TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ASTU & AASTU ትናንት ምሽቱን ተማሪዎች ውጤታቸው እየተመለከቱ እንደነበር በእኛ በኩል በርከት ያሉ ተማሪዎችን ውጤት እና ምደባ ለማየት ብንችልም ዌብሳይቱ ከለሊቱ 7 ሰዓት ጀምሮ እየሰራ እንዳልሆነ ተመልክተናል። የተፈጠረውን ለማጣራት ጥረት እናደርጋለን።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለመላው ክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነት እና የበረከት ይሁንላችሁ!

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GONDAR

የመስቀል ደመራ በዓል በጎንደር ከተማ መከበር ጀምሯል፡፡ ጧት ላይ በየቤቱ የተጀመረው የደመራ መለኮስ ሥነ ስርዓት ረፋድ ላይ ደግሞ በመስቀል አደባባይ በድምቀት በከተማ ደረጃ የሚከናወን መሆኑ ታውቋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SEKOTA

በሰቆጣ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነው፡፡ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነው፡፡ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደርና በጎንደር አካባቢዎች የደመራ በዓል በመስቀል ዕለት ነው የሚከወነው፡፡ ምዕመናን በተገኙበት ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ተከትሎ ዛሬ የደመራ መለኮስ መርሀ ግብር እየተካደ ነው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DOHA

ሁሉም አትሌቶቻችን ውድድር ሲያቋርጡ፤ ሮዛ ህመም አጋጥሟት ሆስፒታል ተወስዳለች!

መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ሌሊት 6፡00 ሰዓት ላይ በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ውድድር ላይ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ሁሉም አቋርጠዋል፡፡

አንደኛዋ ተወዳዳሪ ሮዛ ደምሴ ህመም ያጋጠማትና ሙቀቱን ልትቋቋም ባለመቻሏ ወደ ሆስፒታል ተወስዳለች፡፡ ሮዛን ተከትላ ያቋረጠችው ደግሞ ሩቲ አጋ ስትሆን መጀመሪያ አካባቢ የነበራት አቅምና ፊቷ ላይ ይነበብ የነበረው የውድድር መንፈስ በጣም ጥሩ ቢሆንም ከ15 ኪ.ሜ በኋላ ግን መቀጠል አልቻለችም ሲል ፌዴሬሽኑ አስታውቋል፡፡

ሙቀቱን በከፍተኛ እልህ ለመቋቋም የሞከረችው ሶስተኛዋ ተወዳዳሪ ሹሬ ደምሴም ከነ ሩቲ በኋላ አቋርጣለች፡፡ በእለቱ የነበረው ሙቀት መጠን 32 እና ከዚያ በላይ ዲግሪ ሴንቲግሬድ መድረሱ ተገልጿል፡፡

Via #EPA
PHOTO: #AryatRyan
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰራተኞች በመገደላቸው ፋብሪካው ስራ እንዳቆም ተሰምቷል!

በኦሞ ሸለቆ ተፋሰስ ላይ በተገነቡት ሁለት የስኳር ፋብሪካዎች በማገልገል ላይ የሚገኙ አራት ሰራተኞች በስራ ላይ እያሉ መገደላቸውና ሰራተኞች የፀጥታ ስጋት ላይ በመውደቃቸው ፋብሪካው ስራ እንዳቆመ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የሰራተኞች ማህበር አስታወቀ።

በአካባቢው ላይ ያለው የእርስ በእርስ ግጭትም በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጋሻው አይችልሁም ተናግረዋል።

የስኳር ኮርፖሬሽን መሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር ሊቀ መንበር ጋዲሳ ደሳለኝ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንዳስታወቁት ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በአከባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በፋብሪካ ሰራተኞች ላይ የሚፈፅሙት የግድያ ጥቃት እየተበራከተ መጥቷል ብለዋል። እንደ ሊቀ መንበሩ ገለፃ ታጣቂዎቹ ሰሞኑን ብቻ በተከታታይ በፈፀሙት ጥቃት የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ሹፌርን ጨምሮ በሸንኮራ ማሳ ላይ የተሰማሩ በርካታ ወዛደሮች ለሞትና ለጉዳት ተዳርገዋል ሲሉ ገልፀዋል። ለዚህም ግጭት መነሻ የሆነው የአካባቢው አርብቶ አደሮች አርስ በእርስ በመጋጨታቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

በወቅቱ በፋብሪካው ለሚሰሩ ሰራተኞች ምግብ የሚመጣው ከጂንካ ከተማ ቢሆንም በአካባቢው ባለው አለመረጋጋት የተነሳ ቀርቷል። በዚህም ምክንያት በርካታ ሰራተኞች ስራቸውን ለቀዋል።

ምንጭ፦ መሰረት አበጀ/Addis Maleda/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ.ም መደበኛ ተማሪዎችን ለመቀበል ሲያደርገ የቆየውን ዝግጅት አጠናቆ ተማሪዎችን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የስራ ኃላፊዎችም ትላንት መስከረም 16/2012 ዓ.ም የተማሪዎቹን አገልግሎት መስጫ ማዕከላት (የተማሪዎች ማደሪያ፣ መመገቢያ አዳራሾችን እና የመዝናኛ ቦታዎችን) ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱም የተቋሙ ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ የኮሌጅ ዲኖች እና የተቋማት ዳይሬክተሮች ተማሪዎቻቸው የሚያርፉባቸውን ማደሪያ ክፍሎችና ሌሎች አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ዝግጁ መሆናቸውን በማረጋገጥ የተማሪዎቹን መግባት በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በወላይታ ሶዶ ከተማ ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ከ2 ሚሊዮን 400 ሺ ብር በላይ የመንግስት ገንዘብ በመመዝበር በከፍተኛ የሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ፡፡

ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት የመንግስትን ገንዘብ ወደግል ሂሳብ ሲያዛዉሩ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወላይታ ሶዶ ዲስትሪክትና ነዋሪዎች ባደረሱት ጥቆማ ፖሊሲ ያዝኳቸው ያላቸው ከ22 በላይ ግለሰቦች በከተማ አስተዳደሩ የመንግስት የስራ ሃላፊነት ላይ ያሉ ናቸው፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ስነ-ምግባር ኦፊሰር አቶ ቶማስ ገብረየሱስ እንደገለጹት ግለሰቦቹ ሃሰተኛ ሰነድ በማዘጋጀት ተገቢ ያልሆነ የአትክልትና ማሳ ግምት፤ ገማች ባለሙያና ተቀባይ በማዘጋጀት ከ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የመንግስት ገንዘብ በመመዝበር ወንጀል የተጠረጠሩ ናቸው፡፡

ቀጥተኛና ቀጥተኛ ባልሆነ መልኩ ወንጀሉን በማቀናበር እጃቸዉ ያለባቸዉ ግለሰቦችን በህግ ጥላ ስር በማዋል የህግ የበላይነትን ለማስከበር ከተማ አስተዳደሩ ማህበረሰቡን በማሳተፍና የምርመራ ቡድን በማቋቋም ተግቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-28
ፎቶ📸የኢሬቻ በዓል በዛሬው ዕለት በሃዋሳ ከተማ እየተከበረ እንደሚገኝ SMN ዘግቧል። #Irrecha #HAWASSA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና!

በተሽከርካሪ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ዛሬ ሌሊት በተከሰተ የተሽከርካሪ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንስፔክተር መሃመድ አሊ እንደገለጹት ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በደረሰው የትራፊክ አደጋ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ በ14 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። ከሟቾቹ መካከል የደብረብርሃን ከተማ ትራፊክ ፖሊስ አባልን ጨምሮ ሦስት የአንድ ሰው ቤተሰቦችና ሁለት ህጻናት እንደሚገኙበት ኢንስፔክተር መሃመድ አስታውቀዋል።

ጉዳት የደረባቸውን ሰዎች ወደ ደሴ ሪፈራል ሆስፒታና አጣዬ የመጀመ ደረጃ ሆስታል በማጓጓዝ ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ነው ተብሏል። አደጋው የደረሰው 24 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስ አባ ወደ ደሴ ሲጓዝ የነበር ኮድ3- ኤ71430 አአ ሀይሩፍ ከተቃራኒ አቅጫ ይጓዝ ከነበረ ኢት- ኮድ 3- 91889 ከሆነ ተሳቢ መኪና ጋር በመጋጨቱ መሆኑ ተመልክቷል።

የተሳቢዉ አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የሀይሩፉ አሽከርካሪ በህይወት መኖሩ አለመኖሩን ለማረጋገጥ የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል። የአደጋው መንስኤም መንገዱ ጠመዝዛ ከመሆኑ አንጻር ከፍጥነት በላይ በማሽከርከር ሳይሆን እንደማይቀር አስታውቃል። የሌሊት ጉዞ ህገ ወጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ቢገለጸም አሽከርካሪዎችም ሆኑ ህብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነት ህገ ወጥ ድርጊት በመቆጠብ ህይወትንና ንብረትን ለማዳን የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቦሮ-ሽናሻ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የ«ጋሪ-ዎሮ» በዓል ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ነው፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#WashingtonDC

በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ የሚገኙ ሁለት ገዳማትን ጨምሮ 40 አብያተ ክርስቲያናት በ40 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድነት ሆነው የመስቀል ደመራን በዓልን ማክበራቸው ተገለጸ፡፡

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ በበዓሉ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት አብያተ ክርስቲያናቱ በዓሉን በአንድነትና በድምቀት በማክበራቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

‹‹አብሮነቱ ተጠናክሮ ቀጥሎ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚገኙ ወግኖቻችንን አንድነት ይበልጥ በማጎልበት ኢትዮጵያን ታላቅ እናድርግ›› የሚል ጥሪም አምባሳደር ፍጹም አቅርበዋል።

ምንጭ፡- በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመስቀል ደመራ በዓል በዛሬው ዕለት በተለያዩ ከተሞች በደማቅ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት እየተከበረ ይገኛል። በዛሬው ዕለት የመስቀል ደመራ በዓል ከሚከበርባቸው ከተሞች መካከል ጎንደር፣ ሞጣ፣ እስቴ መካነ ኢየሱስ፣ ገንዳ ውኃ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ ሰቆጣ ይጠቀሳሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዉስጥ ሱሪ (በፓንት) ዉስጥ ተደብቆ ሊወጣ የነበረ 12 ሺህ ዶላር ተያዘ!

አንድ ግለሰብ 12 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በፓንቱ ውስጥ ደብቆ ከሀገር ሊያስወጣ ሲሞክር በቶጎጫሌ ኬላ ፈታሾች እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡ ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ተጠርጣሪው ይህንኑ ተግባር ለመፈጸም ሲጠቀምባቸው የነበሩ የ3 የተለያዩ ባንክ ደብተሮችም አብረው ተይዘዋል።

ምንጭ፦ የገቢዎች ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#HAWASSA የኢሬቻ በዓል በሃዋሳ ከተማ ተከብሮ ውሏል። በበዓሉ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች ተገኝተው ነበር። የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ እንዲሁም የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ አደም በበዓሉ ላይ ተገኝተው መልዕክት ኣአስተላልፈዋል። የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ በቀናት በኃላ በአዲስ አበባ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች ለመገኘት ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የግሸን ደብረ ከርቤ ሙዚየም የምረቃ ሥነ ስርዓት በአሁን ሰዓት እየተከናወነ ነው። በሥነ-ስርዓቱ የደቡብ ወሎ ዞንና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል አቡነ አትናቲዮስን ጨምሮ የዞንና የፌዴራል የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ሙዚዬሙ በግሸን ደብረ ከርቤ የሚገኙ ጥንታዊ ቅርሶችን በዘመናዊ መንገድ ለመሰነድና ለጎብኝዎች ምቹ ለማድረግ እንደሚያግዝ ታስቦ የተገነባ ነው።

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BBC

የትናንቱ የመስቀል ደመራ አከባበር ውዝግብ በቢሺፍቱ ከተማ!

ትናንት ከኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ተነስተው፤ ወደ ደመራ ለመሄድ መንገድ ላይ ሳሉ፤ "ያልተፈቀደ ሰንደቅ አላማ ይዛችኋል" በሚል ማለፍ መከልከላቸውን የቢሾፍቱ ኪዳነ ምሕረት አገልጋዮችና ምዕመናን ለቢቢሲ ተናገሩ።

የዓደአ ወረዳ ቤተክህነት ጸሀፊ መጋቤ ጥበብ እውነቱ ጥላሁን፤ ከደመራው ዕለት ቀደም ብለው ከከተማው አስተዳደር ጋር በበዓሉ አከባበር ዙሪያ ለመነጋገር ስብሰባ ቢያደርጉም ባለመግባባት እንደተለያዩ ያስታውሳሉ።

የኢሬቻ እና የመስቀል በዓል በሰላም እንዲያልፍ ከአድባራት ኃላፊዎች፣ ከምንጣፍ አንጣፊ ማኅበራት እና ከሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ጋር በመሆን ውይይት ተካሂዶ እንደነበር የሚያስታውሱት ጸሀፊው፤ "ልሙጥ ባንዲራ መያዝ ትችላላችሁ፣ አትችሉም" የሚለው ውይይት ላይ የሌሎች እምነት ተከታይ ኃላፊዎች መሳተፋቸው እንዳላስደሰታቸው ይናገራሉ።

ከዚህ ስብሰባ በኋላ ግን፤ የከተማው ከንቲባ ጠርተዋቸው ይቅርታ እንደጠየቋቸውና በሰንደቅ አላማ ጉዳይ ተነጋግረው፤ ልሙጥ (ኮከብ የሌለው) ባንዲራ መያዝ በሕግ ስለማይፈቀድ፤ ይዘው መውጣት እንደሌለባቸው መስማማታቸውን ይናገራሉ። የበዓል ማድመቂያ ሪቫኖችን ግን በአደባባይ ላይ አስረው በዓሉ በድምቀት እንዲከበር እንደተስማሙ ያክላሉ።

መላከ ሰላም አባ ሩፋኤል በቢሾፍቱ የደብረ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ሲሆኑ፤ የመስቀል በዓልን ለማክበር በቢሾፍቱ የሚገኙ አድባራት በአጠቃላይ ወደ መስቀል አደባባይ እንደሚወጡ አስታውሰው፤ ሁሉም ቤተክርስቲያናት በወጣላቸው መርሃ ግብር መሰረት ወደ መስቀል አደባባይ መምጣታቸውን ይገልፃሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BBC-09-28
https://www.bbc.com/amharic/49862568
ፎቶ📸በዛሬው ዕለት በውቢቷ ሃዋሳ ከተማ በተከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ነበር። #HAWASSA #IRRECHA2019

PHOTO : OROMIA MEDIA NETWORK

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ዮዮ_ጊፋታ

የአማራ ክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ በዮዮ ጊፋታ (የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል) ለመሳተፍ ወላይታ ገብቷል። ልዑኩ በወላይታ ቆይታው የሁለቱን ሕዝቦች ትስስር የሚያጠናክሩ ተግባራትን እንደሚያከናውን ታውቋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በመስቀል በዓል ወቅት በየአካባቢው እርድ እንደሚከናወን ይታወቃል፤ በዚህ ወቅት ለምግብነት የማያሆኑ የእንስሳት ሰውነት ክፍሎች በየሜዳው ይጣላሉ ይህ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ ድርጊት ነው። እየቆየ ሲሄድም በሚፈጥረው ከባድ ሽታ ለሰዎች #ህመም ምክንያትም ይሆናል። ህብረተሳቡ ከበዓሉ ጎን ለጎን በእርድ ወቅት ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል። አካባቢውንም ከብክለት ሊጠብቅ ይገባል።" መስፍን አየለ

@tsegabwolde @tikvahethiopia