TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል! #TIKVAH_ETHIOPIA

PHOTO: TESFAYE & ROBEL
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሆራ ፊንፊኔ #Irreechaa2019

PHOTO: EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ!

የሙዚቃው ሰው ኤልያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ። የሙዚቃ አቀናባሪ፣ ገጣሚ፣ የዜማ ደራሲ እና ጊታሪስት የሆነው ኤልያስ መልካ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያኖረ አርቲስት ነው።

ሙዚቀኛ ኤልያስ መልካ የስኳር እና ኩላሊት ህመም ገጥሞት ህክምናውን ሲከታተል ቆይቷል። እስከ ባለፈው ቅዳሜ ድረስ ኤልያስ መልካ በፋና ላምሮት የድምፀውያን ተስጥኦ ውድድር ላይ #በዳኝነት ሲያገለግል ቆይቶ ነበር። ለሊቱንም በመኖሪያ ቤቱ ህይወቱ እንዳለፈ ተሰምቷል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያን ሙዚቃ ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረው እውቁ የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ ሰሞኑን በኢትዮ-ጠቢብ ሆስፒታል ተኝቶ ህክምና ሲከታተል እንደነበረ ታውቋል።

RIP!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#RIP

ኤልያስ መልካ የሙዚቃ አቀናባሪ፣ የዜማና ግጥም ደራሲ፣ ጊታሪስት፣ ፒያኒስት ሲሆን፥ አዳዲስ ሙዚቀኞችን ለሀገራችን በማስተዋወቅና ችሎታቸውን ለይቶ በዚያ እንዲያልፉ በማድረግ ይታወቃል።

ከያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ቼሎ የሙዚቃ መሳሪያን ተምሮ ከጨረሰ በኋላ ከመምህሩ አክሊሉ ዘውዴ፣ ከእዝራ አባተና ከያሬድ ተፈራና ከሌሎችም ጋር በመሆን በመዲና ባንድ ውስጥ ሰርቷል። ከዚያ በኃላ ከዜማ ላስታስና ከአፍሮ ሳውንድስ ባንዶች ጋር የሰራበት ጊዜ ነበር ። ከ30 በላይ ሙሉ አልበሞችን ልዩ አድርጎም አቀናብሯል።

ከመሃሙድ አህመድ፣ ከኩኩ ሰብስቤ፣ ከፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ከአለማየሁ እሸቴ ጋር የሰራ ሲሆን፥ ቴዲ አፍሮ፣ እዮብ መኮንን፣ ሚካኤል በላይነህ፣ ዘሪቱ ከበደ፣ ልኡል ሀይሉ ሀይሌ ሩትስ፣ ሚካያ በሃይሉ፣ ትግስት በቀለ፣ ቤሪ፣ ዳን አድማሱ ጥቂቶቹ ናቸው። “ሙዚቃ በኤልያስ መልካ ከነሙሉ ክብሯ ታልፋለች”ይላሉ ብዙ ድምፃውያን።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIKVAH_ETHIOPIA በታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለመላው ቤተሰቦቹ፣ ወዳጆቹ፣ ጓደኞቹ እንዲሁም ለመላው አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በተያዘው የበጀት ዓመት 6.8 ሚሊዮን የሀገር ውስጥና 38ሺህ የውጪ ሀገር ቱሪስቶች በወላይታ ዞን ያሉትን የቱሪስት መስዕቦች ይጎበኛሉ ተብሎ መታቀዱን በዞኑ ባህል፣ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ልማትና ብቃት መረጋገጫ ዋና የስራ ሂደት መሪ አቶ አለሙ አሰሌ ተናግረዋል፡፡ የወላይታ ዞን እንደአንጃራ ፏፏቴ፣ ከ58 ሺህ ዓመት በፊት የሰው ልጅ ይኖርበት የነበረው ዋሻ፣ የአባያ ፍል ውሃ፣ አባያ ሀይቅ፣ የተፈጥሮ ድልድይ፣ የወላይታን ህዝብ ባህልና ዕሴትን በስፋት የሚያስተዋውቅ ሙዚየም እና ሌሎችም በርካታ የቱሪስት መስዕቦች እንዳሉ አቶ አለሙ ገልፀዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና

አትሌት ደምስ ፀጋው አረፈ!

ባለፉት በርካታ አመታት ሀገሩ ኢትዮጵያን ወክሎ በተለያዩ ውድድሮች ሲወዳደር የነበረው አትሌት ደምስ ፀጋው ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡ አትሌቱ ኢትዮጵያን በመወከል በሀገር አቋራጭ እና የአስፓልት ላይ ውድድሮችን በርካታ ጊዜ ያደረገ ሲሆን በአደረበት ህመም ምክንያት ህይወቱ አልፏል፡፡

አትሌት ደምስ #በግሉ እና #ሀገር በመወከል በርካታ ውድድሮችን አድርጎ ጥሩ ውጤት ያመጣ እንደነበርም ታውቋል፡፡ አትሌቱ ህይወቱ ያለፈው በአሜሪካ ሀገር ሲሆን በቅርብ ቀናት አስከሬኑ ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ይገባል ተብሏል፡፡

ምንጭ፦ አውሎ ሚዲያ/Bekal Alamirew/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ታርጫ

በአሁኑ ሰዓት በዳውሮ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ታርጫ የዞኑ ተወላጅ ምሁራን፣ ከፍተኛ አመራሮች እና የአገር ሽማግሌዎች በተገኙበት "የዳውሮ ምሁራንና አጋሮች ማህበር ምስረታ" የመክፈቻ ስነስርዓት እየተደረገ ይገኛል። ስነስርዓቱ በአገር ሽማግሌዎች ምርቃት ተከፍቷል።

Via Haile/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ተከበረ!

በገዳ ሥርዓት መሰረት በአባ ገዳዎች ምርቃት የተጀመረው የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ተከብሯል። በአዲስ አበባ የሚከበረውን ኢሬቻ ለመታደም ከኦሮሚያ፣ ከአዲስ አበባና ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በርካታ ሕዝብ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ተገኝተዋል። በአሁኑ ሠዓት በዓሉ በሠላም ተከብሮ ታዳሚዎችም ወደየመጡባቸው አካባቢዎች በመመለስ ላይ ይገኛሉ። ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ በዓመት ሁለት ጊዜ በፀደይ በውሃማ አካላት፤ በበልግ ደግሞ በተራራማ አካባቢዎች ላይ የሚከበር የምስጋና በዓል ነው።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
PHOTO📸በታሪካዊ ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ላይ የጋብቻ ስነ ስርዓታቸውን የፈፀሙ ጥንዶች!

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UNIVERSITY

በዘንድሮው ዓመት በመንግስት #ዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ የሚያገኙ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 46 ሺህ 416፣ ሴት 32 ሺህ 865 በድምሩ 79 ሺህ 281 ሲሆኑ ፥ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ወንድ 34 ሺህ 838 ሴት 28 ሺህ 702 በድምሩ 63 ሺህ 540 መሆናቸው ተገልጿል።

በዚህ መሰረትም ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከሚገቡ ተማሪዎች 55 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፥44 ነጥብ 5 በመቶዎቹ ደግሞ የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በዘንድሮው ዓመት በአጠቃላይ ወደ መንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር 142 ሺህ 821 ነው። የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች መግቢያ አራት መሰረታዊ የትምህርት አይነቶችን ውጤት መሠረት አድርጎ እንደሚወሰን መገለጹ ይታወሳል።

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዩኒቨርሲቲ መቀያየር አይቻልም!

በአንዳንድ ማህበራዊ ገፆች ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲ እናቀያይራለን የሚሉ መልዕክቶች እየተሰራጩ ይገኛሉ፤ ይህ ከእውነት የራቀ ነው። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለTIKVAH-ETH እንዳሳወቀው ምንም አይነት የዩኒቨርሲቲ ቅይይር አይቻልም። በማህበራዊ ሚዲያዎችም እየተሰራጩ የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ቅይይር መልዕክቶች ሀሰተኞችና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እውቅና የሌላቸው ናቸው።

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጥብቅ ማሳሰቢያ!

ማንኛውም ተማሪ #ከተመደበበት ዩኒቨርስቲ ወደሌላ ዩኒቨርስቲ መቀያየር እንደማይቻል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ያስታውቃል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል እጅግ በደማቅ ሁኔታ በሰላም ተጠናቋል!

PHOTO: AMANUEL ETICHA & EYASU G.

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia