TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በጋምቤላ ከተማ በደረሰ የመብረቅ አደጋ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ!

በጋምቤላ ከተማ ትናንት በወደቀ መብረቅ የአንድ ሰው ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ቱት ኮርን እንደገለጹት ጉዳቱ የደረሰው ትናንት በከተማው ከቀኑ 11፣00 ሰዓት አካባቢ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በቀበሌ 04 እና 05  በወደቀው መብረቅ ነው።

በአደጋው የአንድ ሰው ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። የቆሰሉ ሰዎች በጋምቤላ ሆስፒታል ሕክምና የተደረገላቸው ሲሆን ከአንዷ ተጎጂ በስተቀር በአሁኑ ወቅት ሦስቱ የህክምና እርዳታ አግኝተው ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ምክትል ኮሚሽነሩ ተናግረዋል። በደረሰው የመብረቅ አደጋ ሁለት የቀንድ ከብቶች መሞታቸውንም ምክትል ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጉጉት የሚጠበቁት የዛሬ የፍጻሜ ውድድሮች!

በዛሬው እለት በጉጉት የሚጠበቁ ሁለት የፍጻሜ ውድድሮች አሉ።

1. የ5,000 ሜትር የወንዶች የፍጻሜ ውድድር (3፡10 ሰዓት 9፡10 PM)

•ሰለሞን ባረጋ
•ሙክታር እድሪስ
•ጥላሁን ኃይሌ

2. የ3,000 ሜትር መሰናክል ሴቶች ፍጻሜ ውድድር (3፡50 ሰዓት 9፡50 PM)

•መቅደስ አበበ

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን🇪🇹

Via Ethiopian Embassy in Doha
@tsegabwolde @tikvahethiopia
DOHA የምትገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ይህ መልዕክት ይድረሳችሁ--ለሌሎች ኢትዮጵያውያንም አጋሩ!

የዛሬ ትኬቶች እና ትራንስፖርት፦

በዛሬው እለት በኸሊፋ ስታድዮም የሚካሄዱትን አጓጊ የፍጻሜ ውድድሮች ለመከታተል እንዲቻል ነጻ ትኬቶች እና ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል። በዚህ መሰረት፡-

1. ደዋር ኩቱብ - አብዱራዛቅ - 70942736
2. J & P እና ካርዋ (አውቶቡስ የሚቆመው J & P በር ላይ) - ገላን -70770855
3. ረያን ሻፊ መስጊድ - ታጁ - 50460642
4. ሙራ ደዋር ሱዳን - ሙዘሚር -74724591
5. ነጅማ - አብዲሳ - 77391868

የሁሉም አውቶብሶች የመነሻ ሰዓታቸው 11፡15 (5:15 PM) ነው።

Ethiopian Embassy in Doha የተላለፈላችሁ መልዕክት!

#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአልሸባብ የሽብር ቡድን ጥቃት ፈፀመ!

ከሶማሊያ የወጡ መረጃዎች እንዳመለከቱት የአሜሪካ ወታደሮች የሶማሊያ አቻቸውን በሚያሰለጥኑበት ወታደራዊ ካምፕ ላይ የአልሸባብ ታጣቂ ኃይሎች ጥቃት መፈጸማቸው ተነግሯል።

የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት በደቡባዊ ሶማሊያ የታችኛው ሸበሌ ክልል ውስጥ ባሊዶግሌ የአውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ ተኩስና ከባድ ፍንዳታ እንደነበር ተናግረዋል። ጥቃት አድራሹ ቡድን መኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ መግቢያ በሩ አካባቢ ያፈነዱ ሲሆን ከፍንዳታው በኋላ ታጣቂዎቻቸው ወደ ውስጥ እንዲገቡ አድርገዋል።

የወታደራዊ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ወደ ኋላ አፈግፍገዋል። አልሻባብ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱን እንደፈጸመ አስታውቋል። "በከባድ የሚጠበቀውን ካምፕ ጥሰው ከገቡ በኋላ ወታደራዊ ተቋሙ ውስጥ ከነበሩት የውጪ ኃይሎች ጋር ታተኩሰዋል" ብሏል በመግለጫው።

ወታደራዊ ካምፑ ከዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በስተምዕራብ 100 ኪሎ ሜትሮች ያህል ርቆ የሚገኝ ሲሆን፤ ካምፑ የአሜሪካና የሶማሊያ ልዩ ኃይሎች እንዲሁም የኡጋንዳ ሠላም አስከባሪዎች የሚገኙበት መሆኑም ተነግሯል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ 6 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ #ጎን የሚገኘው የእቴጌ መነን አዳሪ ትምህርት ቤት ለ2012 የትምህርት ዘመን በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያላቸው 500 ሴት ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የእቴጌ መነን ትምህርት ቤት እያደረገ ያለውን ዝግጅት ተመልክተዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dr. ABIY

