TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬ ጥዋት ሒልተን ሆቴል መዋኛ ገንዳ ውስጥ ህይወታቸው ያለፈው ታዋቂው ባለሀብት አቶ #ምንውየለት_አጥናፉ ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ናቸው። ለታዋቂው ባለሃብት ለሞት መንስኤው #ስትሮክ ሳይሆን እንደማይቀር የቅርብ ጓደኞቻቸው ለአዲስ ፎርቹን ተናግረዋል። የስር ቢዝነስ ግሩፕ መስራችና ባለአክሲዮን የሆኑት አቶ ምንውየለት እድሜያቸው በ60ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ሲሆን የአራት ልጆች አባት ነበሩ።

ሙሉውን የአዲስ ፎርቹን ዘገባ ማንበብ ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/ADDISFORTUNE-09-21

Via https://addisfortune.news/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ታዋቂው ባለሃብት አቶ ምንውየለት አጥናፉ⬆️
#ኢሬቻ2012

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በጋራ በመሆን ዛሬ መስከረም 10 ቀን 2012 ጠዋት ከአባ ገዳዎችና ሌሎችም የሀገር ሽማግሌዎች ጋር የመጪውን ኢሬቻ በዓል አከባበርና በተጨማሪ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-21-4
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ኢሬቻ2012

"ከማንኛውም የፖለቲካ አቋም፣ እምነት ውጪ መደረግ አለበት። ባህላዊ ፕሮግራማችን ነው፤ ስለዚህ የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አርማ፣ ባንዲራ መታየት አይፈቀድም። ባህሉም ይከለክላል። ዩኔስኮ ውስጥም አንዱ ይህን ባህል የምናቆይበት መንገድ አንዱ ይሄ ነው፤ ከዚህ መጠበቅ አለበት። ነፃ ሆኖ ሁሉም ሰው በዚህ ውስጥ መሳተፍ አለበት። የፖለቲካ ምልክቶች፣ አርማዎች በዚህ ውስጥ መኖር የለባቸውም ይሄንን ህዝቡ እርስ በእርሱ ተባብሮ ፈትሾ፤ ሲታዩም በሰላማዊ መንገድ አውርዶ አጣጥፎ በክብር የሚያስቀምጥበት፤ ምንም አይነት እንደዚህ አይነት ነገር የማይታይበት በዓል እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል።" አቶ ሽመልስ አብዲሳ/የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ዛሬ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ኮሌጅ ተገኝተው ነበር። ዲያሊስ ሲያደርጉ ለነበሩ 64 ታካሚዎች ለአንድ ዓመት የሚያስፈልጋቸውን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሸፍነውላቸዋል። ዲያሌስስ የሚያደርጉ ሕሙማንን ጎብኝተዋል።

ምንጭ፦ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
worabe 2012
<unknown>
ነፃ የህክምና ጥሪ!
2765 ጩቤ እና ገጀራ ደብረብርሃን በሚገኝ የፍተሻ ጣቢያ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ትናንት ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ከደሴ ወደ ደብረ ብርሃን በአይሱዙ መኪና ተጭኖ ሲጓጓዝ መጣ የነበረ ህገ ወጥ ድምፅ የሌለው መሳሪያ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ነው የተገለፀው። በአሁኑ ሰዓት የአይሱዙው ሹፌር እና የህገ ወጥ መሳሪያዎቹ ባለቤት ነው ተብሎ የተጠረጠረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ ገልፀዋል።

ከተያዙት ህገ ወጥ መሳሪያዎች መካከል 62 ትላልቅ ገጀራ፣ 2217 መካከለኛ ጩቤ፣ 306 ከመካከለኛ ከፍ ያለ ጩቤ እና 180 በሁለት በኩል ስለት ያለው ቢላዋ ባጠቃላይ 2765 ህገ ወጥ ድምፅ የሌለው መሳሪያ በቁጥጥር ስር እንደዋለ ነው የተገለፀው። ኢትዮጵያዊነትን እያቀነቀንን በምንገኝበት በዚህ ወቅት ወንድም ወንድሙን ለመግደል ህገ ወጥ መሳሪያ ከቦታ ወደ ቦታ ማዘዋወር ተገቢ አለመሆኑን ነው አቶ ዋሲሁን የተናገሩት።

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቡሬ ወረዳ አደንዛዥ እፅ ሲያለሙ የተገኙ ግለሰቦች ተያዙ!

በኢሉአባቦር ዞን ቡሬ ወረዳ በድብቅ በማሳቸው ላይ አደንዛዥ ዕፅ ሲያለሙ ተገኝተዋል ያላቸውን ሶስት ግለሰቦች መያዙን ፖሊስ አስታወቀ። የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታረቀኝ አሰፋ እንደገለፁት በወረዳው ዕድገት ፋና ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ሶስት ግለሰቦች ከመኖሪያ ቤታቸው ጓሮ አደንዛዥ ዕፅ ሲያለሙ ተደርሶባቸዋል።

ግለሰቦቹ የመኖሪያ ቤታቸውን ጓሮ በአጥር በመከለል ዕፅ እያለሙ እንደሆነ ፖሊስ ከህብረተሰቡ  በደረሰ ጥቆማ መሰረት ተከታተሎ ሊይዛቸው እንደቻለ ተናግረዋል። በተጨማሪ ተሳታፊ ነበር የተባለ  ሌላ  አንድ ግለሰብ ለጊዜው በመሰወሩ ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ገልጸዋል።

ለጊዜው የተሰወረው ግለሰብ ለስራ ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሲዘዋወር ከሌላ አካባቢ ያመጣውን እፅ የሰጣቸውን መሆኑን የተያዙት ሰዎች በሰጡት ቃል መግለጻቸውን  ኮማንደሩ አመልክተዋል። እንደ ኮማንደር ታረቀኝ ገለጻ ግለሰቦቹ ተይዘው  ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው፤ በማሳቸው ላይ የነበረው ዕፁ ተነቅሎ እንዲወገድ ተደርጓል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አማካይነት 18 ሺህ 576 የ40/60 የጋራ መኖርያ ኮንደሚኒየም ቤቶች የካቲት ወር ላይ ለባለ እድለኞች እጣ መውጣቱ የሚታወስ ነው።

ከሰኔ ወር ጀምሮም ባለ እድለኞቹ የ40/60 የጋራ መኖርያ ቤቶች ምዝገባን ያከናወነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመሄድ የቤቱን ዋጋ አርባ በመቶ ክፍያ በማጠናቀቅ የቀሪ 60 በመቶ የቤቱን ዋጋ ከባንኩ ጋር የብድር ውል በማድረግ የቤት ርክክብ ሂደቱን ማከናወን ተጀምሯል።

ነገር ግን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጋራ መኖርያ ቤት እድለኞቹ ንግድ ባንክ ውል ለመፈጸም ሲሄዱ ለባንኩ ያቀረቡት የስምና እንዲሁም የጋብቻ መረጃ ለማጭበርበር ከፍተኛ አዝማሚያን ያሳየ መሆኑን የባንኩን ምንጮች ጠቅሶ ዋዜማ ራዲዮ ዘግቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-21-5
ፎቶ📸ነገ በደብረ ማርቆስ ከተማ እና በሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታትዮች ለሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁ በየከተሞቹ የሚገኙ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ሆሳዕና ከተማ ነገ የሚገቡትን እንግዶች ለመቀበል በዛሬው ዕለት ሙሉ ቅድመ ዝግጅቷን አጠናቃለች። #ETH

Via Tsadiki/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ

የቀድሞው የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ጄኔራል #ሰዓረ_መኮንን የ80 ቀን መታሰቢያና የሃውልት ምረቃ በነገው ዕለት ከጧቱ አራት ሰዓት ጀምሮ መቐለ ከተማ በሚገኘው ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፅረሃርያም ግቢ ይካሄዳል። በዕለቱም የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት፣ የመከላከያ ከፍተኛ መኮንኖችና ወዳጅ ጓደኞቻቸው እንደሚገኙም ቤተሰቦቻቸው አሳውቀዋል።

"ፅባሕ 11 መስከረም 2012 ዓ.ም ካብ ረፋድ 4:00 ጀሚሩ ዝኽሪ 80 መዓልቲ መስዋእትን ምርቓ ሓወልትን ስውእ ኢታማዦር ሹም ሓይሊ ምክልኻል ሃገር ጀነራል ሰዓረ መኮነን፣ ላዕለዎት ኣመራርሓ ፌደራልን ክልልን፣ ላዕለዎት መኮነናት ሓይሊ ምክልኻል ሃገር፣ ዕድመ ዝተገበረሎም ኣጋይሽን መራኸብቲ ሓፋሽን ኣብ ዝተረኸብሉ ኣብ ከተማ መቐለ ቀፅሪ ፀርሃ ኣርያም ቤተ ክርስትያን ቅዱስ ገብሪኤል መቐለ ክሳለጥ ምዃኑ ስድራ እንዳ ጀነራል ሰዓረ መኮነን ገሊፆም።"

Via Petros Ashenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነገ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚካሄደው "ኢሬቻ ለሰላም ሩጫ" አስፈላጊው ሁሉ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል!

ፎቶ: Qabsoo Sorsuu
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ የሚዘጉ መንገዶች!

ውድድሩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ የሚዘጉ መንገዶች፡-

• ከቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከልደታ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ
• ከዋቢ ሸበሌ ሆቴል ወደ ቄራ
• ከአፍሪካ ህብረት አደባባይ ወደ ቡልጋሪያ ማዞሪያ
• ከሳርቤቶች አደባባይ ወደ ቄራ
• ከጎፋ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከቂርቆስ አዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር
• ከቂርቆስ ወደ ገነት ሆቴል
• ከመስቀል ፍላወር ወደ አጎና ሲኒማ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው
• ከኡራኤል ወደ ጦርኃይሎች አደባባይ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ካዛንቺስ->አራት ኪሎ->ሸራተን አዲስ->ሃራም ቤሆቴል->ጎማ ቁጠባ
• ከፒያሳ ወደ ቦሌ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ሃራምቤ ሆቴል->ፍልውሃ->ካዛንቺስ->ኡራኤል->አትላ ስሆቴል->ቦሌ
• ከሳርቤት ወደ ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
መካኒሳ አቦ መታጠፊያ->መድሃኒት ፋብሪካ->ሦስት ቁጥር ማዞሪያ->ብስራተ- ገብርኤል አቅጣጫ->በካርል አደባባይ->ቴሌ->ልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት
• ከፒያሳ ሳሪስ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ቸርችል ጎዳና->ጥቁር አንበሳ->ኦርማ ጋራዥ->በዘውዲቱ ሆስፒታል->በፍልውሃ->በኡራኤል
• እንዲሁም ከፒያሳ እስከ ብሄራዊ ቲያትር ያለውን መንገድ በአማራጭነት መጠቀም ይቻላል።

አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙ የፖሊስን አገልግሎት ለማግኘት በነፃ የስልክ መስመሮች 991 ፣6727 ፣816 እና በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ011-1-01-02-97

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የISIS እና የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዝግጅት የነበራቸውየአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። ጉዳዩን አስመልክቶ የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት የሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-21-6

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኤመን ጡሚን ኢሊሾኔ!

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ሕዝቦች የዘመን መለወጫ የመሳላ በዓል በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ በሚቆመው ሰጦ የገበያ ቦታ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነገ በከምባታ ጠምባሮ ዞን መዲና - ዱራሜ የሰላም ሩጫ ይካሄዳል!

ጥቂት ስለሩጫው፦

• በኢቲቪ የቀጥታ ስርጭት ለዓለም ሕዝብ ይተላለፋል፥
• ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ በሩጫው እንደሚሳተፉ ይጠበቃል፥
• ታዋቂ አትሌቶች ሩጫውን ያስጀምሩታል፥
• ከሊቅ እስከ ደቂቅ በሩጫው ለመሳተፍ ከተለያየ ቦታ ወደ ዱራሜ ያቀናል፥
• ሰላም፥ ፍቅር፥ አንድነት የሚቀነቀንበት ታላቅ ሩጫ ይሆናል፥

ዱራሜ ዝግጅቷን አጠና እንግዶቿን እየተጠባበቀች ነውና መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ/ም ዱራሜ እንገናኝ!! ሁሉም በሰላም ሩጫው እንዲሳተፍ ተጋብዟል።

የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አልሸባብ እና አይ ኤስ የሽብር ቡድኖቻቸውን ወደ አዲስ አበባ እና የተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመላክ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት በመፈፀም በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳይ ለማድረስ እንዲሁም የሀገራችንን በጎ ገፅታ ለማበላሸት በዝግጅት ላይ እንዳሉ ብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ጥብቅና የተቀናጀ ክትትል ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ አድርጓል።

https://telegra.ph/ETH-09-21-6

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸የብሄራዊ የመረጃ ደህንነት አገልግሎት ክትትል ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ከዋሉት የአልሸባብ እና የአይ ኤስ የሽብር ቡድን አባላት መካከል የተወሰኑት ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ናቸው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከድሬዳዋ...

"ዛሬ በ10/01/2012 ዓ.ም ድሬዳዋ ከተማ ውስጥ ደቻቱና ኮኔል አመሻሹ ላይ አለመረጋጋት ነበረ። የፀጥታ አካላት ግን ምንም ጉዳት ከመድረሱ በፊት ተቆጣጥረውታል። ይህ ዓይነቱ ፈጣን ምላሽ በሌሎችም አካባቢዎች ቢለመድ ጥሩ እላለሁ። ችግሩ ወደ ሌሎች የከተማዋ ቀበሌዎች ከመዛመቱ በፊት ሰላሙን ወደነበረበት በመመለስ የከተማዋ የፀጥታ አካላት አኩሪ ሥራ ሰርተዋል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከኮሜድያን ዶክሌ የማይረሱ የኮሜዲ ስራዎች መካከል አንዱን ጋበዝናችሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia