TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#HAWASSA የሀዋሳ ታቦር ሕይወት ብርሃን ወጣቶች በTIKVAH 5 ኛው አመት የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ላይ በመሳተፍ ያሰባሰቡትን መፅሃፍት ለግሰዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በ5ኛው ዐመት የመፅሃፍት ማሰባሰብ ላይ የበጎ አድራጎት ማህበራት እድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን። ሰፋ ባለመልኩ የመፅሃፍት ማሰባሰብ ስራው ይቀጥላል።

በየትኛውም የኢትዮጵያ ከተሞች የምትገኙ የበጎ አድራጎት ማህበራት በዚህ ቁጥር በመደወል ተመዝገቡ 0926429534

ከከተማ አካባቢ የሚሰባሰቡ መፅሃፍትን በተለይ በመፅሃፍ እጥረት ለሚቸገሩ ገጠራማ አካባቢዎች የምናደርስ ይሆናል።

መፅሃፍት መለገስ ለምትፈልጉ ወላጆች እና ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ከገለፅነው በተጨማሪ በምን መልኩ መስጠት እንደምትችሉ በቀጣይ ቀናት እናሳውቃለን።

በውጭ ሀገራት የምትኖሩ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላትም በዚህ ትውልድ የመገንባት ስራ ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን!

ኑ ትውልድ እንገንባ!
TIKVAH-FAMILY


@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TIGRAY

የ15 ሀገራት አምባሳደሮችን ያካተተ ልዑክ በትግራይ ክልል ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርግ ነው። ልዑኩ የትግራይ ክልል የድህነት ቅነሳ ፕሮጀክቶችን፣ ቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ልማት እንቅቃሴዎችን ተዘዋውሮ እንደሚጎበኝ ነው የተገለጸው፡፡ የአውስትራልያ፣ አዘርባጃን ፣ ባንግላድሽ፣ ቻይና፣ ፊጂ፣ ኢንዶኖዥያ፣ ህንድ፣ ኢራን፣ ጃፖን፣ ካዛኪስታን፣ ደቡብ ኮርያ፣ ኒውዝላንድ፣ ፓኪስታን፣ ስሪላንካ እና የቱርክ አምባሳደሮች የጉብኝቶ ተሳታፊዎች ናቸው፡፡ ለዚህም አሁን ላይ የአራት ሀገራት አምባሰደሮች መቐለ ገብተዋል። እንግዶቹ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች አቀባበል ተድርጎላቸዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች ቀሪ የልዑኩ አባላትም ዛሬ ከሰዓት ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ፓልም ዘይት ጤና ላይ ጉዳት አያስከትልም" - ፓልም ኦይል!

በተለምዶ የሚረጋው ዘይት እየተባለ የሚጠራው ፓልም ኦይል በጤና ላይ ጉዳት ያደርሳል በሚል የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው ተባለ፡፡

የማሌዢያ የፓልም ኦይል ምክር ቤት በሀገሪቱ የሚረጋው ዘይት በጤና ላይ ጉዳት ያመጣል የሚለው ግንዛቤ የተሳሳተ መሆኑን ገልጾ ምርቱ ምንም ዓይነት የጎንዮሽ ጉዳት አያመጣም ሲል አስተባብሏል፡፡ በኢትዮጵያ የሚረጋው ዘይት ከሌሎች የዘይት ዓይነቶች በዋጋ የሚቀንስ መሆኑን ተከትሎ የሕዝቡ ፍላጐት ከፍተኛ መሆኑ ይነገራል፡፡

ኢትዮጵያ 70 በመቶ የሚሆነውን የሚረጋ ዘይት ከማሌዢያ የምታስገባ ሲሆን፣ የተፈጠረውን የአረዳድ ብዥታ ማጥራት ላይ ትኩረት ያደረገ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡

በማሌዥያ የፓልም ዘይት የሚያመርቱ ተቋማት የአለም የጤና ደርጅትን መስፈርት በሟላ መልኩ እንዲሰሩ የጥራት ቁጥጥር ይደረጋልም ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ በበኩሏ ከውጭ ሀገር የሚገቡ የዘይት ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ እየሰራሁ ነው ብላለች፡፡

ምንጭ፦ #AhaduFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GONDAR

በጎንደር ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የንግድ ማዕከላት፣ የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ ነው። መደበኛ እንቅስቃሴው ተቀዛቅዞ የነበረው የአዘዞ ክፍለ ከተማ ትናንት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መግባቱን አብመድ ዘግቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH ETH FAMILY

"ትላንት ጠዋት 3 ሰአት አካባቢ ከአውቶቢስ ተራ አየር ጤና ታክሲ ውስጥ #samsung ሞባይል ጥሎ የወረደ ካለ ምልክት ተናግሮ መውሰድ ይችላል። ስልኩ ሲም ስለሌለው ባለቤቱን ማግኘት ስለከበደኝ ነው። አመሰግናለው!"

