TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከጅማ⬆️

"ዛሬ በጅማ በሰማ አካባቢ ልጆች አስተባባሪነት የደም ልገሳ ፕሮግራም እየተካሄደ ነው፤ በጣም ብዙ ሰው ደም ለግሷል። በተለይ የአካባቢው ወጣት፣ ሴት ወንድ ሳይል ብዙ ሰው ተሳትፏል። ለመላው የእርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የመስቀል ደመራ በዓል እንዲሆንም እንመኛለን!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DebreTabor

የደብረ ታቦር ከተማ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የመስቀል በዓል የሚከበርበትን የዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ አደባባይን ዛሬ አጽድተዋል። ‹‹የእስልምና ሃይማኖት ከክርስትና ሃይማኖት ጋር አብሮ የኖረ እና የተዛመደ በመሆኑ አብሮነታችንን ለመግለፅ የጽዳት ሥራውን አከናውነናል›› ብለዋል። ‹‹አንዳንድ አካላት የእስልምና እና የክርስትና ሃይማኖትን በማጋጨት የራሳቸውን የፖለቲካ አጀንዳ ለማስተላለፍ ቢጥሩም አብሮነታችንን ከጥንት ጀምሮ የቆየ በመሆኑ ሊነጣጥሉን አይችሉም›› የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል።

ባለፈው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በዓል በሚያከብሩበት ወቅት የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች መስጅድ እና የመስገጃ ቦታዎችን ማጽዳታቸው የሚታወስ ነው።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...ምንም የተደበቀ ዓላማ የለውም!" የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን
.
.
ትላንት መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ.ም በሚዲያ አማካኝነት የተሰራጨው ጋዜጣዊ መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የራሷ አርማና ሎጎ መያዝ አትችልም አላልንም እኛ ያልነው የኢትዮጵያ ህዝብ ያልተግባበት የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አርማ ይዞ መምጣት አይቻልም ነው ያልነው። ምክንያቱም በዓሉ የሀይማኖት መሆኑ ቀርቶ በፖለቲካ ፓርቲዎች ተጠልፎ የፖለቲካ አጀንዳ መጠቀሚያ ሆኖ ወደ ግጭት እንዳያመራ ነው። ይህንን ታላቅ በዓል በርካታ የዓለም ሚዲያዎች የሚዘግቡት ስለሆነ መንገዱን ስቶ ገጽታችንን ማበላሸት የለበትም ፣ ወደ ግጭት የሚያመሩ ነገሮች ሁሉ ይወገዱ፤ ህዝበ ክርስቲያን ይህንን በዓል በድምቀት አክብሮ አምላኩን አመስግኖ በደስታ ያለምንም የፀጥታ ችግር ወደ ቤቱ እንዲመለስ ነው። ከዚህ ውጭ ምንም የተደበቀ ዓላማ የለውም።

ፖሊስ ለሰላም፤ ሰላም ለሁሉም!

ETHIOPIAN FEDERAL POLICE COMMISSION

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ሽጉጥና ልዩ ልዩ ድምፅ የሌላቸው መሳሪያዎች በትናንትናው ዕለት መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ!

በትናንትናው ዕለት በአዲስ አበባ በመንገድ ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ሽጉጥና ልዩ ልዩ ድምፅ የሌላቸው መሳሪያዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመጣመር በምሽቱ ክፍለ ጊዜ በአስሩም ክፍለ ከተሞች ድንገተኛ የመንገድ ላይ ፍተሻ አድርጓል፡፡

በዚህም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ልዩ ስፍራው ሳሪስ አቦ አካባቢ ዓይነቱ ካሪና የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2-69099 አ.አ መኪና ውስጥ 8 ስታር ሽጉጦች ከአምስት ተጠርጣሪዎች ጋር ተይዟል፡፡ በተመሳሳይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ12 ግለሰቦች ላይ 3 ገጀራ፣ 12 ጩቤ እንዲሁም ዓይነቱ ቪትዝ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 2B-36293 አ.አ ተሽከርካሪ ውስጥ 1300 የአሜሪካ ዶላር መያዙን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ የተሳተፉ ግለሰቦችን ጉዳይ እያጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቆ ህብረተሰቡ የፀጥታ ጉዳይ የጋራ ጉዳይ መሆኑን በመረዳት በፍተሻ ወቅት ላደረገው ከፍተኛ ትብብር ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ ይኸው የህብረተሰቡ ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Via Addis Abeba Police Commission
@tsegabwolde @tikvahethioia
#AAWSA

በቀን 40 ሺህ ሜትር ኪዩብ ውሃ የሚያመርተው የለገዳዲ ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት ከትናንት ጀምሮ አገልግሎት እየሰጠ አለመሆኑን የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ቦሌ አራብሳ፣ ቦሌ አያት (1፣ 2፣ 3፣ እና 4)፣ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ አያት፣ የካ አባዶ፣ የካ ጣፎ እና ኮተቤ ገብርዔል አካባቢ ላሉ ደንበኞቹ ውሃ ማሰራጨት አለመቻሉን የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን የስራ ሂደት መሪ ሰርካለም ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

የኢ/ኤ/ አ ለተፈጠረው የትራንስፎርመር ችግር መፍትሄ ለመስጠት እየሰራሁ ነው ቢልም እስካሁን ለችግሩ እልባት መስጠት አለመቻሉን የተናገሩት ወይዘሮ ሰርካለም ጌታቸው የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ በዚህ ወር በተደጋጋሚ የተከሰተ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እፀገነት አንተነህ⬆️ "የ27 አመቷ የአየር መንገድ ሒሳብ ሰራተኛ እፀገነት አንተነህ ትናንት ማክሰኞ ጠዋት ወደ ሰራ በምታመራበት ወቅት #ጭካኔ በተሞላበት ወንጀል አቃቂ መንገድ ላይ ተገድላ ተጥላ ተገኘች። ፓሊስ ምርመራ ላይ ነው። ቀብሯ ዛሬ ተፈፅሟል። ቀለበት አድርጋ ሰርግ ለመደገስ ዝግጅት ላይ ነበረች።" ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት/#CAPITAL/ @tsegabwolde @tikvahethiopia

እፀገነትን የገደሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የነበረችውን ወ/ሮ እፀገነት አንተነህን የገደሉ ሦስት #ተጠርጣሪዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ወ/ሮ እፀገነት አንተነህ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12 ሰዓት 30 አቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ወደ ስራ ለመሄድ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ወንጀል ለመፈፀም አቅደው የትራንስፖረት አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል ሟችን በባጃጅ ተሽከርካሪ ከሳፈሯት በኋላ አንቀው እንደገደሏት ተጠርጥረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የሟችን አስክሬን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ አካባቢ መንገድ ላይ ጥለዋት እንደተሰወሩ ነው ፓሊስ የገለፀው፡፡ ወንጀሉን የፈፀሙ ግለሰቦች አለመታወቁ የፖሊስን ስራ እጅግ አስቸጋሪ ቢያደርገውም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀሉ ከተፈፀመ ጀምሮ ቀንና ሌሊት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ሦስቱን ተጠርጣሪዎች በዘጠነኛው ቀን በትናትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በርካታ የአካባቢው ሰዎችና የሟች ቤተሰቦች በተገኙበት መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ/ም ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙት መርተው አሳይተዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ፒያሳ አካባቢ በአንድ ግለሰብ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መያዙን አስታውሷል፡፡ ህብረተሰቡም ወንጀለኞችን አጋልጦ በመስጠት እና ምስክር በመሆን እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አድንቆ ይህንኑን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸እፀገነትን የገደሉት ሦስት ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙ መርተው አሳይተዋል፡፡ #AddisAbeba
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ እነዚህን #ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከፍተኛ ክትትል እንዳደረገና፤ ሦስቱን ወንጀል ፈፃሚዎች ወንጀሉን በፈፀሙ በዘጠነኛው ቀን መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ/ም በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸እፀገነትን የገደሉት ተጠርጣሪዎች ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙ መርተው ባሳዩበት ወቅት በርካታ የአካባቢው ሰዎችና የሟች ቤተሰቦች ተገኝተው ነበር።

Photo: Addis Abeba Police Commission

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸በትላንትናው ዕለት የጅማ ከተማ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች አሁን የመስቀል ደመራ የተከናወነ የሚገኝበትን ቦታ አፅድተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸በጅማ ከተማ የደመራ በዓል ስነ ስርዓት #ሰላማዊ በሆነ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል። በስፍራው የሚገኙ የበዓሉ ተሳታፊዎች ያለውን ድባብ በፎቶ አስደግፈው ልከውልናል።

PHOTO: MILVER/TIKVAH-ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸በዛሬው ዕለት በዓዲግራት ከተማ እየተከበረ ያለው #ደማቅ የመስቀል በዓል ምክንያት በማድረግ የተካሄደው ታላቅ ሩጫ #መስቀል_ዓጋመ #ADIGRAT #ETHIOPIA

PHOTO: JOHN/TIKVAH-ETHIOIA
@tsegabwolde @tikvahethioia
"የጋራ ሀብታችን የሆነውን ሰላም እና አንድነት እንጠብቅ"- ብጹ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የኢትዮጵያዊያን የጋራ ሀብት የሆነውን ሰላም እና እንደነት እንጠብቅ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላለፉ፡፡ ብጹነታቸው ይህንን መልክታቸውን ያስተላለፉት ዛሬ ማምሻውን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በመስቀል ደመራ ስነ ስረዓት ላይ በአደረጉት ንግግራቸው ነው፡፡

በደመራ ስነ ስርዓቱ ላይ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር #ሂሩት_ካሳው፣ ሌሎች ከፍተኛ መንግስት የስራ ሃፊዎች፣ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች የተለያዩ ሀገራት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች እና ጎብኝዎች ተገኝተዋል፡፡

ብጹነታቸው በዚሁ ንግገራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረሰው ግፍና በደል ሊቆም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ኢትዮጵያን አበው መስቀሉን ያከብሩታል እንጅ አይዳፈሩትም፤ ይሰግዱለታል እንጅ አያቃልሉትም ያሉት ብጹ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ አብው ኢትዮጵያን መተባበርን አንድነት እና ፍቅርን ለትውልዱ ማስተላላፋቸውን አስታውሰዋል፡፡ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ ምሁራን እና የማህበረሰብ እንቂዎች ከመዘላለፍ በመተባበር ከመጠላላፍ በመደጋገፍ ላይ ትኩረት በማድረግ የሀገር አንድነትን ሰላምን እና ፍቅርን ማስቀጠል እንደሚገባቸው ጥሪያቸወን አስተላልፈዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓልን እያከበረች ነው!

ቤተክርስቲያንዋ በአዲስ አበባ ከተማ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ በሚገኘው ጽዮን ማሪያም ገዳም ነው በዓሉን እያከበረች ያለችው፡፡ በዓሉ በመዝሙር፣ በቅዳሴ፣ በትምህርትና በተለያዩ መንፈሳዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ሲሆን በበዓሉ መጨረሻም የደመራ ማብራት ስነ ስርዓት ይካሄዳል፡፡ የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከእግዚአብሄር የተሰጠና ታላቅ ፍቅሩን የገለጸበት መሆኑን በማመን መስቀልን በየዓመቱ ታከብረዋለች፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋምቤላ ክልል የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ47 ታራሚዎች ዛሬ ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚራሚዎች ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የበደሉትን ህዝብና መንግስት ለመካስ ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሳስበዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግብፅ በተቃውሞ እየተናጠች ነው!

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ሥልጣን እንዲለቁ የሚጠይቀው የአደባባይ ተቃውሞ አድማሱን ማስፋቱን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ ከካይሮ የተጀመረው ተቃውሞ ወደ ሌሎች ከተሞችም ተዛምቷል፡፡ በአመጽ በሚናጡ ከተሞች ንግድ መደብሮች ተዘግተዋል፤ የጸጥታ ጥበቃውም ተጠናክሯል፡፡ 

ምንጭ፦ አልጀዚራ/wazema/
📹MiddleEastEye
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#TahrirSquare

የግብፅ ፖሊስ የርዕሠ-ከተማ ካይሮን የተሕሪር አደባባይን ዛሬ ሙሉ በሙሉ ዘግቶ ውሏል። እንደ ግሪጎሪያኑ አቆጣጠር በ2011 የተደረገዉ ሕዝባዊ አመፅ ዋና ማዕከል የነበረዉን አደባባይ ፖሊስ የዘጋዉ ፕሬዝደንት አብድል ፈታሕ አል ሲሲን አገዛዝ #የሚቃወመዉ ሕዝብ ተቃዉሞዉን ባደባባይ እንዳያሰማ ለማገድ ነዉ።ፕሬዝደንቱና ከፍተኛ የጦር ጄኔራሎቻቸዉ በሙስና ተዘፍቀዋል የሚል ዘገባ ከተሰራጨ ወዲሕ ፕሬዝደንቱ ሥልጣን እንዲለቁ የግብፅ ሕዝብ በተለይም ወጣቶች ባደባባይ ሰልፍ እየጠየቁ ነዉ።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ!

የመስቀል በዓል በአካባቢ ልምላሜ ተውቦ፣ በአበቦች ደምቆ፣ የክረምቱ ዝናብ አልፎ የፀደይ ብርሃን በሚፈካበት ወቅት የሚከበር በዓል  በአል እንደሆነ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ፡፡ በክርስትና ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በልዩ ሁኔታ የሚታወሰውና በዚህ ወቅት የሚከበረው የመስቀል በዓል ፍቅር፣ መስዋዕትነትና ለእውነት የመታመን ዕሴቶችን የያዘ እንደሆነም ነው የጠቀሱት፤ የዘንድሮ የመስቀል በዓል የብዙ ዓመታት የልፋት ውጤት ፍሬው የሚገኝበት፣ እንደ ቤተሰብና ማህበረሰብ፣ እንደ ክልልና እንደ አገር ስኬት የሚመዘገብበት እንዲሆን ያላቸውን መልካም ምኞት ም ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba "የኢትዮጵያ ህዝብ እኩልነትን ከአንድነት፣ ነፃነትን ከወንድማማችነት አጥብቆ የሚወድ በመሆኑ የአገሪቱ ምሁራን፣ ፖለቲከኞች፣ ሊህቃንና አክቲቪስቶች ከጥላቻና ከመወራረፍ ፣ ከስድብና ከመጠላለፍ፣ ከፉከራና ከመዘላለፍ ተቆጥባችሁ በቅንነትና በአስተዋይነት፣ በይቅርታና በፍቅር ይህን ታላቅ ህዝብ በእኩልነት በማገልገል አንድነታችንንና ሰላማችንን እንድታፀኑ አባታዊ መልዕክት አስተላልፋለሁ።" ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ

የመስቀል ደመራ በዓል በመቀለ ጮምአ ተራራ በሚባል ስፍራ ዛሬ በድምቀት ተከበረ። በበዓሉ ላይ አቡነ ኢሳያስ እንደተናገሩት የመስቀል በዓል የህዝቡ ሰላምና አንድነት የሚሰበክበት እለት ነው፤ በመሆኑም በህዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ በየጊዜው የሚከበሩ ሃይማኖታዊ በአላት እሴቶቻቸው ተጠብቆ ለሰላምና ልማት ልንጠቀምባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።

በበዓሉ ላይ የተገኙት ዶክተር ደብረጽዮን ባስተላለፉት መልዕክት ህዝቡ ከእምነቱ ባለፈ ለአካባቢው ሰላምና እድገት የድርሻውን ሊወጣ ይገባል። “በተለይም የወጣቶች የስራ ዕድል ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት በዚህ አመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል። ለዚሁ ዕቅድ ተግባራዊነት ደግሞ ሁሉም የመንግስት ሴክተሮች በቅንጅት እንዲሰሩ አሳስበው አመቱ የሰላምና የልማት እንዲሆን ምኞታቸውን ገልጸዋል። በበዓሉ ላይ የሃገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የመቀሌ ከተማ ምክትል ከንቲባን ጨምሮ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችና ህዝበ ክርስቲያኑ ተሳታፊ ሆነዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethioia
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረው የደመራ በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ተከብሯል፡፡

https://telegra.ph/ETH-09-27-2