የገቢዎች ሚኒስቴር ሀሰተኛ ማንነት ያላቸው፣ ህገ-ወጥ ደረሰኞችን የሚያትሙ እና ለታክስ ህግ ተገዢ ያልሆኑ ያላቸውን 166 ድርጅቶች ዝርዝር ይፋ አድርጓል፦
አጠቃላይ ዝርዝሩን በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/ETH-10-19-2
አጠቃላይ ዝርዝሩን በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/ETH-10-19-2
በትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ...
በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ባንጃ ወረዳ ከእንጂባራ በቅርብ ርቀት የሚገኘው ዘንገና ሀይቅ አካባቢ በተከሰተ የተሽከርካሪ ግጭት አደጋ የሰዎች ህይዎት አልፏል። አደጋው የተከሰተው ከባህር ዳር የተነሳ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስና ከቲሊሊ ወደ እንጂባራ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ የነበረ ሚኒባስ ዛሬ ከጠዋቱ 12:00 ላይ ፊት ለፊት በመጋጨታቸው መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።
የአደጋዉ ምክንያትም እየተጣራ መሆኑን የባንጃ ወረዳ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ዋና ሳጅን ዘመኑ ቅዱስ ገልፀዋል። በአደጋው የሚኒባሱን አሽከርካሪ ጨምሮ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ከሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ አምስት መንገደኞች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ እንጂባራ ሆስፒታል ተወስደዋል ብለዋል ዋና ሳጅን ዘመኑ። በአውቶብሱ ውስጥ የነበሩ ሁሉም መንገደኞች እና አሽከርካሪው ምንም አካላዊ ጉዳት ያልደረሰባቸው መሆኑን አብመድ ዘግቧል።
Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ የግብር ትምህርትን በመደበኛ ትምህርት ተካቶ መሰጠት ይጀምሯል!
የግብር ትምህርትን ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ በስርዓተ ትምህርት ውስጥ አካቶ ለመስጠት የሚያስችል መርሃ-ትምህርት ተዘጋጀ።
ከትምህርት ሚኒስቴርና ከገቢዎች ሚኒስቴር የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የግብር ትምህርትን በመደበኛው ስርዓተ ትምህርት ውስጥ ለማካተት የተዘጋጀውን መርሃ-ትምህርት አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
በመርሃ-ትምህርቱ መሰረት የግብር ትምህርት በአፍ መፍቻና እንግሊዝኛ ቋንቋ፣ በስነዜጋና ስነምግባር፣ በታሪክ፣ ሂሳብ እንዲሁም በአካባቢ ሳይንስ ትምህርቶች ውስጥ ተካቶ እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በተጨማሪም በአጋዥና በተጨማሪ የንባብ መጽሐፍት ውስጥም ተካተው ለተማሪዎች ተደራሽ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
መርሃ ትምህርቱ በግብር ምንነት፣ የግብር ከፋዮች መብትና ግዴታዎች፣ የግብር ማጭበርበርና ስወራ፣ ኮንትሮባንድ እንዲሁም ግብር አጣጣል ጭብጦች በዋና ዋና እንዲሁም በንዑስ ይዘቶች መከፋፈሉ ተጠቁሟል።
Via ENA

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመቐለ ሊካሄድ የነበረ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ!
“ሰብ ሕድሪ ሲቪክ ማሕበረሰብ ትግራይ” የተሰኘው ድርጅት ዛሬ ረፋዱን በመቐለ ከተማ ሊያደርግ የነበረው ሰልፍ በትግራይ ፖሊስ ተበተነ። ሰልፉ ከክልላቸው ውጪ የሚማሩ የትግራይ ተማሪዎች ደህንነትን በተመለከተ የተጠራ ነበር።
የ“ሰብ ሕድሪ ሲቪክ ማሕበረሰብ ትግራይ” ሊቀ መንበር አቶ መሓሪ ዮሐንስ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ እንደገለፁት ሰልፉን ለማድረግ ሁሉንም ቅድመ ዝግጅት አሟልተው የነበረ ቢሆንም ሰልፉ “በክልሉ አድማ በታኝ በኃይል እንዲበተን ተደርጓል” ብለዋል።
በዚህ ጉዳይ ዙርሪያ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት የመቐለ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ “የከተማው አስተዳደር ሰልፍ እንዳያደርጉ አልከለከለም” ሲሉ አስተባብለዋል። “ሰልፉ እንደሚካሄድ የሚያሳውቅ ደብዳቤ አልደረሰንም” ሲሉ ተናግረዋል።
Via DW

TIKVAH-ETHIOPIA
ኢ/ር ታከለ ከስልጣናቸው አይነሱም! @tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከስልጣናቸው አይነሱም...
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማን ለማንሳት እንዳልወሰነ የፓርቲው ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሥልጣናቸው ይነሣሉ የሚሉ መረጃዎች ሰሞኑን ሲናፈሱ እንደነበር ይታወቃል።
Via VOA AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማን ለማንሳት እንዳልወሰነ የፓርቲው ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሥልጣናቸው ይነሣሉ የሚሉ መረጃዎች ሰሞኑን ሲናፈሱ እንደነበር ይታወቃል።
Via VOA AMHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
AMHARA BANK S.C.
በምስረታ ላይ የሚገኘው "አማራ ባንክ" ከግማሽ ቢሊየን ብር በላይ በመሰብሰቡ በህዳር ወር መጨረሻ ባንኩን እውን እንደሚያደርግ አስታወቀ። በ10 ባንኮችና በአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በመሸጥ ላይ የሚገኘውን አክሲዮን ከ15ሺ በላይ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በመግዛታቸው ከ500 ሚሊየን ብር በላይ መገኘቱን መስራች ኮሚቴው አስታውቋል፡፡ 2 ቢሊየን መነሻ ካፒታል ለማድረስ ያቀደው ባንኩ እስከ ባንኩ የምስረታ ጊዜ ህዳር መጨረሻ ድረስ የአክሲዮን ሽያጩ እንሚቀጥል የመስራች ኮሚቴው ሠብሳቢ አቶ መላኩ ፈንታ አስታውቀዋል።

የ'መደመር' መጽሀፍን በሚኒሶታ ለመመረቅ ዝግጅት ተደርጓል!
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተፃፈው የ'መደመር' መጽሀፍ በሚኒሶታ ለመመረቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው። መጽሀፉ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትከተለውን የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ፤ማህበራዊ እና የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ የሚተነትንና ፍኖተ ካርታን የሚያስቀምጥ እንደሆነም ተጠቅሷል። መፅሃፉ በአማርኛ፣አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች ነው የተፃፈው።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተፃፈው የ'መደመር' መጽሀፍ በሚኒሶታ ለመመረቅ ዝግጅት እየተደረገ ነው። መጽሀፉ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትከተለውን የኢኮኖሚ፣ ፖለቲካዊ፤ማህበራዊ እና የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ የሚተነትንና ፍኖተ ካርታን የሚያስቀምጥ እንደሆነም ተጠቅሷል። መፅሃፉ በአማርኛ፣አፋን ኦሮሞ እና እንግሊዘኛ ቋንቋዎች ነው የተፃፈው።
Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
WOLAITA SODO
በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ የተጻፈው ‘’መደመር’’ መጽሐፍ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተመርቋል፡፡
Via SRTA

#JIMMA
ዛሬ በጅማ ከተማ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ የፃፉት "መደመር" መፅሃፍ ተመርቋል። በምርቃት ስነስርዓት ላይ የገቢዎች ሚኒስትር አደነች አቤቤ ተገኝተው ነበር።

🔖እናስተዋዉቅዎ!
⚜️ሺባ⚜️
ሌግዠሪስ -- ለሡ እና ለሷ እቃዎች ከምርጥ አገልግሎት ጋር። ቻናላችንን በመቀላቀል በተመጣጣኝ ዋጋ አግልግሎታችንን ያግኙ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAFfS1CHMcuedhCLPBQ
ማዘዝ ይችሉ 0941158969
💫መልካም ምሽት ይሁንላችሁ--#ETHIOPIA💫

#BONGA
በደቡብ ክልል ካፋ ዞን የዶክተር አብይ አህመድ "መደመር" የተሰኘ መጽሐፍ በዛሬው ዕለት በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል። የተከበሩ አቶ መለስ ዓለሙ የዲሞክራሲ ማዕከል አስተባበሪ ሚኒሲትር ዴእታ እና የቀድሞ የዞኑ አስተዳዳሪ የአሁኑ የደቡብ ክልል በም/ርዕሰ መስተዳድር የመሠረተ ልማት አስተባባሪ እና የመንገድና የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተገኙበት ተመርቋል።
Via ሀብታሙ ኃይሌ ከቦንጋ

አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ከተቀመጠው ደረጃ በታች ናቸው!
በአዲስ አበባ ከሚገኙ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ካሉ ትምህርት ቤቶች አብዛኞቹ ከተቀመጠው ደረጃ በታች መሆናቸውን የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ስልጠና ጥራት የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን አስታወቀ። በተደጋጋሚ ጥራታቸው ከተቀመጠው መስፈርት በታች የሆኑ 51 ትምሀርት ቤቶች ፈቃዳቸው ተሰርዞ እንዲዘጉ ተደርጓል።
ባለስልጣኑ በ2011 ዓ.ም በትምህርት ተቋማቱ ላይ ያደረገውን ምርመራ ይፋ አደርጓል። በዚህም ወቅት የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ እንዳሉት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 1233 የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ላይ የምርመራ ስራ አካሂዷል። ከእነዚህ ውስጥ ደረጃቸውን አሟልተው የተገኙት 24 በመቶ ብቻ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 76 ነጥብ 85 በመቶው በመንግስት ከተቀመጠው ደረጃ በታች መሆናቸውን ገልጸዋል።

Audio
Elias Meseret : የሀሳብ ማዕድ
በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው ሁለተኛው "የሀሳብ ማዕድ" ዝግጅት በስኬት፣ በሰላም ተጠናቋል!
#ከትግራይ
#ከኦሮሚያ
#ከደቡብ
#ከአፋር
#ከአማራ
#ከሱማሌ...የተጋበዙ አክቲቪስቶች እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተፅእኖ የሚፈጥሩ ግለሰቦች ተገኝተው ነበር👏
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ የተካሄደው ሁለተኛው "የሀሳብ ማዕድ" ዝግጅት በስኬት፣ በሰላም ተጠናቋል!
#ከትግራይ
#ከኦሮሚያ
#ከደቡብ
#ከአፋር
#ከአማራ
#ከሱማሌ...የተጋበዙ አክቲቪስቶች እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተፅእኖ የሚፈጥሩ ግለሰቦች ተገኝተው ነበር👏
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስረኞች አመለጡ!
ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዞን አንድ በነፍስ ግድያ ጥፈተኛ ተብለው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የነበሩት 2 ታራሚዎች አሸናፊ መለሰ፤ ሳሙኤል መካ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ. ም ከረፋዱ 3 እስከ 4 ባለው ሰአት ውስጥ ከማረሚያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ያመለጡ ሲሆን፤ ኤፍሬም ገ/ ጊዩርጊስ የተባለ ሌላ እስረኛ ደግሞ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ሲወሰድ ከመኪና ላይ ዘሎ ማምለጡን ተሰማ፡፡
ማረሚያ ቤቱ የሁለቱ የታራሚዎቹን ማምለጥ ማታ በቆጠራ ሰአት እንዳወቀ ዋዜማ ሬድዮ ምንጮቹ እንደገለፁለት ተናግሯል፡፡ ይህን ተከትሎ ማረሚያ ቤቱ በእስረኞች ላይ ቁጥጥሩን ማጥበቁን ተሰምቷል። “እንደሚያመልጡ ታውቁ ነበር” ፣ “ያያችሁት ነገር አለ” በሚል ታራሚዎች ላይ ከፍተኛ ወከባ እየደረሰ እንደሆነ የታራሚ ቤተሰቦች ተናግረዋል። እስረኞች የጣት ቀለበትና የአንገት ሀብልም እንዲያወልቁ መደረጋቸው አግባብ አይደለም ይላሉ።
የእስረኞቹን እንዴት አንዳመለጡ እና አሁንስ በቁጥጥር ስር ውለዋል ወይ? ብለን ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ ወደ ማረሚያ ቤቶች የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ገረመው አያሌው ስልክ የደወልንላቸው ሲሆን ከጠየቅናቸው በኃላ “የማይመች ቦታ ነኝ መልሼ ልደውል” በማለት የእጅ ስልካቸውን ዘግተውታል ፣ በተደጋጋሚ ብንደውልም ሊሰራልን አልቻለም፡፡
ምንጭ፦ ዋዜማ ራዲዮ/Ethio FM.

Tayyip Erdogan
«የሽብርተኞቹን ጭንቅላት ማፍረሳችንን እንቀጥላለን» -- Tayyip Erdogan
.
.
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረቺብ ጣይብ ኤርዶኻን የኩርድ ታጣቂዎች በአሜሪካ አሸማጋይነት ተግባራዊ የሆነው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ከማብቃቱ በፊት ከሰሜን ምሥራቅ የሶርያ ክፍል ለቀው ካልወጡ «ጭንቅላታቸውን እንደሚያፈርሱ» ዛቱ።
ፕሬዝዳንቱ በማዕከላዊ ቱርክ በምትገኘው የካይሴሪ ከተማ ለደጋፊዎቻቸው ባደረጉት ንግግር ለ120 ሰዓታት የሚዘልቀው የተኩስ አቁም ስምምነት ተጨባጭ ለውጥ ካላመጣ አገራቸው የሶርያ ዘመቻዋን ትቀጥላለች ብለዋል።
ከደጋፊዎቻቸው ፊት ቆመው ወታደራዊ ሰላምታ ሲሰጡ የታዩት ኤርዶኻን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ካልዘለቀ «የሽብርተኞቹን ጭንቅላት ማፍረሳችንን እንቀጥላለን» ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ፕሬዝዳንቱ እንዲህ አይነት ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ የዛሬው ሁለተኛቸው ነው።
ለአምስት ቀናት በሚዘልቀው የተኩስ አቁም ስምምነት የኩርድ ታጣቂዎች ከተወሰኑ አካባቢዎች ለቀው እንዲወጡ ቱርክ ትሻለች። ይሁንና በዛሬው ዕለት ሁለቱም ወገኖች የተኩስ አቁሙ ተጥሷል ሲሉ ተወነጃጅለዋል። ቱርክ በኩርዶች የሚመራው እና የሶርያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ተብሎ የሚጠራው ኃይል አገሪቱ ከሶርያ ከምትዋሰንበት 444 ኪሎ ሜትር የድንበር አካባቢ 32 ኪሎ ሜትር እንዲርቁ ትሻለች።

የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ሂደት የህዝቦችን አብሮነት መሰረት ባደረገ መልኩ ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ!
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስዳተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣው መግለጫ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ምርጫ ሂደት የህዝቦችን አብሮነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የደቡብ ክልል በመረጋጋት ላይ እንደሆነ ርዕሰ መስዳተድሩ ገልፀው ክልሉ እንዲረጋጋ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የክልሉ ህዝብና የጸጥታ መዋቅር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣው መግለጫ የመዋቅር ጥቄዎች በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖች መጠየቁን አንስተዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-19-3

#ትዴት
ተቃዋሚው የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ ባካሄደው ውይይት ትግራይ ውስጥ አሁንም አፈና ቀጥሏል አለ። ህዝብን ከድህነት ለማላቀቅ የሚጥሩ ፓርቲዎች በነጻነት መንቀሳቀስ እንዳልቻሉም ገልጿል። የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት) ትግራይ ውስጥ አሁንም አፈና መቀጠሉን እና ህዝቡን ከድህነት ለማላቀቅ የሚጥሩ ፓርቲዎች በነጻነት የመንቀሳቀስ መብት ለውጥ እንዳልታየበት ገለጸ።
“የትግራይ ህዝብ በጠላት ተከብበሃል እየተባለ በህወሓት ሽብር እና ፍርሃት እየተለቀቀበት ለግጭትም እንዲጋበዝ እየተገፋ ነው” ያሉት የትዴት ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ “ችግሩ የጋራ በመሆኑ በትብብር ልንታገለው ይገባል” ሲል በአዲስ አበባው ውይይት ላይ አሳስበዋል። “ህዝቡ ህወሓት እንደሚለው ጠላት የለውም” ሲሉም ለተሳታፊዎቹ ተናግረዋል።
“አብዛኛው የትግራይ ህዝብ ድህነት ውስጥ ነው” ያለው ትዴት በትግራይ ያለው ችግር ተባብሶ በመቀጠሉ “ሕወሃት በቃንየሚለው ህዝብ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል” ብሏል። ተቃዋሚ ፓርቲው በዛሬው የአዲስ አበባ ስብሰባው “ሶሻል ዴሞክራሲ” የፖለቲካ መርህን እንደሚከተል ለደጋፊዎቹ እና ለውይይት ተሳታፊዎቹ አስታውቋል። “ዴሞክራሲ እና ፍትሃዊነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ እንድትገነባም የድርሻዬን እጥራለሁ” ሲል ቃል ገብቷል።
Via የጀርመን ድምፅ ራድዮ