ስልኩ የጠፋበት ሰው ምልክቱን ተናግሮ መውሰድ ይችላል፦ 0912309040 /Hikmet Abdu/

ለሁላችንም ትምህርት የሚሆን ተግባር!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አፍሪፖል

እ.ኤ.አ በመጋቢት ወር 2019 ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ናይሮቢ በረራዉን ሲያደርግ በነበረዉ ET 302 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በመከስከሱ የ35 ሀገራት መንገደኞች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡ አደጋዉ ከደረሰ ከሁለት ቀናት በኃላ ኢትዮጵያ በጠየቀችዉ ጥያቄ መሰረት ኢንተርፖል ምላሽ ሰጪ ቡድን በመላክ ምርመራዉን ሲያከናዉን ቆይቷል፡፡ ለህልፈተ ህይወት የተዳረጉትን ለመለየት እንዲረዳዉም ኢንተርፖል የተጎጂ ቤተሰቦች ዲ ኤን ኤ በማሰባሰብ ምርመራ አድርጓል፡፡ ኢንተርፖል ለአደጋዉ ምላሽ ሰጪ ቡድን በማሰማራት ስሰራ የነበረዉን ተጎጂዎችን የመለየት ስራ ከ 6 ወራት በኃላ በተሳካ ሁነታ ማጠናቀቅ መቻሉን አፍሪፖል በድህረ ገፁ ባወጣዉ መረጃ አስነብቧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-04-2

Ethiopian Federal Police Commission

@tsegabwolde @tikvahethiopia
⬆️በDV 2021 ለማመልከት የታደሰ እና የሚያገለግል ፓስፖርት ሊኖሮት ይገባል! ግዴታ ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ከለገ ጣፎ ለገዳዲ ከተማ 50 ፈረሰኞችና በርካታ ፎሌዎች የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀው የተለያየ የባህል ትርኢት ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እያቀኑ ነው፡፡

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ነገ መስከረም 24 በሆራ ፊንፊኔ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የመጡ የባህል ቡድኖች አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምድረ_ገነት

በምእራብ ጎንደር ዞን በሁመራ በኩል ወደ ምድረ ገነት ከተማ በጭነት ተሸከርካሪ በድብቅ ተጭኖ ሊገባ የነበረ 20 ኩንታል ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕፅ መያዙን ፖሊስ ገለፀ ፡፡ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አባይ አሻግሬ እንደተናገሩት ትናንት ረፋድ ላይ ሃሺሹ ሊያዝ የቻለው በከተማው ኬላ ላይ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ ነው፡፡

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 8173 አዲስ አበባ የሆነው አይሱዚ ተሸከርካሪ ከጫነው 30 ኩንታል ጥቅል ጎመን ስር አደንዛዥ ዕፁን በድብቅ ጭኖ መገኘቱን ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡ የጭነት ተሸከርካሪው ሃሺሹን ከሻሸመኔ በመጫን በአፋር አድርጎ መቀሌ ፣ ሁመራንና ማይካድራ ከተሞችን በማለፍ በዞኑ ምድረ ገነት ከተባለው ከተማ ሊያዝ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የመኪናው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቺክቭ በድሬዳዋ በተከሰተው ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ቢመጣም በሽታው ሙሉ በሙሉ ባለመጥፋቱ የመቆጣጠር ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የከተማዋ የጤና ቢሮ አስታውቋል። ከወር በፊት “ችጉንጉኒያ” ተብሎ የሚጠራው የበሽታ ወረርሽኝ  በድሬደዋ መከሰቱ ይታወሳል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Baga nagaan Irreecha bara 2019 geessan!
እንኳን ለ2012 ኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!


#TIKVAH_ETHIOPIA
PHOTO: TRAVEL ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ዳያስፖራ ቅርንጫፍ ከፈተ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዳያስፖራው ማህበረሰብ ብቻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ልዩ ቅርንጫፍ በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡ ቅርንጫፉን መርቀው የከፈቱት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና፤ ልዩ ቅርንጫፉ ለዳያስፖራው ማህበረሰብ የቤት መሥሪያና መግዣ የብድር አገልግሎት የሚመቻችበት፣ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት፣ ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች የሚሰጡበት፣ እንዲሁም ሌሎች ለዳያስፖራው የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚቀርቡበት ነው ብለዋል፡፡

Via CBE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣሪ አመራሮች እና ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው!

በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ተከስቶ በነበረ የፀጥታ ችግር የተጠረጠሩ ግለሰቦችና አመራሮች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።

የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥና የኮማንድ ፖስቱ አባል ምክትል ኮማንደር ምናሉ ታደሰ እንደገለጹት ባለፉት ወራት በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረ ግጭት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በዋናነት በሸኮ ወረዳ በተፈጠረ ግጭት የሰባት ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ በ25 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውሰዋል፡፡

“በግጭቱ ከ4ሺህ 500 በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን 322 ሰዎች ሙሉ በሙሉ ንብረታቸው ወድሞባቸዋል” ብለዋል ኮማንደር ምናሉ። በግጭቱ 178 የሳር ክዳንና የቆርቆሮ መኖሪያ ቤቶች ሲቃጠሉ ከ320 በላይ የጦር መሳሪያዎችም መዘረፋቸውን ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች በወረዳው ተከስቶ በነበረ ግጭት ወንጀሎችን በመፈጸምና በማስፈፀም የተጠረጠሩ መሆናቸውን ኮማንደር ምናሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ነገ በሆራ ፊንፊኔ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ ይገኛል። በፕሮግራሙ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ፕሬዝደንት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ከ49 ኩንታል በሶና ከ3 ሺ 5 መቶ 35 ኪ.ግ ቅቤ የተሰራው 4 ሺህ ሜትር ጩኮ ለእይታ ቀርቧል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia