ልጄ ወራሼ ነው!
“ለዚች ምድር ጥዬ የማልፈው ትልቁ ስጦታ ልጄን ነው” ይሄ ዝግጅት የመነጨው ባለራዕይ እና አገር ወዳድ የሆኑ ትውልድን ለማስነሳት ከመፈለግ ሲሆን ይህም የአንድ ወገን ስራ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ትብብር ይሻልና ፤ ባለድርሻ አካላትን በአንድ ቦታ ለመጥራትና ህብረትን ለመፍጠር ታቅዶ የተዘጋጀ ነው፡፡
•ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ልጅ ሆነው የሚውሉበት (ጭቃ የሚያቦኩበት ፤ ውሀ የሚራጩበት ፤ አብረው የሚጫወቱበት)
•ወላጆች ደግሞ ከልጆቻቸውም ጋር የበለጠ እንዴት መግባባት እና መቅረጽ እንደሚችሉ በሞያው ብዙ አመት በሰሩና በሚታወቁ ባለሞያዎች በነጻ ስልጠና የሚያገኙበት
Do not miss it!!
Date: November 2 & 3, 2019
Venue: St. Joseph School, Addis Ababa Call : +251911331019 መግቢያ ለወላጆች 100 ብር
ለልጆች 50 ብር
#festival #kids #parents #fun #mesaleevents #mychildmylegacy

ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ ተለቀቁ!
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የኮሙዩኒኬሽንና ሚዲያ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ሰዒድ አህመድ በክልላችን ሰኔ 15 ቀን 2011ዓ.ም በተከሰተው የከፍተኛ አመራሮች ግድያ ተጠርጥረው ምርመራ ሲጣራባቸው ቆይቶ የምርመራ መዝገቡ በ18/2/2012 ዓ.ም ለክልሉ ለአቃቤ ህግ የተላከ ሲሆን እስካሁን ባለው የምርመራ ውጤት ግድያውን ለመምራትም ሆነ ለመሳተፍ በቂ መረጃ ባለመገኘቱ የባህረዳር እና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በ 20/2/2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ዐቃቤ ህግ የዋስትና አስተያየት እንዲሰጥ በተጠየቀው መሰረት የተጠርጣሪው የዋስትና ጥያቄ የማይቃወም መሆኑን የገለፀ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ዛሬ በዋለው ችሎት ከዐቃቤ ህግ የተሠጠውን የውሳኔ አስተያየት መሰረት በማድረግ በ10 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ወስኗል፡፡
ምንጭ፦ የአማራ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ሃብት እንደወደመበት የኦሞ ማይክሮ ፋይናስ አስታወቀ!
በደቡብ ክልል ተከስቶ በነበረው የጸጥታ መደፍረስ ምክንያት ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ሃብት እንደወደመበት የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አስታወቀ፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አለማየሁ ኃይለጊዮርጊስ ባለፉት ጊዜያት በክልሉ ባጋጠመው የጸጥታ መደፍረስ የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ጉዳት ደርሶበታል።
በጸጥታ መደፍረስ ችግር ምክንያት ተቋሙ በ12 ዲስትሪክቶችና ጽህፈት ቤቶቹ ላይ ቃጠሎ፣ ዝርፊያና የተለያዩ ጉዳቶች እንደደረሱበትም ገልጸዋል።
ጥሬ ገንዘብ፣ የወደሙ ቋሚ ንብረቶች፣ የጽህፈት ዕቃዎች፣ የተለያዩ ህትመቶችና የሕዳሴ ግድብ ቦንድን ጨምሮ 30 ሚሊዮን 659 ሺህ ብር የሚያወጣ ሃብት መውደሙንም ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-31-3

#FakeNewsAlert
በጅማ ከተማ በዛሬው ዕለት ምንም አይነት የድጋፍ ሰልፍ እንዳልነበረ የቲክቫህ ጅማ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡ የተለያዩ የቆዩ ፎቶዎችን በመጠቀም በጅማ ከተማ ሰልፍ ተደርጓል ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ ውሸት ነው።

#FakeNews
ይህ በማህበራዊ ሚዲያ በብዛት ሼር ሲደረግ የነበረ "ሀሰተኛ ዜና" ደግሞ አምቦ ከተማን የሚመለከት ሲሆን "በአምቦ ከፍተኛ ብጥብጥ ተነስቷል፣ ግርግርም አለ፤ ቤተክርስቲያንም ሊቃጠል ነው" የሚል ነው። አምቦ ፍፁም ሰላማዊ እንቅስቅሴ ውስጥ ነው የዋለችው። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ወደ እልቂት እንዲገባ የሚያነሳሱ ብዙ የፌስቡክ ሰዎች ስላሉ ከፍተኛ ማስተዋል እና ጥንቃቄ ይጠይቃል። በተለይም ሀይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ የሚፃፉ ፅሁፎችን ደግሞ ደጋግሞ ማረጋገጥ ተገቢ ነው። የምትሰሙትን መረጃ ሁሉ ሼር ከማድረግ ተቆጠቡ።
ሌላው አምቦ ከተማ ዛሬ "ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ታግተው ነበር፤ በሂሊኮፕተር ነው ያመለጡት" እየተባለ በተለያዩ ገፆች ሲወጡ የነበሩት መረጃዎች ፍፁም ከእውነት የራቁ ሀሰተኛ መረጃዎች ናቸው። ይህም ሆን ተብሎ ሌላ አከባቢ ያለው ህዝብ ለማነሳሳት እና ወደጥፋት ለመውሰድ የተደረገ ድርጊት ነው። የአምቦ ወጣቶች ጥያቄዎቻቸው፣ ቅሬታቸውን ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ አሰምተው ወደየቤቶቻቸው እንደገቡ ቀን ገልጬላችሁ ነበር።

አሳዛኝ ዜና!
ከባሕር ዳር ወደ መርጦ ለማርያም ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና ተገልብጦ ቢያንስ የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በርካቶች መቁሰላቸውን የዓይን እማኞች ተናገሩ።
ዛሬ አመሻሽ የተከሰተው የትራፊክ አደጋ የደረሰው በምዕራብ ጎጃም ዞን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ከገረገራ ከተማ አለፍ ብሎ ከሚገኝ ቁልቁለት ላይ መሆኑ ተገልጿል።
መኪናው መስመሩን ስቶ ወደ ገደል መግባቱን ነው የዓይን እማኞች የተናገሩት። ተጎጅዎቹ በአዴት ከተማ አስተዳደር እና ጎንጅ ቆለላ ወረዳ አምቡላንሶች ወደ ጤና ተቋማት እየተወሰዱ መሆኑን አብመድ ዘግቧል።
Via አብመድ

1634ኛው መደበኛ ሎተሪ ሐሙስ ጥቅምት 20/ 2012 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል፡፡
👉1ኛ. 600,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 178065
👉2ኛ. 300,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 265561
👉3ኛ. 150,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 000565
More👇
https://telegra.ph/ETH-10-31-4

“እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር #ብንበተን እንኳን ሩጠን የምንሸሽበት ጤናማ ጎረቤት ሀገር የለንም"-የጋሞ የሀገር ሽማግሌ
.
.
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ የተቀበላቸውን ከ5ሺህ በላይ አዳዲስ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት እንኳን ደህና መጣቹልኝ ብሏል። በሥነስርዓቱም ላይ የጋሞ አባቶች በሥፍራው ተገኝተው ለተማሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል እንዲሁም ምክርም ለግሰዋል።
በመድረኩ ላይ የጋሞ አባቶችን በመወከል ንግግር ያሰሙት ጋሽ ሳዲቃ ስሜ እንደተናገሩት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች የነገዋ ኢትዮጵያ ተረካቢዎች በመሆናቹ የዘረኝነት እና ጎሰኝነት ሐኪሞች መሆን ከናንተ ይጠበቃል ሲሉ ገልጸዋል።
"እኛ ኢትዮጵያውያን ማስተዋል ያለብን እንደ ሀገር ብንበተን እንኳን ሩጠን ለመሸሽ ጤናማ ጎረቤት ሀገርም የለንም" ያሉት እኚው የሀገር ሽማግሌ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ቆይታቸው ጋሞ በሚታወቅበት ፍጹም ኢትዮጵያዊ እሴት ውስጥ እንዲያልፉ ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህ የእንኳን ደህና መጣችሁ ዝግጅት ላይ ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ሙዚቃ ተጫዋቹ ድምጻዊ ”ሮፍናን“ ተገኝቶ ለተማሪዎች የህይወት ልምዱን አካፍሏል። ድምጻዊው ”ጋሞ ደሬ“ በተሰኘው ሥራው አካባቢውን በማስተዋወቁ ዕውቅና ተሰቶታል።
Via GMN

አይ ኤስ መሪው አል ባግዳዲ መገደሉን አረጋገጠ!
አሸባሪው አይ ኤስመሪው አቡበከር አልባድጋጊ መገደሉን አረጋገጠ። አሸባሪው አይ ኤስ አዲሱ ቃል አቀባይ አቡ ሀምዛ አልቁራይሽ በዛሬው እለት እንዳስታወቀው፥ የአይ ኤስ መሪ የነበረው አቡበከር አልባግዳዲ ተገድሏል።
አቡበከር አል ባግዳዲን ይተካል ተብሎ ሰጠበቅ የነበረው አቡ አል ሀሳን አልሙጃሂርም መገደሉንም ነው ቃል አቀባዩ በአሸባሪ ቡድኑ መገናኛ ብዙሃን ላይ በድምጽ ባሰራጨው መልእክት ገልጿል።
ይህንን ተከትሎም አይ ኤስ በሟቹ አቡበከር አልባግዳዲ ምትክ አዲስ መሪ መሾሙን ያስታወቀ ሲሆን፥ አዲሱ የአይ ኤስ መሪም አቡ ኢብራሂም አል ሀሺም አልቁራይሽ መሆኑን አስታውቋል።
አይ ኤስ የሽብር ቡድን መሪ አቡበከር አል ባግዳዲ በአሜሪካ ወታደሮች በተፈፀመ ጥቃት ባሳለፍነው እሁድ ማለትን ጥቅምት 16 2012 መገደሉ ይታወሳል።
የአሜሪካ ልዩ ሃይሎች አል ባግዳዲ የሚገኝብትን ዋሻ መክበባቸውን ተከትሎ ታጥቆት የነበረው ቦምብ በማፈንዳት እራሱን ማጥፋቱም ነው የተነገረው።
ምንጭ፦ www.aljazeera.com(FBC)

በአፍሪካ ትልቁ እና ተሸላሚ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ ጭነት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ወደ ኒውዮርክ ከተማ በረራ ሊጀምር ነው። ኒውዮርክ የካርጎ ጭነት አገልግሎት መዳረሻዎቹን 58 ያደርሰዋል። #EthiopianAirlines
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በምዕራብ ጎጃም ዞን የጎንጂ ቆለላ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው ከባህርዳር ወደ መርጦ ለማርያም ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ህይወት አልፏል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሌላው አሳዛኝ የመኪና አደጋ...
ዛሬ በይርጋጨፌ ወረዳ ቆንጋ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ የቲክቫህ ይርጋጨፌ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ በይርጋጨፌ ወረዳ ቆንጋ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ህይወት ሳያልፍ እንዳልቀረ የቲክቫህ ይርጋጨፌ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SPHMMC
ነዋሪነታቸው በአሜሪካ ሀገር ቨርጅኒያ የሆኑት ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ አንተነህ ብርሀኑ እና ጓደኞቻቸው ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ግምቱ አንድ ሚሊዮን ብር(1,000,000 ብር) የሚያወጣ ለቀዶ ሕክምና የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለግሰዋል፡፡ አንተነህ ብርሀኑ በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ወደ ኮሌጁ አምጥተው አስረክበዋል፡፡ የሕክምና ቁሳቁሶቹ ለቀዶ ህክምና ክፍሉ በጣም አስፈላጊ የሆኑና እና አንዳንዶቹ በኮሌጁ የሌሉ ናቸው፡፡ አንተነህ ብርሀኑ እና በዚህ በጎ ተግባር የተሳተፉ ወገኖቻችንን ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
(SPHMMC)

