TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአለም ባንክ ጋር በመተባበር ያስጠናው የብሄራዊ መሰረተ ልማት ማሻሻያ ፕሮጀክት ላይ ነገ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ያካሂዳል፡፡#ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EthioTelecom

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ የሚገኙና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ አንድ መቶ ሴቶችን በፋሽን ዲዛይን ለማሰልጠን የሚረዳ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ፡፡ ተቋሙ ዜጎችን በመደገፍ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነም ገልጿል፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በተጓዳኝ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት እድሎችን ባለማግኘት በብዙ ችግሮች ውስጥ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎችን የመደገፍ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡

Via AMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
አቶ ፍሰሃ ተክሌ በአሚኒስት ኢንተርናሽናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ተመራማሪ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው አጭር ቆይታ በተለምዶ ጥላቻ ንግግር በምንለውና በአለም አቀፉ ህግ ላይ እንደተቀመጠው ደግሞ ጥቃትን ወይም አድሎን የሚቀሰቅሱ ንግግሮችን በሚመለከት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አቶ ፍሰሃ እንደገለጹት ከሆነ የጥላቻ ንግግር ላይ የሚደረጉ ገደቦች ብሄራዊ ደህንነትን በማረጋገጥ ላይ ያተኮረ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡ እንደ አቶ ፍስሃ አገላለፅ አድሎን/ጥቃትን የሚቀሰቅስ ንግግር በህግ ብቻ የምንታገለው ሳይሆን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ እኩልነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡

ሙሉውን መልዕክት ከላይ ያዳምጡ!

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

በመጪው አርብ ኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በሚከናወነው የ2019 "የሰላም ኖቤል ሽልማት" አሰጣጥ ላይ ያሸንፋሉ ተብለው የተገመቱ ሰዎች ስም እየወጣ ይገኛል። Associated Press እንደዘገበው ከሆነ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ፣ የኒውዘርላንድ ጠ/ሚ ጀሲንዳ አርደን፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱት ውስጥ ይገኙበታል። ነገር ግን የአየር ለውጥ አክቲቪስቷ ስውዲናዊቷ ታዳጊ ግሬታ ተንበርግ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷታል።

ሙሉውን ከላይ ያዳምጡ!

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

ሰኔ 15 ጀነራል ሰአረ መኮንን ላይ ግድያ እንደፈፀመ የተጠረጠረው ጠባቂ መንቀሳቀስ እና መናገር ጀምሯል!

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


በአሁን ወቅት የግልም ሆነ የመንግስት ሚዲያዎች ሽፋን ያልሰጡትና ያልዘገቡትን የአፋርና የሱማሌ ክልል አጎራባች ስፍራዎች ላይ ያለውን ችግር የAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ከተለያዩ አካላት ማጣራት አድርጎ ያገኘውን መረጃ ለህዝብ አካፍሏል።

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአትፓ ስም ጥፋት ቢፈፀም ተጠያቂ አይደለንም – የ”ፓርቲው” አመራሮችና አባላት!

ነባር አባላቱን ባገለለውና ህገወጥ በሆነው የአዲስ ትውልድ ፓርቲ ስም ጥፋት ቢፈፀም ተጠያቂ እንደማይሆኑ የፓርቲው የማዕከላዊ ምክር ቤት የቀድሞ አባላትና አመራሮች አስታወቁ።

የፓርቲው ፕሬዚዳነት አቶ ሰለሞን ታፈሰ በበኩላቸው ቅሬታው ለፓርቲው ህልውና የማይቆረቆሩ አባላት ስሜን ለማጥፋት ያደረጉት ነው ብለዋል።

የአዲስ ትውልድ ፓርቲ /አትፓ/ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አስፋው ጌታቸው በ2007 ዓ.ም ወደ አሜሪካ ካቀኑ በኋላ በፓርቲው ውስጥ ሁለት ቡድን ተፈጥሮ ውዝግብ ውስጥ ገብቷል።

በአሁኑ ወቅት አቶ ሰለሞን ታፈሰ ፓርቲውን በፕሬዚዳንትነት እያንቀሳቀሱ ሲሆን የቀድሞው ጠቅላላ ጉባኤ አባላትና በአመራር ላይ የነበሩ አባላት ግን ፓርቲው ህጋዊ አይደለም ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-09-4

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጥቂት ሰአት በፊት በአንፈራራ አካባቢ አሳዛኝ የመኪና አደጋ ደረሷል!

ከአዲስ አበባ ተነስቶ ወደ ሻኪሶ ሲጓዝ የነበረ TATA ባስ #አዶላ (ክብረ መንግስት) ከመድረሱ በፊት አንፈራራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተገልብጦ ከፍተኛ አደጋ ደርሷል፡፡ በስፍራው የነበሩ የቤተሰባችን አባላት በአደጋው የሰዎች ህይወት እንዳለፈ ግልፀዋል። በርካቶች ላይም ጉዳት ደርሶ ወደ አዶላ ሆስፒታል ተወስደዋል፡፡

Via አስቹ ከአዶላ/TIKVAH-ETH/

ተጨማሪ መረጃ ይኖረናል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የአንዱ ህመም ሌላውንም ሊሰማው ይገባል፡፡ ይህ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያስተማሩን የሰብዓዊነት፤ የመደጋገፍ እና ችግርን በደቦ የማሸነፍ መልካም እሴታችን ነው፡፡ ሁላችንም የሀገራችን ባለቤቶች ነን፡፡ ምትክ ለሌላት ሀገራችን ዕውቀታችንን፣ ጉልበታችንን፣ ሀብታችንን እና ቀና ልቡናችንን ሁሉ ይዘን እንነሳ፡፡” (ክብርት ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ - የሕዝብ ተወካዮችና የፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab

ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


#FactCheck

የAvoxx Travel Agency ጉዳይ!

- በመጀመርያ እንደ ጋዜጠኛ ሳይሆን እንደ አንድ አገልግሎት ፈላጊ በመሆን የሄድኩት ቄራ ወደሚገኘው የኤጀንሲው ቢሮ ነበር። በቢሮው ሰራተኞች እንደተነገረኝ ውጭ ሀገር (በተለይ ካናዳ እና አሜሪካ) ለትምህርት እና ለስራ ለሚሄዱ ሰዎች ድርጅቱ ዩኒቨርሲቲዎችን እና አሰሪዎችን መፈለግ፣ ከዛ Apply ማድረግ በመጨረሻም የኤምባሲ ማማከር ስራ ይሰራል። ለዚህም ገንዘብ ይቀበላል፣ ካናዳ እና አሜሪካ ከሆነ ቅድመ ክፍያው 10,000 ብር ሲሆን ስራው ወይም ትምህርቱ ከተሳካ ደግሞ ቀሪው 120,000 ብር ይከፈላቸዋል።
.
.
ከላይ ባለው የድምፅ ፋይል ሙሉውን ያዳምጡ!

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEW

•ለራያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች አቀባበል ተደረጎላቸዋል።

•የጅማ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎቹ የሚገቡበት ቀንን ይፋ አድርጓል።

•የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ ዓመት ተማሪዎች ቅሬታ

•ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎቹን መቀበል ጀምሯል

•የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት የሚጠበቅበትን ውጤታማ ስራ አላከናወነም ተብሏል።

•አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአገር ውስጥ ባሻገር በምስራቅ አፍሪካም የልህቀት ማዕከል ለመሆን ፖሊሲዎችን ነድፎ እየተገበረ መሆኑን ገልጿል።

•የወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች መግቢያ ይፋ ተደርጓል።

•የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎችን አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃዎችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ጉዳዮችን በTIKVAH-MAGAZINE መከታተል ትችላላችሁ!

Join👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

@tikvahethmagazine
ወደከፋ ጦርነት እንዳያመራ ተሰግቷል!

የቱርክ ወታደሮች በሰሜናዊ ሶሪያ ዘመቻ ጀምረዋል፤ ይህም በአሜሪካ ከሚደገፈው የኩርዲሽ መር ጦር ጋር ወደ ከፋ ጦርነት ሊያመራ እንደሚችል ተሰግቷል፡፡ የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ጅማሮውን ‹‹ሠላማዊ ቀጣና የመፍጠር ዘመቻ›› ብለውታል፡፡

በዘመቻውም የኩርድ ታጣቂዎችን ከቀጣናው ለመደምሰስ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡ በኩርዶች የሚመራው የሶሪያ ዴሞክራሲያዊ ኃይልም ንጹኃን በቱርክ የአየር ጥቃት እየተፈጸመባቸው እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአወዛጋቢ ሁኔታ ወታደሮቻቸውን ከሰሜን ሶሪያ ማስወጣታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ትራምፕ ወታደሮቻቸውን ከአካባቢው ያስወጡት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከኤርዶሃን ጋር በስልክ ከተነጋገሩ በኋላ መሆኑ ደግሞ ትችት እያስከተለባቸው ነው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ/አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ንቁ!

በፎቶው የምትመለከቱት ሩዋንዳ ኪጋሊ ውስጥ የሚገኘውን "የኪጋሊ የዘር ማጥፋት መታሰቢያ ሙዚየም" ነው። ይህን ለሰው ልጆች ሁሉ ትልቅ ትምህርት የሚሰጥን ሙዚየም የጎበኘ አንድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ይህን ብሏል፦

"ይህ ለኛ ትልቅ ትምህርት ይሁነን፤ ጆሮ ያለው ይስማ፤ ልብ ያለው ልብ ይበል። ይሄ ታሪክ ተደግሞ ተገዳድለው አለቁ የሚባል ሙዝየም ለማሰራት አንደርደር። በአንድነት እና በፍቅር ስለመኖራችን ለልጆቻችን ሃውልት እናቁም!"

#ሼር #share

PHOTO: D/TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሡዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ!

የሡዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ አምዶክ ዛሬ ረፋዱ ላይ አዲስ አበባ ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላህ በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ እና ከሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ እንዲሁም የአንድነት ፓርክ ምረቃ ስነስርዓት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GELAN

በኦሮሚያ ልዩ ዞን ገላን ከተማ በ42 ሚሊዮን ብር የተገነባ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተመረቀ፡፡ ፋብሪካው በኦሮሚያ ግብርና ኅብረት ሥራ ማኅበራት ፌዴሬሽን የተገነባ ነው፡፡ በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የፌደራል እና የክልሉ የሥራ ሓላፊዎች ተገኝተዋል።

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia