የእግር ኳስ ውድድሮቹ በፀጥታ ችግር ላይካሄዱ ይችላሉ!
የእግር ኳስ ክለቦችን የሚያሳትፈው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ፣ የደቡብ ካስትል ዋንጫ እና የአዳማ ከተማ ዋንጫ በሀገሪቱ እየታየ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ላይደረግ ይችላል የተባለ ሲሆን የፀጥታ አካላትም ሀላፊነት አንወስድም እያሉ ነው፡፡
ምንጭ፦ ቴዎድሮስ ታከለ (ቴዲ ሶከር)
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ግብጽ በዓባይ ዙሪያ ናይጀሪያ እንድታደራድራት መጠይቋ ተሰማ!
ግብጽ በዓባይ ዙሪያ ከኢትጵያ ጋር የገባቸውን ውዝግብ ለመፍታት ናይጀሪያን በአደራዳሪነት ጠየቀች። ብሎምበርግ እንደዘገበው የግብጽ የሕዝብ እንደራሴው አፈ ጉባዔ የናይጀሪያውን ፕሬዘዳንት ሙሐሙድ ቦሃሪን በአደራዳሪነት መጠየቃቸውን አስነብቧል።
ከምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጀሪያ ጋር ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የገለፁት አፈ ጉባዔው ጥቅምት 18/2012 ከናይጀሪያ ምክትል ፕሬዘዳንት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ግብጽ ከዓባይ ወንዝ ምታገኘውን የውሃ መጠን ይቀንሳል በሚል የምታቀርበውን መከራከሪያ ኢትዮጵያ ሳትቀበል መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን፤ 40 ቢሊዮን ኪዮቢክ ወሃ ለማግኘት ብትጠይቅም ኢትዮጵያ ግን 30 ቢሊዮን ብቻ እንደምትለቅ ማሳወቋ የሚታወስ ነው።
5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት የታላቁ የኅዳሴ ግድብ መሰረት አድርጎ የተባበሩት መንግስታት ባስቀመጡት ግምት በፈረንጆች 2025 ግብጽ ውሃ እጥረት እንደሚያጋጥማት ይፋ አድርጓል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

#BreakingNews
የፀጥታ አካላት ሀላፊነት መውሰድ ካልቻሉ የ2012 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና የእግር ኳስ ውድድሮች ላይካሄዱ ይችላሉ ተብሏል፡፡ ውድድሮቹ ሚካሄዱ ከሆነ ግን በዝግ እንዲደረጉ እንቅስቃሴ መጀመሩን የስፖርት ጋዜጠኛው ቴዎድሮስ ታከለ(ቴዲ ሶከር) አገኘሁት ባለው መረጃ ጠቁሟል፡፡

#NewsAlert 737 ማክስ ጄቶቹ ላይ የቴክኒክና የንድፍ ችግር እንደነበረባቸው አምራቹ ቦይንግ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ አምኗል። የኩባያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው ትናንትና ዛሬ እየተጠየቁ ናቸው።
Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AMNESTY INTERNATIONAL
የኢትዮጵያ መንግሥት "የፀረ ሽብሩን ሕግን" አላግባብ በመጠቀም ተተቸ። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግሥትን ይተቹ ነበር የተባሉ 22 ሰዎች ለፍርድ ሳይቀርቡ ለ4 ወራት ታስረው ትናንት መለቀቃቸውን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም የፀረ-ሽብር ሕጉን አለአግባብ መጠቀሙን አላቆመም ሲል ወቅሷል።
በድርጅቱ የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ አቶ ፍስሃ ተክሌ ዛሬ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ትንናት የተለቀቁት 22 ሰዎች ከሰኔ 15ቱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ግድያ በኋላ ከተያዙት ከ200 ይበልጣሉ ካሏቸው ሰዎች መካከል መሆናቸውን ገልጸው ለፍርድ ሳይቀርቡ ለአራት ወራት መታሰራቸዉ ኢፍትሀዊ እንደነበረ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-30-5
ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ

ባለፈው ሳምንት በኦሮምያ የተለያዩ ከተሞች ከተነሳው ተቃውሞ በኋላ በተከተሉት ግጭቶች እና ጥቃቶች የደረሰው ጉዳት ዓይነት ብዛት እና የተፈጸመበት መንገድ አሳሳቢ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
በድርጅቱ የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ አቶ ፍስሃ ተክሌ ለጀርመን ራድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ከዚህ ቀደም ምልክቶች እንደነበሩ አስታውሰው መንግሥት ምልክቶቹን አንብቦ መዘጋጀት፣ ሲከሰቱም በተቻለ መጠን ለመከላከል ጥረት ማድረግ ነበረበት ብለዋል።
ከተቃውሞው ጋር ተያይዞ የደረሱት ጥፋቶችም የመንግሥት የመከላከያ አቅም ማነስን ያሳያልም ብለዋል። ወደፊትም ለዚህ የዳረገውን መሠረታዊውን ችግር መፍታት እንደሚገባም አሳስበዋል። መንግሥትም ሕግ ማስከበር ብቻ ሳይሆን የእርቅና የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ችግሮችን ለይቶ አስፈላጊ እርምጃዎችን መውስድ መቻል አለበት ብለዋል።

#HARAR
ሐረር ከተማ ከትላንት ጀምሮ ገበያውም፣ ሥራውም፣ ትምህርቱም ተከፍተው ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች፤ የከተማይቱ ነዋሪም ወደ መደበኛ ህይወቱ ተመልሷል።
Via BETELHEM NEGASH

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
"ቲክቫህ ስፖርት" ስፖርታዊ ጉዳዮችን እጅግ ባማረና ለየት ባለ አቀራረብ መከታተል ትችላላችሁ። እንዲሁም በየጊዜው የተለያዩ ስጦታዎችን ከቲክቫህ ስፖርት አጋሮች የማግኘት እድልም ይኖራችኃል!!
Join @tikvahethsport 👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFb8M0pNEZTiGM68rg
(ከ30,000 በላይ ቤተሰቦች ያሉበት ትክክለኛው)
.
.
"ቲክቫህ መፅሄት" በዋናው ቻናል ላይ በስፋት የማይዳሰሱ ገዳዮች የውጭ ሀገር መረጃዎች፣ የስልጠና ዕድሎች፣ የቴሌቪዥን፣ የሬድዮ ፕሮግራሞች ጥቆማ፣ ቱሪዝም፣ ባህል፣ ኪነ ጥበብ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ።
(87,000 በላይ ቤተሰቦች ያሉበት ትክክለኛው)
Join @tikvahethmagazine👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
ውድ ቤተሰቦቻችን ማንኛውም አስተያየት ሀሳባችሁን በ @tikvahethiopiaBot መላክ ትችላላችሁ!!

思アば:
➡️HYUNDAI STAREX
✔️Model: 2015
✔️KORE🇰🇷
✔️Cc :2500
✔️transmission: Automatic
✔️Full option
✔️amazing Dicor
✔️12 seat leather
✔️rear view camera
✔️Km:33000
✔️orginal left hand
✔️palte no:never used in Ethiopia
💰Price: 1,450,000 ETB slightly negotiable
📩 @zizuu10
☎️ +251945952637
👉 join @halalautomarket

በኢትዮጵያ የህጻናት የልብ ህክምና ማዕከልን ስራዎች ለመደገፍ የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያና የግንዛቤ ማስጨበጫ ዝግጅት በዋሽንግተን ተካሂዷል። የኢትዮጵያ የህጻናት የልብ ህክምና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሄለን በፍቃዱ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ማዕከሉ በሙሉ አቅሙ እንዳይሰራ የአላቂ እቃዎች እጥረት ፈተና እንደሆነበት ገልፀዋል።
ማዕከሉ በሳምንት ሶስት የህጻናት ልብ ህክምና እንደሚያደርግ በመግለጽ፤ ቁሳቁሶች ቢሟሉለት ግን አምስት ህክምናዎችን ማድረግ እንደሚችል ዶክተር ሄለን ተናግረዋል። በአገር ውስጥም በውጭም ያሉ አጋር አካላት ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል። በማዕከሉ የህጻናት ልብ ሃኪም ዶክተር ያዩ መኮንን በበኩላቸው ÷ በማዕከሉ ያላቸውን ተሞክሮና አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች ገለጻ አድርገዋል።
አምባሳደር ፍጹም አረጋ የተካሄደው ዝግጅት አስቸኳይ የልብ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህጻናት ለመድረስ ነው ያሉ ሲሆን የህጻናትን ልብ ለመታደግ ልባችሁ የሚነግራችሁን ስጡ ሲሉ ገልጸዋል። ኤምባሲው አጋር አካላትን በማስተባበር ለማዕከሉ ድጋፍ የሚያስገኙ ተግባራዊ ጥረቶችን እንደሚያደርግም አስታውቀዋል።
Via FBC

#MOJO
ትላንት ለሊት 10:00 በሞጆ ከተማ ገበያ ላይ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር። የሞጆ ቲክቫህ ቤተሰቦች እንደገለፁት ከሆነ ለሊት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ በእሳት አደጋው ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት መረጃው ባይኖራቸውም በንብረት ላይ ግን ጉዳት መድረሱን በስፍራው ተገኝተው አረጋግጠዋል። እሳቱን ከሰዓታት በፊት ነው መቆጥጠር የተቻለው።

በባህር ዳር ከተማ 1661 ዩኒት ደም ተሰብስቧል!
የኢትዮጵያ ህክምና ተማሪዎች ማህበር-ባህር ዳር (EMSA-Bahir Dar) አባላት፣ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ከባህር ዳር ደም ባንክ፣ ከክለብ 2/12፣ ከKeep Hope Alive(KHA) እና ከሌሎች በጎ ፍቃደኞች ጋር በመተባበር ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡
Via EMSA-Bahir Dar
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ህክምና ተማሪዎች ማህበር-ባህር ዳር (EMSA-Bahir Dar) አባላት፣ ከባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ ከባህር ዳር ደም ባንክ፣ ከክለብ 2/12፣ ከKeep Hope Alive(KHA) እና ከሌሎች በጎ ፍቃደኞች ጋር በመተባበር ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡
Via EMSA-Bahir Dar
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦዪንግ አመነ፤ ይቅርታ ጠየቀ!
737 ማክስ ጄቶቹ ላይ የቴክኒክና የንድፍ ችግር እንደነበረባቸው አምራቹ ቦይንግ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ አምኗል። የኩባያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዴኒስ ምዩለንበርግ በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው ከትናንት በስቲያና ትናንት ሲጠየቁ ስሕተትና ጥፋት መፈፀሙን አምነው “እኔም ልቤ ተሰብሯል፤ በጥልቅ አዝናለሁ” ብለዋል። የኩባንያቸው መታመን እንደገና እንዲያንሠራራ ለማድረግ በርትተው እንደሚሠሩና እንዲያ ዓይነት ጥፋት እንደማይደገምም ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ የንግድ፣ የሣይንስና የትራንስፖርት ኮሚቴ ተናግረዋል። የተጎጂዎች ቤተሰቦችና የሕግ ተወካዮቻቸውም ተገኝተዋል። የቦዪንግ ከፍተኛ ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው የመንግሥት ባለሥልጣናት ዛሬም በተወካዮች ምክር ቤቱ የትራንስፖርት ኮሚቴ ፊት ቀርበው ተጠይቀዋል።

ቀይመስመር ተጥሷል!
ክብርት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሰሞኑን ሀገራዊ ጉዳይ አስመልክቶ በቲውተር ገጻቸው እንዲህ ብለዋል፡-
"ዘርና ሀይማኖት ለፖለቲካ ጥቅም እንዲውሉ ሲደረግ፤ ንጹሀን ዜጎቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ፣ ሲፈናቀሉና ሲንከራተቱ ስናይ ስሜትን ለመግለጽ ቃላት ያጥራል፣ ለቅሶ፣ድንጋጤና ሥጋት የብዙዎችን በር አንኳኩቷል ሃዘናቸው ሃዘኔ/ሃዘናችን ነው። ለሀገርና ለህዝብ ጥቅም ሲባል ልናሰምረው እና ልናከብረው የሚገባን ቀይ መስመር ተጥሷል። አገራችንን ካንዣበበባት ክፉ አዳጋ ለማዳን ሁላችንም ሚና አለን፤ የሚመለከታቸው ሁሉ የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው፡ቀይ መስመር መጣስ የለበትም እንበል።"

#AMBO
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በአምቦ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር እየተወያዩ ነው። በውይይቱ ላይም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በተጨማሪ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳ እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተገኝተዋል።
በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ባለው ውይይት ላይም የአምቦ ከተማ፣ የምእራብ ሸዋ ዞን፣ የደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን፣ የቡራዩ፣ የሆለታ እና የወሊሶ ከተማ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች ተገኝተዋል። በአምቦ ከተማ እየተካሄደ ያለው ውይይትም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑን ከኦቢኤን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
Via OBN

