TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EGYPT vs #ETHIOPIA | ግብጽ በይፋ ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ ጀምራለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ #ሳሜሕ_ሽኩሪ በካይሮ የአረብ ሊግ ስብሰባ ላይ በድርድሮቹ ኢትዮጵያ «ግትር» ሆናለች ሲሉ መውቀሳቸውን አል ሞኒተር የተባለው የግብጽ ጋዜጣ ዘግቧል። የግብጽ ውጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ሐምዲ ሎዛ በበኩላቸው መቀመጫቸውን በካይሮ ካደረጉ የአውሮፓ አገራት አምባሳደሮች ጋር በጉዳዩ ላይ ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያ የሌሎች አገሮችን ጥቅም ችላ በማለት የራሷን አተያይ ብቻ ለመጫን ጥረት እያደረገች ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከምባታ ጠምባሮ ዞን ምክር ቤት 17ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከመስከረም 21- 23 ቀን 2012 ዓ/ም ያደርጋል። #ዱራሜ

Via Z/TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሰሞኑን በግብፅ ከነበረው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የግብፅ መንግስት እስካሁን 1,100 ሰዎችን ማሰሩ ተሰምቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
☺️ባለፉት 10 ቀናት 12,480 አዳዲስ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ተቀላቅለውናል! TIKVAH/HOPE/ተስፋ

🤔የቤተሰቡ ቁጥር በየደቂቃው ተለዋዋጭ ስለሆነ Edit ይደረግ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Alert

የሚመለከታችሁ የፀጥታ አካላት በአርሲ ሮቤ ከተማ ስለተፈጠረው ጉዳይ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ እንድትፈልጉ እንዲሁም ለተፈጠረው ችግር ትኩረት እንድትሰጡ በከተማዋ የሚኖሩ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባላት ተደጋጋሚ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ። ችግሮች አሁን ካሉባት እንዳይሰፉም የሚመለከተው አካል ሁሉ በሰከነ መንፈስ እንዲወያይም ጥሪ አቅርበዋል።

ስለጉዳዩ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎች ይኖሩናል!

Via Frew/ TIKVAH-ETH/
@tikvahethiopia @tikvahethiopia
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ #የመምህራን ፍልሰት #አሳሳቢ ሆኗል፤ ባለፉት 2 ወራት ብቻ እስከ 10 የሚደርሱ ሲኒየር መምህራን ዩኒቨርሲቲውን ለቀዋል ሲሉ አንድ ስማቸውን እንዲገለፅ ያልፈለጉ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባል ተናግረዋል። ለመምህራኑ ዩኒቨርሲቲውን መልቀቅ እንደ ምክንያትነት የሚነሳውም የአካባቢው ፀጥታ ሁኔታ/TEPI/፣ የመምህራን አያያዝ እና የአስተዳደር ችግር ነው። ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ሲነፃፀር ወደኃላ ቀርቷል ጉዳዩ ትኩረት ይፈልጋል ሲሉ መልዕክቱን ያደረሱት የቤተሰባችን አባል ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዘንድሮው የትምህርት መርሃ ግብር በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የነበሩ ውስጣዊ ችግሮች በአብዛኛው የተፈቱ በመሆናቸውና ውጫዊ ተብለው ሊያጋጥሙ ይችላሉ የተባሉትም ቢሆኑ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ዝግጅት በመደረጉ ወላጆች ስጋት አይግባችሁ ሰላም ላይ ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ሲሉ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍል ጥሪ አቅርበዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዘንድሮ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር መንግስት በቂ ዝግጅት አድርጓል!

"የወላጆች ስጋት ይገባኛል፤ በግልም በዙሪያችንም ብዙ ወላጆች ስላሉ ብዙ ቤተሰብም ስለምናውቅ ትክክልም ነው። በባለፉት ዓመታት ካጋጠሙን አንፃር ስጋታቸው ተገቢ ነው። ግን በዚህኛው ዓመት የተደረገው ዝግጅት ከባለፉት ዓመታት እጅግ በጣም ጥልቅም ነው ጠንካራም ነው። በዚህ ረገድ ፀጥታን በተመለከተ መንግስት በቂ ዝግጅት አድርጓል። ከፌደራል መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እስካሉበት ከተሞችና ዞኖች ድረስ ያለው የመንግስት መዋቅር በቂ ዝግጅት አድርጓል። ክልሎች የራሳቸው በክልላቸው ያለ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ሰላም እንዲሆን በቂ ዝግጅት አድርገዋል። ሁሉም በዚህ ደረጃ ከተንቀሳቀሰ ዩኒቨርሲቲዎች የውስጥ ተጋላጭነታቸውን ከቀነሱ ዓመቱ ሰላማዊ ይሆናል ብለን እንወስዳለን። ወላጆችም በዚህ ጉዳይ ላይ በመንግስት በመተማመን ልጆቻቸውን መክረው ከማንኛውም አደጋ ራሳቸውን ጠብቀው እንዲማሩ በማንኛውም ሁከት ውስጥ እንዳይሳተፉ፤ ሰላምን የነሱንም ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ላይ ሳይሳተፉ፡ ትምህርታቸውን አተኩረው እንዲማሩ መክረው ከላኩ ዓመቱ ሰላማዊ ሆኖ ይጠናቀቃል።" ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ - /ከኤፍ ቢ ሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ/

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሎስ አንጀለስ የኦሮሞ ማኅበረስብ ማዕከል አዘጋጅነት ለ6ኛ ጊዜ የእሬቻ በዓልን ባሳለፍነው ቅዳሜ በሎስ አንጀለስ ከተማ የማኅበረስቡ ተወላጆች በተገኙበት አክብረዋል፡፡

Photo: VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኔቶ የአፍሪካ ቀንድ ሰላምን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታወቀ። የኢፌዲሪ ሰላም ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዲኤታ ወ/ሮ አልማዝ መኮንን የሰሜን አትላንቲክ የቃል ኪዳን ሀገሮች ድርጅት (ኔቶ) ንዑስ-ኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑትን ሚሮ ኮቫችን እና ከልዩ ልዩ ሀገራት የተውጣጡ የድርጅቱን የፓርላማ አባላት በሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በማስመልከት ለማካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክቶችን ይፋ አደረገ። ቦርዱ በመጪው ህዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄን በማስመልከት ለማካሄድ ላቀደው ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እያከናወነ ይገኛል።

Via #ETHIO_FM
@tsrgabwolde @tikvahethiopia
1. “ሲዳማ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ውስጥ እንዲቆይ እፈልጋለሁ” ለሚለው አማራጭ የጎጆ ቤት ምልክት፣

2. “ሲዳማ ራሱን ችሎ በክልልነት እንዲደራጅ እፈልጋለሁ” ለሚለው አማራጭ የሻፌታ ምልክት ሆኖ ለህዝበ ውሳኔው ድምጽ መስጫነት እንዲያገለግል የተወሰነ መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#VOA
AudioTrim
ያዳምጡ⬆️

ገመቹ ጋሮምሳ እንዴት ተገደለ?
ገመቹ ጋሮምሳ እንዴት ተገደለ?

በምዕራብ ወለጋ አይራ ወረዳ ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን አሰቃቂ ጥቃት የተፈፀመበት ሰው ምስል ሲታይ መቆየቱንነ የዚህ ሰው ወንድም ነኝ ያሉ ግለሰብ ወጣቱ በፀጥታ ኃይሎች የደረሰበትን ጥቃት ለአሜሪካ ድምፅ ራድዮ ገልፀዋል። የአይራ ወረዳ ፀጥታና አስተዳደር በበኩሉ ወጣቱ በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረ ቢሆንም ለማምለጥ ሙከራ ሲያደርግ ነው የተገደለው ብሏል።
.
.
በፎቶው ላይ የሚታየው ወጣት ገመቹ ጋሮምሳ ይባላል። ወንድሙ እንደሚናገሩት ከዚህ ቀደምም የፀጥታ አካላት በጥብቅ ይፈልጉት ስለነበረ ከቤት ሸሽቶ ጎረቤትና ዘመድ ጋር ነው የቆየው። ነገር ግን በአጋጣሚ በቁጥጥር ስር ካዋሉት በኃላ የፀጥታ አካላት ወንድሙን አሰቃይተው ገለዋል ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

"ስሙ ገመቹ ጋሮምሳ ይባላል። ባለፈው እሮብ ምሽት ለሃሙስ አጥቢያ በመንግስት ታጣቂዎች ተይዞ መንገድ ላይ እየተደበደበ መሬት ላይ እየተጎተተ እጁ ወደኃላ ታስሮ አይራ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ከወሰዱት በኃላ ካሰቃዩት በኃላ ከአይራ ወረዳ 12 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ጫካ ውስጥ ገለው ጣሉት።...እኛ ሬሳውን ያገኘነው አርብ እለት ወደ 4 ሰዓት ገደማ ነው። እስከ 7 ሰዓት እሬሳውን ወደአካባቢያችን አደረስን ወደ 10 ሰዓት ገደማ የቀብር ስነ ስርዓቱ ተፈፀመ።"

የአይራ ወረዳ ፀጥታ እና አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮናስ በቀለ ወጣቱ ገመቹ ጋሮምሳ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንደዋለ ነገር ግን ለማምለጥ ሲሞክር እንደተገደለ ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-26
የአሜሪካ ሙዚየም ከግብፅ ተሰርቆ የተወሰደውን ጥንታዊ የወርቅ መቃብር መለሰ። በአረብ የፀደይ አብዮት ወቅት ተዘርፎ በኒው ዮርክ ሜትሮፖሊታን የሥነ-ጥበብ ሙዚየም የተገኘው የግብፅ የወርቅ የሬሳ ሣጥን ለሀገሪቱ መመለሱ ተገለጸ፡፡

በወርቅ የተንቆጠቆጠውን ጥንታዊ የሬሳ ሣጥን እኤአ በ2017 በ4 ሚሊዮን ዶላር ሙዚየሙ የገዛው ሲሆን ቅርሱ በሕገ-ወጥ መንገድ በግለሰቦች መዘዋወሩ ተደርሶበት በቁጥጥር ስር ውሎ ቆይቷል፡፡ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ በተገኙበት ቅርሱ ለሀገሪቱ መመለሱ ነው የተገለጸው፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉዳዩ የግብፃውያን ብቻ ሳይሆን ሁላችንም እንደ አንድ ዓለም አቀፍ ቤተሰብ ልንጋራው የሚገባ ነው ብለዋል፡፡ እንደ ምርመራው ከሆነ ይህ የወርቅ የሬሳ ሣጥን በተመሳሳይ መንገድ ከተሰረቁ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ጥንታዊ ቅርሶች መካከል አንዱ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በኒው ዮርክ እየተካሄደ ከሚገኘው 74ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን በኢጋድ የሚንስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበርነታቸው የአባል ሃገራት ሚንስትሮች ጋር መክረዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ASOSA

በአሶሳ ከተማ በህገ-ወጥ መንገድ 145 የክላሽ ጥይት ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ም/ኢ/ር ደረጀ ኢታና እንደገለጹት ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ የቻሉት በአሶሳ ከተማ ወረዳ አንድ ቀጠና አንድ አካባቢ አንድ መቶ አርባ አምስት የክላሽ ጥይቶችን ይዘው ለመሸጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ በህብረተሰቡ ጥቆማ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው ችሏል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-26-2

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የኢፌዴሪ ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕና ባለቤታቸው ሜላኒያ ትራምፕ! #ኒውዮርክ #US
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጊፋታ2012

የዘንድሮ የወላይታ ዘመን መለወጫ በዓል ጊፋታ በተለያዩ ፕሮግራሞች ለማክበር ዝግጅቱን እንዳጣናቀቀ የዞኑ ባህልና ቱሪዝም እሴት መምርያ ኃላፊ አቶ ፀጋው ስምኦን ገልፀዋል። እንደ አቶ ፀጋው ገለፃ ከሆነ የወላይታ ዞን መለወጫ በዓል የብሔሩን ባህልና እሴትን ለትውልድ በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸው የዘንድሮ የጊፋታ በዓልን በተለያየ መልኩ ለማክበርም ዝግጅቶች መደረጋቸውንም ሃላፊው ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/TIKVAH-09-26

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጋሞ ዞን ፖሊስ ያስተላለፈው የጥንቃቄ መልዕክት፦

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለመላው የጋሞ ዞን እንኳን ለ2012 ዓ.ም የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብና እርስ በእርስ በመደጋገፍ በጋራ የምናከብረው በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቱን ገልጿል፡፡ የመስቀል በዓልን ያለምንም የፀጥታ ስጋት ለማሳለፍ የዞኑ ጸጥታ አካል ከሚመለከታቸው ባለድርሻአካላት ጋር በመሆን ትኩረት በመስጠት እየሰራ በመሆኑ ህብረተሰቡ የተለመደውን እገዛ ወይም ትብብር አጠናክሮ በመቀጠል ከታች በተቀመጡ ስልኮቻችን መረጃዎችን በማድረስ ለወንጀል መከላከሉ ስራ አጋርነቱን እንዲያረጋግጥ ያሳስባል፡፡

በተጨማሪም ህብረተሰቡ በበዓል ወቅት ሊፈጠሩ ከሚችሉ፡-

• ከበዓል ግብይትጋር ተያይዞ ከሀሰተኛ የብር ኖቶች /ፎርጅድ ገንዘብ/ ዝውውር ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው፣

• ከበዓል ዝግጅት ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ ከሚችሉ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ህብረተሰቡ ለራሱ እና ለንብረቱ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅበት፣

• በሚኖረው ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከታሪፍ በላይ ማስከፈልና አላስፈላጊ መጉላላት በትራንስፖርት ተጠቃሚው ላይ እንዳይደርስ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ክትትል ያደርጋሉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለሚፈጠሩ ችግሮች የፖሊስ የመረጃ ስልኮችን በመጠቀም በፍጥነት ጥቆማ በማድረስ ህገ-ወጥ ተግባራትንና ወንጀሎችን በጋራ መከላከል እንደሚገባ እያሳሰበ የመረጃ ስልኮቹ እነሆ በዝርዝር ቀርበዋል፡፡

የመረጃ ስልኮች፦

የጋሞ ዞን ፖሊስ መረጃ 0468810025
የአርባምንጭ ከተማ ፖሊስ መረጃ 0468814298
ሼቻ ክፍለከተማ ፖሊስ መረጃ 0468810095
ሲቀላ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መረጃ 046881 2637
አባያ ክፍለ ከተማ ፖሊስ 046881 4312
ነጭ ሳር ክፍለ ከተማ ፖሊሰስ 0468813381