TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"አንዳንድ ሚዲያዎች ግጭቱ በአጠቃላይ በባሌ እንደሆነ አስመስለው የሚያቀርቡት ዘገባ ስህተት ነው። በዞኑ ሃያ ወረዳዎች ያሉ ሲሆን ግጭት የተከስቶ የነበረው በሁለቱ ወረዳዎች ከዚያም አልፎ ደግሞ ሁኔታው ጠንከር ያለው በአንድ ከተማ ብቻ ነበር"- የባሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አደም ኢድሪስ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በኢትዮጵያ በቀጣይ 10 ዓመታት ዉስጥ ከ10 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ያገኛሉ ተብሏል፡፡ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ከማስተር ካርድ ፋዉንዴሽን ጋር በመተባበር ለ3 ሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል፡፡

የስራ እድሎቹ የሚፈጠሩትም፣ በቱሪዝም፣ በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪና በአይ ሲቲ ዘርፎች መሆኑ ተገልጧል፡፡ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶር ኤፍሬም ተክሌ ኢትዮጵያ ልትበለጽግ የምትችለዉ፣ሁላችንም በየግላችን የአቅማችንን ስንሰራ ነዉ ብለዋል፡፡

ከተቋቋመ አንድ አመት የሆነዉ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን በተለይም ባለፋት 6 ወራት ጀምሮ የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝና በዚህ ዓመትም ለ 3 ሚሊዮን ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

Via Ethio FM 107.8
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከተማ አጀንዳ አጋሮች ትብብር መድረክ ምስረታ እየተካሄደ ነው!

በከተሞች ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ የሚሰሩ የልማት አጋሮችን የሚያስተሳስረውና የከተሞችን ልማት ለማፋጠን በሚደረገው ጥረት ተባብሮ ለመስራት ከፍተኛ ሚና ሚና እንደሚኖረው የታመነበት የከተማ አጀንዳ አጋሮች መድረክ ምስረታ በኢንተር ኮንቲኔንታል ሆቴል እየተካሄደ ነው።

በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴርና በUN HABITAT ትብብር የተመሰረተው የትብብር መድረኩ በከተሞች አጀንዳ ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ተቋማትን፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችንና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን የሚያስተሳስር እንደሆነ በምስረታው ላይ ይፋ ተደርጓል።

የምስረታውን መድረክ በንግግር የከፈቱት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የትብብር መድረኩ በከተሞች ለጋሽ እና የልማት አጋሮች ድጋፋቸውን በተቀናጀና በተናበበ መልኩ ለማከናወን ትልቅ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።

በምስረታው ላይ ዓለም አቀፍ ፣መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሀላፊዎችና ተወካዮች ፣ አምባሳደሮች ምሁራንና የማህበራት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

Via Ministry of Urban Development and Construction
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሩዋንዳ ካለፈ ታሪኳ ብቻ ሳይሆን ከቴክኖሎጂ አብዮቷም ብዙ የምንማረው አለን!

ሩዋንዳ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ መኪና በኪጋሊ ማሽከርከር ጀምራለች፡፡ ይህ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የቮልስዋገን ምርት ኢ-ጎልፍ የተሰኘች በኤሌክትሪክ የሚሰትራ መኪና የማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የቮልስዋገን እና የሳይመንስ ሙከራ ፕሮጀክት አንድ አካል መሆኑንም ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስነብቧል።

በሩዋንዳ ለሚንቀሳቀሱት አራት ኢ-ጎልፍ ኤሌክትሪክ መኪኖች የሙከራ ኘሮጀክትም የመጀመሪያ ምዕራፍ የሆነ አንድ የኃይል መሙያ ጣቢያ መኖሩም ተጠቅሷል።

ወደፊት 16 የሚሆኑ ተጨማሪ መኪኖች ገበያውን የሚቀላቀሉ መሆናቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጠቁመው፤ ለዚሁ ፕሮጀክት የሚሆኑ 15 የሃይል መሙያ ጣቢያ መሰረት ልማቶች በኪጋሊ እንደሚኖርም ተናግረዋል፡፡

መኪኖቹ የሚሸፍኑት ርቀት እንደ መሬቱ አቀማመጥና የጭነት መጠን የሚወሰን ቢሆንም ሃይል ሙሉ በሙሉ ከተሞላላቸው እስከ 230 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚጓዙ መሆናቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስፍሯል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-30-4

Via EBC
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine
#UPDATE

የቀድሞው ሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ኡመር በሰጡት የእምነት ክህደት ቃል “ክልሉን በጥሩ ሁኔታ ከማስተዳደር ውጪ ወንጀል አልፈጸምኩም፤ ጥፋተኛም አይደለሁም” አሉ፡፡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የወንጀል ችሎት የአቶ አብዲ መሐመድ ኡመርን የእምነት ክህደት ቃል ዛሬ ተቀብሏል፡፡

በሌላ በኩል በአብዲ መሐመድ ኡመር የክስ መዝገብ እስካሁን ያልቀረቡ ሰባት ተከሳሾች የጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸውና ውጤቱ ለህዳር 22/2012 ዓ.ም እንዲቀርቡ ችሎቱ ትዕዛዝ መስጠቱን ዋልታ ኢንፎ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም በቁጥጥር ስር ካልዋሉ ተከሳሾች ጋር በተያያዘ የፍትህ መዛባት እየደረሰባቸው መሆኑን ከጠበቆችና ከተከሳሾች ለፍርድ ቤቱ አቤቱታ ቀርቧል፡፡ ይህም ባለፉት 15 ወራት ያልተያዙ ተከሳሾች እንዲያዙ የሚደረገው ፍለጋ አሁንም ባለመቆሙ ምስክር የመስማትና የማስረጃ ማመሳከር ቀጣይ ሂደት እንዳይፈጸም እንቅፋት ስለመሆኑ ነው የገለጹት፡፡ ፍርድ ቤቱ የተፈጠረው መጓተት ባሉ የተንዛዙ አሰራሮች ጋር በተያያዘ በመሆኑ ወደፊት በተፋጠነ መልኩ ፍትህ የሚሰጥበትን ሁኔታ እንደሚያመቻች አስረድቷል፡፡

አቶ አብዲ መሀመድ ኡመር በሶማሌ ክልል ሐምሌ 2010 ዓ.ም ዘርና ኃይማኖትን ለይቶ በተፈጸመው ጥቃት ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡ በወቅቱም ከደረሰው የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት በተጨማሪ 59 ሰዎች መገደላቸው በክሱ መብራራቱም የሚታወስ ነው፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA #JIMMA #BALE_ROBE

ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ዛሬ በአዳማ ከተማ የሰላም ኮንፈረንስ እየተካሄደ ነው። በኮንፈረንሱ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡

በተመሳሳይም በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ካሉ ዞኖችና ከተሞች የተውጣጡ ነዋሪዎች ተሳታፊ የሆኑበት የሰላም ኮንፈረንስ በጅማ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው። በሰላም ኮንፈረንሱ ላይ ከጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ኢሉ አባቦር ዞን፣ ባሌ ሮቤ እና ከጅማ ከተማ የተውጣጡ ከ1 ሺህ 600 የሚልቁ ነዋሪዎች ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በመምከር ላይ ናቸው። በውይይቱ ላይ የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንዳሉት፥ በጥፋት ድርጊቶች ውስጥ የተሳተፉ አካላትን ለህግ በማቅረብ የህግ የበላይነት ይረጋገጣል።

ባሌ ሮቤ ላይ በተደረገው ውይይት የተገኙት የገቢዎች ሚኒስትሯ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው ሰሞኑን የተፈጸመው ድርጊት ህብረተሰቡን እንደማይወክል ተናግረዋል። አያይዘውም እንደዚህ አይነት ዋጋ መክፈል እንደማያስፈልግ ጠቅሰው፥ ችግሮች ሲከሰቱ መመካከርና መደማመጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ውይይቱ በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የታየውን የሰላም እጦት ችግር ከመሰረቱ ይፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በባሌ ሮቤ የሰላም ኮንፍረንስ በመካሄድ ላይ ነው!