#ነቀምቴ
የአራቱ የወለጋ ዞኖች ማለትም የምስራቅ፣ ምእራብ፣ ሆሮ ጉዱሩ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች እንዲሁም የነቀምቴ ከተማ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የሰላም ኮንፍረንስ በነቀምቴ ከተማ እየተካሄደ ነው። የኢህአዴግ እና የኦዲፒ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ፍቃዱ ተሰማ በኮንፍረንሱ ላይ በመገኘት ተሳታፊዎችን በማወያየት ላይ ይገኛሉ።
በውይይቱ ላይ የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ አቶ በዳሳ ጂንፌሳ ባስተላለፉት መልእክት፥ የኦሮሞ ህዝብ ባለው እሴት አንድ ሆኖ የባርነት ቀንበርን እንደሰበረ ሁሉ ችግሮቹንም በአንድነት በመሆን በውይይት መፍታት አለበት ብለዋል። አንድ መሆን ከቻልን ችግሮችን በቀላሉ መፍታት እንችላለን ሲሉም ከንቲባው መልእክት አስተላልፈዋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#MOJO ትላንት ለሊት 10:00 በሞጆ ከተማ ገበያ ላይ የእሳት አደጋ ደርሶ ነበር። የሞጆ ቲክቫህ ቤተሰቦች እንደገለፁት ከሆነ ለሊት ተደጋጋሚ የተኩስ ድምፅ ይሰማ ነበር፤ በእሳት አደጋው ሰው ላይ ስለደረሰ ጉዳት መረጃው ባይኖራቸውም በንብረት ላይ ግን ጉዳት መድረሱን በስፍራው ተገኝተው አረጋግጠዋል። እሳቱን ከሰዓታት በፊት ነው መቆጥጠር የተቻለው። @tsegabwolde @tikvahethiopia
በሞጆ ከተማ የደረሰው የእሳት አደጋ!
በሞጆ ከተማ " ገበያ " ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ ዛሬ ለሊት 10፡00 ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 60 የሚሆኑ ሱቆች መውደማቸውን ነው የከተማው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያታወስታወቀ፡፡ የእሳት አደጋውም ወደሌሎች አካባቢ እንዳይዛመት በህብረተሰቡና በእሳት አደጋ ሰራተኞች ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉንም ጽህፈት ቤቱ ገልቷል፡፡
አደጋውን ለመከላከልም የእሳት አደጋ ተሸከርካሪዎች ከአዲስ አበባ ከተማ፣ ከአዳማ፣ ከቢሾፍቱ እና ከግል ድርጅቶች የተወጣጡ መሆናቸውንም ኮማንደሩ አመልክተዋል፡፡ በእሳት አደጋውም የወደመውን የንብረት መጠን ተጣርቶ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ የሞጆ ከተማ ፖሊስ መመሪያ ሃላፊ ኮማንደር ሙሃመድ አህመድ መግለጻቸውን የዘገበው ኦቢኤን ነው።

#NewsAlert ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ሆነው አንደሚሾሙ ተገለጸ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ነው። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ነቢያት ጌታቸው እንዳሉት የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የነበሩት ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ጸሃፊ ሆነው አንደሚሾሙ ተናግረዋል።
(Ethio Fm107.8)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
(Ethio Fm107.8)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ትራምፕ ጀግና ለተባለው ውሻ ሜዳሊያ እንደሰጡ የሚያሳይ ሀሰተኛ ፎቶ መልቀቃቸው እያነጋገረ ነው!
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አል ባግዳዲን ለመግደል በተካሄደው ዘመቻ ተሳትፎ ለነበረው ውሻ ሜዳሊያ ሲሰጡ የሚሳይ የተቀነባረ ፎቶ በመልቀቃቸው ተቃውሞ እየቀረበባቸው ነው።
ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ የለቀቁት ፎቶ በአይ ኤስ መሪ አል ባግዳዲ ግድያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለነበረው ጀግና ውሻ በአንገቱ ላይ ሜዳሊያ ሲያጠልቁለት ያሳያል፡፡
ነገር ግን ይህ ፎቶ በተግባር ያልተደረገ እና አሶሴትድ ፕሬስ በ2017 ጄሜስ ማክክሎከን የክብር ሜዳሊያ ሲበረከትላቸው የሚያሳየውን ፎቶ በማቀነባበር የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡
አል ባግዳዲ በተገደለበት ዘመቻ ላይ ተሳትፎ የነበረው ይህ ውሻ ወደ ነጩ ቤተ መንግስት እንዳልገባ እና ጉዳት አጋጥሞት የነበረ ቢሆንም ወደ ሌላኛው ሃላፊነት መሰማራቱ ነው የተነገረው፡፡
ይህ የፕሬዚዳንት ተግባርም በአሁን ወቅት ከፍተኛ ችግር የሆነው የሀሰተኛ ዜናዎች መገለጫ ነው በማለት ክስ አቅርበዋል፡፡ ጄሜስ ማክክሎከን ም ፎቶዋቸውን ተቀነባብሮ ጥቅም ላይ በማወሉ ምን አይነት ምላሽ እንዳልሰጡና በተግባሩ እንደተስማሙ ይመስላል የሚል ግምት እየተሰጠ ነው፡፡
ምንጭ፡- ሃፊንግተንፓስት(ኤፍ ቢ ሲ)