TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
Audio
ወ/ሮ ፅዮን ተክሉ - የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ! #NobelPeacePrize

#TikvahEthiopia
#NobelPeacePrize

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድርስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማት በማግኘታቸው የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላፉ፡፡

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ ለFBC እንደተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ የሰሯቸዉ ስራዎች ከዚህም በላይ ሊያስመሰግኗቸውና ሊያሸልሟቸው የሚችሉ በመሆናቸው ኮርተንባቸዋል ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ትልቅ ሽልማት የኢትዮጵያ ህዝብ አንድ መሆን ነው ያሉት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር በዚህም መላዉ የኢትየጵያ ህዝብ ደስ ሊለው እንደሚገባ ገልፀዋል። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ኡመር ኢድሪስ መልካም ተግባር መስራት ምን ያህል አስፈላጊና ተጽእኖ መፈጥር እንደሚችል ማሳያ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማት ያሳያል ብለዋል።

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጎንደር ዩንቨርሲቲ የፈረንሳይኛ ቋንቋ የስልጠና ማእከል ለመክፈት ከፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር ስምምነት መድረሱን አስታወቀ፡፡ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተማሪዎችን በዲፕሎማ ፕሮግራም ተቀብሎ ለማሰልጠን ተቀማጭነቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆነው የፈረንሳይ ኤምባሲ ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ዩኒቨርስቲው አስታወቋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#MALALA

"የ2019 #የሰላም የኖቤል ሽልማት ተሸላሚ ጠቅላይ ሚኒስተር #AbiyAhmedAli፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያ እና ኤርትራ እርቅ እየሰራችሁ ላላችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ።" -- ፓኪስታናዊቷ ወጣት ማላላ የሱፍዛይ/የ2014 የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸናፊ የ2014 የኖቤል ሰላም ሽልማት አሸናፊ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UAE

የጠቅላይ ሚንስተር ዶክተር አብይ አህመድ ኖቤል ማሸነፍን የUAE ዋና ከተማ #አቡዲያቢ በፌሽታ እያከበረችው ትገኛለች። ማምሻውን #የAdnocGroup ሰማይ ጠቀስ ህንጻን ጨምሮ ሌሎች 'ላንድማርኮች' የኢትዮጵያ ሰንደቃላማ እንዲያንጸባርቁ ተደርገዋል።

Via ELU
PHOTO: SULIMAN DEDEFO

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቡዳቢ የሚገኘው #የAdnocGroup ሰማይ ጠቀስ ህንጻ ማምሻውን በኢትዮጵያ #ሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ ደምቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UAE

በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሱሌይማን ደደፎ በማህበራዊ ገጻቸው ላይ “አቡ ዳቢ የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የኖቤል ሽልማትን እንዲህ እያከበረች ነው” ሲሉ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት የደመቁ የአቡ ዳቢ ህንጻዎቸን የሚያሳዩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለጥፈዋል። በአንዱ ህንጻ ላይ በእንግሊዘኛ “የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህምድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ በመሆነዎ አንኳን ደስ ያልዎ” የሚል መልዕክት ይታያል። የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን እና የልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ዛይድን ምስል የሚያሳይ ፎቶግራፍም በህንጻው ላይ ይታያል።

Via BBC
ምስል፦ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሼር #share

ለማሻሻያ ሥራ የሚቋረጥ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት!

ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ፣ በእህል በረንዳ፣ በአውቶብስ ተራ፣ በአዲስ ከተማ ት/ቤት፣ በገነሜ ት/ቤት፣ በመሳለምያ፣ በእሳት አደጋ፣ በሳንባ ነቀርሳ፣ በአበበ ቢቂላ እስታድየም፣ በታይዋን፣ በሆላንድ ኤምባሲ፣ በፈረንሳይ ኤምባሲ፣ በጉራራ፣ በፊልም ማእከል፣ በራስ ካሳ ክሊኒክ፣ በአቦ ቤ/ክ፣ በእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ፣ በጎፋ ኪዳነ ምህረት፣ በመካኒሳ ቆሬ ኮንደሚኒየም፣ በቆሬ ካምፕ፣ በብስራተ ገብርኤል ፣ በፅዮን ሆቴል፣ በአዲሱ ገበያ፣ በሸጎሌ አንበሳ ሳተላይት ጋራዥ፣ በድሬ ቆዳ እና አካባቢዎቻቸው፣ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ቢሾፍቱ ከተማ/ኡኬ ደንካካ የሚባለው አካባቢ በደረሰው የጦር አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የሁለት አብራሪዎች ህይወት እንዳለፈ ለጉዳዩ ቅርብ ነኝ ያሉ የቤተሰባችን አባል ከቢሾፍቱ መረጃ ሰጥተዋል። Via DIN/TIKVAH ETH FAMILY/ VIDEO: ሮብኤል/TIKVAH ETH FAMILY/ ተጨማሪ መረጃዎች ይፋ ሲደረጉ እናቀርባለን! @tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ

በልምምድ ላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ተከስክሶ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል። አውሮፕላኑ ዛሬ ጠዋት ቢሾፍቱ ከሚገኘው የአየር ሃይል ካምፕ በመነሳት በልምምድ ላይ እያለ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደአ ወረዳ ኡኬ ደንካካ በተሰኘ ቦታ መከስከሱን የምስራቅ ሸዋ ዞን ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አበራ ያሚ ለዶቸ ቨለ አረጋግጠዋል።

በአደጋው የሁለት አብራሪዎች ህይወት ማለፉንም አቶ አበራ ገልጸዋል። ከሟቾች መካከል የአንደኛው አስክሬን አውሮፕላኑ ከተከሰከሰበት ከ100 ሜትር በላይ ርቆ መገኘቱንም ተናግረዋል። የአደጋው መንስኤ ገና በመጣራት ላይ መሆኑንም ነው አቶ አበራ የተናገሩት።

«በደረሰን መረጃ መሰረት የተከሰከሰው አውሮፕላን የጦር መለማመጃ አውሮፕላን ነው። ሁለት ሰዎች በልምምድ ላይ እንደነበሩም ነው ያጣራነው። ከሁለቱ ሰዎች የአንደኛው አስክሬን ሲገኝ የሌላኛው ከአውሮፕላኑ ጋር ቃጠሎ ደርሶበታል። አደጋው የደረሰው ከምሳ ሰአት በፊት ሲሆን እስካሁን የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ነው የምናውቀው» ብለዋል።

Via #DW

PHOTO: TIKVAH-ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዛሬው የጦር አውሮፕላን #በተከሰከሰበት በዚሁ በአደአ ወረዳ፣ ከጥቂት አመታት በፊት በጦር ሂሊኮፕተር ላይ በደረሰ ተመሳሳይ አደጋ የስድስት ሰዎች ህይወት ጠፍቷል። የ157 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የመጋቢት 2011ዱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ የደረሰውም በዚሁ አካባቢ ነበር።

Via የጀርመን ራድዮ
PHOTO: TIKVAH ETH FAMILY

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
UAE #አቡዳቢ በታክሲ ስራ ላይ የተሰማራ ወንድማችንና የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል 'ማሪና ሞል' ያለውን ድባብ በቪድዮ አጋርቶናል!!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Dubai በዱባይ የሚገኘው ሰማይ ጠቀሱ 'ቡርጂ ከሊፋ' ህንፃ የጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድን የኖቤል የሰላም ሽልማት ማሸነፍን አስመልክቶ ከላይ በምታዩት መልኩ ህንፃው ተውቧል! ፎቶውን ያጋራን በአሁን ሰዓት ዱባይ የሚገኝ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የኖቤል የሰላም ሽልማት" በማሸነፋቸው የሀገራችንን ስም በዓለም መድረክ ከማስጠራት ባለፈ 918,000 የአሜሪካ ዶላር በገንዘብ፣ የወርቅ ሜዳልያ እንዲሁም ዲፕሎማ ይሸለማሉ!!

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን ሽልማት በማስመልከት በነገው ዕለት በመላ ኦሮሚያ የደስታ መግለጫ ሰልፎች ይካሄዳሉ!

የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይን የሰላም የኖቤል ሽልማት በማስመልከት በነገው ዕለት በመላ ኦሮሚያ የደስታ መግለጫ ሰልፎች የሚደረጉ መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ። የኦሮሚያ ክልል መንግስትና ሕዝብ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሽልማት በማስመልከትም የደሰታ መግለጫ መልእክት አስተላልፏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን የሰላም የኖቤል ሽልማት በማስመልከት አሁድ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል ዞኖች፣ ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የደስታ መግለጫ ስልፎች ይደረጋሉ ተብሏል።

የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አቶ ዴሬሳ ተረፈ በሰጡት መግለጫ፤ ድሉ የአንድ ሰው ብቻ ሳይሆን የመላው ህዝብ ድል ነው ብለዋል። ይህ ትልቅ እውቅና የተገኘው ሕዝቡ አንድነቱን በማጠናከሩና በመደማመጡ የመጣ ትልቅ ድልም መሆኑን ተናግረዋል። ”ይህ የተገኘው ድል እጥፍ ክብርና ድል ነው” ያሉት አቶ ዴሬሳ የክልሉ ህዝብ ደስታው ከተነገረ ጀምሮ በተለያዩ መልኩ ስሜቱን እየገለጸ ይገኛል ብለዋል።

በተለይ ደግሞ የክልሉ ሕዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ደስታውን ለመግለጽ በተለያየ መልኩ ጥያቄዎችን እያቀረበ ይገኛል ነው ያሉት። የክልሉ መንግስት ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ሕዝቡ በተናበበና በተቀናጀ ሁኔታ ደስታውን እንዲገልፅ ይደረጋል ብለዋል።

ለሰልፉ አስፋለጊው የፀጥታ ጥብቃ ተደርጎለት በቀጣይ እሁድ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የሚካሄድ ይሆናል ነው ያሉት አቶ ዴሬሳ። በቀጣይም የተሻለ ድል እና ውጤት ይገኝ ዘንድ ሕዝቡ አንድነቱን ጠብቆ እንዲሄድም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ፡-ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጂንካ👌

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እየገቡ ይገኛሉ። ነባር ተማሪዎች፣ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ፣ የጂንካ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም የጎርጎቻ 1ኛ ደረጃ፣ የሚለኒዬም 2ኛ ደረጃ፣ የጂንካ 2ኛ ደረጃና የመለስ ዜናዊ መሰናዶ ት/ቤቶች ተማሪዎች መንገድ ዳር ተሰልፈው ጠብቀው በፍቅር ተቀብለዋቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
“ከሽልማቱ ባሻገር የፀረ ሽብር ሕጉን ረቂቅ ላይ ውሳኔ ማሰጠት ይኖርባቸዋል”- አምነስቲ ኢንተርናሽናል
.
.
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድን የኖቤል ሽልማት ምክኒያት በማድረግ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መግለጫ፤ "ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ እ.ኤ.አ በ2018 ዓ.ም ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ለሁለት ዐስርት ዓመታት በኢትዮ ኤርትራ መካከል የነበረውን የድምበር ውዝግብ እልባት በመስጠት ሰላም ማውረድ ችለዋል፡፡ በዚህም ሽልማቱ ተገቢ ነው ብለን እናምናለን፡፡

ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሁን ትልቅ ሥራ ይጠብቃቸዋል፡፡ ይህ ሽልማት በአገሪቱ ላይ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጋሬጣ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት ይበልጥ ሊያበረታታቸው ይገባል፡፡" ይላል።

አያይዞም "በአፋጣኝ ሁኔታም በአገሪቱ ውስጥ እየተፈጠረ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና አለመረጋጋት እንዲሁም የብሄር ግጭቶች እልባት መስጠት ይኖርባቸዋል፡፡" ሲል ማሳሰቢያ ይሰጣል። "መንግሥታቸው በአገሪቱ ውስጥ ጫና ለመፍጠር እንደመሳሪያ እያገለገለ ያለውን የጸረ-ሽብር ህጉ በድጋሚ ረቆ እንዲያፀድቅ እና ከዚህ በፊት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ያደረሱ ተጠርጣሪ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡ ማድረግ ይኖርበታል፡፡"

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-12

@tsegabwolde @tikvahethiopia