TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"እኔ ሰውን አከብራለሁ ነገር ግን እንዲህ መብቴን የሚጥስ ነገር ሲገጥመኝ ከማንም ፈቃድ አልጠይቅም" ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ
.
.
ታዋቂው የኦሮምኛ ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ጎዳና ላይ በመኪና እየተከተሉ ሲሰድቡኝ ነበር ካላቸው ሰዎች ጋር አለመግባባት ውስጥ ገብቶ እንደነበር ተናገረ።

ሃጫሉ ማንነታቸው ካልታወቁ ሰዎች ጋር ሲነጋገርና ሌሎች ሰዎች ደግሞ ለመገላገል ሲጥሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በማሕበራዊ መገናኛ መድረኮች ላይ በስፋት ሲዘዋወር ቆይቷል። ነገሩ የተከሰተው ሜክሲኮ አካባቢ በተለምዶው ኮሜርስ የተባለው ስፍራ ላይ እንደሆነ በተንቀሳቃሽ ምስሉ ላይ ይታያል።

አንዳንዶች ድምጻዊው ጥቃት እንደተፈጸመበት ቢናገሩም በቪዲዮው ላይ እንደሚታየውና እርሱም እንደሚናገረው "ስሜታዊ ከሚያደርጉ" የቃላት ልውውጥ በስተቀር ጉዳት የሚያስከትል ጸብ አልነበረም።

ክስተቱን በሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ድምጻዊው ከመኪናው ወርዶ በሚናገርበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ለመገላገል ሲሞክሩና ሌሎች ሰዎችም በስፍራው ሲሰበሰቡ ይታያል። በተጨማሪም መኪናው የቆመው ሌሎች ተሽከርካሪዎች በሚያልፉበት ቦታ ላይ በመሆኑ መንገድ የተዘጋባቸው መኪኖች የጡሩምባ ድምጽ ይሰማል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-10-2

Via BBC Amharic

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎች ምልመላ ያወጣው ማስታወቂያ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ህዳር 2012 ዓ.ም ለሚያካሂው የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ህዝበ ውሳኔ 6000 የሚሆኑ የህዝበ ውሳኔ አስፈጻሚዎችን በበጎ ፍቃደኝነነት ለአንድ ወር ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውን ና ኮፒ በመያዝ ንፋስ ስልክ ቡና ቦርድ ፊትለፊት በሚገኘው የቦርዱ ማሰልጠኛ ማእከል በአካል በመገኘት ከመስከረም 24 ቀን 2012 ጀምሮ በስራ ሰአት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

• አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
• የማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ያልሆነች
• በትምህርት ዝግጅታቸው በማንኛውም የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ ያለው
• እድሜ ከ20- 45 አመት የሆነች/የሆነ
• በገጠር ቀበሌዎች ተንቀሳቅሰው መስራት የሚችሉ
• የስራ ልምድ አይጠይቅም. ሆኖም በምርጫ አፈጻጸም ዙሪያ ወይም በተለያየ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሳተፉ አመልካቶች ቅድሚያ ይሰጣቸዋል፡፡

ቦርዱ በስራ የሚያሳልፉትን ጊዜ አበል የሚከፍል ሲሆን በተጨማሪም በህዝበ ውሳኔው ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለተሳተፉ አስጻሚዎች የተሳትፎና የእውቅና ምስክር ወረቀት ይሰጣል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንድነት ፓርክ ተመርቋል!

በቤተ መንግስት ግቢ የተሰራው የአንድነት ፓርክ በዛሬው እለት በይፋ ተመርቋል። በፓርኩ ምረቃ ላይም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ፣ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት እና የኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ተወካዮች እና አምባሳደሮች ተገኝተዋል። እንዲሁም የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች እና ምክትል ርእሳነ መስተዳድሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም ተገኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሐምሌ ኤርትራን ሲጎበኙ፣ የውጭ ሚንስቴር ምንም መረጃ እንዳልነበረው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ ባለሥልጣኖቹ ጉብኝቱን እንደ ተራው ዜጋ ከኤርትራ ዜና ምንጮችና ከማኅበራዊ ሜዲያ ነው የሰሙት፡፡ የተቋሙ መገለል፣ የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም አደጋ ላይ ሊልው ይችላል- ብለዋል ስማቸው ያልተጠቀሰ ባለሥልጣን ተናግረዋል፡፡ የዐለም ዐቀፉ ግጭት ተቋም (አይሲጄ) የአፍሪካ ሃላፊ በበኩላቸው፣ ዐቢይ የለውጥ አጀንዳቸውን በተቋማት ካልመሩት መሠረት ሊይዝላቸው አይችልም ሲሉ ተችተዋል፡፡

Via ሮይተርስ/wazema
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትራፊክ አደጋ የሰው ህይወት እየቀጠፈ ነው!

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ፃግብጅ ወረዳ ትናንት ምሽት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ጌጡ መሰለ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው ከሰቆጣ -ፃታ ሸፌሩን ጨምሮ 19 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ ኮድ 3-40474 አ.አ ባለ አንድ ጋቤና ላንድ ክሩዘር መኪና በወረዳው ጅልዋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመገልበጡ ነው።

በደረሰው አደጋም የአሽከርካሪው እና የአንድ ተሳፋሪ ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በ18 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል፡፡ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ስድስት ሰዎችን ጨምሮ ሌሎች ቀላል ጉዳት የደረሰባቸውተሳፋሪዎች በሰቆጣ ከተማ በሚገኘው የተፈራ ሃይሉ መታሰቢያ ሆስፒታልና በፃታ ጤና ጣቢያ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ተደርጓል።

https://telegra.ph/ETH-10-10-3

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba ዛሬ ሐሙስ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ.ም. የተለያዩ የአፍሪካ መሪዎችና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት የተመረቀው የታላቁ ቤተ መንግሥት አንድነት ፓርክ ከፊል ገጽታ በፎቶ፡፡

PHOTO: ዳንኤል ጌታቸው/ሪፖርተር/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ዓለምቀፍ የትግራይ ተወላጆች ንቅናቄ...
#Mekelle | ዓለምቀፍ የትግራይ ተወላጆች ንቅናቄ ለፖለቲካ እስረኞች ተብሎ የተቋቋመ እንቅስቃሴ ለዓለምቀፍ ማኅበረሰብ የሚቀርብ ፊርማ እያሰባሰበ መሆኑ አስታወቀ፡፡ እንቅስቃሴው ከ20 ሺ በላይ ፊርማ በማሰባሰብ "ብበሄራቸው ምክንያት ስለታሰሩ የትግራይ ተወላጆች የፖለቲካ እስረኞች" ያለውን ጉዳይ ለተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንደሚያቀርብ አስታውቋል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤሕግ በበኩሉ በፖለቲካና ብሄር ምክንያት ክስ የተመሰረተበት የትግራይ ተወላጅ የለም ብለዋል፡፡

Via VOA አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Attention

የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ወልድያ/ሃራ ገበያ ባቡር ፕሮጀክት የኃይል አቅርቦት የመንግስትን ትኩረት ይሻል! #ENA #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CBE | የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኘሬዝዳንት ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በትላንትናው ዕለት ከወለድ ነፃ የባንከ አገልግሎት የሚሰጠውን መካ ቅርንጫፍ መርቀው ከፍተዋል፡፡ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ባንኩ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን የሚሰጥ ልዩ ቅርንጫፍ መክፈቱ ለህዝበ ሙስሊሙ ያለውን ከበሬታና የአገልጋይነት ስሜት የሚያሳይ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል፡፡

Via CBE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀድያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ ሰሞኑን የዘነበው ዝናብ ባስከተለው ከፍተኛ ጎርፍ በ14 ቀበሌያት የሚኖሩ 7 መቶ 54 ቤተሰቦች ቤትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ማፈናቀሉን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ አሳወቀ፡፡ የጎርፍ አደጋው ከ 1ሺህ 7 መቶ 22 በላይ ሄክታር መሬት ማሳ የመኸር ሰብልን በማውደም ከ 3 መቶ 5 በላይ እንስሳትን መግደሉን መምሪያው ጨምሮ ገልጿል፡፡ የዞኑ አስተዳደር አደጋው ጉዳት ያደረሰባቸው ቀበሌያትን ተዟዙሮ በመመልከት ችግሩን በጊዜያዊነትና በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው የመንግስት የበላይ አካለት ጋር በመነጋገር በየደረጃው ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁሟል።

Via Sisay Yohannes
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
AudioLab
#Gaas_Ahmed

በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 "ልዩ መረጃ" ላይ የቀረበው መረጃ የተሳሳተ ስለሆነ ሊታርም ይገባል ሲሉ የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድ ለTIKVAH-ETH ተናግረዋል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ጋአስ አህመድ ለTIKVAH-ETH በላኩት የድምፅ መልዕክት ተከታዩን ብለዋል፦

"በሬድዮ ጣቢያው የተሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም፤ ሶስቱ ከተማ የሚባሉት በሱማሌ ክልል ቁጥጥር ስር የነበሩ አልነበሩም፤ የconflict ዞኖች ሲመሰረቱ አመሰራረታቸው ከኮብትሮባንድ ጋር የተያያዘ ስልነበር በሁለቱም በኩል እንዳይተዳደሩና ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በራሱ የኮንትሮባንድ ከተማ ሆኖ የቆየ ነው። በኃላ ውሳኔ ሲሰጥ ወደአፋር የተካለሉ እንጂ በሱማሌ ክልል ስር ሆኖ ሲተዳደሩ ነበሩ አይደሉም። ሌላው ደግሞ የአፋር ኃይሎች የሱማሌ ክልልን ዘልቀው በመግባት ጥቃት ፈፅመዋል የሚለውም ከእውነት የራቀ ነው። ግጭቱ ያለበት አካባቢ እራሱ አፋር አካባቢ ነው፤ ቦታውም ከሱማሌ ክልል ወደ 300 ኪሎሜትር ወደአፋር ውስጥ ገብቶ ነው። ስለዚህ መረጃው የአንድ ወገን ብቻ በመሆኑ ሊታረም ይገባዋል። የአንድ ወገንን ድምፅ ብቻ ይዞ እንዲህ ያለ ፕሮፖጋንድ መስጠት ተገቢ አይደለም። ይሄ ለሁለቱም ህዝቦች መፍትሄ ሊሆን አይችልም።"

አቶ ጋአስ አህመድ ለTIKVAH-ETH ጨምረው እንደገለፁት በአፋር ክልል በሚገኙ አርብቶ አደሮች ላይ ጥቃት እየተፈፀመ ያለው ከተለያዩ አካላት ስለመሆኑ የቪድዮ መረጃ ጭምር አለን ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከተናገሩት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፦

• የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዝምድና ውክልና እስከመሰጣጠት የደረሰ ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ!

• ባቀረብንላችሁ ጥሪ መሰረት የ5 ሚሊዮን ብሩን እራት የታደማችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን እንኳን በሰላም መጣችሁ

• የ5 ሚሊዮን ብሩን እራት እንዲደገም በርካቶች ጥሪ ቢያቀርቡም እራቱ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገ በመሆኑ እንደማይደገም አረጋግጠዋል

• በፕሮጀክቱ ቀን ከለሊት በመስራት ማጠናቀቅ የቻሉ ኢትዮጵያውያንም እንኳን ደስ አላችሁ ተብሏል

• እኛ ኢትዮጵያውያን ታሪክ አለን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ዱካችን በባህርም ሆነ በሰማይ ይታያል

• ስልጣኔ የተከማቸ የእውቀት ጥበብ ነው፣ ስልጣኔ ሳያቋርጥ እንደሚፈስ ጅረት ነው

• አባቶቻችን ጥፋት ቢሰሩም ከነሱ ጥፋት ተምረን አባቶቻችን አንድ አድርገው ያሳለፉልንን አገር አንድ አድርገን ማሻገር ግዴታ እንዳለብን ያሳያል

• ልጆቻችን ቤተመንግስት ፎቶ የማይነሳ የሚያስፈራ ስፍራ ሳይሆን፣ በመገዳደል ብቻ የሚገባበት ሳይሆን የሚጎበኝ ስፍራ መሆኑንም ለማሳየት የሚስችል ስፍራ ነው

• በአዲስ አበባ ከአፍሪካ ትልቁን ፓርክ እንገነባለን

• ይህንን ለማሳካት የሚያቆመን አንዳችም ሀይል የለም

• በዚህ ቤተመንህግስት ርካታ አስደናቂ ግብዣዎች ተደርገዋል በርካቶችም አድንቀውት አልፈዋል

• ዛሬ ለመላ ኢትዮጵያውያን መናገር የምፈልገው እኛ እንቀጥላለን ታሪክን ከዛሬ ጋር ለነገ በሚበጅ መልኩ አስተሳስረን እንቀጥላለን

• የሚያግዘን ካገኘን የወሩን በሳምንት የሳምንቱንም በእለት እንጨርሳለን

• ጨርሰን ሪባን እንቆርጣለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Nobel Peace Prize 2019

ዶክተር አብይ ከ16 አመቷ ታዳጊ ብርቱ ፉክክር ገጥሟቸዋል!

የዘንድሮው የአለም የሰላም ሽልማት(ኖቤል ሽልማት) አሸናፊ ማን ይሆን ? የሚለው ቅድመ ግምት የበርካታ ምእራባዊያን ሚዲያዎችን እና የቁመራ ድርጅቶችን እያነጋገር፣እና የውድድር ገበያቸውንም እያሟሟቀላቸው ይገኛል።

ታዲያ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት በሚጠበቀው አመታዊው የኖቤል ሽልማት ዋንኛ እጩ ተወዳዳሪዎች መካከል ከሰባ ሺህ በላይ ነፍሳት የጠፋበት እና ዳግም ውጥረት የነገሰበት የኢትዬ- ኤርትራ ወታደራዊ ፍጥጫን በሰላማዊ መንገድ እንዲቆም ግንባር ቀደም ሚና እንደተጫወቱ የሚነገርላቸው የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ እንዱ ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-10-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia