TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኤልያስ መሰረት ለቲክቫህ

ይህ ከትናንት ጀምሮ ሶሻል ሚድያ ላይ በስፋት እየተላለፈ ያለ መልእክት ነው!

ለሰላም የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ!

1ሚሊዮን ተከታይ የለኝም። ቢያንስ እያንዳንዳቸው 1000 ጓደኛ ያላቸው እስከ 5000 ጓደኞች ግን አሉኝ:: ከዛሬ ጀምሮ በሃገሬ ጉዳይ ዳር ቁጭ ብዬ ተመልካች ላለመሆን ቃል እገባለሁ። እናንተስ?

የጥላቻ ንግግሮችን ችላ በማለት እና ለሀሰተኛ ዜናዎች ጆሮ ባለመስጠት ሁላችንም ለሰላም እንስራ!

#ሰላምለኢትዮጲያ
#PeaceForEthiopia

@eliasmeseret @tikvahethiopia
የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ዛሬ የተመድ ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሀመድን እና የአፍሪካ ህብረት ሀላፊዎችን አዲ ሀሎ የተባለ ስፍራ አግኝተዋል!

በኤልያስ መሰረት ለቲክቫህ

ፕሬዝደንቱ አሚና መሀመድን እና ሌሎች የአፍሪካ ህብረት ሀላፊዎችን ያገኙት ቡድኑ በኤርትራ ጉብኝት እያደረገ ባለበት ወቅት ነው። የቡድኑ ጉብኝት ሴቶች በሰላም፣ ፀጥታ እና ልማት ላይ ያላቸውን አስተዋፅዎ ለማስገንዘብ ነው ብሎ የኤርትራ ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ዛሬ ገልፁዋል።

"ጉብኝቱ በተባበሩት መንግስታድ ድርጅት እና ኤርትራ መሀከል እያደገ ያለውን ግንኙነት ያሳያል" ብለዋል ፕሬዝደንቱ።

ተመድ እና ኤርትራ ለአመታት የሻከረ ግንኙነት ነበራቸው፣ በተለይ ድርጅቱ ኤርትራ ላይ "አልሻባብን ትደግፋለች" ብሎ የተለያዩ ማእቀቦችን ከጣለ በሁዋላ። በቅርብ ወራት ማእቀቦቹ እንደተነሱ ይታወሳል።

@eliasmeseret @tikvahethiopia
በኤልያስ መሰረት ለቲክቫህ

በናይጄርያዊው ባለሀብት አሊኮ ዳንጎቴ ስም የተከፈተ እና በርካታ ተከታዮች ያሉት ይህ ገፅ የሀሰት እንደሆነ ይታወቅ!

ገፁ ላይ ያሉት አጭበርባሪዎች መኪና፣ ቤት፣ ቪዛ ይሰጣችሁዋል በማለት "በቅድሚያ ግን ይህንን ጉዳይ ለሚያስፈፅመው ጠበቃ 1,000 ዶላር መላክ ያስፈልጋል" በማለት ሰዉን እየዘረፉ ነው።

@eliasmeseret @tikvahethiopia
"ጠ/ሚር አብይ ሚድያዎችን በተመለከተ ሩስያ ላይ ያነሱት በግብፅም፣ በኢትዮጵያም ስላሉት ነው"--- የጠ/ሚሩ ፕረስ ሰክረታሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ማምሻውን ከነገሩኝ

በኤልያስ መሰረት ለቲክቫህ

በቅርቡ ጠ/ሚር አብይ ሩስያ ላይ የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ በሰጡት አስተያየት "ሚድያዎች በሁለቱ ሀገራት መሀል ግጭት ለመፍጠር ይሞክራሉ" ብለው ገልፀው ነበር። አቶ ንጉሱም "ይህ ጉዳይ በግብፅም፣ በኢትዮጵያ ያሉ ሚድያዎችን የተመለከተ ነበር። በተለይ ደግሞ በግብፅ ያሉትን" ብለዋል።

ለዛሬው በዚህ ልሰናበታችሁ! የሳምንት ሰው ይበለን!

@eliasmeseret @tikvahethiopia
የቲክቫህ ቤተሰባችን አባል ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት የተመረጡ መረጃዎችን ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ወዳናተ ማድረስ ጀምሯል። ጥሩ ቆይታ፣ ጠቃሚ መረጃዎችን እንዳገኛችሁ ተስፋ እናደርጋለን። አስተያየት መስጫ @tikvahethiopiaBot
#DODOLA

በምዕራብ አርሲ ዞን በምትገኘው ዶዶላ ከተማ ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የአስራ አራት ሰዎች ሥርዓተ ቀብር መፈጸሙን የከተማዋ ነዋሪዎች ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ተናግሩ። በከተማዋ በተቀሰቀሰ ኹከት ምክንያት ቆስለው በአብያተ ክርስቲያን የተጠለሉ ነዋሪዎች ወደ ሕክምና ማዕከል ለመጓዝ ሥጋት እንዳደረባቸው ገልጸዋል።

Via የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥተዋል።

የመግለጫው ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የተከበራችሁ የሀገሬ ሕዝቦች!

ሰሞኑን በተከሠተው እጅግ አሳዛኝ ግጭት በዜጎቻችንና በንብረታቸው ላይ በደረሰው ሁሉ ማዘኔን አስቀድሜ ለመግለጥ እወዳለሁ።

ያጋጠመን ፈተና ኢትዮጵያውያን ካልተባበርንና አንድ ሆነን ካልቆምን መንገዳችን ምን ያህል አስቸጋሪና አስፈሪ ሊሆን እንደሚችል ማሳያ ነው፡፡ ችግሩ የብሔርና የሃይማኖት መልክ እንዲኖረው ለማድረግ ተሞክሯል፡፡ በዚህም የተነሣ ወገኖቻችን በአሰቃቂ ሁኔታ መሥዋዕት ሆነዋል።

የጸሎት ቤቶች ተቃጥለዋል፡፡ የንግድ ድርጅቶችና የመኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። የተፈናቀሉ ወገኖች በተለያዩ ቦታዎች ተጠልለዋል፡፡ መተላለፊያ ያጡ ዜጎችም በየከተሞቹ ከርመዋል፡፡ እንኳንስ ለማየት ለመስማት የሚዘገንን እኩይ ተግባር በወገናችን ላይ ተፈጽሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-26-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንጠንቀቅ!

እጅግ በጣም ዘግናኝ የሆኑ ተንቀሳቀሽ የቪዲዮ ምስሎች በተለያየ ብሄር ሙዚቃዎች እየታጀቡ በማህበራዊ ድረገፆች በስፋት እየተለቀቁ እንደሆነ እየተመለከትን ነው። አንዳንዶቹ ከዛሬ ሁለት ዓመት በፊት የተፈፀሙ ነገር ግን ሰሞኑን እንደተደረጉ ተደርጎ እየቀረበ ነው።

እንጠንቀቅ…

ስሜታዊ ሆኖ ሼር ከማድረግ በፊት እነዚህ ምስሎችን በደንብ መመልከት፣ አላማቸው ምን እንደሆነ ማወቅ፣ ከምስሎቹ ጀርባ ለሀገራችን ምን እየታሰበ እንደሆነ መረዳት ሁላችንም ግድ ይለናል።

#ሸገርታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለሰላም_የምችለውን_ሁሉ_አደርጋለሁ!

1ሚሊዮን ተከታይ የለኝም። ቢያንስ እያንዳንዳቸው 1000 ጓደኛ ያላቸው እስከ 5000 ጓደኞች ግን አሉኝ።

#ከዛሬ_ጀምሮ_በሃገሬ_ጉዳይ_ዳር_ቁጭ_ብዬ_ተመልካች_ላለመሆን_ቃል_እገባለሁ

እናንተስ?

#ሰላምለኢትዮጲያ
#PeaceForEthiopia

#ሼር #share
Nagaaf waanan danda'uu hunda nan goodha!!!

Hordoftoota Miliyoona 1 qabaachuu baadhuus hiriyoota hanga 5000 gahaan yoo xiqaatee tokkon tokkon isaani hiriyoota 1000 qaban ni qaba.

#Har'a irraa eggalee dhimma biya koo irratti qarqara taa'ee kanan hinilaalee ta'uu waada nan seena ! !

Isiin hoo?

#NagaaEthiopiafi
#PeaceForEthiopia
#ሠላምለኢትዮጲያ

#share #ሼር
#ንሰላም_ዝኽእሎ_ኹሉ_ክገብር_ድልዊ_እየ!

1,000,000 ተኸተልቲ የብለይን። ብውሑዱ ግን ነን ሕድሕዶም 1000 አዕርኽቲ ዘለዎም 5000 አዕርኽቲ አለዉኒ።

#ካብ_ሎምዓንቲ_ጀሚሩ_ኣብ #ጉዳይ_ዓደይ_አብ_ጸግዒ_ተቀሚጠ_ተመልካቲ_ንዘይምኻን_ወሲነ_ቃል_የአቱ_ኣለኹ

ንስኻ ንስኺ ንስኻትኩም ከ?
#ሰላምንንኢትዮጵያ
#PeaceForEthiopia

#ሼር #share
#UPDATE በአገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 10 ሺህ ዩኒት ደም በመሰብሰብ የበርካቶችን ሕይወት ለመታደግ ታቅዶ ከ11 ሺህ ዩኒት በላይ ደም ለመሰብሰብ መቻሉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቅዱስ ሲኖዶሱ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አደረገ። በውይይቱ ላይ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የኢፌዴሪ ም/ጠቅላይ ሚንስተር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የመከላከያ ሚንስትር አቶ ለማ መገርሣ፣ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል እና በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ በተገኙበት በዝግ ተደርጓል። በውይይቱ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ምክክር መደረጉን ከኢትዮጵያ ኮርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DIREDAWA

መንግስት በድሬዳዋ ከተማ ለተፈጠረው ችግር እጃቸው ያለበትን አካላት ለህግ በማቅረብ የህዝቡን ሰላም በአስተማማኝ መንገድ እንዲጠብቅ ነዋሪዎች ጠየቁ።

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ከነዋሪዎች ወኪሎች፤ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ከኃይማኖት አባቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

በድሬዳዋ ከተማም ሆነ በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች በተፈጠረው ሁከት ለተገደሉት ዜጎች የህሊና ፀሎት በማድረግ በተጀመረው ውይይት ላይ ነዋሪዎቹ ችግሩን የፈጠሩ አካላት በህግ ተጠያቂ ሊደረጉ እንደሚገባ አመልክተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የድሬዳዋ ነዋሪዎች የአንበጣ መንጋ በየአከባቢያችሁ ስታዩ ወዲያውኑ በዚህ ስልክ ቁጥር ደውላችሁ +251251121099 አሳውቁ!
.
.
የአንበጣ መንጋ በድሬዳዋ መከሰቱን የከተማ አስተዳደሩ የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስታወቀ። ከመካከለኛው ምሥራቅ ተነስቶ በየመንና በሶማሌ ላንድ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገባው የአንበጣ መንጋ በድሬደዋ ጃልዴሳ ክላስተር በሚገኙ አምስት ቀበሌዎች መታየቱንም ቢሮው ገልጿል።

በሰዓት ከ60 እስከ 70 እንዲሁም አለፍ ሲል በቀን እስከ 300 ኪሎ ሜትር ሚበረው የበረሃ አንበጣ በኢትዮጵያ በተለያዩ ሞቃታማ ስፍራዎች ላይ በስፋት የተከሰተ መሆኑን እና የዕፀዋት አይነቶች ሙሉ በሙሉ የሚያወድም መሆኑንም ቢሮው ገልጿል። የአንበጣ መንጋው መከሰቱን ተከትሎም የከተማ አስተዳደሩ ከፌደራልና ሌሎች አጎራባች ክልሎች ጋር በመተባበር የመከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-26-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኤልያስ መሰረት ዙሪያ ለሰጣችሁት አስተያየት እናመሰግናለን!

በአዲሱ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ፀሃፊ (የረጅም ጊዜ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰባችን አባል) ዓለም አቀፉ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ዙሪያ ለሰጣችሁት ገንቢ እና አነቃቂ አስተያያየት ከልብ እናመሰግናለን።

ውድ ቤተሰቦቻችን በዚህ #ፈታኝ ወቅት በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳትታለሉ፣ በፈጠራ ወሬዎችም ሀገራችን እንዳትተራመስ የኤልያስ መሰረት አይነት ሀቀኛ፣ ገለልተኛ፣ ፕሮፌሽናል ጋዜጠኛ መረጃዎች እንዲያደርሷቹ እንሰራለን። የወቅቱን ፈተና በጋራ እናልፈው ዘንድ ሌሎች በርካታ ስራዎችን ከናተው ከቤተሰቦቻችን ጋር በመሆን እንሰራለን!! ለአዲሱ የቲክቫህ ፀሃፊ ኤልያስ መሰረት ላሳያችሁት ክብርና ፍቅር ከልብ እናመሰግናለን!! በቀጣይም በህዝብ ዘንድ የሚታመኑ የቤተሰባችን አባል የሆኑ ጋዜጠኞች እንዲሳተፉ እናደርጋለን።
.
.
ውድ የምንወዳችሁ፤ እጅግ በጣም የምናከብራችሁ ስለኢትዮጵያ ስናስብ በናተ ደስ የሚለን ውስጣችንም በተስፋ የሚሞላው ቤተሰቦቻችን ዘወትር ከሀሰተኛ መረጃዎች እንድትርቁልን ሁሉንም መረጃዎች በፍጥነት በዚህ ገፅ ላይ ልናስቀምጥላችሁ ጥረት እናደርጋለን።

እንደ ሁልጊዜው ምንም የምንደብቃችሁ መረጃ አይኖርም ግን በጥንቃቄ፤ ተጨማሪ ችግር በማይፈጥር መልኩ፤ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ እናቀርብላችኃለን! እናተም በማህበራዊ ሚዲያ የምታዩትን ሁሉ ሼር እያደረጋችሁ ሀገራችንን ተጨማሪ ፈተና ውስጥ እንዳትወድቅ እርዱን!!

አስተያየት መቀበያ @tikvahethiopiaBot
የኦሮሞ ህዝብ በትልቅ መስዋዕትነት ያገኘውን ድል በአንድነት መጠበቅ እንዳለበት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጠየቀ!

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ከፍያለው ተፈራ ከOBN ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በክልሉ ተደርገው በነበሩ ሰልፎች ላይ ህዝቡን በብሔርና በሃይማኖት ለማጋጨት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ህዝቡ በትልቅ መስዋዕትነት ያገኘውን ድል በአንድነት መጠበቅ አለበትም ብለዋል ኮሚሽነሩ፡፡ ከሰልፉ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ ክልል 4 ዞኖችና 9 ከተሞች ውስጥ የ67 ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን፣ 213 ሰዎች መቁሰላቸውንና በርካታ ንብረት መውደሙን ኮሚሽነር ከፍያለው ገልጸዋል፡፡

የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ሕግ የጣሱ አካላት በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ኮሚሽኑ እየሰራ መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽነሩ ለኦሮሚያ ሰላም ከፍተኛ መስዋትነት ከፍለው እየሰሩ ላሉ ለክልሉ የጸጥታ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Via OBN/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሰው ልጅ በጣም በቀላሉ በፍቅር መኖር ስንችል ለምን ግን ከባዱን የጥላቻን መንገድ እንደምመርጥ ሳስበው ለምን እያልኩ እገረማለሁ! በፍቅር መኖርን አስባችሁ ታውቃላችሁ? በፍቅር መኖር ማለት እኮ ያለምክንያት፣ ያለገደብ፣ ያለሰአት፣ ሁኔታዎች ሳውስኑ፣ በሰዎች ሳንወሰን ዝምምምም ብለን በደስታ መኖር ማለት እኮ ነው። እስቲ ሁላችንም ወደን እንሞክር ምክንያቱም መቼም ቢሆን ወደን አንክስርም እናተርፋለን እንጂ። በፍቅር ብንኖርባት ይች አለም በእውነት ከገነት በላይ ምቹ ትሆን ነበር።

Via Fitawrari Awoke/Tikvah Family/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BreakingNews

የአይኤስ-አይኤስ መሪው አቡባክር አል-ባግዳዲ ሶሪያ ውስጥ በተደረገ ኦፕሬሽን ሳይገደል እንዳልቀረ ተሰምቷል። አሜሪካ በትላንትናው ዕለት ሶሪያ ውስጥ የISIS መሪውን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ሰንዝራ ነበር።

#CNN

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HAWASSA

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የ9ኙ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና የ2ቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች የተሳተፉበት የሀገሪቱንና ህዝቦቿን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የተዘጋጀ የምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ ተጀምሯል፡፡ የምክክር መድረኩን የከፈቱት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው ጣሰው ያለፈው 2011 በጀት ዓመት እጅግ ውስብስብና አስቸጋሪ እንደነበር ጠቅሰው የፖሊስ ኮሚሽኑ ይህንን ወቅት በጥንካሬ እንዳሳለፈው ገልፀዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አሳዛኝ_ዜና | አርቲስት ጫንያለሁ ወልደጊዮርጊስ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia