TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ የጤና ሁኔታ!

ሰኔ 15 ጀነራል ሰአረ መኮንን ላይ ግድያ እንደፈፀመ የተጠረጠረው ጠባቂ መንቀሳቀስ እና መናገር እንደጀመረ ተሰማ። ግለሰቡ በአሁን ሰአት በአራት የፌደራል እና አራት መከላከያ አባላት ጥበቃ ተደርጎለት ህክምና እየተከታተለ ነው ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪ ግለሰቡ በግድያው ቀን በነበረው ተኩስ አንድ አይኑን አጥቷል። አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ የተባለው ይህ የጀነራሉ ጠባቂ ሰኔ 15 ግድያውን እንደፈፀመ ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዳለ ይታወቃል። የመንግስት አካላትም በወቅቱ ይህ ግለሰብ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ሰንዝሮ ነገር ግን ቆስሎ በህይወት እንደተረፈ በወቅቱ ገልፀው ነበር። ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ በጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በኩል የተጠየቀው የፌደራል ፖሊስ ፤አሁን ላይ ምንም ተጨማሪ መረጃ እንደሌለው፣ ሲኖር ግን ለህዝብ ይፋ እንደሚገረግ ገልጿል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/AP/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በሶማሌ ክልል የዋቢ ሸበሌ እና ሌሎች ወንዞች ሞልተው ባስከተሉት የጎርፍ አደጋ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ማስታወቂያ ቢሮ አስታወቀ። ጉዳቱ ሊደርስ የቻለው በክልሉ ካለፈው ሀሙስ ጀምሮ እየጣለ ባለው ዝናብ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ባሌና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች ከፍታ ቦታዎች ላይ ተነስተው ወደ ሶማሌ ክልሉ የሚፈሱ ወንዞች ሞልተው በመፍሰሳቸው መሆኑ ተገልጿል።

የክልሉ ማስታወቂያ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወይዘሮ ሂቦ አህመድ ጉዳዩን አስመልክተው ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። በእዚህም የሰባት ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ የንብረት ጉዳትም መድረሱን ነው የገለጹት። ከእዚህ በተጨማሪ በፈፋን ዞን በደረሰ የጎርፍ አደጋ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን ወይዘሮ ሂቦ ተናግረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

#የተሳሳተ_ዜና_ጥቆማ - #MisinformationAlert
ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፓለቲካ ፓርቲዎች ሊያደርጉት የነበረው ውይይት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ” በሚል ርእስ በኢትዮጵያ ብርድካስቲንግ ኮርፓሬሽን ፌስቡክ ገጽ የተዘገበው ዜና የተሳሳተ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለማሳወቅ ይወዳል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዛሬ እለት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያደረገው ምንም አይነት ውይይትም ሆነ ድርድር ያላደረገ ሲሆን የኢቢሲም ሆነ የኢቢሲን ዜና መሰረት በማድረግ የዘገቡ ሌሎች ሚዲያዎች ዜናዎችን ከማሰራጨታቸው በፊት ማጣራት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያሳስባል፡፡ ቦርዱ ማንኛውንም የመረጃ ጥያቄዎች ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ ይወዳል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
ረዳት ፕሮፌሰር አበበ አሰፋ  በኢትዮጵያ የህግ ትምህርት ቤቶች ህብረት ሰብሳቢ እና በጎንደር ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ቤት ዲን ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ያደረጉት ቆይታ!

- የህግ ተማሪዎችና መምህራን ስለ ፍትህና ስለ ዲሞክራሲ የተሻለ ግንዛቤ አላቸው!

- ወጣቶች በምርጫ እንዲሳተፉ የህግ መምህራንና ተማሪዎች ያላቸውን ግንዛቤ ለሌሎች ጓደኞቻቸው እንዲያስተላልፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvagethiopia
Audio
ፕሮፌሰር ኢታሂሩ ጄጋ የቀድሞ የናይጄሪያ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ሊቀ-መንበር የነበሩ ሲሆን በአምስት አመታት ውስጥ በሀገራቸው የተደረጉ ሁለት ምርጫዎችን በበላይነት መርተው የተሻለ አፈጻጸም አስመዝግበዋል፡፡ በኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አዘጋጅነትና በ USAID ድጋፍ "አገራዊ ምርጫና የምርጫ ባለድርሻ አካላት ሚና" በሚል ርዕስ በተዘጋጀው አለማቀፍ ኮንፍረንስ ላይ በመገኘት በምርጫ ኮሚሽን ሰብሳቢነት ወቅት የነበራቸውን ተሞክሮ ለተሳታፊዎቹ አቅርበዋል፡፡ ፕ/ር ኢታሂሩ ጄጋን ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸውም ቆይታ ትክክለኛ እና ታማኝ ምርጫ ለማካሄድ ይረዳል ያሉትን ሀሳብና ወጣቶችን ያማከለ የምርጫ ስራ አስፈላጊነት ላይ አጭር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

"ሀገራዊ ምርጫ እና የምርጫ ባለድርሻ አካላት ሚና!" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የአለማቀፍ ኮንፍረንስ በከሰዓቱ መርኃግብር የምርጫ ቦርድ አባላትና ስራ አስፈጻሚዎች በአጠቃላይ ቦርዱ የሰራቸውን ስራ አብራርተዋል፡፡ እንደ ዶ/ር ጌታሁን ካሳ ገለጻ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ቦርዱ ካከናወናቸው ቁልፍ ተግባራት አንዱ ሲሆን ይህ 164 አንቀጾችን ያካተተው የምርጫ አዋጅ ምርጫን በተመለከተ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎችን በተመለከተ፣ የስነምግባር ህግና በምርጫ የሚነሱ አለመግባባቶች የሚፈቱበትን አራት ክፍሎችን የያዘ ነው ብለዋል፡፡

ዶክተር ጌታሁን አክለውም ይህ አዋጅ ከ35-40 የሚሆኑ ዝርዝር መመሪያዎች እንዲወጡ የሚያዝ ሲሆን አሁን ላይ ህዝበ ውሳኔን በተመለከተ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች ፋይናንስ፣ የምርጫ ፓርቲዎች አደረጃጀትን ጨምሮ 7 ረቂቅ መመሪያዎችን ቅድሚያ ሰጥተን በማጠናቀቅ በቅርቡ ለምክክር እናቀርባቸዋለን ቀሪዎቹን እስከ ጥር ድረስ ለማጠናቀቅ አቅደናል ያሉ ሲሆን በምርጫ ወቅት የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ፣ የፓለቲካ ፓርቲዎች መድረክ፣ የምርጫ ቦርድ የሚያዋቅራቸው ገለልተኛ የባለሞያዎች ቡድን፣ ምርጫ ቦርድ በራሱ እስከታች ያለው መዋቅርና ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

ወ/ሮ ብዙወርቅ ከተተ በዛሬው መድረክ ላይ እንደገለጹት እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ የምርጫ ቦርድን መዋቅር ማጥናት፣ የሰው ኃይል ፍላጎት እቅድ እና ምዘና ላይ ከኢትዮጵያ ማኔጅመንት ኢንስቲቲውት ጋር በመተባበር ጥናት አስጠንቶ ወደ ተግባር ለመግባት ቅድመ ዝግጅት ላይ እንዳሉና እስካሁንም የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ባለመኖሩ ቦርዱ ተጨማሪ ስራዎችን ለመስራት መገደዱን ጠቅሰዋል፡፡ ይህ ችግርም ተለይቶ በቅርቡ ቅጥሩ ይፈጸማል ብለዋል፡፡ የክልል ቢሮ ኃላፊ ለመቅጠር ግልጽ ማስታወቂያ አውጥተናል ያሉት ወ/ሮ ብዙወርቅ በቅርቡም ለዚሁ ጉዳይ የቦርድ አባላቱ ወደ 5 ክልሎች እንደሚጓዙ የጠቀሱ ሲሆን በክልል በሚኖሩን ቅጥሮች ላይ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ ይህም በክልል ቢሮ ኃላፊነት የሚመረጠው ሰው ከፓለቲካ ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡በዚህ ገለጻቸው ላይ የጠቀሱት ሌላው ጉዳይ የምርጫ ቦርድ ድረ-ገጽና አርማ የሚመለከት ሲሆን ማሻሻያዎች እንደሚደረጉና በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል ዓዲ ዳዕሮ ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች በዜጎች ላይ በደል ፈፅሟል ያሉት ኃላፊ “ከሕግ አግባብ ውጪ በዋስ ተለቋል” ሲሉ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ወጡ።

በሰሜን ምዕራብ ዞን የላይኛው አድያቦ ወረዳ ዓዲ ዳዕሮ ከተማ የሚገኙ ቁጥራቸው ወደ 15 ሺሕ የሚገመቱ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን የሚገልፁበት መፈክር ይዘው፤ ስሙን ለይተው በጠቀሱት አንድ የወረዳ አመራር ሳጅን አማካኝነት በዜጎች ላይ ደረሰ ያሉትን በደል በመዘርዘር ድምፃቸውን አሰምተዋል።

በሰልፉ ላይ የተሳተፉት ስለ ተቃውሞው ምክኒያት ሲናገሩ፤ በመንግሥት የሥራ ኃላፊነት ላይ የሚገኘው ግለሰብ ፤ በተለይ ቁጥራቸው ለጊዜ ያልተረጋገጠ ነገር ግን ከአስር በላይ የሆኑ ባለትዳር ሴቶችን በመድፈር በሴቶች ላይ ባደረሰው ተደጋጋሚ ጥቃት ምክኒያት ግምገማ ቀርቦበት ነበር።

በግምገማው ላይም ጉዳቱ ደርሶብናል ያሉ ሴቶች ፊት ለፊት እየተነሱ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተው ነበር። ከሴቶቹ በተጨማሪም በሐሰት በማስመስከር ወንዶች ያለ አግባብ እንዲታሠሩ አድርጓል በሚል ሰልፈኞቹ አቤቱታ አሰምተዋል። ከዚህ ግምገማ በኋላ ግለሰቡ እንዲታሰር ቢደረግም ብዙም ሳይቆይ ወዲያውኑ በዋስ እንዲፈታ መደረጉ ቁጣን ቀስቅሷል ብለዋል - የሰልፉ አስተባባሪዎች።

በሰልፉ ላይ ተሳታፊ ከነበሩት አንዱ ሌተናል ኮረኔል መኮንን አማረ ለአሜሪካ ድምፅ ስለ ሰልፉ ዓላማ ሲያስረዱ፤ “ኅብረተሰቡ በተለይ በሴቶች ላይ የደረሰውን በደል ተቃውሞ ድምፃችን ይሰማ ሲል ነው አደባባይ የወጣው” ብለዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ድንገት ነገሮች ተቀየሩ፤ ሰዎች እርስበርስ መገዳደል ጀመሩ››

ከታሪክ እንማር!

አንድሪዉ ባለበት ቦታ ሁሉ ካሊክስት ከጎኑ አይጠፋም፡፡ በአንድ የቡና ማሳ ዉስጥ አብረዉ እያወሩ ሲሰሩ ይዉላሉ፡፡ የሚዝናንቱም ከቤተሰቦቻቸዉ፣ ከሚስቶቻቸዉና ከልጆቻቸዉ ጋር በጊታር በታጀበ ሙዚቃ አብረዉ እየተመገቡ ነዉ፡፡ በቤተ ክርስትያን ዉስጥም ካሊክስት ወንጌል ሲያነብ አንድሪዉ ይሰብካል፤ ልጆቻቸዉም በደስታ ይዘምራሉ፡፡ 

በእነዚህ አብሮአደጎች መሀል ንፋስ እንኳን ይገባል ብሎ መገመት ከባድ ነዉ፡፡ ነገር ግን ጥልቅ የሆነ ጥላቻ ለያያቸዉ፡፡ እ.ኤ.አ በሚየዚያ ወር 1994 በተቀሰቀሰ ግጭት ጎረቤት በጎረቤት ላይ፣ ቤተሰብ በቤተሰብ ላይ ተነሳ፡፡ ፍቅር በጥላቻ ተተካ፡፡ የእርስ በርስ ጦርነት ጓደኛሞችንም ወደ ጠላትነት ቀየራቸዉ፡፡ ይህ እዉነተኛ ታሪክ ከ25 ዓመታት በፊት ከሀገራችን ኢትዮጵያ በ1000ኪሜ ርቀት በስተደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘዉ ሩዋንዳ የተከሰተ ነዉ፡፡

‹‹ሰዎችን መርዳት ስለምወድ ዶክተር ነበር መሆን ምፈልገዉ›› ይላል የሀምሳ አመቱ አንድሪዉ በጽዱ ቤቱ ዉስጥ ቁጭ ብሎ፡፡ ነገር ግን ድህነት ሌላ እቅድ አዘጋጅቶለታል፡፡ ለትምህርት የሚከፍለዉ ገንዘብ ስላልነበረዉ ከ1985 ጀምሮ በወላጆቹ መኖሪያ አካባቢ የራሱን ቤት ሰርቶ መኖር ጀመረ፡፡

ከሁለት አመታት በኋላ ማድሪንን አግብቶ ቤተሰብ መሰረተ፡፡ ‹‹በወቅቱ ጥሩ ህይወት ነበረኝ፡፡ ብዙ ዘመዶችና እንደ አንድ ቤተሰብ የምንተያይ ብዙ ጓደኞች እንዲሁም ጎረቤቶች ነበሩኝ፡፡ ነገሮች ሁሉ እጅግ በጣም ጥሩ ነበሩ፡፡›› አንድሪዉ ያንን ጊዜ በዚህ መልኩ ነበር የሚገልፀዉ፡፡ 

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-08-5

ኅሩይ
ከጎንደር ዪኒቨርሲቲ


@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከትላንት የቀጠለ...

ወይዘሪት #ብርትኳን_ሚደቅሳ የምርጫ ኦፕሬሽንን አስመልክተው ትላንት በሰጡት ማብራሪያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና እገዛ ላይ ከፍተኛ ተግባራት አየተከናወነ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

ሁሉም ፓርቲዎች በእኩል የመወዳደሪያ መድረክ ላይ እንዲገኙ ለማስቻል ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ቢሆንም እስካሁን ፓርቲዎች ሟሟላት የሚገባቸውን ነገር ቶሎ ባለመሟላታቸው ፍጥነታችንን ቀንሶታል ብለዋል፡፡ እንደ ሰብሳቢዋ ገለጻ የምርጫ ኦፕሬሽን ዋናው ተግባር የመራጮች ምዝገባ ሲሆን ይህም የምርጫ ታአማኒነት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

የምርጫ ክልል አደረጃጀትና የምርጫ ጣቢያ ልየታ ከሞላ ጎደል የተጠናቀቀ ሲሆን ለዚህ የሚመጥን የሰው ኃይል ሟሟላት በጣም ከባዱ ሥራ ይሆናል ብለዋል፡፡ በዘንድሮ ምርጫ ብቻ 250, 000 ምርጫ አስፈጻሚዎች የሚያስፈልጉ ሲሆን ለእነዚህ ሥራ አስፈጻሚዎች በሙሉ ሥልጠና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የምርጫ ቆጠራን በተመለከተ ልዩ ልዩ ጥናቶች የተጠንቶ በዘንድሮው አመት በምርጫ ምዝገባውም ሆነ ቆጠራው ላይ የቴክኖሎጂ ማሻሻያ እንደማይደረግ ነገር ግን የውጤት አገላለፅ ፍጥነትን ለመጨመር ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም እንደታሰበ ጠቁመዋል፡፡

ይህም ቴክኖሎጂው በራሱ 80 ሚሊየን ዶላር የሚጠይቅ በመሆኑና አዲስ ቴክኖሎጂን ስንጠቀም ከሚያስፈልጉት የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት አንጻር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህብረተሰባችን ስለምርጫም ሆነ ስለ ምርጫ ቦርድ ያለው አመለካከት የተዛባ ነው እንዴት ይስተካከል?

በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ ምርጫ ዋናው ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡ ሀገራችንም በዘንድሮው አመት 6ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ለማካሄድ እየተዘጋጀች ሲሆን ይህንን የማስፈጸም ስልጣን የተሰጠው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት በርካታ ሪፎርሞችን በማድረግ ገለልተኛና ብቁ ተቋም በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ ይህም ሆኖ ግን ዜጎች ከዚህ በፊት በነበሩት ምርጫዎች ምክንያት ስለ ምርጫና ምርጫቦርድ ያላቸው አመለካከት የተዛባ መሆኑ እንደሚያሳስባቸው የጠቀሱት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አባል የሆኑት ዶክተር አበራ ይህንንም ችግር ለመፍታት የመራጮች ትምህርት ለመስጠት ዕቅድ መያዛቸውን ጠቁመዋል፡፡ ለዚህም አዲስ የመራጮች ማኑዋል ተዘጋጅቶ ለቦርድ ቀርቦ ከጸደቀ በኀላ በሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል ብለዋል፡፡ እንደ ዶ/ር አበራ ገለጻ ይህ የስልጠና ማኑዋል በቦርዱ ከጸደቀ በኃላ በተለያዪ ቋንቋዎች እንደሚተረጎምና አካል ጉዳተኞችን ባካተተ መልኩ እንደሚቀርብ ጠቅሰዋል፡፡

#TIKVAH_ETH

ተጨማሪ ያንብቡ👉 https://telegra.ph/ምርጫ-10-08

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ መንገድ መፍትሄ ይፈልጋል...

"ኢ ነኝ ከአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ነው፤ ይህ የምትመለከተው በቆጂ ከተማን ከሽርካ ወረዳ ሚያገናኝ መንገድ ሲሆን ተደጋጋሚ መለስተኛ ጥገና በኦሮሚያ መንገዶች ባለስልጣን በደረግለትም አሁንም በሚታየው መልከ ተበላሽቶ ለጉዞ አስቸጋሪ ሆኗል። የሚመለከተው የመንግሥት አካላት ትኩረት ቢሰጠው ስል በእናቶችና በሚጉላሉ ህፃናት ስም በአክብሮት እለምንሃለሁ፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HARAR

ከሐረር ከተማ በህገ ወጥ መንገድ ወደመሀል አገር ሲዘዋወሩ የነበሩ የተለያዩ መድኃኒችን መያዙን የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የኦፕሬሽን ኃይል አመራር የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር ወንደሰን ካሳሁን እንደገለጹት ባለፉት ሳምንታት በህገ ወጥ መንገድ ወደመሀል አገር ሲጓጓዙ የነበሩ መድኃኒቶች የተያዙት በክልሉ ሐማሬሳ የመቆጣጠሪያ ስፍራ ነው። የጸጥታ ኃይሉ ከህብረተሰቡ ጋር በተደራጀ መልኩ ባከናወናቸው ሥራዎች ግምታቸው 100 ሺህ ብር የሚጠጋ የተለያዩ ህገ ወጥ መድኃኒቶች መያዛቸውን አመልክተዋል። በ21 የተለያዩ ካርቶኖች ተቀምጠው ሊተላለፉ ከነበሩ መድኃኒቶች መካከል በመርፌ፣ በደረቅና በፈሳሽ መልክ የሚወሰዱ የተለያዩ መድኃኒቶች እንዲሁም ሲሪንጅ ይገኙበታል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahehiopia
#FAKE

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከላይ የምትመለከቱ የአዲስ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥሪን የሚመለከተው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ አሳውቋል። "ETHIOPIA UNIVERSITY NEWS" ይህን ገፅ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አያውቀውም።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE ይህ BBC Amharic News ተብሎ የተከፈተና ከ4 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው። የሚተላለፉት መረጃዎችም BBC የአማርኛው አገልግሎትን የሚወክሉ አይደሉም። ገፁ እንዲዘጋ ለማድረግም እየተሰራ እንደሆነ ተነግሮናል።

ትክክለኛው የBBC አማርኛ የፌስቡክ ገፅ Verify የተደረገና ከ300 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ነው👇
https://m.facebook.com/BBCnewsAmharic/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DOHA2019 በ2 ወርቅ፣ በ5 ብር እና በ1 ነሃስ ድምር 8 ሜዳልያ በማግኘት ኢትዮጵያ ከአለም 5ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን ይዛ የዘንድሮውን 17ኛ የዶኃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ያጠናቀቀዉ ስፖርት ልዑካን አአ ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DEBRETABOR

ከሁለት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ለሱስ ተጠቂዎች የሕክምና አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የደብረ ታቦር ጠቅላላ ሆስፒታል እና የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ አስታወቁ፡፡ በኢትዮጵያ ወጣቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሱስ ተጠቂ እየሆነ በመምጣቱ እና በአማራ ክልል የሱስ ማገገሚያ ተቋም ባለመኖሩ የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲና የደብረ ታቦር ጠቅላላ ሆስፒታል በጋራ በመተባበር ለሥነ አዕምሮ ታካሚዎችና ለሱስ ተጠቂዎች የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ማዕከል አቋቁመዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አዲስ አበባ ከተማ በቴክኖሎጂ ቀዳሚ መሆን አለባት" ኢንጂነር #ታከለ_ኡማ
-
ኢ/ር ታከለ ኡማ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የታክሲ አገልግሎት (ኤታስ) ከሚሰጡ 13 ተቋማት ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡ በዋነኛነት የከተማ አስተዳደሩ በቅርቡ የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከተሉት ባወጣው መመሪያ ዙሪያ እና የትራንስፖርት ሴክተሩን በዘላቂነት ዘመናዊ ለማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከኤታስ እና ሶፍትዌር ማበልፀጊያ ተቋማት ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-09

ምንጭ፦ Mayor Office Of AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HERQA

የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተለያዩ መስፈርቶችን ሳያሟሉ ተምረው ያስመረቋቸውና በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎችን በተመለከተ መንግስት ውሳኔ እንዲሰጥበት ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ማቅረቡን አስታወቀ።

በኤጀንሲ የዕውቅና አሰጣጥ ዳይሬክተር አቶ አብይ ደባይ፤ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ ባለፉት ዓመታት የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተለያዩ መስፈርቶችን ሳያሟሉ አስተምረው ያስመረቋቸውና በማስተማር ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ቁጥር በርካታ ነው። የተማሪዎችን መረጃ ለመደበቅ ሁለት ሬጅስትራር ያሏቸው፤ ግብር እንዳይከፍሉ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያቀርቡ ተቋማት እንዳሉ ተገንዝበናል።

ተቋማቱ አስተምረው ያስመረቋቸውና ተጠያቂነትን በመሸሽ ለኤጀንሲው ያላቀረ ቧቸው ሊኖሩ ስለሚችሉ ችግሩ የሰፋና ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚዊና ማህበራዊ በመሆኑ ከፍተኛ አመራሩ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ቀርቧል::

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምርጫው በዘንድሮው ዓመት ይከናወናል ወይ ተብለው ከተሳታፊዎች ለቀረበላቸው ጥያቄ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርትኳን ሚዴቅሳ ሲመልሱ፡- "ፓርቲዎች ከራሳቸው ፍላጎት ተነስተው ምርጫው እንዲራዘምላቸው የሚጠይቁ አሉ እኛ ግን ምርጫውን በስኬት ለማከናወን የሚያስፈልጉ ጉዳዮችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለምርጫው እየተዘጋጀን ነው" ብለዋል።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Johannesburg

ዓመታዊው የኮካ ኮላ የደቡብ እና የምስራቅ አፍሪካ ስብሰባ በአሁን ሰዓት በጁሃንስበርግ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። በስፍራው የሚገኘው የቤተሰባችን አባልም በአሁን ሰዓት ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ የማነቃቂያ ንግግር እያደረገ እንደሚገኝ ገልጾ ይህንኑ የሚያሳይ ቪድዮ እንድናይ አጋርቶናል። ተጨማሪ ቪድዮዎች ከተላኩ እናጋራለን!

#TikvahEthFamily
@tsegabwolde @tikvahethiopia