TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የእገዳ ውሳኔ አልተላለፈም...

የኢትዮጵያ የማራቶን ውድድር ሯጮች ላይ ምንም አይነት የእገዳ ውሳኔ እንዳልተላለፈ ከአትሌቶቹ ጋር ካታር የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክትር ዱቤ ጂሎ ለቢቢሲ ተናገሩ።

በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌቶች ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት እረፍት አድርገው እንዲያገግሙ እንጂ እገዳ አለመሆኑን ገልጸዋል።

ውሳኔው ከ42 ኪሎሜትሮች በላይ በሚሮጥበት ከባድ በሚባለው የማራቶን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሯጮችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰድ ተቀባይነት ያለው እረፍት ነው ብለዋል ዱቤ ጅሎ።

አትሌቶች የሦስት ወራት #የማገገሚያ ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ በዓለም አቀፍ የውድድር ሕግና ደንብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውና በሌሎችም ሃገራት የሚሰራበት እንደሆነ አመልክተዋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
VOA -TK Trim
AudioTrim
ማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ ወረዳ!

Via #VOA

@tikvahethiopia
#ጭልጋ

"ችግሩ የተፈጠረው ቅማንት ኮሚቴውን መያዝ መቻል አለብን፤ ወንጀለኛ ነው ብሎ ነው እያሰማራ ያለው ይሄን ፋኖ፤ ወደ 8 -9 ሰው ሞቶብናል፤ 7-8 ሰው ቁስለኛ አለ።...ፋኖ የሚባለው እራሱን የቻለ ልብስ ነው ያለው። ፋኖ ነው የሚለው..." የቅማንት ማህበረሰብ አባል
.
.
"ፋኖ የሚባል ጦር የለም! እውነታው ይሄ ነው" የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ
.
.
"በክልሉ ውስጥ በህዝቦች መካከል ግጭት እንዲነሳ ለማድረግ አጀንዳ ይዞ የሚሰራ ኃይል አለ። ይሄ ኃይል አሁን ፅንፈኛ የቅማንት ኮሚቴ አባላት ክልሉን ማተራመስ እንዲችሉ ማስታጠቅ ነው አንደኛው፤ ባለፉት አመታት እኔም ወደዚህ ቢሮ ከመምጣቴ በፊት ጄነራል አሳምነው በነበረ ጊዜም ከዚያም በፊት ሌሎች ቢሮ ኃላፊዎች በነበሩ ጊዜ ግጭት ነበር። ስለዚህ እዚህ ቢሮ ያለ ሰው በሙሉ ለቅማንት ፅንፈኛ ኮሚቴ ጠላት ነው። ጄነራል አሳምነው ነበር ጠላት ነው፤ ከዚያ በፊት አቶ ደሴ አሰሜ ነበር ጠላት ነው፤ ከዚያ በፊት አቶ እዘዝ ዋሴ ነበር ጠላት ነው፤ አሁን ደግሞ እኔ መጣሁ ጠላት ነኝ፤ ስለዚህ አጀንዳ መቅርፅ ነው። እዚህ ቢሮ ላይ የምንመደብ ሰዎች ህግና ስርዓት ለማስከበር በምናደርገው እንቅስቃሴ ስም ማጥፋት ነው፤ ስም ማብጠልጠል ነው።" የአማራ ክልል ሰላምና ግንባታ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘው ተሻገር

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ አመት የሥራ ዘመን የፊታችን ሰኞ መስከረም 26 በይፋ ይከፈታል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakePage ይህ ከ260,000 በላይ ተከታይ ያለውና በገጣሚ ሜሮን ጌትነት ስም ታየተከፈተ የፌስቡክ ገፅ ሀሰተኛ ነው። እጅግ በሚገርም ሁኔታ በገፁ የሚሰራጩት መልእክቶችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይክ እና ሼር ያደርጉታል። ፖስት የሚደረጉት ፎቶዎችም ከኢንስታግራም ገጿን የሚወሰዱ ናቸው።

Meron Getnet

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሜሮን ትክክለኛ የፌስቡክ አካውንቷ⬆️

ከወራት በፊት ታዋቂዋ ገጣሚ እና ተዋናይት ሜሮን ጌትነት በትክክለኛው የኢንስታግራም ገጿ እሷ የምትጠቀምበት የፌስቡክ አካውንቷ Meron Ghetnet የሚል ላይክ ፔጅ ያልሆነ እንደሆነ ገልፃ ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ #ሼር ያደረገችው September 24 2019 ነው።

Meron Ghetnet ላይክ ፔጅ አይደለም!

•Meron Getnet
•Meron Ghetnet

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን አቅም በተሻለ አግባብ ለማሳደግ መንግስት በዓለም አቀፍ የአጋርነት ትስስር ፈጠራ ዙሪያ በትኩረት እንደሚሰራ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ።

"በሳይንስ እና በከፍተኛ ትምህርት" ዙሪያ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሆኑ ዓለም አቀፍ ድርጅት ተዎካዮች፥ አጋር የልማት ድርጅቶች እና የውጭ ዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ "የአጋርነት እና የትስስር" መፍጠሪያ መድረክ በሸራተን አዲስ ሆቴል ተካሄዷል።

በመድረኩ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አቅም በተሻለ አግባብ ለማሳደግ መንግሥት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በዚህ ረገድ መንግስት ዓለም አቀፍ የአጋርነት ትስስር ፈጠራ ዙሪያ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አቅም ለማሻሻል ከአጋር አካላት እና ወዳጅ ሃገራት በትብብር እና በቅንጅት መስራት ወቅታዊ መሆኑን በአፅንኦት አብራርተዋል።

መንግሥት የጀመረውን ሃገራዊ የለውጥ ጉዞ ትርጉም ባለው ደረጃ በከፍተኛ ምርምር እና ቴክኖሎጂ ለማስደገፍ አጋር አካላትን እና ወዳጅ ሃገራትን ድጋፋቸው እንዲጠናከር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው።

ምንጭ፦የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት/EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Photoshop የ2012 የዩኒቨርሲቲ ምደባን በሚመለከት በርካታ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰረጩ ይገኛሉ። በተለይ የTIKVAH-ETHን ስም በመጠቀም የውሸት መረጃዎች እየተሰራጩ ስለሆነ ጥንቃቄ ይደረግ።

ከምደባ ጋር በተያያዘ አዲስ ጉዳይ ሲኖር እናሳውቃለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተመልከቱ⬆️

የኛም የኢትዮጵያውያን ነገር እንደዚህ እንዳይሆን ከመለያየት ይልቅ መቀራረብ፤ ከመጠላላት ይልቅ መዋደድ፤ ወንድምን እንደ ጠላት ከማየት ይልቅ ቀርቦ መነጋገር፤ ከጥላቻ ይልቅ ፍቅርን፤ ለጦርነት ከመዘጋጀት ይልቅ ለሰላም ዘብ መቆም በዚህች ሀገር ማንስፈን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። የኛ መበላላትን በጉጉት የሚጠብቁ የውጭ ኃይሎች አሉና እርስ በእርስ መተባበራችን እጅግ በጣም ወሳኝ ነው!!

ያለ ሀገር ሁሉም ከንቱ ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8

በTIKVAH-ETH ስም እየተሰራጨ ስለነበረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዩኒፎርም ጉዳይ ሀሰት ስለመሆኑ በAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት!


@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቻግኒ-ግልገል በለስ-ጃዊ መንገድ በአፈር መንሸራተት ተዘጋ!

ከቻግኒ ግልገል በለስ ጃዊ እና ሕዳሴ ግድብ በሚወስደው መንገድ የካር ተራራ ተደርምሶ በትራንስፖርት አግልግሎት ላይ መስተጓጓል ተጥሯል፡፡ የካር ተራራ ተደርምሶ መንገዱን በመዝጋቱ ተሽከርካሪዎች በቅብብሎሽ አግልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ከቻግኒ ግልገል በለስ ጃዊ እና ሕዳሴ ግድብ በሚወስደው መንገድ በተደጋጋሚ ብልሽት የሚደርስበት እና ዘላቂ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑን ደግሞ የግልገል በለስ የትራፊክ ቁጥጥርና ውሳኔ ሰጪ ባለሙያ ምክትል ሳጅን ፍቅሬ ኦጄ ተናግረዋል፡፡ የተደረመሰውን አፈር ለማንሳት እና መንገዱን ለመክፈት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ባለሙያው ተናግረዋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን መኖርያ ግቢ ውስጥ በቅርቡ ተከስቶ የነበረው ችግር ምንድን ነበር?

በAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ማረጋገጥ የተቻለው የዛሬ ሳምንት ማክሰኞ ለሊት ለእሮብ አጥቢያ ከለሊቱ 10:30 ላይ ግርግር ተፈጥሮ ነበር፦

- ግቢው ውስጥ አራት መንግስት የመደባቸው ጥበቃዎች ነበሩ፣ ነገር ግን የወ/ሮ ጠይባ መኪና ተሰባብሮ በዛውም ላፕቶፕ እንደተወሰደ ተሰምቷል። ነገር ግን ሁኔታው ዘረፋ ብቻ ይሁን ወይስ ሌላ በሀላፊዋ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር ገና እየተጣራ ነው ተብሏል።

- አራቱ ጠባቂዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል። ሌላው ይህ ሁኔታ ሲከሰት በግቢው ውስጥ አራት ሌሎች መኪናዎች እንደነበሩ እና ሰበራ እና ዘረፋ የተደረገበት ሀላፊዋ የሚጠቀሙበት መኪና ብቻ መሆኑን ነው።

- ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችም ከመኪናው ስር ትናንት እንደተገኙ ተሰምቷል።

Via Elias Meseret - ልዩ መረጃ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳ ከጥቅምት 18 እስከ 22 ድረስ እንደሚካሄድ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ክልልነት ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሃ ግብር ላይ ለውጥ መደረጉን በዛሬው እለት አስታውቋል። በሲዳማ ክልልነት ህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም መርሃ ግብር መሰረት የቅስቀሳ ጊዜ ከመስከረም 23 እስከ መስከረም 28 2012 ዓ.ም በሚል ታቅዶ እንደነበረ ይታወሳል።

ነገር ግን የህዝበ ውሳኔ ቅስቀሳው የመራጮች ምዝገባ ከሚደረግበት ጊዜ ጋር የተቀራረበ ቢሆን ይሻላል በሚል ስለታመነበት የቅስቀሳ መርሃ ግብሩ ከጥቅምት 18 እስከ ጥቅምት 22 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት እንዲሆን ማሻሻያ መደረጉን አስታውቋል። ቦርዱ በአፈጻጸም ጉዳዮች የተነሳ የሚኖሩ የቀናት ለውጥና መሸጋሸጎችን ወደፊትም ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ነው የገለፀው።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ልብስ በመስፋት የሚተዳደረው ወጣት የቶምቦላ ሎተሪ ሽልማቱን ተረከበ!

አቶ በላይ አሰፋ ይባላል፡፡ ነዋሪነቱ ደግሞ ከአዲስ አበባ ከተማ በ60 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው አስጎሪ ከተማ ነው፡፡ አቶ አሰፋ የ35 ዓመት ወጣት ሲሆን ልብስ በመስፋትና በመሸጥ ይተዳደራል፡፡ አንድ ቀን ልብስ እየሰፋ ሎተሪ አዟሪ ጠርቶ በ25 ብር የገዛት ቶምቦላ ሎተሪ በ5ኛ እጣ ዘመናዊ ሃይወንዳይ ክሬታ የቤት አውቶሞቢል ዕድለኛ አድርገዋለች፡፡ ዕድለኛውም እዛው በሚኖርበት አስጎሪ ከተማ የመኪና ሽልማቱን ሊረከብ ችሏል፡፡ ዕድለኛው ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው፡፡

Via የብሄራዊ ሎተሪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


አልሸባብ የሽብር ቡድን በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ አደጋ ሊያደርስ አስቦ ነበር ተብሏል!

የቀድሞዋ የአሜሪካ የተመድ አምባሳደር #ሱዛን_ራይስ ፕሬዝደንት ኦባማ ኢትዮጵያን በ2015 በጎበኙበት ወቅት አልሸባብ ጥቃት ለማድረስ እንቅስቃሴ አድርጎ እንደነበር ገልፀዋል። አክለውም በወቅቱ የኢትዮጵያ የደህንነት ሀላፊ የነበሩት ተጠርጣሪው በክትትላቸው ስር እንደሆነ ቢነግሯቸውም እነሱ ግን ጥርጣሬ ነበራቸው።

በመጨረሻም የደህንነት ሀላፊው ከተጠርጣሪው ጋር አየር መንገድ እንዳሉ (ተይዞ መሆኑ ነው) ሲነግሯቸው በፍጥነት ከነበሩበት የአፍሪካ ህብረት ወጥተው ወደ አየር ማረፊያው በማምራት ከኢትዮጵያ እንደወጡ በቴክሳስ ትሪብዩን ፌስቲቫል ላይ ተናግረዋል።

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


@tikvahethiopia @tsegabwolde
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የገዛቸውን 100 አውቶብሶችን ለአንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት አስረከበ። የርክክብ ስነ ስርዓቱ በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተገኙበት በመስቀል አደባባይ ተከናውኗል። አውቶቢሶቹ በአሁን ወቅት በአዲስ አበባ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል አስተዋፆኦ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡:

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መብረቅ ሶስት የቤተሰብ አባላት ገደለ!

በዋግህምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ ትናንት አመሻሽ ላይ በወደቀው መብረቅ ሶስት የቤተሰብ አባላት መሞታቸውን የወረዳው ፖሊስ ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡ የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ኢንስፔክተር ደጀን ወዳጅ እንደገለፁት የመብረቅ አደጋው የተከሰተው በወረዳው 02 ቀበሌ አሏቅ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትላንት ከቀኑ 12 ሰአት ላይ ነው።

አደጋው የደረሰው አንድ አባት ከሶስት ልጆቻቸው ጋር ሆነው እህል በመውቃት ላይ እንዳሉ ድንገት መጣል የጀመረውን ዝናብ ተከትሎ በወደቀው መብረቅ ምክንያት ነው ብለዋል። በመብረቁ የተመቱት አባት ከአንድ ወንድና አንድ ሴት ልጆቻቸው ጋር ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፉን ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል። የአራት ዓመት አድሜ ያላት አራተኛው የቤተሰብ አባል ደግሞ በመብረቁ ጉዳት ደርሶባት በተፈራ ሃይሉ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ትገኛለች ተብሏል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
ያዳምጡ⬆️

ልዩ መረጃ ከኤልያስ ጋር
በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8


17ኛው የዶሃ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናና የታላቁ ሩጫ ሽልማት ጉዳይ በAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በዋጋ ሊተመን የማይችል የተባለው እና የበ18ኛው ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ የነበረ የዘውድ ቅርስ ከኔዘርላንድስ ወደ አዲስ አበባ ሊመለስ መሆኑ ተገለፀ። የዘውድ ቅርሱ ሲራክ አስፋው በተባለ ኢትዮጵያዊ እጅ ላይ እንደነበረ እና ለሁለት አስርት አመታት በመኖሪያ ቤቱ ተደብቆ እንደቆየ ነው የተነገረው። በወርቅ ቅብ ያሸበረቀው የመዳብ የዘውድ ቅርስ ላይ የእየሱስ ክርስቶስ እና የአስራ ሁለቱ ሃዋሪያት ምስል ይታያል።

ይህ የዘውድ ቅርስ በአሁን ወቅት ደህንነቱ በተጠበቀ ስፍራ ላይ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን፥ በቅርቡ ለኢትዮጰያ መንግስት እንደሚተላለፍ የዘውድ ቅርሱን ለ21 ዓመታት ጠብቀው ያቆዩት አቶ ሲራክ አስፋው ተናግረዋል። ባለሙያዎች ይህ የዘውድ ቅርስ የኢትዮጵያን ባህላዊ የጥበብ ውጤቶች በከፍተኛ ሁኔታ ከሚያሳዩት አንዱ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የነብርጋዴር ተፈራ ማሞ ጉዳይ...
/በጀርመን ሬድዮ/

ከሰኔ 15 ቀን፣ 2011 ዓ.ም የባህርዳሩ ጥቃት ጋር በተያያዘ የእነ ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ሲመለከት የነበረው ባህር ዳር ወረዳ ፍረድ ቤት የተጠርጣሪዎችን ምርመራ አጠናቅቆ ተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ እንደማስፈልግ በማመልከት ሐምሌ 29 ቀን፣ 2011 ዓ.ም የ15 ቀናት የክስ መመስረቻ ጊዜ ፈቅዶ ፋይሉን ዘግቶ ለባህር ዳርና አካባቢው ፍርድ ቤት መላኩ ይታወሳል።

ኾኖም ቀሪ የምርመራ ሥራዎች አሉኝ በማለት መርማሪ ቡድኑ ለባሕርዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ጠይቆ ሲከራከር ቆይቷል፡፡ የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ነሐሴ 22 ቀን፣ 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት የባህር ዳር ወረዳ ፍርድ ቤት የወሰነውን ውሳኔ በማፅደቅ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ኤስፈልግም በሚል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

የመርማሪ ቡድኑ ጉዳዩን ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት በማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ ይግባኙ እንደፈቀድለት ቀደም ሲል ይግባኝ ጠይቋል፡፡ ዛሬ ለጋዜጠኞች ዝግ የሆነው የፍርድቤት ውሎን አስመልክተው ከተጠርጣሪ ጠበቆች አንዱ ለጀርመን ራድዮ በስልክ እንደተናገሩት ጉዳዩን ዛሬ 5 ዳኞች በተሰየሙበት ማብራራታቸውንና ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጥ ወይስ አይሰጥ በሚለው ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለመስከረም 27 ቀን፣ 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል፡፡

የባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ አያስፈልግም በማለት መዝገቡን ዘግቶ ወደ ባህርዳርና አካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት የላከው ሐምሌ 29 ቀን፣ 2011 ዓ.ም ነበር፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia