#MEDEMER
በሀላባ ዞን የክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ "መደመር" የተሰኘ መፅሐፍ በዛሬው እለት በደማቅ ስነ-ስረዓት ተመርቋል። መጽሐፉን የደቡብ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሄለን ደበበ እና የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ (የክልሉ ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን እንዲሁም የደኢህዴን ማዕከላዊ ጽ/ቤት ከተማ ዘርፍ ም/ኃላፊ አቶ ታምራት ከሀላባ አባቶች ጋር በጋራ በመሆን በይፋ ያስመረቁ ሲሆን በመድረኩ የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶችና በርካታ የህብረተሰ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
PHOTO: MEHIR/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia

የሀሳብ ማዕድ!
አክቲቪስቶች ለሀገራዊ ጥቅም ምን አስተዋጽኦ ማድረግ እንችላለን?
አቤል ዋቤላ፦
"አክቲቪስቶች አንድ ላይ ብንሆን የፖለቲካ ስለልጣንን መግራት እንችላለን፡፡ ይህም ማለት አንድ ስልጣን ላይ ያለ ሰው ስልጣኑን ሲጠቀም ሁሉም አክቲቪስት በጋራ በመተባበር መኮነንና ስልጣንን በአግባቡ እንዲጠቀም ማስቻል ላይ በጋራ መስራት እንችላለን፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያ ክፍሎች ያሉት ክፍተቶች ሁሉም አክቲቪስቶች ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡ በዚህ መተባበር እንችላለን፡፡"
ታምራት ነገራ፦
"አሁን ያለው ስርዓት ሰዎች የመጨረሻውን ጥግ ይዘው እንዲቆሙና በዛ ትርፋማ እንደሚሆኑ ማሰባቸው ነው፡፡ ብሔራዊ መግባባት የሚባል ነገር የለም ሁሉም ስርዓት ጽንፈኛ የሚያደርግ ነገር ነው ያለው፡፡ ከዛም በላይ ስርዓትና ህግ ማስጠበቅ ወደ ማይቻልበት ሁኔታ እየሄድን ስለሆነ ሰዎች ስለ ጋራ መግባባት ሲያስቡ ተጠቃሚ ሊያደርጋቸው የሚችል ነገር ሳይሆን ስለጎጥ ሲታሰብ ነው ተጠቃሚ እየሆነ ያለው ስለዚህ ስርዓቱ በራሱ ሀገራዊ ተግባቦት እንዲሆን አያስችልም፡፡"
ፍጹም፦
"አዲስ አበባን እንደ ኢትዮጵያ ማሰብ ተገቢ አይደለም፡፡ ወጣ ብለን ማህበረሰቡን እንመልከት ለጋራ ምንቆምበት ነገር ብንቆም መግባባት ይፈጠራል፡፡"
ዶ/ር እንዳለማው፦
"እኩልነት ምንድነው የሰውዓዊ ክብር ምንድነው በነዚህ ነገሮች ላይ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ብንሰብክበት ግንዛቤ ማስጨበጫ መስጠት ቢቻል ቢያንስ በዚህ ላይ በጋራ መስራት እንችላለን፡፡"

የቀጠለ...
ኪያ፦
"ሶሻል ሚዲያው ላይ ላለው አክቲቪስት የፖለቲካ ታሪካችን ውጤት ነው ብዬ ነው ማስበው፡፡ ምን አስተዋጽዖ ማድረግ ችላሉ ለሚለው ግን ብዙ ማድረግ ይችላሉ ባይ ነኝ ተጽዕኖ ፈጣሪነታቸውን ለመልካም ዓላማ መጠቀም ይችላሉ፡፡ የአክቲቪስቶች ስራ ሙሉ ሰዓት መቃወም ብቻ አይመስለኝም ሀገራዊ ስራዎች ላይ ሰላም ላይ መስራት ይቻላል።"
አሁን ላይ የሚታየው የሚዲያና የአክቲቪዝም መደበላለቅ እንዴት ትመለከቱታላችሁ፦
• ሚዲያና አክቲቪዝም መለያየት ያለባቸው ነገሮች ናቸው፡፡ ከአክቲቪዚሙ ይልቅ ለፖለቲካ አቋም ያላቸው አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች በዝተዋል በግሌ ይሄ መሆን አለበት ብዬ አላምንም (ታምራት )
• ፐብሊክ ሚዲያው ነጻ መሆን አለበት፡፡ የመንግስት የአቋም መግለጫ ሙሉውን የሚያነብ ሚዲያ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስብሰባ እንኳን ሳይጠቅስ ያልፋል፡፡ ይህ ትክክል አይደለም፡፡ (ዶ/ር እንዳለማው)
• አሁንም ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ ሚዲያ ኖሮ አያውቅም፡፡ አሁን ላይ የሀሰት ዜናዎችን እያሰራጩ ያሉት የመንግስት ሚዲያዎች ናቸው፡፡ አሁንም ቢሆን ሶሻል ሚዲያውን እንዴት በአግባቡ መጠቀም አለብን በሚለው ላይ ተስፋ ይታየኛል፡፡ (ኤቤል)
• በተለይ ዋና ዋና አክቲቪስቶች ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ከሁሉም ክፍል ያሉ ህዝባችንን እንወክላለን ያሉ ተሰብስበው በፈቃደኝነት ተሰብስበው ለራሳቸው ህግ ቢያወጡ ጥሩ ነው፡፡ በተረፈ ግን እንደ ሀገር ያለንበትን ጉዳይ አልተረዳነውም ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ እያገናዘብን እንቀሳቀስ እንጂ በዲሞክራሲና በፕሬስ ሚዲያ ሩቅ የደረሱ ሀገሮችን እንደ ምሳሌ እየጠቀስን መነቃቀፍ የትም አያደርሰንም። (ኪያ)
• ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ብሔርና እንደ ፖለቲካ የተመሰረተ ሚዲያ እንጂ ነጻ ሚዲያ የለም፡፡ አሁን ላይ ስለ ሚዲያ ማውራት አንችልም። (አልበርቱ ቢጠና)
#ቲክቫህ

#HARAR
በሀረር ከተማ በነበረው የ"መደመር" መፅሃፍ ምርቃ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ተገኝተው ነበር።
PHOTO: Ablity/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀረር ከተማ በነበረው የ"መደመር" መፅሃፍ ምርቃ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አቶ ንጉሱ ጥላሁን እንዲሁም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ተገኝተው ነበር።
PHOTO: Ablity/TIKVAH FAMILY/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀሳብ ማዕድ!
ክፍል ሁለት!
አክቲቪስቶች በጋራ ሆነው የሚመሩበት ህግ በማውጣትና እርስ በእርስ መገማገሚያ መድረክ ቢያመቻቹ ጥቅሙ ምንድን ነው?
• ይህንን ማድረግ የፖለቲካ ስርዓቱ መስተካከል አለበት፡፡ ፖለቲከኞቹ ባለመግባባታቸው ህግ እየተከበረ አይደለም በማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ግጭት የሚፈጥሩ ሰዎች በህግ ተጠያቂ እየሆኑ አደለም ስለዚህ መጀመሪያ ህግ መፍራት ለህግ ተገዢ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ከዛ ይልቅ ግን እንደዚህ አይነት መድረኮች መኖራቸው እርስ በዕርስ ተቀራርቦ ማውራቱ ቀዳሚ መሆን ይኖርበታል። (ዮናታን)
• አክቲቪዝሙ በራሱ በአንድ ወገን ላይ ያነጣጠረ እንጂ ሌላውን ማህበረሰብ ለማካተት አይፈቅዱም፡፡ አሁን ያለው አክቲቪዝም ላይ ያሉ አክቲቪስቶች ቁጭ ብሎ ለማውራት እንኳን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡(በፍቃዱ)
• መጀመሪያ ላይ ችግሩ ላይ መስማማት ያለብን ይመስለኛል በዚህ ላይ ካልተስማማን የራሳችንን ጽንፍ ይዘን እንቀሳቀሳለን እንጂ መግባባት አንችልም፡፡ አቋም እንዳለን እንስማማ አንድ ላይ ቁጭ ብለን ስንደራደር መፍትሔ እንደምናገኝ እንመን ሁላችንም ያገባናል የምንል ከሆነ ሀሳባችንን ለድርድር ማቅረብ አለብን፡፡
• አብዛኛው ሰው ተስፋ የቆረጠ ነው፡፡ ይህ ደግሞ መሸሸጊያ ምሽግ እንዲፈልግ ያደርገዋል፡፡ እንደዚህ አይነት መድረኮች መኖሩ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋ ይሰጣል፡፡(ያሬድ ሹመቴ)
• መሰረታዊ ችግሩን ሳናወራው ስለመፍትሔ ማውራ መፍተሔ አያመጣም፡፡ የጋራ ሀገራዊ ማንነት ላይ መግባባት ያስፈልጋል፡፡ የብሔር ማንነትና ብሔራዊ ማንነትን ማስታረቅ በጣም ያስፈልጋል፡፡ ጥላቻን ማደስ ላይ ተጠምደናል፡፡ (አንሙት)