በባሌ ሮቤ የአገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች የሮቤ ነዋሪዎች ከፌዴራልና ከክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ጋር የሰላም ኮንፍረንስ በማካሄድ ላይ ናቸው፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ወ/ሮ አዳነች ሀቤቤ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በም/ርዕሰ መስተዳዳር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶ/ር ግርማ አመንቴ መድረኩን የእየመሩ ነው፡፡

ባሌ የምትታወቀው በሃይማኖትና በብሄር መቻቻል መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሯ ባሳለፍነው ሳምንት በሮቤ የተከሰተው ሁከት በፍፅም ይህንን ህዝብ የሚወክል ተግባር አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እንደዚህ አይነት ድርጊቶች ሰላማችንን እያወኩ በመሆናቸው አሰልችተውናል ያሉት ሚኒስትሯ መቼም ቢሆን የሃሳብ ልዩነት ሊፈጠር ይችላል፤ ይሁንና ለችግሮች መፍትሄ የሚገኘው በመነጋገር እንጂ ልዩነትን በሃይል በማራመድ አይደለም ብለዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም የስልጣናችን ምንጭ የኦሮሞ ህዝብ እንደመሆኑ የዚህን ህዝብ ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ ነዋሪዎቹ የተለያዩ ጥያቄዎችን እና አስተያየቶችን አንስተው በመድረኩ ላይ ውይይት እየተደረገባቸው መሆኑም ተገልጿል።
ኮንፍረንሱ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት መጀመሩንም ከኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዓሉ ግርማ ሀዲስ በተባለው መጽሃፉ 'ሀዲስ' የተባለውን መሪ ገጸ-ባህሪ ያናገረው ቃል እስከወዲያኛው ዘመን በህሊናዬ ይጮሃል-“የኢትዮጵያ ፈውስ የሚሰሩ እጆች ናቸው!”

Via ዶክተር በላቸው መኩሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በድሬዳዋ አሁንም የፀጥታ ችግር አልተፈታም!

በድሬዳዋ ከተማ አሁንም የፀጥታው ችግር እንዳልተፈታ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ምን ግን ጠቅሶ ዘግቧል። ጋዜጣው አገኘሁት ያለው መረጃ እንደሚያመለክተው ጥቅምት 18 ለ19/2012 አጥቢያ ሌሊት ላይ በከተማዋ ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ድምፅ መሰማቱን እና ማለዳ አካባቢ ረገብ ማለቱን ታውቋል።

ገንደ ተስፋ እና መስቀለኛ በተባሉ አካባቢዎች ግጭቶች ያጋጠሙ ሲሆን በተለይም ደግሞ በድሬዳዋ ከተማ መስቀለኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተጠልለው በሚገኙ ሰዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት በመፈፀሙ እና የአካባቢው ሰዎችም ጥቃቱን ለመከላከል ባደረጉት ጥረት ግጭት መቀስቀሱን እና መከላከያ መሐል በመግባት ማብረዱን ለማወቅ ተችሏል። ጥቃት አድራሾቹ ከድሬዳዋ ዙሪያ ገጠር ቀበሌዎች በመኪና ተጭነው መምጣታቸውን እና ድንገተኛ ጥቃት ማድረሳቸውን የአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ገልፀውልኛል ብሏላ።

በግጭቱ የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውንም የዓይን እማኞች አስታውቀዋል። መከላከያ ወደ ከተማዋ ሙሉ በሙሉ በመግባት ከተማዋን የማረጋጋት እና ግጭቶችን የመከላከል ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ምንጮች ከስፍራው ገልፀዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሦስቱ የዓባይ ተፋሰስ አገራት በዋሽንግተን ሊገናኙ ነው! የላይኛው የዓባይ ተፋሰስ አገራት የሚባሉት ኢትዮጵያ፣ሱዳን እና ግብጽ ድርድር አዘል ውይይቶችን ለማድረግ በኅዳር 26/2012 በአሜሪካ ዋሽንግተን እንደሚገናኙ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ የምትገነባው የኃይል ማመንጫ ግድብ በግብጽ በኩል ከፍተኛ የሆነ የውሃ መቀነስ ያጋጥማል የሚል ቅሬታ ሲቀርብበት ነበር።…
ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በዋሸንግተን ስለሚካሄደው የሶሰትዮሽ ስብሰባ የማውቀው ነገር የለም አለች!

ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለመወያየት ከአንድ ሳምንት በኃላ በዋሽንግተን ሊገናኙ እንደሆነ እየተዘገበ ይግኛል። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አፈፃፀም ላይ የተቋረጡ ውይይቶችን ለመቀጠል ግብፅ ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም በአሜሪካ ዋሸንግተን ከተማ እንደሚገናኙ የግብጹ አህራም ኦን ላየን ዘግቧል፡፡

የዋሸንግተኑ ስብሰባ ግብጽ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ አሜሪካ በአደራዳሪነት እንድትሳተፍ በቀረበ ጥያቄ መሰረት መዘጋጀቱ ተገልጿል። የሽምግልናው ሀሳብ በሶስቱ ሀገራት የተፈረመውን የ 2015 መርሆዎች መሰረት ያደረገ መሆኑንም ሾክሪ ተናግረዋል ፡፡

በመርሁ መሰረት ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በክርክር ወይም በድርድር ለመፍታት ካልቻሉ የሌላ ገለልተኛ አካል ሽምግልናን መጠየቅ እንደሚችሉ ይገልጻል፡፡ ግብጽ በ2017 በግድቡ ዙሪያ የዓለም ባንክ እንዲያደራድር ጠይቃ የነበረ ቢሆንም በኢትዮጵያ ተቀባይነት አላገኘም ነበር፡፡

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው ግብጽ ስላለችው የዋሸንግተን ድርድር ጉዳይ "እስካሁን የደረሰን መረጃ የለም" ብለዋል፡፡ ግድቡ የውሃ ድርሻዬን ይጎዳል የምትለው ግብጽ የግድቡን የመሙላት ሂደት ሰባት አመት እንዲሆን ስትል ብትጠይቅም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ግድቡን በሶስት አመት ውስጥ ለመሙላት ማቀዱን አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 (ያይኔአበባ ሻምበል)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ መርከቦች ወደ ምፅዋ መሄድ አቆሙ!

የኢትዮጵያ መርከቦች አሁን ወደ ምፅዋ እንደማይሄዱ ከባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ አገልግሎት ድርጅት ተሰምቷል። የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሮባ መገርሳ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 እንደገለፁት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል በወደብ አጠቃቀም ጉዳይ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈርሞ የመርከብ አገልግሎቱ ይጀመራል ተብሎ የነበር ሲሆን ይህ ባለመሆኑ በቅርብ ጊዜ አገልግሎቱ ይከናወናል ተብሎ አይጠበቅም ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በሀረር ህዝባዊ ውይይት አደረጉ!


ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከመከላከያ ሚንስትሩ አቶ ለማ መገርሳ ጋር በመሆን ከሀረሪ ክልል፣ ከምስራቅ እና ምእራብ ሀረርጌ ዞኖች እንዲሁም ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች ጋር የሰላም ኮንፈረንስ አካሂደዋል፡፡ በጨለንቆ አዳራሽ በተካሄደው ህዝባዊ ውይይት ላይ ከተሳታፊዎች ለጠቅላይ ሚንስትሩ እና መከላከያ ሚንስትሩ ከተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የምስራቅ ኢትዮጵያ ህዝቦች እንደከዚህ ቀደሙ አንድነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸውም ነው ከመድረኩ የተገለፀው፡፡ የፍቅር እና የጀግኖች ምሳሌ የሆነው የሀረር ህዝብም ሰላሙን በጋራ መጠበቅ እንዳለበት ጠቅላይ ሚንስትሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ምንጭ፡- ኦቢኤን(OBN)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Social Enterprise Challenge!!

Apply by Nov 8!
www.bluemoonethiopia.com

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእግር ኳስ ውድድሮቹ በፀጥታ ችግር ላይካሄዱ ይችላሉ!

የእግር ኳስ ክለቦችን የሚያሳትፈው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ፣ የደቡብ ካስትል ዋንጫ እና የአዳማ ከተማ ዋንጫ በሀገሪቱ እየታየ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ላይደረግ ይችላል የተባለ ሲሆን የፀጥታ አካላትም ሀላፊነት አንወስድም እያሉ ነው፡፡

ምንጭ፦ ቴዎድሮስ ታከለ (ቴዲ ሶከር)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግብጽ በዓባይ ዙሪያ ናይጀሪያ እንድታደራድራት መጠይቋ ተሰማ!

