#Breaking
የአብን እና የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት አባላት እንዲፈቱ ተወሰነ!
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የአዲስ አበባ ከተማ ባላደራ ምክር ቤት አባላት ከእስር እንዲፈቱ ተወሰነ። የባለአደራ ምክር ቤተ ሰብሳቢ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደገለፁት ሁሉም የባላደራ ምክር ቤቱ አባላት በመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ መወሰኑን አስታውቀዋል።
ከባላደራ ምክር ቤት በተጨማሪም የአብን(አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ) አባላትም እንዲፈቱ መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል። እስክንድር ነጋ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ እስረኞች እንዲፈቱ የተወሰነ መሆኑን እና ከእነዚህም ውስጥ የአብን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ክርስቲያን ታደለ እንደሚገኙበትም ታውቋል።
Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia

#ArbaMinch
"የአርባምንጭ ደም ባንክ" ሰሞኑን በተካሄደው ሀገር አቀፍ የደም ልገሳ መረሃ ግብር 411 ዩኒት ደም መሰብሰቡን ገለፀ፡፡

ለ36ኛ ጊዜ ደም የለገሰው ወጣት ሄኖክ!
ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ወጣት ሄኖክ ኮይራ ይባላል፡፡ የ27 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ደም ለግሶ ሕይወት በመስጠት በአርባምንጭ ከተማ ግንባር ቀደም ነው፡፡ ለ36ኛ ጊዜ ዘንድሮ ደም ለግሷል፡፡ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ደም በመለገስ ሄኖክን የሚስተካከለው የለም፡፡ የዚህ ወጣት አርዓያነት በመከተል ደም በመለገስ ”ሕይወትን ሰጥተን ሕይወት እናድን ”
Via Gamo Zone Administration public Relation office

#መልካም_ዜና
በትግራይ ክልል #ህዝቡ ባደረገው ከፍተኛ ተሳትፎና የመከላከል ስራ ራያ አዘቦ፣ ራያ አላማጣ እና እንደርታ ወረዳዎች ከአንበጣ መንጋ ነፃ መሆናቸው ተገለፀ። ትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባለፉት ሳምንታት በተለያዩ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ መከሰቱ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም በትግራይ ክልል መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሰራተኞች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በክልሉ ያሉ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች፣ የክልሉ ልዩ ሀይል፣ ተማሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባደረጉት የመከላከል ስራ በራያ አዘቦ፣ ራያ አላማጣ እና እንደርታ ተከስቶ የነበረው አንበጣ መንጋ መወገዱን የክልሉ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ አስታውቋል።
Via FBC

#ETHIOPIA የወልዋሎና የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች የኣንበጣ መንጋን በማስወገድ ዘመቻ ላይ!
PHOTO: JHON
@tsegabwolde @tikvahethiopia
PHOTO: JHON
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CBE
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጥቅምት 03/2012 ከ30,000 ለሚልቁ ሰራተኞቹ በላከው የውስጥ ማስታወሻ የደንበኛ አገልግሎት የሚሰጡ የድርጅቱ ሠራተኞች በሥራ ሰዓት የስልክ ጥሪን ጨምሮ የማህበራዊ ሚድያ እና ሌሎች የሞባይል ስልክ አገልግሎቶችን እንዳይጠቀሙ ከልክሏል።
በሲስተም መጨናነቅ ምክንያትና የኤቲኤም ማሽኖች በአግባቡ ባለመሥራታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ የደንበኞቹ ቅሬታ እየጠነከረ የመጣበት ባንኩ፣ በስትራቴጂክ እና ኢኖቬሽን ክፍሉ አማካኝነት አጠናሁ ባለው የዳሰሳ ጥናት መሠረት፤ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ መጥቶ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል።
ለዚህም አንኳር ተብለው ከተቀመጡ ምክንያቶች መካከል የደንበኞች አገልግሎት ሰጪ ሠራተኞች የሞባይል ስልክ አጠቃቀም ሆኖ በመገኘቱ በውስጥ እርምጃው እንዳስፈለገ የውስጥ ማስታወሻው ላይ መጠቀሱን አዲስ ማለዳ ጋዜጣ ዘግቧል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

በሰሜን ወሎ ዞን በአፋር ክልል እና አማራ ክልሎች አጎራባች ቀበሌዎች ላይ ያለው የፀጥታ ሁኔታ የአንበጣ መንጋውን በሙሉ አቅም ለመከላከል እንዳስቸገራቸው የአካባቢው አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡ የበረሃ አንበጣው በተከሰተባቸው የሀብሩ እና ራያ ቆቦ ወረዳዎች ላይ በእንስሳት መኖ እና በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA
ባሳለፍነው በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የፀጥታ መደፍረስ አጋጥሞ እንደነበር ይታወቃል፤ ከሰሞኑ ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያዎች በሚሰራጩ ወሬዎች ግጭት ተፈጥሮባቸው በነበሩ አካባቢዎች የሚኖሩ ዜጎች ስጋት ውስጥ ወድቀው እንደነበር አይዘነጋም። በሁሉም አካባቢዎች በሚባል ደረጃ ሁኔታዎች ተረጋግተዋል። አንፃራዊ ሰላምም ሰፍኗል። አባ ገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች ታች ድረስ ወርደው ህዝቡን የማረጋጋት ስራ፣ የማወያየት ስራ እየሰሩ ይገኛሉ። በተለይ በማህበራዊ ሚዳያዎች ትላንት ሰኞ ግጭት ሊፈጠር ነው፣ መንገድ ሊዘጋ ነው፣ እልቂት ይፈፀማል ተብሎ ሲወራባቸው የነበሩት ከተሞች ከባለፈው ሳምንት በተሻለ ሰላም እና መረጋጋት ሰፍኖባቸው መደበኛ እንቅስቃሴዎች ተጀምረው ነው የዋሉት።

#ባሌ_ሮቤ | ባለፉት ሁለት እና ሶስት ቀናት በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ሲባልባት የነበረችው የባሌ ሮቤ ከተማ ወደ ቀደመው ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ እየተመለሰች እንደምትገኝ ተገልጿል። የንግድ እና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ወደነበረበት ተመልሷል። በሁሉም ቀበሌዎች ውይይቶች እየተደረጉ ይገኛሉ። የሀገር ሽማግሌዎች እና አባ ገዳዎች ህዝቡ ወደቀደመው ሰላማዊ ኑሮው እንዲመለስ ከፍተኛ ስራ እየሰሩ ናቸው። ከሰሞኑ ግጭት ጋር በተያያዘ 27 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
Via NIGI
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via NIGI
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA
የአዳማ ከተማ የዛሬ ውሎ ፍፁም የተረጋጋና ሰላማዊ ነው። የንግድ ተቋማት ወደስራቸው ተመልሰዋል፤ የትራንስፖርት አገልግሎት ወደቀደመው ሁኔታ እየተመለሰ ይገኛል። አብዛኛው የትምህርት ተቋማት ግን ዛሬም እንደተዘጉ ናቸው ተማሪዎች አልተገኙም። የቲክቫህ ቤተሰቦች እንደሚሉት በተማሪዎች መካከል ግጭት እንዳይፈጠር በመስጋት ወላጆች ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት አላኩም ብለዋል። በትላናንትናው ዕለት የአዳማ ከተማ አስተዳደር ከተማይቱ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷን ገልፆ በቀጣይ ቀናትም ትምህርት ቤቶች ወደ ስራ ይመለሳሉ ሲል ገልጿል።
PHOTO: IBRO(አዳማ ቲክቫህ ቤተሰብ)

ሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ባሉበት ቦታ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን ገለፀ።
የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ባለፈው ሳምንት ተከስቶ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኞች ለአንድ ወር የሚሆን የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ተልኳል።
ከምዕራብ አርሲ ዶዶላ ተፈናቅለው በሁለት ቤተክርስቲያናት ለሚገኙ ዜጎች የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
በዚሁ መሰረት በዶዶላ ለተፈናቀሉ 3 ሺህ 366 ዜጎች እህል፣ አልሚ ምግብ፣ ዘይት፣ ጥራጥሬ፣ ብስኩትና ሌሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ተልከውላቸዋል ነው ያሉት።
https://telegra.ph/ETH-10-29-5
Via ENA

TIKVAH-ETHIOPIA
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ! @tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት!
የሀገሪቱን ሰላም ማስጠበቅ የሁሉም ኢትዮያውያን የጋራ ኃላፊነት መሆኑን የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል። ጠቅላይ ምክር ቤቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የሃይማኖት ተቋማትም ይህን የጋራ ኃላፊነት የመወጣትና በዚህ ረገድ ህዝቡን የመምከር ሀገራዊ ግዴታ አለባቸው ብሏል፡፡ ባለፉት ወራት በቤተ አምልኮዎች እና በመስጅዶች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት ቢፈፀምም ህብረተሰቡን በማረጋጋት ነገሩን በትእግስት ሲያልፍ መቆየቱን ምክር ቤቱ ገልጿል።
More👇
https://telegra.ph/ETH-10-29-9
Via ኢቢሲ

359 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል!
ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች አጋጥሞ ከነበረው ግጭትና ጥቃት ጋር በተያያዘ 359 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በአሁኑ ወቅት በኦሮሚያ ያለው ሁኔታ እየተረጋጋ መምጣቱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል ከፍያለው ተፈራ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇(BBC)
https://telegra.ph/ETH-10-29-7

#ASTU
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) ዛሬ ጠዋት ለ4 ቀናት የሚቆይ የደም ልገሳ ፕሮግራም ተጀምሯል። የደም ልገሳ ፕሮግራሙን ያዘጋጁት ክለብ 20/25 ከአዳማ ከተማ ደም ባንክ ጋር በመተባበር ነው። ዛሬ በነበረው የደም ልገሳ ላይ በርካታ ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
Via Hiwi(ቲክቫህ አዳማ-ASTU ቤተሰብ)

#BreakingNews
የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳድ ሀሪሪ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ገለፁ። በዋትስ አፕ ላይ የተጣለ ታክስን በመቃወም ተጀምሮ በሀገሪቱ አለ የተባለውን የፖለቲካ ሙስና እና የኢኮኖሚ ቀውስን ወደ መቃወም በተቀየረ አመፅ ሀገሪቱ ስትናጥ ቆይታለች። አመፁ ከተቀሰቀሰ ጀምሮም ሊባኖስ ለ13 ቀናት ሙሉ በሙሉ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋ ተዘግቶ፣ ባንኮች እና ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ተቋርጠውባት ሰንብታለች።
https://telegra.ph/LBN-10-29
ምንጭ፦ አልጀዚራ( ኤፍ ቢ ሲ)

#ETHIOPIA | የገምሹ በየነ የግንባታ ኩባንያ ሰራተኞች በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መርሐቤቴ ወረዳ ከሚገኝ የሥራ ቦታቸው ለቀው መውጣት ጀመሩ።
ሰራተኞቹ ባለፈው እሁድ በኩባንያው ንብረቶች ላይ ጥቃት ከተፈጸመ በኋላ ከአካባቢው ለቀው እንዳይወጡ በአካባቢው ነዋሪዎች ታግደው እንደነበር ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።
ከሰራተኞቹ መካከል አንዱ የሆኑት አቶ እንዳልካቸው በላይ ወደ 300 ገደማ ይሆናሉ የተባሉት ሰራተኞች በመከላከያ ሰራዊት ታጅበው ከመረሐቤቴ መውጣታቸውን ለጀርመን ሬድዮ ጣቢያ አረጋግጠዋል።