(የጅማ ዞን ኮሚኒኬሽን)
"በዛሬው እለት አምቦ ከተማ ላይ መድረክ የመሳተፍ እድል ይሠጠን በማለት ወጣቶች ያቀረቡትን ጥያቄ የተቃዉሞና የሁከት በማስመሰል ካቀረቡ በኋላ ጅማዎች ደግሞ ይህን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ በማለት በተለያዩ ማህበራዊ ሚድያዎች የተሰራጩ መረጃዎች የተሳሳቱና የዉሸት ትርክት መሆኑን እንገልፃለን።"

Vote!
ፍሬወይኒ መብራቶም የ2019 CNN Hero ምርጥ አስር ውስጥ ገብታለች፡፡ ለዚህም የበቃችው የሚታጠብና መልሶ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ (ሞዲየስ) በመስራቷና ሴቶች ተማሪዎች ተፈጥሯዊ በሆነው የወር አበባ ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ በምትሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዋ ነው፡፡ እንደ ዩኒሴፍ ጥናት በኢትዮጵያ ከ10 ሴቶች አንዷ በዚህ ምክንያት ትምህርቷን ታቋርጣለች፡፡ ፍሬወይኒ ይህንን ውድድር ካሸነፈች 100,000 የአሜሪካን ዶላር አሸናፊ ትሆናለች፡፡
ምረጧት 👉 https://edition.cnn.com/SPECIALS/cnn.heroes/vote/10/
የድምጽ አሰጣጥ ሂደት:
1. ሊንኩን (ማስፈንጠሪያውን) መጫን። ከተጫን ነው ቡሃላ ውደድ የCNN የአመቱ 10 ጀግኖች ዝርዝር እንግርባለን ከዛ የፍሬወይን መብራቶም ስምችና ፎቶዋ ዜግነት Ethiopian የሚል ፈልገን እንጫናለኝ።
2. የሷን ፎቶ ከተጫንን ቡሃላ ዝቅ ብለን ከሷ ፎቶ በታች 1 or 0 ቁጥር ይኖራል vote ከሚለው በላይ slide for more ከሚለው በታች የለቸውን መሳቢያ ወደቀኝ በመሳብ 10 ድምጽ መስጠት ይችላሉ።
3. Vote የሚለውን ከተጫንን ቡሃላ email or fb account ያለን ብቻ ነው የምን መርጠው ከላይ አንብባቿል ዲስኮርሱን የሚል ሲመጣ ማንበብ ወይም አንቢብያለሁ ማለት ከዛ account ይጠይቀናል እናስገባና ማረጋገጫውን እንጫን ከዛ አበቃ።
ማሳሰቢያ:- ሁሉም ሰው በየቀኑ 10 ድምጽ መስጠት ይችላል። ማብቂያው ህዳር 21 ነው፡፡
#ቲክቫህ_ኢትዮጵያ(@tikvahethmagazine)

Freweini Mebrahtu
Mekelle, Ethiopia, Freweini is fighting the cultural stigma around menstruation in Ethiopia by educating students and producing reusable pads that help girls stay in school.
Vote for the CNN Hero of the Year!
https://www.cnn.com/SPECIALS/cnn.heroes/vote/10/?source=instagram

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በስልክ ተወያዩ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በስልክ ውይይት አድርገዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጋር ያደረጉትን የስልክ ውይይት አስመልክቶ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፒዮ በትዊተር ገፃቸው ላይ መልእክት አስፍረዋል፡፡
እንደ ኢቢሲ ዘገባ የውጭ ጉዳይ ሚንትስር ማይክ ፖምፒዮ ጠቅላይ ሚንስትሩ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው እንኳን ደስ አለዎት በማለት መልእክት ማስተላለፋቸውን አስታውቀዋል፡፡ ጠንካራ ግንኙነታችን እና ዘላቂ የሰላም ስምምነትን በሱዳን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን መወያየታቸውንም ነው የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ያስታወቁት፡፡
ምንጭ፦ (ኢፕድ)

እነአቶ በረከት ስምዖን በተከሰሱባቸው ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በማዬት ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ ፍርድ ቤቱ መስከረም 30 ቀን 2012ዓ.ም በዋለው ችሎት ከፍርድ በፊት የሚቀርብ ማንኛውም ማስረጃ መርምሮ ትክክለኛ ብይን ለመስጠት አጋዥ ስለሚሆን ዐቃቤ ሕግ እንዲያዝለት ያቀረበውን 141 ገፅ ማስረጃ ከዚህ ቀደም የቀረበው የሰነድ ማስረጃ አካል እንዲሆን ሊያያዝ ይገባል ብሎ ነበር፤ ሰነዱን መርምሮ ብይን ለመስጠም ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በተከሰሱባቸው ጉዳዮች ላይ መከላከያ እንዲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ ለሕዳር 24 ቀን 2012ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመቐለ ዩኒቨርስቲ የከፈተውን የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ ሊስያመርቅ ነው!
ከአራት ዓመት በፊት ሃሳቡን ጠንስሶ ወደ ስራ የገባው ‹‹ሞሞና›› የተሰኘው የማህበረሰብ የሬድዮ ጣቢያ እስከ 60 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የስርጭት ተደራሽነት እንዳለው ታውቋል፡፡ ከነሀሴ 9 ጀምሮ በሙከራ ስርጭት ላይ የሚገኘው ሬድዮ ጣቢያው በ96.4 ፍሬኩዌንሲ ማሰራጨት ጀምሯል፡፡
በዩኒቨርሰቲው የሚማሩ ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብ የቀሰሟቸውን ትምህርቶች በተግባር እንዲያጎለብቱ ብሎም በዩኒቨርስቲው እና በአካባቢው ማህበረሰብ መካከል ትስስር ለመፍጠር እና አንዱ የአንዱን ስራ እንዲገነዘብ ለማስቻል ታስቦ ሬድዮ ጣቢያው መከፈቱን አሐዱ ቴሌቪዥን አገኘሁት ባለው መረጃ ጠቁሟል፡፡
የጤና ሳይንስ ኮሌጆች የመለማመጃ ሆስፒታል እንዳላቸው ሁሉ የጋዜጠኝነት እና ተያያዥ የትምህርት ክፍሎችም የራሳቸውን ባለሙያዎች በእውቀቱ የበቁ ሆነው እንዲመረቁ የሬድዮ ጣቢያው መከፈት አይነተኛ አስተዋጽኦ እዳለው ዩኒቨርሰቲው ተናግሯል፡፡
ህዳር 6 የፌዴራል መንግስትና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በሚገኙበት የሬድዮ ጣቢያው ይመረቃል፡፡ መቐለ ዩኒቨርስቲ ከሬድዮ ጣቢያው ባሻገር፣ በቴሌቪዥን በህትመትና በማህበራዊ ሚዲያ ዘርፍም ስርጭት ለመጀመር ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ተጠቁሟል፡፡
ምንጭ፦ አሃዱ ቴሌቪዥን

በሊባኖስ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ #በኢትዮጵያዊያን ዜጎች ጉዳይ ላይ የቅርብ ክትትል የሚያደርግ ግብረ ኃይል ወደ ስፍራው እንደሚጓዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
https://telegra.ph/ETH-11-01
@tsegabwolde @tikvahethiopia
https://telegra.ph/ETH-11-01
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚሊዮን ማቲዎስ የትምህርት ሚንስቴር ሚንስትር ዲኤታ ሆነው ተሾሙ!
የቀድሞው የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት እና ክልሉን ለአንድ ዓመት የመሩት ሚሊዮን ማቲዎስ የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ሆነው መሾማቸውን የትምህርት ሚኒስቴር ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ አስታውቋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሀረጓ ማሞ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደተናገሩት የሚሊዮን ማቲዎስ የሹመት ደብዳቤ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መድረሱን እና በቅርቡም ስራ እንደሚጀምሩ አረጋግጠዋል።
በሰባተኛው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች መደበኛ ጉባኤ ላይ ደቡብ ክልልን እንዲመሩ የተመረጡት ሚሊዮን ማቲዎስ በጊዜው ደቡብ ክልልን ይመሩ የነበሩትን ደሴ ዳልኬን በመተካት ነበር ወደ ስልጣን የመጡት።
ሚሊዮን ማቲዎስ የአንድ ዓመት ክልሉን የማስተዳደር ጉዞም በነሐሴ 2012 ተገቶ በምትካቸው ርስቱ ይርዳው የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሹመዋል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