TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#USA

የአይ ኤስ-አይ ኤስ (ISIS) መሪ አቡ በከር አል-ባግዳዲ መገደልን መሰረት በማድረግ “በከፍትኛ የተጠንቀቅ ሁኔታ” እየሰራ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስቴር ገለፀ። ይሁንና ተጨባጭ የሆነ የአደጋ መረጃ ከሌለ በስተቀር ማስጠንቀቅያ የማውጣት ዕቅድ እንደሌለው አክሎ ገልጿል።

የUS ልዩ ወታደራዊ ኃይል በሰሜን ምዕራብ ሶርያ በጥንቃቄ ባካሄደው ተልዕኮ ባግዳዲንን መግደሉን ፕረዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ካስታወቁ በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ የአገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስቴር መግለጫ አውጥቷል። “የፀጥታ ተቋማችን በንቃት መከታተሉን ይቀጥላል። ለሚከሰቱ ሁነቶች ምላሽ መስጠቱን እንቀጥላለን” ይላል መግለጫው። በኩርዶች የሚመራው የሶርያ ዲሞክራስያዊ ኃይሎች እንደሚለው የባግዳዲ ቀኝ እጅ የነበረው የዳዕሽ ቃል አቀባይ አቡ ሐሰን ዐል-ሙሓጂርም በዩናይትድ ስቴትስ ተልዕኮው ተግድሏል። የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣኖች ግን ገና አላረጋገጡትም።

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች መካከል በትምህርት ዘርፍ ያለውን ትስስር ለማጠናከርና አዳዲስ ግንኙነቶችን ለመፍጠር ያለመ ምክክር ዛሬ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ በምክክር መድረኩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ በአገራችን ያሉ ዩኒቨርስቲዎች ፕሬዚዳንቶች እና የዩኒቨርስቲዎቹ የዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሮች ከየአሜሪካ ፐብሊክ ላንድ ግራንት ዩኒቨርስቲዎች ማህበር ተወካዮች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

Via የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኃይማኖት መሪዎች የሰላም ጥሪ!

የፌደራልና የክልል መንግሥታት የብዙኃኑ ፍላጎት ሰላም መሆኑን ተረድተው ለዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት እንዲሰሩ የኃይማኖት መሪዎች ተማፀኑ፡፡

የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰጠው መግለጫ የተገኙ የእምነት መሪዎች ሰሞነኛውን ግጭትና ጥቃት በምሬት በማውገዝ ወንጀለኞች ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡

እንባ እየተናነቃቸው መግለጫ ሲሰጡ የተስተዋሉት አባቶች በኢትዮጵያ ሰው በአደባባይ ሲገደልና ሲታረድ እንደማየት ቀውስ የለም ብለዋል፡፡

በክልሎች መንግስታት መካከል የሚታየው ውጥረት የፖለቲካ ኃይሎች የሚፈጥሩት አጀንዳ መሆኑን ኣባቶቹ አስምረውበታል፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያ ደረጃ የመንግሥት አካላት እርስ በርሳቸው እርቅ እንዲፈፅሙም በአጽንኦት ጠይቀዋል፡፡

የፌደራልና የክልል የጸጥታ አካላት የኢትዮጵያን ሰላም ሁሌም ነቅተው እንዲጠብቁና ተገቢ ያልሆኑ አዝማሚያዎችን ቀድመው በመገንዘብ እንዲከላከሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሰሞኑን የተከሰተው ግጭት ኃይማኖታዊ ገፅታ እንዲላበስ እየተደረገ ያለው በሌሎች ኃይሎች እንጅ ፍፁም ሃይማኖታዊ መሠረት እንደሌለው እንገልፃለን ሲሉም አሳስበዋል፡፡

Via #AHADUTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለሐያት ሪጀንሲ የባለ 5 ኮኮብ ለኤልያና ሆቴል ደግሞ የባለ 4 ኮኮብ ደረጃ ሰጠ። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እያካሄደ በሚገኘው የሆቴሎች ደረጃ ምደባ ምዘና ሲካሄድባቸው ቆይቶ ውጤታቸው ለተጠናቀቀ ሁለት ሆቴሎች በዛሬው ዕለት የኮከብ ደረጃ የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል የባለ 5 ኮከብ እንዲሁም የኤልያና ሆቴል የባለ 4 ኮከብ ደረጃ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ሚኒስቴሩ ባሳለፍነው ነሃሴ 2011 ዓ.ም 12 ባለ አራት፣ 13 ባለ ሶስት፣ 31 ባለሁለት እንዲሁም 27 ባለ አንድ ኮከብ ደረጃ በአጠቃላይ 81 የኮከብ ደረጃ የተሰጣቸው ሆቴሎች ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

Via ETHIO FM 107.8
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ላይ የሠጠው መግለጫ፦

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያዊያን ልጆቻችን፤- 

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ባሳለፍነው ሳምንት በአገራችን አንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በአሮሚያ ብሔራዊ ክልል በተፈጠረው ሁከት፣ አለመረጋጋት እና ግጭት ምክንያት ሕይወታቸው ባጡት ወገኖቻችን የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለሟቾች ቤተሠቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአካል እና የሥነ ልቦና ጉዳት ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንም ፈጣን ፈውስን እንዲያገኙ እየተመኘን በጸሎታችንም እንደምናስባችሁ ለመግለጽ እንወዳለን!! እንደሀገር እየታየ ያለው ያለመረጋጋት እና የግጭት አዝማሚያ ተወግዶ  ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታና ወደሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለስ፣ ሁከትንና ግጭትን ከሚያባብሱ ሀሳቦችና ድርጊቶች በመታቀብ የየበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን ሁሉ  በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/የኢትዮጵያ-የሃይማኖት-ጉባኤ-ተቋማት-10-29

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለኢትዮጵያውያን ርዳታ በኢትዮጵያውያን!

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ለተገደሉ ቤተሰቦች፤ ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች በሐገር ፍቅር ቴአትር ቅጥር ግቢ ውስጥ የርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ትናንትና ጀምሮ ዛሬም ቀጥሏል። 25 በሚደርሱ በጎ ፈቃደኞች የተጀመረውን የርዳታ ማሰባሰብ ተግባር በዋናነት «የጉዞ አድዋ» መርኃ-ግብር አዘጋጆች አስተባባሪ ናቸው። ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተዉ አለመረጋጋት የተጎዱ ወገኖችን ለመርዳት ከትናንትና ማክሰኞ አንስቶ የተጀመረዉ ርዳታ ማሰባሰብ ሥራ በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የኮሚቴዉ አስተባባሪዎች ገልጠዋል። ከገንዘብ ውጪ የዕለት ርዳታ በቁሳቁስ የሚሰበሰበው ሐገር ፍቅር ቴአትር ቤት ውስጥ ነው። ዛሬም እየተኪያሄደ ነው። የቁሳቁስ ርዳታውን መንግሥት ተረክቦ እንደሚያጓጉዝ አዘጋጆቹ ገልጠዋል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ የሰባት ዓመት እስራት ተፈረደበት!

ጋዜጠኛ ፍቃዱ ማኅተመወርቅ ከአምስት ዓመታ በፊት በዕንቁ መጽሔት በተመሰረት ክስ ማክሰኞ ጥቅምት 18/2012 በዋለው ችሎት ጥፋተኛ በመባሉ በሰባት ዓመት እስራታ እና ሰባት ሽሕ ብር የገንዘብ መቀጮ ተፈርዶበታል። ፍርድ ቤቱ ግለሰቡን ከታክስ ስወራ ጋር በተያያዘ ክስ መስርቶበት የነበረ ሲሆን ከዚህም ጋር በተያያዘ ከ2004 እስከ 2006 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ 179ሽሕ 411 ብር ከ65 ሳንቲም ለመንግስት መክፈል የነበረበትን ግብር ስወራ አድርጓል የሚል ክስ ተመስርቶበት ነበር።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ክስ ቀርቦባቸው ችሎቱ ጥፋተኛ ያላቸው ጌታቸር እሸቴ እና ፍፁም ጌታቸው በ12 አመት ፅኑ እስራት ቶፊቅ ሽኩር እና ሸምሱ ሰይድ ደግሞ የ11 አመት ፅኑ እስራት ቅጣት ዛሬ ተላልፎባቸዋል። በዚህ መዝገብ ክስ የተመሰረተው 38 ሰዎች ላይ የነበረ ቢሆንም ከ4ቱ ውጭ ያሉት በምህረት ከእስር መውጣታቸው ይታወሳል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ለታራሚዎቹ ደህንነት በማለት የቅጣት ውሳኔው ባሉበት ማረምያ በደብዳቤ የወሰነ ሲሆን ለቤተሰብ እና ጋዜጠኞች ውሳኔው በፅህፈት ቤት ተነቧል።

Via ሳምራዊት አመለወርቅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

ከሰኔ 15 የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያ ጋር በተያያዘ በሽብር ትጠረጠራላችሁ በሚል ላለፉት አራት ወራት በእስር ላይ የቆዩት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮች ዛሬ የፌድራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበዋል፡፡

በዕለቱ የችሎት ውሎ የንቅናቄው የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በለጠ ካሳ አቃቤ ሕግ የጠየቀባቸው አምስት ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ሲፈቀድባቸው፣ ሌሎች አምስት የንቅናቄው የአዲስ አበባ አመራሮች ደግሞ በገንዘብ ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ፍ/ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

በዚህ መሠረትም፦

1ኛ) አንተነህ ስለሺ (የአብን የአዲስ አበባ ፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ)

2ኛ) ንጉሡ ይልቃል (የአብን የካ ክ/ከተማ ወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ)

እያንዳንዳቸው በ5ሺ ብር ዋስ፣

3ኛ) ዮናስ አሰፋ (የአብን ቦሌ ክ/ከተማ ሰብሳቢ)

4ኛ) ሽገዛ ሙሉጌታ (የአብን ኪልፌ ክ/ከተማ አደረጃጀት ኃላፊ)

5ኛ) በዕውቀቱ በላቸው (የአብን ቄርቆስ ክ/ከተማ አደረጃጀት ኃላፊ)

እያንዳንዳቸው በሰባት ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ችሎቱ ወስኗል፡፡

Via #AsratTV
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AdigratUniversity

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከ 414 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የማስፋፊያ ግንባታዎች እያካሔደ መሆኑን አስታወቀ። የዩኒቨርስቲው የግንባታ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ኪደይ ገብረማርያም ለኢዜአ  እንዳሉት፣ የፕሮጀክቶቹ ግንባታ ተማሪዎች፣መምህራንና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ውብና ጽዱ የሆነ አከባቢ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው።

https://telegra.ph/ETH-10-29-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA

"አዳማ ዛሬ ከነጋ ጀምሮ በሁሉም አቅጣጫ #ሠላም ነው። ሠላማዊ ህይወት እንድቀጥል ህዝባችን በማህበራዊ ሚድያ በማይታወቁ እና አከባቢው ላይ በማይገኙ ሰዎች የሚረጨውን የክፍፍል ወሬ ችላ በማለት ለሠላም ሊተጋ ይገባል።" ባይሳ(ቲክቫህ ቤተሰብ) ከአዳማ ፖስታቤት አከባቢ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking

የአብን እና የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት አባላት እንዲፈቱ ተወሰነ!

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የአዲስ አበባ ከተማ ባላደራ ምክር ቤት አባላት ከእስር እንዲፈቱ ተወሰነ። የባለአደራ ምክር ቤተ ሰብሳቢ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደገለፁት ሁሉም የባላደራ ምክር ቤቱ አባላት በመታወቂያ ዋስ እንዲፈቱ መወሰኑን አስታውቀዋል።

ከባላደራ ምክር ቤት በተጨማሪም የአብን(አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ) አባላትም እንዲፈቱ መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል። እስክንድር ነጋ ለአዲስ ማለዳ እንዳስታወቁት ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ እስረኞች እንዲፈቱ የተወሰነ መሆኑን እና ከእነዚህም ውስጥ የአብን ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ክርስቲያን ታደለ እንደሚገኙበትም ታውቋል።

Via አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ArbaMinch

"የአርባምንጭ ደም ባንክ" ሰሞኑን በተካሄደው ሀገር አቀፍ የደም ልገሳ መረሃ ግብር 411 ዩኒት ደም መሰብሰቡን ገለፀ፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ36ኛ ጊዜ ደም የለገሰው ወጣት ሄኖክ!

ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ወጣት ሄኖክ ኮይራ ይባላል፡፡ የ27 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ደም ለግሶ ሕይወት በመስጠት በአርባምንጭ ከተማ ግንባር ቀደም ነው፡፡ ለ36ኛ ጊዜ ዘንድሮ ደም ለግሷል፡፡ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ደም በመለገስ ሄኖክን የሚስተካከለው የለም፡፡ የዚህ ወጣት አርዓያነት በመከተል ደም በመለገስ ”ሕይወትን ሰጥተን ሕይወት እናድን ”

Via Gamo Zone Administration public Relation office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መልካም_ዜና

በትግራይ ክልል #ህዝቡ ባደረገው ከፍተኛ ተሳትፎና የመከላከል ስራ ራያ አዘቦ፣ ራያ አላማጣ እና እንደርታ ወረዳዎች ከአንበጣ መንጋ ነፃ መሆናቸው ተገለፀ። ትግራይ ክልልን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ባለፉት ሳምንታት በተለያዩ አካባቢዎች የአንበጣ መንጋ መከሰቱ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎም በትግራይ ክልል መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሰራተኞች፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ በክልሉ ያሉ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች፣ የክልሉ ልዩ ሀይል፣ ተማሪዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ባደረጉት የመከላከል ስራ በራያ አዘቦ፣ ራያ አላማጣ እና እንደርታ ተከስቶ የነበረው አንበጣ መንጋ መወገዱን የክልሉ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ አስታውቋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA የወልዋሎና የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች የኣንበጣ መንጋን በማስወገድ ዘመቻ ላይ!

PHOTO: JHON
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ በውቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ መግለጫ!

@tsegabwolde @tikvahethiopia