TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
‹‹ምርጫው የሚካሄድ ከሆነ ሰላም እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን መሥራት ይገባቸዋል፤›› ሜጀር ጄኔራል ዓለም እሸት

ሪፖርተር👇
https://telegra.ph/ETH-10-14

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews

የህዳሴው ግድብ የማመንጨት አቅሙ በ1ሺህ300 ሜጋዋ ዋት ቀነሰ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሐሰት ነው ተባለ። የግብጽና የተለያዩ የአገር ወስጥ መገናኛ ብዙሃን ስለ ህዳሴው ግድብ ያወጡት መረጃ ከእውነት የራቀ እንሆነ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል።

የተቋሙ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳሉት የግድቡ የማመንጨት አቅም እንዲቀንስ ተደርጓል የሚባለው መረጃ ትክክል አይደለም ብለዋል። የግድቡ የማመንጨት አቅም የሚወሰነው ግድቡ በሚይዘው የውሀ መጠን እና ውሀ ከተርባይን ማእከል በሚኖረው ከፍታ ነው ብለዋል አቶ ሞገስ፡፡

የግድቡ ውሀ ከፍታ በጨመረ ቁጥር የተርባኖች የማመንጨት አቅም ከፍ ያደርገዋል እንጂ ተርባይኖች ብዛት የማመንጨት አቅም እንደማይጨምረው ነው ዳይሬክተሩ የነገሩን። አሁን ባለው ሁኔታ የግድቡን የውሀ መጠን የሚቀንስ ስራ ወይም የግድቡን ከፍታ የሚቀንስ ስራ እየተሰራ አይደለም እየተደረገ ያለው የተርባኖች ቁጥር የመቀነስ ስራ ነው ብለዋል፡፡

የተርባይኖች ቁጥር እንዲቀንስ ቢደረግም በማመንጨት አቅሙ ላይ ምንም ተጽእኖ አይኖረውም ምክንያቱም የግድቦች የማመንጨት አቅም የሚወሰነው በተርባይኖች ብዛት ሳይሆን ግድቡ በሚይዘው የውሀ መጠን ስለሆነ ነው ብለዋል፡፡ ከግብጾች አንጻር አሁን የተነሳው ጥያቄ ግድቡ የሚይዘው የውሀ መጠን የግድቡ ከፍታ እንደማይቀንስ ካሁን በፊት የግብጽ ባለሙያዎች እርግጠኛ ነበሩ ስለሆነም ያንን ተከትሎ የተነሳ እንደሆነም ነው አቶ ሞገስ የተናገሩት፡፡ በመሆኑም የህዳሴው ገድብ 6400 ሜጋዋ ዋት እንዲያመነጭ ከዚህ በፊት በታቀደው መሰረት ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#attention የአፋር TIKVAH-ETH ቤተሰቦቻችን፦ በትናንትናው እለት የጁቡቲ ሠርጎ ገብ ታጣቂዎች በአፋር ክልል የአፋምቦ ወረዳ ነዋሪዎች በተኙበት ጨለማን ተገን በማድረግ ጥቃት አድርሰዋል። በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ህፃናት በዱቡቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል። ዛሬ ጥዋት የአፋር አርብቶ አደሮች መልሶ በማጥቃት በከፈቱት ተኩስ ከታጣቂዎቹ በርካታ የፈረንሳይ ጦር…
"የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት ነው"- የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር

“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ወደ አፋር ክልል በመግባት ጉዳት አደረሰ በሚል የሚሰራጨው ወሬ ሐሰት ነው” ሲል የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።

“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዥር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።

በተለያዩ የማሕበራዊ ሚዲዎችና አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን “በአፋር ድንበር በኩል የጅቡቲ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ጉዳት አደረሰ” በሚል የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑም ተገልጿል።

ጅቡቲም ኢትዮጵያን የመውረር ሐሳብ እንደማታራምድና የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጥብቅ መሆኑንም ተናግረዋል። በሁለቱ አገሮች መካከል ለግጭት የሚዳርግ ምንም አይነት ተጨባጭ ምክንያት አለመኖሩን የገለጹት ኮሎኔል ተስፋዬ እየተሰራጨ ያለው መረጃም ትክክል አለመሆኑን አብራርተዋል።

ይሁን እንጂ በአካባቢው አልፎ አልፎ በግጦሽ፣ ውሃና በሌሎች ምክንያቶች የሚከሰቱ ግጭቶች መኖራቸውን አስታውሰው፤ በክልሉ በዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የመከላከያ ሰራዊት በስፍራው ተገኝቶ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ተናግረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SUDAN

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦት የነበረውን የቪዛ አገልግሎት መጀመሩን ገለፀ። በካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መስከረም 25 ባወጣው ማስታወቂያ የቪዛ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦ የነበረ ሲሆን፣ ተቋርጦ የነበረውን የተጓዦች የቪዛ አገልግሎት ረቡዕ መስከረም 28 ቀን መጀመሩን አስታውቋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢያት ጌታቸው ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ የቪዛ አገልግሎት ለመስጠት የሚለጠፉ ስቲከሮች በኤምባሲው በማለቃቸው ለሁለት ተከታተይ ቀናት ቪዛ አገልግሎት ለመስጠት ችግር አጋጥሞ እንደነበር የገለፁ ሲሆን፣ የአገልገሎቱ መቋረጥ በተወሰኑ ተገልጋዮች ላይ እንግልት እና ቅሬታ ፈጥሮ ነበር ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ከኢትዮጵያ ኢምግሬሽን እና ዜግነት ዋና መምሪያ ስቲከሮችን በመውሰድ ረቡዕ መስከረም 28 ቀን አገልግሎቱ እንዲጀመር ተደርጓል። ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን በርካታ ሰዎች እንደሚጓጓዙ የገለጹት ነቢያት፣ የስቲከሮች ማለቅ ከዛ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"የኢትዮጵያ መንግስት ምን እንደሚጠብቅ አልገባንም!" አቶ ጋአስ አህመድ በትላንትናው ዕለት ከጅቡቲ የመጡ ወታደሮች "ኦብኖ" በሚባል አካባቢ ጥቃት ፈፅመው የ16 ሰዎችን ህይወት ማጥፋታቸውን የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድ ለTIKVAH-ETH በላኩት የድምፅ መልዕክት ገልፀዋል። አቶ ጋአስ እንደሚሉት ወታደሮቹ የመጡት ከጅቡቲ ነው፤ ከባድ መሳሪያም የታጠቁ ነበሩ፤ ስልጠናም…
🤔ከቀናት በኃላ በአፋር ስለተገደሉ ዜጎች የመንግስት ሚዲያዎች መዘገብ ጀምረዋል!

#EBC

በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ሜጉ ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች በፈፀሙት ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡ ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ መሆኑን የአፋር ክልል የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አህመድ ኡመድ ለኢቢሲ ተናግረዋል።

በጥቃቱ እስካሁን 16 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከእነዚህም መካከል 3ቱ ህፃናት እና 4ቱ ደግሞ ሴቶች ናቸው ብለዋል። ጥቃቱ በተሸከርካሪ የታገዘ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የሰነድ ማስረጃዎችን ማግኘት እንደተቻለም ነው ም/ል ኮሚሽነሩ የተናገሩት፡፡

በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ህፃናት በዱቡቲ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ተብሏል። የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት መሆኑን አስታውቋል፡፡

“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዦር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ በቦሌ አየር መንገድ ካርጎ ተርሚናል እስካሁን የነበረው የቦይንግ 737 ET 302 የመንገደኞች እና የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ቅሪተ-አካል ዛሬ የDNA እና የForensic ማጣሪያውን ጨርሰው ለተጎጂ ቤተሰቦች በመሸኘት ላይ ነው። Via Signorina solomon/TIKVAH ETH FAMILY/ @tsegabwolde @tikvahethiopia
#ET302

ከወራት በፊት በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ግለሰቦች አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው። የሟቾቹን አስከሬን ለመለየት የዲኤንኤ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፤ የሰባት ወራት ጊዜም ፈጅቷል። በቦሌ አየር ማረፊያ የቤተሰቦቻቸውን፣ የዘመድ ወዳጆቻቸውን አስከሬን ሊወስዱ የመጡ ግለሰቦች በሃዘን ድባብ ውስጥ ነበሩ። ከአደጋው በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ ነው አስከሬናቸውን ማየት የቻሉት። በዛሬው ዕለትም በኬንያ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ግለሰቦች የሃዘን ሥነ ሥርዓትም ይካሄዳል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለስልጣናት እንደተናገሩት መለየት ያልተቻለ አስከሬን እንዲሁም ሌሎች ቁሳቁሶች አደጋው በተከሰተበት አካባቢ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ግለሰቦች በሚሰራው የማስታወሻ ስፍራ የሚቀበር ይሆናል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት
PHOTO: TIKVAH-ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ ወደ ቴፒ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ጅማ ከተማ መዳራሻ ላይ የመገልበጥ አደጋ ደረሰበት። በውስጡ የነበሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት እንደገለፁት በአደጋው የሰው ህይወት ባያልፍም የተጎዱ ሰዎች እንዳሉ ገልፀዋል። በመኪና ውስጥ የነበሩት አብዛኞቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነበሩ። የቤተሰባችን አባላት እንደገለፁት በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሶስት ሰዎች ወደ ጅማ ሆስፒታል ተወስደዋል። ለአደጋው ምክንያት የሆነው በፍጥነት ማሽከርከር ሳይሆን እንዳልቀረ የቤተሰባችን አባላት ገልፀዋል።

አሽከርካሪዎች እባካችሁ እየተጠነቀቃችሁ አሽከርክሩ!

Via Zeyni
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

በአዲስ አበባ ከተማ አስተደዳደር በመንግስት ትምህርት ቤቶች 300 ሺህ ያህል የተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደረገው የምገባ ፕሮግራሙ ተጀመረ፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ የምገባ ፕሮግራሙን በመዲናዋ ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ባሉ ሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች በይፋ አስጀምረዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NAMA

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)ከክልሉ መንግስት ጋር ያለን ትብብር እስከ ውህደት ሊደርስ ይችላል አለ፡፡ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ራድዮ እንደገለጹት ክልሉ በዚህ ሰአት በትብብር መስራትን ይፈልጋል፡፡

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አዴፓ የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ አለመሆኑን የሚያነሱት ዶ/ር ደሳለኝ "የክልሉን ሰላም የማይፈልጉ አካላት የሚፈጥሩት ብጥብጥ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተለያይተን ሳይሆን ተቀራርበን እንድንሰራ የሚያስገድደን ሁኔታን ፈጥሯል" ብለዋል፡፡

"ከአዴፓ ጋር የፖለቲካ ርእዮተ አለም ልዩነት ቢኖረንም የህዝባችንን ደህንነት ለማረጋገጥ ግን መቅረብ ያለብን ደረጃ ድረስ ቀርበን እንሰራለን" ነው ያሉት፡፡ ከመንግስት ጋር የመስራታችሁ ደረጃ እስከ ውህደት አሊያም ጥምረት ድረስ ሊሆን ይችላል ወይ ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር ደሳለኝ ፦ "እኛ ለጊዜው ከአዴፓ ጋር የመዋሃድ ሃሳብ የለንም፤ ነገር ግን የህዝባችን ፍላጎት ከሆነና ጠቃሚ ሆኖ ካገኘነው ልንዋሃድ እንችላለን" ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

ከሰኔ 15 ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በማረፊያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ እና ኮሎኔል ባምላኩ እያንዳንዳቸው በአስር ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ መወሰኑን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡

Via #AMMA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እነጀነራል ተፈራ ማሞ በዋስ ተለቀቁ!

ከሰኔ 15 ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በማረፊያ ቤት ሆነው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩት ብርጋዲዬር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረ እና ኮሎኔል ባምላኩ ዐባይ እያንዳንዳቸው በአስር ሺህ ብር ዋስ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ተለቀቁ፡፡ በሰኔ 15 ጥቃት ተጠርጥረው ጉዳያቸው እየተጣራ በእስር የቆዩት ተጠርጣሪዎቹ ባለፈው ሐሙስ ዋስትና ጠይቀው ነበር፤ መዝገቡን ተመልከቶ ውሳኔ ለመስጠትም ለዛሬ ተቀጥሮ ነበር፡፡

Via AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የአፋር ክልል የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሕመድ ካሎይታ፤ በክልሉ ዞን አንድ፣ አፋንቦ ወረዳ ላይ በአርብቶ አደሮች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መፈፀሙን ይናገራሉ። ጥቃቱም ከጅቡቲ በመጡ ከባድ መሳሪያ በታጠቁ ኃይሎች መፈፀሙንም ያስረዳሉ። በጥቃቱ ሴቶችና ህፃናትም ሰለባ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።" BBC የአማርኛው አገልግሎት
.
.
"የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዥር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።" ENA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AFAR

17 ሰዎች ተገድለዋል የስድስት ወር ህፃንን ጨምሮ ሴቶችና አረጋዊያን ይገኙበታል፤ በ34 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ ደርሷል - አራቱ ከ7 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ሲሆኑ፤ ዘጠኙ ደግሞ ሴቶች ናቸው!

ተጨማሪ ያንብቡ ቢቢሲ አማርኛ👇
https://telegra.ph/ETH-10-14-2
#Sauli_Niinistö

የፊንላንድ ፕሬዚዳንት ሶሊ ኒኒስቶ ከነገ ጀምሮ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ። የ71 ዓመቱ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Addis - global fashion provides only orginal products. We offer quality service and commited to deliver comfort to our clients.
Free delivery is available.

Call us : 0923 29 52 32
Subscribe us on our telegram chanel :
Join👇
https://t.iss.one/addisglobalfashion upgrade your class!

🌟መልካም ምሽት ይሁንላችሁ #ETHIOPIA🌟
የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የደቡብ ሱዳን ማዕቀብ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን አምባሳደር ጆዋና ሮኔካን ዛሬ በጽ/ቤተቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ሁለቱ ወገኖች በነበራቸው ውይይት በደቡብ ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እና በደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የተወሰኑ ሀይሎች ላይ የተጣለው ማዕቅብ አፈፃፀም በተመለከተ ውይይት አድርገዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Vodacom

የዐለም ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያ #ቮዳኮም በኢትዮጵያ ገበያ ለመግባት እያሟሟቀ እንደሆነ ካፒታል አስነብቧል፡፡ የኩባንያው የአፍሪካ መካከለኛው መስራቅና እስያቀ ቀጠና ሃላፊ የመሩት ልዑክ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ቴሌኮም ሃላፊዎች ጋር ተወያይቷል፡፡ የቴሌኮም ገበያ ፍላጎት ዳሰሳም አድርጓል፡፡

Via CAPITAL/wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
5,000,000 ብር

“ሎተሪው ከእግዚአብሔር ለአዲስ አመት የተሰጠኝ ስጦታ ነው” አቶ አለማየሁ

በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክ/ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አለማየሁ አባተ በእንቁጣጣሽ ሎተሪ 2ኛ ዕጣ 5,000,000 ብር ዕድለኛ ሆነው ሽልማታቸውን ተረከቡ፡፡ ዕድለኛው በአንድ የኮንስትራክሽን ድርጅት ተቀጥረው የሚሰሩ ሲሆን ሎተሪ የቆረጡበትን አጋጣሚ ሲጠየቁ “ሎተሪውን የቆረጥሁት ልደታ ቤተክርስቲያን ተሳልሜ ስወጣ ነበር፤ ያየሁትም በተመሳሳይ እዛው ቦታ ልደታ ቤተ ክርስቲያን ተሳልሜ ስወጣ ነበር፤ እንግዲህ እግዚአብሔር ለአዲስ አመት የተሰጠኝ ስጦታ ነው”በማለት ተናግረዋል፡፡ የሽልማት ቼካቸውን ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ም/ዳይሬክር አቶ ሙሉጌታ ታደሰ እጅ ተረክበዋል፡፡

ምንጭ፦ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dr. ABIY AHEMED #SOUTH_SUDAN

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ሱዳን በተካሄደዉ የዕርቅ ምክክር መድረክ ላይ ዛሬ በሱዳን የሽግግር መንግሥት እና የሱዳን ታጣቂዎች ቡድን መካከል የተጀመረዉ የሰላም ድርድር በሁለቱም ወገኖች ሰላም ለማምጣትና ዕርቅ ለማዉረድ ያላቸዉን ፍላጎት ማሳያ ነዉ ብለዋል። ሁለቱም ወገኖች ስምምነት ላይ ደርሰዉ ያላቸዉን አቅም አካታች የሆነችና የበለጸገች ሱዳን ለመገንባት እንዲያተኩሩ ጥሪ አቅርበዋል። ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ ሱዳን የነበራቸዉን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አባል ሀገራት መሪዎች ምክክር መድረክ አገባደዉ አዲስ አበባ ገብተዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Mogadishu | በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ የሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ ትናንትና ማለዳ በመድፍ በመደብደቡ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን በተባበሩት መንግሥታት የሶማሊያ ልዑክ አስታወቀ። የመድፍ ጥይቶቹ ያረፉት በአየር ማረፊያው ውስጥ በሚገኙ የተባበሩት መንግሥታት እና የአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢዎች ውስጥ ነው።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለ30 ሺህ ሠዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው ተባለ!

በመጪው ህዳር ወር ለ30 ሺ ሠዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል። ነፃ የህክምና አገልግሎቱ የሚሰጠው በአዲስ አበባ በሚገኙ የግል የጤና ተቋማት አማካኝነት መሆኑን የአዲስ አበባ የግል ጤና ተቋማት አሰሪዎች ማህበር አስታወቋል፡፡

የማህበሩ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ዳዊት ሞጎስ ለአሐዱ ራድዮ እንደገለፁት የግል ተቋማት ትርፍ ተኮር ብቻ አድርጎ ታሳቢ ማድረጉ ስህተት መሆኑን እና ጎን ለጎን የሚጠበቅባቸውን ማህበራዊ ኃላፊነት መወጣት የሚችሉ መሆናቸውን ለማሳየት ነፃ የህክምና አገልግሎቱ ይሰጣል፡፡

ከህዳር 25 አስከ 28 በሚቆየው ነፃ የህክምና አገልግሎት 30 ሺ ሰዎችን ተደራሽ ለማድረግ መታቀዱንም ነው አቶ ዳዊት ለአሐዱ ራድዮ የተናገሩት፡፡ አገልግሎቱ የሚሰጠው በሚሊንየም አዳራሻ ሲሆን ማንኛውም ዜጋ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላል ተብሏል፡፡ የምርመራ እና የማማከር አገልግሎቶች በመርሃ ግብሩ መካተታቸውንም አቶ ዳዊት ጠቁመዋል፡፡

Via AHADU RADIO
@tsegabwolde @tikvahethiopia