ግብጽ በዓባይ ዙሪያ ከኢትጵያ ጋር የገባቸውን ውዝግብ ለመፍታት ናይጀሪያን በአደራዳሪነት ጠየቀች። ብሎምበርግ እንደዘገበው የግብጽ የሕዝብ እንደራሴው አፈ ጉባዔ የናይጀሪያውን ፕሬዘዳንት ሙሐሙድ ቦሃሪን በአደራዳሪነት መጠየቃቸውን አስነብቧል።

ከምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ናይጀሪያ ጋር ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን የገለፁት አፈ ጉባዔው ጥቅምት 18/2012 ከናይጀሪያ ምክትል ፕሬዘዳንት ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ግብጽ ከዓባይ ወንዝ ምታገኘውን የውሃ መጠን ይቀንሳል በሚል የምታቀርበውን መከራከሪያ ኢትዮጵያ ሳትቀበል መቆየቷ የሚታወስ ሲሆን፤ 40 ቢሊዮን ኪዮቢክ ወሃ ለማግኘት ብትጠይቅም ኢትዮጵያ ግን 30 ቢሊዮን ብቻ እንደምትለቅ ማሳወቋ የሚታወስ ነው።

5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት የታላቁ የኅዳሴ ግድብ መሰረት አድርጎ የተባበሩት መንግስታት ባስቀመጡት ግምት በፈረንጆች 2025 ግብጽ ውሃ እጥረት እንደሚያጋጥማት ይፋ አድርጓል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BreakingNews

የፀጥታ አካላት ሀላፊነት መውሰድ ካልቻሉ የ2012 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እና የእግር ኳስ ውድድሮች ላይካሄዱ ይችላሉ ተብሏል፡፡ ውድድሮቹ ሚካሄዱ ከሆነ ግን በዝግ እንዲደረጉ እንቅስቃሴ መጀመሩን የስፖርት ጋዜጠኛው ቴዎድሮስ ታከለ(ቴዲ ሶከር) አገኘሁት ባለው መረጃ ጠቁሟል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert 737 ማክስ ጄቶቹ ላይ የቴክኒክና የንድፍ ችግር እንደነበረባቸው አምራቹ ቦይንግ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ አምኗል። የኩባያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት ፊት ቀርበው ትናንትና ዛሬ እየተጠየቁ ናቸው።

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AMNESTY INTERNATIONAL

የኢትዮጵያ መንግሥት "የፀረ ሽብሩን ሕግን" አላግባብ በመጠቀም ተተቸ። ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግሥትን ይተቹ ነበር የተባሉ 22 ሰዎች ለፍርድ ሳይቀርቡ ለ4 ወራት ታስረው ትናንት መለቀቃቸውን አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት አሁንም የፀረ-ሽብር ሕጉን አለአግባብ መጠቀሙን አላቆመም ሲል ወቅሷል።

በድርጅቱ የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ አቶ ፍስሃ ተክሌ ዛሬ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ትንናት የተለቀቁት 22 ሰዎች ከሰኔ 15ቱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ግድያ በኋላ ከተያዙት ከ200 ይበልጣሉ ካሏቸው ሰዎች መካከል መሆናቸውን ገልጸው ለፍርድ ሳይቀርቡ ለአራት ወራት መታሰራቸዉ ኢፍትሀዊ እንደነበረ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-30-5

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AMNESTY INTERNATIONAL

ባለፈው ሳምንት በኦሮምያ የተለያዩ ከተሞች ከተነሳው ተቃውሞ በኋላ በተከተሉት ግጭቶች እና ጥቃቶች የደረሰው ጉዳት ዓይነት ብዛት እና የተፈጸመበት መንገድ አሳሳቢ ነው ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።

በድርጅቱ የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ አቶ ፍስሃ ተክሌ ለጀርመን ራድዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ ከዚህ ቀደም ምልክቶች እንደነበሩ አስታውሰው መንግሥት ምልክቶቹን አንብቦ መዘጋጀት፣ ሲከሰቱም በተቻለ መጠን ለመከላከል ጥረት ማድረግ ነበረበት ብለዋል።

ከተቃውሞው ጋር ተያይዞ የደረሱት ጥፋቶችም የመንግሥት የመከላከያ አቅም ማነስን ያሳያልም ብለዋል። ወደፊትም ለዚህ የዳረገውን መሠረታዊውን ችግር መፍታት እንደሚገባም አሳስበዋል። መንግሥትም ሕግ ማስከበር ብቻ ሳይሆን የእርቅና የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ችግሮችን ለይቶ አስፈላጊ እርምጃዎችን መውስድ መቻል አለበት ብለዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

ሐረር ከተማ ከትላንት ጀምሮ ገበያውም፣ ሥራውም፣ ትምህርቱም ተከፍተው ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች፤ የከተማይቱ ነዋሪም ወደ መደበኛ ህይወቱ ተመልሷል።

Via BETELHEM NEGASH
@tsegabwolde @tikvahethiopia