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በቱሪዝም ዘርፍ ላደረጉት አስተዋጽኦ ያገኙትን የ2019 የወርልድ ቱሪዝም ፎረም ሽልማት ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀበሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሽልማቱን ከወርልድ ቱሪዝም ፎረም ፕሬዚዳንት ቡሉት ባጊቺ ነው የተቀበሉት። እ.አ.አ በ2020 የሚካሄደው የዓለም የቱሪዝም ፎረም በአዲስ አበባ እንዲካሄድም ተወስኗል።

ምንጭ፦ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝደንት ሽመልስ አብዲሳ እና የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትሯ ዶ/ር ሒሩት ካሳው የኢሬቻ ባዛር እና ኤግዚቢሽን በይፋ ከፈቱ። በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የተከፈተው ባዛር እና ኤግዚቢሽኑ ከዛሬ ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
“የጥፋት ሀይሉ ዋና ዓላማው የመተማ–ጎንደር መንገድን ዘግቶ ባለሀብቶች ምርታቸውን በወቅቱ እንዳይሰበስቡ እና ለገበያ እንዳያደርሱ በማድረግ በኢኮኖሚ ማዳከም ነው፣ በዚህ ደግሞ አንደራደርም፤ በአጭር ጊዜ መንገዱ ክፍት ይሆናል” የአማራ ክልል የሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ኃለፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር 
.
.
የጸጥታ ችግር በተከሰተበት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ ዛሬ አንጻራዊ #ሰላም መኖሩን የክልሉ ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ ማምሻውን አስታውቋል፡፡ በጭልጋና አካባቢው በተፈጠረው ግጭት የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ ንብረት ወድሟል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎችም ችግሩ እልባት እንዲያገኝ እየጠየቁ ነው፡፡ 

የተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-30

ምንጭ፦ AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ እድገት ላበረከቱት አስተዋጽዖ የዓለም የቱሪዝም ፎረም የሰጣቸውን እውቅና ሲቀበሉ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ18 አመት በታች ለሆኑ ልጆች ፓስፖርት ለማውጣት!

ከ14-18 አመት ለሆኑ ልጆች፦

1. የልደት ምስክር ወረቀት
2. የህፃኑ ሁለት ጉርድ ፎቶ
3. ከወላጆች አንዱ እና ፓስፖርት የሚወጣለት ህፃን በአካል መቅረብ አለባቸው።

ከ14 አመት በታች ለሆኑ ደግሞ፦

1. የልደት ምስክር ወረቀት
2. የህፃኑ ሁለት ጉርድ ፎቶ
3. ከወላጆች አንዱ የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ
4. ከወላጆች አንዱ እና ፓስፖርት የሚወጣለት ህፃን በአካል መቅረብ አለባቸው።

#INVEA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፓስፖርት እድሳትን እና አዲስ ፓስፖርት ማውጣትን በሚመለከት በተደጋጋሚ ለሚነሱ ጥያቄዎች ከINVEA የተሰጠ ማብራሪያ!

አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፦

የሚያስፈልጉት የልደት ምስክር ወረቀት እና የአገልግሎት ጊዜው ያላለቀ የቀበሌ መታወቂያ ብቻ ሲሆኑ ምንም አይነት ተጨማሪ ማስረጃ አያስፈልግም፡፡ የሚወስደው ጊዜ ከአመለከቱ በኋላ ከ45 ቀን በኃላ ነው፡፡ ሆኖም በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ፓስፖርት #በአስቸኳይ ማግኘት ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጉዳዩን አስቸኳይነት የሚያሳዩ ማስረጃዎች ያስፈልጋሉ፦
ጉዳዩ የስራ ከሆነ ከመስሪያቤት የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ እና የመስሪያ ቤቱ መታወቂያ
የህክምና ወረቀት(ሪፈር)
ጊዜ ያለው የውጪ ሃገር መኖሪያ ፍቃድ
ጊዜ ያለው የውጪ ሃገር የስራ ፍቃድ
የኢምባሲ ቀጠሮ
ተመላላሽ መንገደኞች ሆነው ፓስፖርት ገፁ ያለቀባቸው ፓስፖርቱን ይዞ መቅረብ
የአለም አቀፍ ድርጅቶች
ጊዜ ያለው የባህረኞች መታወቂያ (ሲማንቡክ) ሆነው የሁሉም አገልግሎቶች አከፋፈል ሁኔታ እንደአገልግሎቶ የተለያየ ነው፡፡

ለፓስፖርት እድሳት፦
የቀበሌ መታወቂያ እና ፓስፖርት ኮፒ

የጠፋ ፓስፖርት፦
የቀበሌ መታወቂያ እና የፖሊስ ማስረጃ

ስለሆነም ማንኛውም ዜጋ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ ከቀረበ አገልግሎቱን የማግኘት ሙሉ መብት እንዳለው #INVEA ይገልጻል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ4G ኢንተርኔት በክልል ከተሞች...

ኢትዮ ቴሌኮም/ethio telecom/ በኢትዮጵያ ክልል ከተሞች የአራተኛ ትውልድ ወይም 4G ኢንተርኔት አገልግሎት ሊጀምር መሆኑ አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ ክልል ከተሞች የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር መጨመሩን የጠቀሰው ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ያለውንየኢንተርኔት አገልግሎት ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከያዝነው ዓመት ጀምሮ የ4G ኢንተርኔት አገልግሎትን እንደሚያስፋፋ ገልፅዋል፡፡ ባህርዳር፣ መቐለና አዳማ የአራተኛ ትውልድ ወይም 4G ኢንተርኔት ዝርጋታ ከሚደረግባቸው የኢትዮጵያ ክልል ከተሞች መካከል ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ በአዲስአበባ ብቻ ተወስኖ የቆየው የአራተኛ ትውልድ ኢንተርኔት አገልግሎትን ወደ ክልል ከተሞች  የማስፋፋት ስራ የኢትዮ ቴሌኮም የሶስት ዓመት የስራ እቅድ አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via #DW/የጀርመንር ድምፅ ሬድዮ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዋልታ_ቲቪ

የ5,000 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ውድድር በቀጥታ በዋልታ ቴሌቪዥን መከታተል ትችላላችሁ። #DOHA #ETHIOPIA

መልዕካም እድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ አትሌቶች!

በተጨማሪ፦

HD on AD Sports 4 (Nile Sat)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አለን! ወርቅ እና ብር ለእናታችን!

1ኛ ሙክታር እድሪስ🇪🇹
2ኛ ሰለሞን ባረጋ🇪🇹
4ኛ ጥላሁን ኃይሌ🇪🇹

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ አለን!!

ኢትዮጵያችን!!
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እኛም ኮራን በናተ...
እውነት ኮራን በናተ...


@tsegabwolde @tikvahethiopia
አንድነት ፤ መተጋገዝ ፤ ፍቅር እንዲሁም አሸናፊነት በ5,000 ሜትር ዉድድር ላይ...

የሙክታር እድሪስ የመጨረሻዎቹ መስመር ደስታ አገላለፅ ሁሉንም ይናገራል።

እንኳን ደስ አለን በድጋሚ!!!

Join @tikvahethsport
#DOHA

#WorldAthleticsChamps
3000m steeplechase

🇰🇪#beasteeple 🥇
🇺🇸 #emmajcoburn 🥈
🇩🇪#GesaFK 🥉

@tsegabwolde @tikvahethiopia

የመግቢያ ነጥብ ዝቅ ተደረገ!

#ASTU #AASTU

የአዲስ አበበ እና አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲትዎች መግቢያ ነጥብ ዝቅ አለ!

የተማሪዎችን ፍላጎትና በተደጋጋሚ የሚነሳውን የመግቢያ ነጥብ ዝቅ ይበልልን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት የAPPLIED SCIENCE መግቢያ ሆኖ በማስታወቂያ የተገለጸው ለወንድ፡190 እና ለሴት፡185 ከነበረው ዝቅ ተደርጎ

ለወንድ፡ 176 እና
ለሴት፡166

የAPPLIED SCIENCE መግቢያ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን እያሳወቅን እስከ ነገ መስከረም 20/01/2012 ዓ.ም. ማታ 12፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዚህ መስክ መመደብ የምትፈልጉ የ2011ዓ.ም. የዪኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈታኞች፤ ለት/ቤታችሁ ፍላጎታችሁን በመግለጽ ምርጫችሁን ት/ቤታችሁ እንዲያስገባላችሁ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

https://app.neaea.gov.et/

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ


@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲ ምደባን በተመለከተ ይፋ የተደረገ መረጃ የለም አዲስ መረጃ ሲኖር ቲክቫህ ኢትዮጵያ አጣርቶ ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia