TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#attention

ከአጣዬ የTIKVAH ቤተሰቦቻችን እየተላከልን የሚገኘው መልዕክት በአከባቢው የተፈጠረው አለመረጋጋት አሁንም እንዳልረገበ የሚገልፅ ነው። ሁኔታዎች ወደከፋ ደረጃ እንዳይደርሱ መንግስት መፍትሄ መፈለግ አለበት፤ ችግሩም የኢትዮጵያን መንግስት ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሸኖ ላይ የተዘጋው መንገድ አልተከፈተም!

በስፍራው የሚገኙ የTIKVAH ቤተሰቦች ሸኖ ላይ የተዘጋው መንገድ እስካሁን ድርሰ እንዳልተከፈተ፤ እነሱም መኪና ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

"እስካሁን ድረስ እዛው ሸኖ ላይ በዛ ብርድ መኪና ውስጥ ተቀምጠናል። እኛ ያለነው ወደ አዲስ አበባ መስመር ነው።" B.M

"ሸኖ አካባቢ መንገድ ስለተዘጋ ወደአዲስ አበባ ለመመለስ ስላልፈቀዱልን ለ5 ሰዓት መኪና ውስጥ እየጠበቅን ነው። አሁንም ድረስ ሊያሳልፉን አልፈቀዱም። ማንም ሊረዳን አልፈቀደም።" S

ዘግየት ብላችሁ ጉዳዩን የሰማችሁ ካላችሁ፦ መንገዱ የተዘጋው የኢሬቻን በዐል አክብረው ወደ ከሚሴ ሲሄዱ የነበሩ ወጣቶች ደብረ ብርሃን አካባቢ ታስረዋል፤ እነዚህ ወጣቶች ይፈቱ በሚሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

ሸኖ ላይ መንገድ የተዘጋባቸው መንገደኞች እዛው ለማደር ተገደዋል፤ እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የተዘጋው መንገድ አልተከፈተም። በስፍራው ከሚገኙ የTIKVAH ቤተሰቦቻችን የሚላኩልን አዲስ ነገር ካለ እናጋራዋለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention | የተዘጋው መስመር ከነገ ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሄዱበት በመሆኑ፤ ጉዞ ለማድረግም ትኬት የቆረጡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በመኖራቸው መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በሙሉ በመነጋገር ችግሩን መፍታት ይኖርበታል። አሁንም በመንገድ ላይ የሚገኙ እናቶች፣ ህፃናት፣ እድሜያቸው የገፉ አባቶች ስለሆኑ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሄ ያሻዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዱ ተከፍቷል!

ሸኖ ላይ ለሰዓታት ተዘግቶ የቆየው መንገድ በአሁን ሰዓት ተከፍቶ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። መንገዱ በሁለቱም አቅጣጫ ነው የተከፈተው። ደብረ ብርሃን ላይ ታሰሩ የተባሉት ወጣቶችም #መፈታታቸው ተሰምቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዱ ተከፍቷል!

በሸኖ የሚገኙ የTIKVAH ቤተሰቦች መንገዱ መከፈቱን አረጋግጠው፤ የተሽከርካሪዎችን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ፎቶ ልከውልናል።

PHOTO: KAACHI/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአለባበስ ሕግ ይፋ ሊደረግ ነው!

የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የአለባበስ ስነምግባር ደንብን ለመወሰን በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሚኒስቴር የተጠናው ጥናት ተጠናቆ ከጥር 2012 ጀምሮ ይፋ ሊደረግ ነው።

ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መደበኛ ተብሎ በጥናት የሚረጋገጠውን አለባበስ፣ ሀይማኖታዊ አለባበስ እና ባህላዊ አለባበሶችን ይደነግጋል የተባለው ይህ መመሪያ እስከዛሬ በየዩኒቨርሲቲው ተበታትኖ የሚገኘውን የተማሪዎች መተዳደሪያ ደንብ ይተካል ሲልም ሚኒስቴሩ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

‹‹በርካታ ተማሪዎች ሥነ ምግባር የጎደለው አለባበስ በመጠቀም መማር ማስተማሩን ሲያውኩ ነበር›› በማት ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ የገለፁት የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር #ደቻሳ_ግሩም ‹‹በተለይም ፀጉራቸውን አንጨባረው የሚመጡ በርካታ ወንድ ተማሪዎች በየዩኒቨርስቲው ማየት የተለመደ ነው›› ሲሉም ገልፀዋል።

በአዲሱ መመሪያ መሰረትም የፓርቲ አርማ ያለበት ልብስ እና ለግጭት የሚዳርጉ የተለያዩ አለባበሶችን ለብሰው የሚመጡ ተማሪዎችን የሚገድብ እና ችግሩንም የሚፈታ እንደሆነ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-07

Via AddisMaleda
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዩኒቨርሲቲ...

አዲሱ መመሪያ የፓርቲ አርማ ያለበት ልብስ እና ለግጭት የሚዳርጉ የተለያዩ አለባበሶችን ለብሰው የሚመጡ ተማሪዎችን የሚገድብ እና ችግሩንም የሚፈታ እንደሆነ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ደቻሳ ግሩም ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Attention

ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በአፋር ክልል በርካታ የቀድሞ አመራሮች እና አንዳንድ ባለሀብቶች በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሆነ ተሰምቷል። የጉዳዩ መነሻ ሶስት አወዛጋቢ ቀበሌዎች የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት ስልጣን ላይ እያሉ ወደ አፋር ክልል መካተታቸው ነበር።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው ከፍተኛ የፌደራል ባለስልጣናት ጭምር በተገኙበት ነበር። በቅርቡ ደግሞ የሶማሌ ክልል እነዚህ ቀበሌዎች የእኔ ናቸው ብሎ የካቢኔ ውሳኔ አሳልፎ ነበር። በነዚህ ምክንያቶች አካባቢው ሰላም ማግኘት አልቻለም። አሁን ችግሩ ከነዚህ ሶስት ቀበሌዎች አልፎ ሌሎች የሶማሌ ክልል ስፍራዎችን እያዳረሰ ነው።

ይህንን እንቅስቃሴ በአፋር በኩል በገንዘብ እና ቁሳቁስ ሲደግፉ የነበሩ ነጋዴዎች እና የቀድሞ አመራሮች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ ባለፈው ሳምንት ብቻ ብዙ ሰው ህይወቱን አጥቷል። ያልተረጋገጡ ሪፖርቶች በሶማሌ በኩል 18፣ እንዲሁም በአፋር በኩል ወደ 30 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ይጠቁማሉ።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/Associated Press/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIGRAY

ተቀማጭነታቸውን በኢትዮጵያ ያደረጉ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች በትግራይ ክልል ያለውን የቱሪዝምና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ እንዲሳተፉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤልጥሪ አቀረቡ። አምባሳደሮቹ ላለፉት ሁለት ቀናት በክልሉ ሲያካሔዱት በቆዩት ጉብኝት ማጠቃለያ ውይይት ላይ ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ እንደገለጹት፥ የትግራይ ክልል ከመካ ቀጥሎ በእስልምና ተከታዮች ዘንድ ታሪካዊና ጥንታዊ የሆነውን አልነጃሺ መስጊድን ጨምሮ የተለያዩ የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች ባለቤት ነው።

ተጫማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-07-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#UnityPark

"አንድነት ፓርክ" መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ.ም ተመርቆ ለህዝብ ጉብኝት ክፍት ይሆናል። በአንድነት ፓርክ ዘጠኙም ክልሎች በአግባቡ ተወክለው በቤተ መንግስቱ እልፍኝ ተበጅቶላቸዋል። ታላቁ ቤተ መንግስት ስያሜው አንድነት ፓርክ ሆኖ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ.ም ተመርቆ ለህዝብ ጉብኝት ክፍት ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEBE

ለሐረሪ ክልል፣ ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ ለጋምቤላ ክልል እና ለአማራ ክልል የምርጫ ክልል ኃላፊነት በቂ አመልካቾች አለመቅረባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ፡፡

ቦርዱ ለ9ኙ ክልሎችና ለ2ቱ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ክልል ኃላፊነት ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመመደብ የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።

መስፈርቱን ለሚያሟሉ እና በሶስቱ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር መስራት ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የማመልከቻ ጊዜው መራዘሙን ቦርዱ ገልጿል፡፡ የማመልከቻ ጊዜው በአንድ ሳምንት በመራዘሙ አመልካቾች ከዛሬ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ማመልከቻቸውን ማስገባት እንደሚችሉም ቦርዱ አስታውቋል፡፡

Via #ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

"ከሃረር ወደ ጅግጅጋ የሚወስደው መንገድ ለባቢሌ 10 ኪሜ ሲቀረው ያለው ድልድይ በመሰበሩ ከባለፈው እሮብ ዕለት ጀምሮ መንገዱን መሻገር አስቸጋሪ ሆኗል። ቅያሪ መንገድ ለማዘጋጀት ሞክረው ነበር ግን ጭቃ እየሆነ ከባድ መኪኖች በጭቃ እየተያዙ ነገሩን አስቸጋሪ አድርጎታል፤ አሽከርካሪዎችም እየተንገላቱ ነውና የሚመለከተው አካል መፍትሄ አስቸኳይ መፍትሄ ቢፈልግለት መልካም ነው።"

PHOTO: MERHAWI/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
https://unitypark.et/

መስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ለጉብኝት ክፍት የሚሆነው የታላቁ ቤተ መንግሥት <<አንድነት ፓርክ>> ድረ ገጽ ይፋ ሆነ፡፡ ጎብኚዎች ስለ ፓርኩ ገጽታና ስለሚጎበኙ ስፍራዎች መረጃ ከድረ ገጹ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን፣ የመጎብኛ ቀንና ሰዓት በመጥቀስ ትኬት መቁረጥም ያስችላል። ለፓርኩ ጉብኝት በተንቀሳቃሽ ስልክ ክፍያ ለመፈጸም የሚያስችል አሠራር በኢትዮ ቴሌኮም አማካይነት ተዘርገቷል።

https://unitypark.et/

#REPORTER
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ የስንብት ፕሮግራም በአሁኑ ሰዓት ላይ ቤተሰቦቹ፣ የሞያ አጋሮቹ እንዲሁም ወዳጆቹ በተገኙበት በብሔራዊ ቴአትር እየተካሄደ ይገኛል። የቀብር ሥነ ስርአቱም ከቀኑ በ9 ሰአት በጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአጣዬ 8 ሰዎች ተገደሉ!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማና አካባቢዉ ከትናንት በስቲያ በተቀሰቀሰዉ ግጭት የ5 ሰላማዊ ዜጎች እና ሕይወት ማለፉ ተገለፀ። በግጭቱ ከመንግሥት ወገን 3 የፀጥታ ኃይላት መሞታቸውንና 5 መቁሰላቸውም ተገልጧል።

የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ ጌታቸዉ በቀለ እንደገለፁት በአካባቢዉ ግጭቱ የተቀሰቀሰዉ ከ3 ቀን በፊት አንድ የታጠቀ ግለሰብ የክልሉ ልዩ ኃይል በሚገኝበት የጥበቃ ማማ ላይ በከፈተዉ ተኩስ ነዉ።

ግለሰቡ ጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በማይቻልበትና በኮማንድ ፖስት ስር ባለ አካባቢ 3 የእጅ ቦንቦች፤ ክላሽንኮቭ እና በርካታ ጥይቶችን ይዞ በመገኘቱ በተኩስ ልዉዉጥ እንደተገደለ አቶ ጌታቸዉ ዐስታዉቀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-07-3

Via #DW

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸በብሄራዊ ቴአትር የተካሄደው የሙዚቀኛ ኤሊያስ መልካ የስንብት መርሃ-ግብር። በመርሃ ግብሩ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳሁን ፣ ረ/ፕሮፌሰር ነብዩ ባዩን ጨምሮ ቤተሰቦቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎቹ ተገኝተው ነበር፡፡

PHOTO: Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ መንግስት በ2012 በጀት ዓመት ትኩረት ሰጥቶ ስለሚሰራቸው ጉዳዮች በንግግራቸው ካነሷቸው አንኳር ነጥቦች መሃል፡-

• በ2012 የለውጡን ጉዞ የተሻለ ቁመና ላይ እንዲገኝ በትኩረት ይሰራል

• በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን ከፍታ እንዲረጋገጥ መሰረት ይጣላል

• በኢኮኖሚ፣ በድፕሎማሲ እና መሰል ተግባራት የተገኙ ስኬቶችን ለቀጣይ አገራዊ ስንቅ እንዲሆኑ ይደረጋል፡፡

• እኩልነት፣ ፍትሃዊነት፣ መከባበር እና አንድነትን ሊያመጡ የሚያስችሉ፣ ከጉድለታችን እየተማርን፣ እያረምን እና እየገነባን ያጋጥሙንን ውዝፍ እዳዎች ለማስወገድ እንጥራለን።

• ለቀጣዩ ትውልድ ከእኛ የተሻለ ስራ ሰርተን ለማስረከብ እንጥራለን።

• ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎቻችን በመደመር እሴቶች ተዋጅተው የሚፈፀሙ ይሆናል።

• ውስጣዊ አለመረጋጋት እና ግጭቶች ተፈናቃዮችን ሜዳ ከቀያቸው እንዲሰደዱ በማድረግ ለአገሪቱ ፈታኝ የነበረ ቢሆንም ችግሩን በአገራዊ አቅም ለመቋቋም ተችሏል።

• በቀጣይ ችግሮች ሳይከሰቱ መቆጣጠር የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል።

• የፀጥታውን ዘርፍ ለማጠናከር የተደራጀ የፌደራል ፖሊስ እና የክልል ኃይሎች እንዲሁም የመከላከያ ኃይል የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ትግበራ በአዲስ መልክ ተጠናክሮ እውን ይሆናል።

• አገራዊ የሰላም ግንባታውን በህዝብ ተሳትፎ ለማረጋጥ የሚያስችል ስራ ይሰራል።

• አንዳችን ለአንዳችን የሰላም ምንጭ እንጂ የቁርሾ መነሻ እንዳንሆን በጋራ አብሮነት ልንሰራ ይገባል።

• ይህን ታላቅ ህዝብ እዚህም እዚያም የሚወረወሩ አሉቧልታዎች ሊረቱት አይገባም፣ በአርቆ አሳተዋይነት የጋራ ቤታችንን መጠበቅ ይኖርብናል።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በህዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ስለ አገራዊ የፖለቲካና ዲሞክራሲ ግንብታ ጉዳዮች የተናገሩት ፡-

• በመግባባትና በመመካር ላይ የተመሰረተ የፖለቲካ ስትርዓት ለመገንባት መንግስት የሚጠበቅበትን ያደርጋል፡፡

• የትብብርና የአንድነት ፖለቲካ እንዲሰፍን ይሰራል፡፡

• የዘንድሮው ምርጫ ነፃና ፍትሃዊ እንዲሁም ተቀባይነት ያለው ፣ ምልዓተ ህዝቡን ያሳተፈና ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ላይ የታዩ ህፀፆችን ያረመ ምርጫ ለማካሄድ መንግስት ዝግጁ ነው፡፡

• ፍርድ ቤቶችን ለመሻሻል የሶስት ዓመት ማሻሻያ ስራ በመስራት የተጀመረውን የለውጥ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል፣የፍትህ ተደራሽነትና ቅልጥፍናን የሚያመጣ የፍትህ ስርዓት የመዘርጋቱ ሂደት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ይከናወናል፡፡

• ላለፉት 60 ዓመታት ስራ ላይ የዋሉ የወንጀልና የንግድ ህጎች ፣ የአስተዳደር ስርዓት ህግን ጨምሮ በአዲስ መልክ ፀድቀው ወደ ስራ ይገባሉ፡፡

• ሙያዊ ጋዜጠኝነት ተላብሰው ለሚሰሩ ጋዜጠኞች መንግስት ድጋፍ ያደርጋል፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሙዚቃ አቀናባሪው የኤልያስ መልካ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ። በዚህ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ከአርቲስቱ ጋር አብረው የሰሩ አንጋፋ እና ወጣት የጥበብ ባለሙያዎች፣ ቤተሰቡ፣ የሙዚቃ አፍቃሪያን እንዲሁም በያሬድ ትምህርት ቤት ያስተማሩት መምህራን እና ሌሎችም በርካታ ሰዎች ተገኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
75,900+ ትክክለኛው የTIKVAH-MAGAZINE ገፅ!

በስፋት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮች የሚዳሰሱበት የTIKVAH-ETH አንዱ አካል!

Join👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