ለሚመለከታችሁ አካላት፦
ከየረር ወደ ጎሮ በሚወስደው መንገድ ላይ ነዳጅ ጫኝ ቦቴ መኪና ተገልብጦ ከጃክሮስ ጀምሮ እስከ ጎሮ መንገድ ተዘግቷል። #AddisAbeba

#GONDAR | በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተፃፈው "መደመር" መፅሀፍ በጎንደር ከተማ ተመረቀ። በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት፣ ነዋሪዎችና የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Congratulations
የቅዱስ አማኑኤል የአእምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከጎንደር ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በተቀናጀ የክሊኒካልና ህብረተሰብ አቀፍ የአእምሮ ጤና በሁለተኛ ዲግሪ ያስመረቃቸውን 25 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡ ሆስፒታሉ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ተማሪዎቹን ሲያስመርቅ የዘንድሮው ለአስረኛ ግዜ ሲሆን፤ ከ25ቱ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ሶስቱ ሴቶች ናቸው። ሆስፒታሉ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ ከጎንደር ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር በተቀናጀ የክሊኒካልና ህብረተሰብ አቀፍ ጤና ትምህርት ዘርፍ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ የቆየ ሲሆን፤ የዘንድሮዎቹን ጨምሮ የተመራቂዎችን ቁጥር ወደ 245 ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡
Via EPA

የገቢዎች ሚኒስቴር ሀሰተኛ ማንነት ያላቸው፣ ህገ-ወጥ ደረሰኞችን የሚያትሙ እና ለታክስ ህግ ተገዢ ያልሆኑ ያላቸውን 166 ድርጅቶች ዝርዝር ይፋ አድርጓል፦
አጠቃላይ ዝርዝሩን በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/ETH-10-19-2
አጠቃላይ ዝርዝሩን በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/ETH-10-19-2
በትራፊክ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ...
በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ባንጃ ወረዳ ከእንጂባራ በቅርብ ርቀት የሚገኘው ዘንገና ሀይቅ አካባቢ በተከሰተ የተሽከርካሪ ግጭት አደጋ የሰዎች ህይዎት አልፏል። አደጋው የተከሰተው ከባህር ዳር የተነሳ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስና ከቲሊሊ ወደ እንጂባራ አቅጣጫ በመጓዝ ላይ የነበረ ሚኒባስ ዛሬ ከጠዋቱ 12:00 ላይ ፊት ለፊት በመጋጨታቸው መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል።
የአደጋዉ ምክንያትም እየተጣራ መሆኑን የባንጃ ወረዳ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ዋና ሳጅን ዘመኑ ቅዱስ ገልፀዋል። በአደጋው የሚኒባሱን አሽከርካሪ ጨምሮ የ10 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ ከሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ አምስት መንገደኞች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ እንጂባራ ሆስፒታል ተወስደዋል ብለዋል ዋና ሳጅን ዘመኑ። በአውቶብሱ ውስጥ የነበሩ ሁሉም መንገደኞች እና አሽከርካሪው ምንም አካላዊ ጉዳት ያልደረሰባቸው መሆኑን አብመድ ዘግቧል።
Via AMMA

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ትግበራ የግብር ትምህርትን በመደበኛ ትምህርት ተካቶ መሰጠት ይጀምሯል!
የግብር ትምህርትን ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ በስርዓተ ትምህርት ውስጥ አካቶ ለመስጠት የሚያስችል መርሃ-ትምህርት ተዘጋጀ።
ከትምህርት ሚኒስቴርና ከገቢዎች ሚኒስቴር የተውጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የግብር ትምህርትን በመደበኛው ስርዓተ ትምህርት ውስጥ ለማካተት የተዘጋጀውን መርሃ-ትምህርት አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል።
በመርሃ-ትምህርቱ መሰረት የግብር ትምህርት በአፍ መፍቻና እንግሊዝኛ ቋንቋ፣ በስነዜጋና ስነምግባር፣ በታሪክ፣ ሂሳብ እንዲሁም በአካባቢ ሳይንስ ትምህርቶች ውስጥ ተካቶ እንደሚሰጥ ተመላክቷል። በተጨማሪም በአጋዥና በተጨማሪ የንባብ መጽሐፍት ውስጥም ተካተው ለተማሪዎች ተደራሽ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
መርሃ ትምህርቱ በግብር ምንነት፣ የግብር ከፋዮች መብትና ግዴታዎች፣ የግብር ማጭበርበርና ስወራ፣ ኮንትሮባንድ እንዲሁም ግብር አጣጣል ጭብጦች በዋና ዋና እንዲሁም በንዑስ ይዘቶች መከፋፈሉ ተጠቁሟል።
Via ENA

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በመቐለ ሊካሄድ የነበረ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ!
“ሰብ ሕድሪ ሲቪክ ማሕበረሰብ ትግራይ” የተሰኘው ድርጅት ዛሬ ረፋዱን በመቐለ ከተማ ሊያደርግ የነበረው ሰልፍ በትግራይ ፖሊስ ተበተነ። ሰልፉ ከክልላቸው ውጪ የሚማሩ የትግራይ ተማሪዎች ደህንነትን በተመለከተ የተጠራ ነበር።
የ“ሰብ ሕድሪ ሲቪክ ማሕበረሰብ ትግራይ” ሊቀ መንበር አቶ መሓሪ ዮሐንስ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ እንደገለፁት ሰልፉን ለማድረግ ሁሉንም ቅድመ ዝግጅት አሟልተው የነበረ ቢሆንም ሰልፉ “በክልሉ አድማ በታኝ በኃይል እንዲበተን ተደርጓል” ብለዋል።
በዚህ ጉዳይ ዙርሪያ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት የመቐለ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ግንኙነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘመንፈስ ቅዱስ ፍስሃ “የከተማው አስተዳደር ሰልፍ እንዳያደርጉ አልከለከለም” ሲሉ አስተባብለዋል። “ሰልፉ እንደሚካሄድ የሚያሳውቅ ደብዳቤ አልደረሰንም” ሲሉ ተናግረዋል።
Via DW

TIKVAH-ETHIOPIA
ኢ/ር ታከለ ከስልጣናቸው አይነሱም! @tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢ/ር ታከለ ኡማ ከስልጣናቸው አይነሱም...
የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማን ለማንሳት እንዳልወሰነ የፓርቲው ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከሥልጣናቸው ይነሣሉ የሚሉ መረጃዎች ሰሞኑን ሲናፈሱ እንደነበር ይታወቃል።
Via VOA AMHARIC