀይሎች ህይወታቸው ማለፉንም ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ ለ86 ሰዎች ሞት ምክንያት ስለሆነው የሰሞኑን ግጭት ይህን ብለዋል፦ "ይህ ክፉ ክስተት በኢትዮጵያ የግጭት እሳት ሲነሳ አንዱን ክፍል አቃጥሎ ሌላውን አሙቆ የሚያልፍ እንዳልሆነ ያሳየ ነው!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በስልጤ ዞን የእሳት ቃጠሎ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት አወደመ!

በስልጤ ዞን ሚቶ ወረዳ ዛሬ ረፋድ ላይ የተከሰተዉ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ። የወረዳው ዋና አስተዳደሪ አቶ ከድር መሀመድ እንደገለፁት ዛሬ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ በወረዳዉ ዋና ከተማ 01 ቀበሌ የተከሰተው የእሳት ቃጠሎ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።

ለጊዜው መነሻ ምክንያቱ ባልታወቀው በዚህ የእሳት ቃጠሎ 11 ሱቆችና የተለያዩ ድርጅቶች ያሉበት ሕንጻ ላይ ጉዳት ደርሷል። በስፍራው የሚገኘው የወረዳ የነዳጅ ማከፋፈያ የንግድ ተቋምና ሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ጉዳቱ ከፍ እንዲል እንዳደረጉት ገልጸው ቃጠሎው በቁጥጥር ስር እንዲውል ህብረተሰቡና የጸጥታ አካላት ያደረጉት ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። በቃጠሎው ንብረታቸውን ያጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለማቋቋም ከዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጋር በመነጋገር የተለያየ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን አቶ ከድር ገልጸው በቃጠሎው በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም አስረድተዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በነገው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክቡር አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዋና መ/ቤት መስብስቢያ አዳራሽ በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ውስጥ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ/ም በክልሉ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በፀጥታ አካላት እንዲሁም በመከላከያ ጄኔራሎች ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ዙሪያ አንድሁም ስለተቋሙ ሌሎች የሥራ እንቅስቃሴ አሰመልክቶ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ይስጣሉ።

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ

@tikvahethiopiaBot
ሞባይል ለመስረቅ ግብግብ የገጠመው ተከሳሽ የሰው ነፍስ አጠፋ!

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በውንብድና ወንጅል የሰው ነፍስ ያጠፋው ተከሳሽ ባዬ አዱኛ ዐቃቤ ሕግ በመሰረተው ክስ በጽኑ እስራት ተቀጣ።

ተከሳሽ የወንጅል ሕግ አንቀፅ 671/2 ላይ የተመለከተዉን በመተላለፍ የማይገባውን ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ቦታው ወታደር ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሟች የወ/ሮ በድሪያን ሞባይል ሲወስድ ከሟች የገጠመውን ተቃውሞ ለማስቀረት ሲል ነውረኝነቱንና ጨካኝነቱን በሚያሳይ ሁኔታ በያዘው ስለት ሟችን አንገቷ ሰር በመውጋት ባደረሰባት ጉዳት ምክንያት በተፈጠረባት የመተንፈሻ አካል ጉዳት ህይወቷ ያለፈ በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመው ከባድ ውንብድና ወንጅል መከሰሱን የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡

ዐቃቤ ሕግ በምርምራ መዝገቡ መሰረት የሰዉ፣ የሰነድ እና ገላጭ በሆነ የሰነድ ማስረጃ አስደግፎ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት አቅርቧል።

ተከሳሽ በችሎት ቀርቦ ማንነቱ ከተረጋግጠ በኃላ ክሱ ተነቦለት እንዲረዳዉ የተደረገ ሲሆን ተከላከል በተባለበት የክስ መዝገብ የወንጀል ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለት ክዶ በመከራከሩ የዐቃቤ ሕግ ምስከሮች ቀርበው ተሰምተዋል፡፡ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን መርምሮ ተከሳሹን በቀረበበት የክስ መዝገብ ጥፋተኛ ነህ ብሎታል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤቱም መዝገቡን መርምሮ የቅጣት ሀሳብ ተገቢ ከሆነዉ የህግ ድንጋጌና የቅጣት አወሳሰን መመሪያ ጋር በማገናዘብ ተከሳሽ የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን ማቅለያ በመያዝ ተከሳሽን ያርማል ሌሎችን ያስተምራል በሚል በ20 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ወስኗል።

@tikvahethiopiaBot
ከ10 ዓመት በፊት ጠ/ሚ ዐብይ መረጃ አቀብለውት እንደነበር ኦነግ ገለጸ!

ጠቅላይ ሚንስር ዐብይ አህመድ ከ11 ዓመት በፊት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የምዕራብ ዕዝ መሪ በነበረው ለገሰ ወጊ ላይ መንግሥት ሊፈጽም አቅዶት የነበረውን ጥቃት በተመለከተ ለግንባሩ አመራር መረጃ አቀብለው እንደነበረ ግንባሩ ገለጸ።

ኦነግ አርብ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስት ከጥቃቱ ቀደም ብለው በግንባሩ የጦር መሪ ላይ ሊፈጸም ስለታቀደው ጥቃት መረጃ በውጪ ለሚገኙት አመራሮች መስጠታቸውን አረጋግጧል።

ለገሰ ወጊ የተገደለው ከ10 ዓመት በፊት የነበረ ሲሆን ግድያው እንዴት እንደተፈጸመ በጊዜው ዘጋቢ ፊልም ተዘጋጅቶ በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ተላልፎ እንደነበር ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰሞኑን ከከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ተከስቶ የ78 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈውን ጥቃትና ግጭት ለማረጋጋት ከህዝብ ጋር ውይይት ባካሄዱበት ወቅት መቀመጫውን ኤርትራ አድርጎ ከነበረው ኦነግ ጋር ስለነበራቸው ግንኙነት ጠቅሰው እንደነበር ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-03-5

Via (BBC)

@tsegabwolde @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር እኛ ለእኛ በጎፈቃደኞች መርሃ ግብር በቶታል ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ትብብር ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የበጎ ፍቃደኞች ሳምንት የ"እኛ ለእኛ" የኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር መስራች የሆኑት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ ፣ አርቲስት ቻቺ ታደሰ እንዲሁም የታላቁ ሩጫ ስራ አስኪያጅ አቶ ኤርሚያስ በተገኙበት ትላንት በይፋ ተጀምሯል። በተያዘው ሳምንትም ዕሮብ የደም ልገሳ አርብ ደግሞ የጽዳት ዘመቻ እንደሚኖር ለማወቅ ተችሏል፡፡ የዘንድሮው የቶታል ታላቁ ሩጫ ውድድር ከሚገኘው ገቢ አንድ የዳስ ትምህርት ቤት ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ ለማሰራት ማቀዱን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FirewAsrat #TikvahSportFamily

የቲክቫህ ስፖርት ቤተሰባችን አባል የሆነው ዓለም አቀፉ የስፖርት ፀሀፊ ፍሬው አስራት በሳምንት አንዴ ለእናንተ ለውድ ቤተሰቦቻችን የተመረጡ መረጃዎችን ሊያደርሳችሁ ከወዲሁ ዝግጅቱን ጀምሯል።

አለም አቀፉ የስፖርት ፀሀፊ ፍሬው አስራት ቀደም ሲል በአፍሪካ ብሎም በአለም አቀፍ ዌብሳይቶች ላይ ሲሰራ ለአብነት የኬንያውቹ Soka25East እና Jwsports1 እንዲሁም ለጋናው FootyGhana በኢትዮጵያ ዘጋቢ ሲሆን ለ ሩሲያው RFL ተጋባዥ ፀሃፊ በመሆን በኢትዮጵያ ስፖርት በተለይም እግር ኳሱን በተመለከተ ፅሁፎችን ያሰፍራል።

አሁን በ TIKVAH SPORT እርሶ ሊሰሙት እና ሊያውቁት ይገባል የሚላቸውን ሀተታዊ ፅሁፎችን በሳምንት አንዴ ይዞላችሁ የሚቀርብ ይሆናል ።

የቲኪቫህ ስፖርት ቤተሰባችንን ፍሬው አስራት በእናንተ ቤተሰቦቻችን ስም ከልብ እናመሰግናለን!

Join👉@tikvahethsport

https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg

@tikvahethiopiaBot👈አስተያየት መቀበያ!
የገቢ_ማስገኛ_ድርጅቶች_ማቋቋሚያ_ደንብ_Proclamation.pdf
3.8 MB
የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገቢ ማስገኛ ድርጅቶች ማቋቋሚያ ደንብ ጸድቆ ስራ ላይ ዋለ!

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የገቢ ማስገኛ ድርጅቶችን የሚያስተዳድሩበትና የሚመሩበት ወጥ የሆነ አሰራር ባለመኖሩ ምክንያት እየተስተዋለ ያለዉን የተዘበራረቀ አሰራር በማስወገድ ወጥ አሰራር እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገቢ ማስገኛ ድርጅቶች ማቋቋሚያ ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸደቆ ስራ ላይ እንዲዉል ተደረገ፡፡

Via MSHE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DIREDAWA

በድሬዳዋ ተከስቶ የነበረውን ሁከትና ብጥብጥ ተከትሎ ለጠፋው የሰው ሕይወትና ንብረት ተጠርጥረው በተያዙ ሰዎች ላይ ክስ ለመመስረት ምርመራ መጀመሩን በኢፌድሪ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ረድኤት ግርማ እንደተናገሩት ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ እጃቸው አለበት የተባሉ 51 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተቀናጀ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

https://telegra.ph/ETH-11-04

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ!

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክቡር አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ዛሬ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ በኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዋና መ/ቤት መስብስቢያ አዳራሽ በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ ውስጥ እና በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ/ም በክልሉ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና በፀጥታ አካላት እንዲሁም በመከላከያ ጄኔራሎች ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች ዙሪያ አንድሁም ስለተቋሙ ሌሎች የሥራ እንቅስቃሴ አሰመልክቶ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ ይስጣሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ60 ዓመቷን አዛውንት የደፈረው ግለሰብ ተቀጣ!

በአዲስ አበባ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፖሊስ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ60 ዓመቷን አዛውንት አስገድዶ የደፈረው የ 18 ዓመት ወጣት በ18 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እስራት ተቀጣ።

መኪና በመጠበቅ ሥራ ላይ የተሰማራው ግለሰቡ ድርጊቱን በፈጸመበት እለት ሐምሌ 8 ቀን 2009 ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ላይ፤ ማደሪያ የሌላቸው፣ ሸራ ወጥረው ጎዳና ላይ የሚኖሩና በዛም ላይ ሳንባ በሽታ ያለባቸውን አዛውንት ከሚጠብቀው መኪና በአንዱ ውስጥ በተኙበት ድብደባ በመፈፀም እና ራሳቸውን መካላከል እንዳይችሉ በማድረግ ጥቃቱን አድርሷል።

የግል ተበዳይም አንድ የሚያውቁት የመኪና ባለቤት ብርድ በሚሆን ጊዜ በመኪና ውስጥ እንዲያድሩ በነገራቸው መሰረት ለመኪኖቹ ጠባቂ በማሳወቅ በሰጣቸው ፈቃድ መሰረት ወደ መኪናው ያመራሉ። ብርድ ልብሳቸውን ይዞ እንዲሔድ ቀድመው ሰጥተውት የቀረ ልብሳቸውን ይዘው የተከተሉት አዛውንት መኪና ውስጥ ገብተውም የያዙትን ልብስ ደራርበው ለብሰው ይተኛሉ።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-04-2

(አዲስ ማለዳ ጋዜጣ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀብሩ ወረዳ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተማሪዎች ማጣት ሊዘጋ ነው!

ሰሜን ወሎ ዞን በሀብሩ ወረዳ የተገነባው አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተማሪዎች ማጣት ምክንያት ሊዘጋ መቃረቡን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ገልጿል።

ትምህርት ቤቱ እንዳይዘጋ ህብረተሰቡና በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በመፍትሔው ዙሪያ እየመከሩ ነው ተብሏል።

የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸጋው አገሸን እንደገለፁት በሀብሩ ወረዳ በ5 ሚሊዮን ብር ተገንብቶ በ2009 ዓም ስራየጀመረው የአረሪት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተማሪዎች ማጣት  ትርጉም ያለው አገልግሎት ሳይሰጥ የመዘጋት አደጋ ተጋርጦበታል።

በአካባቢው እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ የሚያስተምሩ 7 መጋቢ ትምህርት ቤቶች ታሳቢ በማድረግ የተከፈተ ቢሆንም ህብረተሰቡ 8ኛ ክፍል ያጠናቀቁ ልጆቹን ወደ ትምህርት ቤት ባለመላኩ ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳልቻለ አስረድተዋል ።

More👇
https://telegra.ph/ETH-11-04-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
IBSA GAADDISA HOOGGANSA OROMOO

"ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝምን ለማጠናከርና በህዝቦች መካከል አንድነትና እኩልነት እንዲኖር ይሰራል":- ጋድሰ ሆገንሰ ኦሮሞ

በጋድሰ ሆገንሰ ኦሮሞ ስር የተደራጁ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ፌዴራሊዝምን ለማጠናከርና በህዝቦች መካከል አንድነት፣ እኩልነትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲኖር ይሰራሉ፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች አሁን የምንወስዳቸው እርምጃዎች ለቀጣይ የኦሮሞና የአገሪቱ ህዝቦች ዕጣ ፋንታ ወሳኝ ናቸው ብለዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በአጠቃላይ በኦሮሚያ ክልል እየታዩ ባሉ የጸጥታ ችግሮችና ሰሞኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር መሰረታዊ መንስኤዎች ላይ ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት የስራ ክፍፍል ማድረጋቸውም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

በአገሪቱ የሚደረገው ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞራሲያዊ እና ፍትሓዊ እንዲሆን መደረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ ጥናት ከተደረገ በኋላ ጥልቀት ያለው ውይይት ተደርጎ ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥም ፓርቲዎቹ ወስነዋል፡፡

ፓርቲዎቹ በመካከላቸው ያሉትን ልዩነቶች በውይይት ለመፍታት ተስማምተዋል፡፡ በአገሪቱ የመጣው ለውጥ አስተማማኝ መሰረት እንዲኖረው ለማድረግ በአገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ድርሻ ካላቸው ሁሉም አካላት ጋር ቀጣይነት ያለው ውይይት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia