TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የዓለም መንግስታት ለአየር ንብረት ለውጥ ድርጅት ስብሰባን መሰረት በማድረግ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ሰልፍ መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡

እየተስተዋለ ያለውን የዓለም የአየር ንብረት መዛባት ጉዳይ ጉዳዬ ያሉ የተለያዩ ሀገራት ተማሪዎች “ተለዋጭ ፕላኔት የለንም’’ በሚል ሃሳብ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል፡፡

በጎርፍ እየተጥለቀለቁ ያሉ የፓስፊክ ደሴቶች፣ ኒው ዚላንድ፣ የአውስትራሊያ፣ የባንኮክ እና የታይላንድ ሰልፈኞች የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስን ለማቃለል የዓለም መንግስታት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-20-4

Via አልጀዚራ/etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ ባልቻ ሬባ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ። ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ስለ ቴሌኮሙዩኒኬሽን በጸደቀው አዋጅ ቁጥር 1148/2011 መሰረት፥ የቴሌኮም ዘርፉን በመቆጣጠር በዘርፉ ለሚሰማሩ የግል ተቋማት የውድድር ሜዳውን ምቹ ለማድረግ የተቋቋመ ነው። አቶ ባልቻ ሬባም ተቋሙን ከመስከረም 2 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተሾመዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሚካኤል አፅብሃ ገብሩ⬆️ በአራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ በተለምዶ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተገደለው ሚካኤል አፅብሃ ገብሩ ካላይ በፎቶው የምትመለከቱት ነው። ከካናዳ/ቶሮንቶ/ ወደኢትዮጵያ የመጣውም በቅርቡ ነበር። አቶ ሚካኤል ከአመት በፊት በካናዳ ሀገር የሎተሪ እድለኛ ሆኖ እንደነበር ወዳጆቹ ገልፀዋል። @tsegabwolde @tikvahethiopia
በአቶ #ሚካኤል_አፅብሃ_ገብሩ የግድያ ወንጀል የተጠረጠሩ ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ተሰምቷል!

በአራዳ ክ/ከተማ ፒያሳ በተለምዶ መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎችን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

መስከረም 3 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 6 ሰዓት ሲሆን በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፒያሳ ልዩ ቦታው መሀሙድ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በአቶ ሚካኤል አጽበኻ ገብሩ ላይ የግድያ ወንጀል ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ 2 ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያጣራመ ሆኑን የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ኮሚሽኑ እንደገለፀው ብዛታቸው 3 የሆኑ ተጠርጣሪዎች በዕለቱ ሟች ሚካኤል አፅበኻ ከጓደኛቸው ጋር እየተዝናኑ ከቆዩ በኋላ ወደ ማደሪያቸው ለመሄድ ታክሲ እየጠበቁ በነበሩበት አጋጣሚ ንብረት ለመዝረፍ በማሰብ ጉዳት አድርሰውባቸው ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀሉ መፈፀም ሪፖርት እንደደረሰው ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር ቀንና ሌሊት ባደረገው ብርቱ ጥረት 48 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል ሁለቱን በ05/01/2012 ዓ.ም ማምሻውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑንና ቀሪውን አንድ ተጠርጣሪ ለመያዝ ክትትሉ መቀጠሉን አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ ወንጀልፈፃሚዎቹ እንዲያዙ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋናውን በማቅረብ ወንጀልን የመከላከል ስራ ላይ የሚሰጠውን ድጋፍና ተሳትፎን አጠናክሮ አንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

ምንጭ፦ አ/አ ፖሊስ ኮሚሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በ2012 ዓ.ም ለሚቀበሏቸው አዲስ ተማሪዎች የቅድመ መግቢያ ፈተና ዛሬ መስጠት ጀመሩ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በአዲስ አለም ከተማ የደረሰ የመኪና አደጋ ነው። በአደጋው ጉዳት የደረሰበት አሽከርካሪ ወደ አምቦ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዷል።

አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ እያደረጋችሁ አሽከርክሩ!

Via Fire/TIKVAH-ETH - ከአምቦ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ደግሞ ከ10 ደቂቃ በፊት አዲስ አበባ እስጢፋኖስ ድልድይ ውስጥ የገባ አንበሳ አውቶብስ ነው። በአካባቢው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት አምቡላስ ወደአካባቢው እንዲመጣ ጠይቀዋል። በአደጋው የተጎዱ ሰዎች እንዳሉም ነግረውናል።

ተጨማሪ መረጃዎች ይኖሩናል!
ፎቶ:TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሁን ሰዓት እስጢፋኖስ አካባቢ በርካታ አምቡላንሶች እንዲሁም የፖሊስ አባላት እንደሚገኙ ቤተሰቦቻችን ገልፀውልናል። ከመስቀል አደባባይ ወደ 4 ኪሎ የሚወስደው መንገድ ለጊዜው ተዘግቷል።

ፎቶ: TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይህ ባነር የተለጠፈው ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አቅራቢያ ነው

"የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር አብይ አህመድ እንኳን ደህና መጡ! ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እያበረከቱት ላለው ጉልህ አስተዋፆ #እናመሰግናለን!" ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

Via AB/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአ/አ እስጢፋኖስ አከባቢ...

"አሁን አንበሳ አውቶብስ #የተገለበጠበት ቦታ እገኛለሁ አደጋው በጣም አስከፊ ይመስላል። እስካሁን ሁለት ሰዎች መሞታቸውን አረጋግጫለሁ። ሌሎች የተጎዱ ሰዎች ደግሞ ወደ ዘውዲቱ ሆስፒታል ተወስደዋል።" D/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሆሳዕና⬆️

"ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ፍቅር ከተማ ወደሆነችው ሆሳዕና ይመጠሉ። አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል።"

Via Elias/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#GRAPHIC_CONTENT ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ኢትዮጵያዊ ዜጋ በፖሊሶች የተያዘበት መንገድ በርካቶችን አስቆጥቷል፤ በርካቶች በማህበራዊ ሚዲያ እየተቀባበሉት ነው፤ በርካቶችም ድርጊቱን አውግዘዋል።

በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ስለጉዳዩ ተጠይቆ ይህን ምላሽ ሰጥቷል፦

የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር #ታዬ_ግርማ  ባለፉት ሁለት ቀናት ውስጥ በኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ችግር እንደተፈጠረ ተደርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተሰራጨ ስላለው ምስል በኮሚሽኑ በኩል በትክክል አለመረጋገጡን ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈ ግን ችግሩ በማን እና እንዴት እንደተፈጠረ #እያጣራ እንደሚገኝም ነው የገለጹት። የክልሉ ፖሊስ ለኦሮሞ ህዝብ አለኝታውና መከታው ሆኖ በርካታ ችግሮችን እየተጋፈጠ ሲታገል የቆየና አሁንም በዚያው ቁርጠኝነት እያገለገለ እንዳለም አስረድተዋል፡፡ ድርጊቱ የክልሉን ፖሊስ ስም ለማጥፋት የተፈጸመ በመሆኑ የፖሊስ ኮሚሽንም ይሁን ሌላ አካል ጉዳዩን በፈጸሙ አካላት ላይ #እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል። በምስሉ ላይ የሚታዩ ግለሰቦችንም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽንን የደንብ ልብስ ከመልበሳቸው ውጭ ማንነታቸውን ማረጋገጥ እንዳልተቻለም ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADDISABEBA

ከህጋዊ የንግድ ሥርዓት ውጪ በህገ ወጥ መንገድ ለገበያ ሊቀርብ የነበረ በ52 አይሱዙ ተሽከርካሪ የተጫነ እህል እና ጥራጥሬ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡ መስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም በአ/ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ አካባቢ ከእህል በረንዳ ውጪ ያለአግባብ የቆሙ 52 አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገው ቁጥጥር የተለያዩ እህል እና ጥራጥሬዎችን በደላሎች ጣልቃ ገብነት ለመሸጥ የተዘጋጁ መሆናቸው መረጋገጡን የክ/ከተማው ንግድና ኢንዱስትሪ ፅ/ቤት አስታወቋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ዋሽንግቶን_ዲሲ

ትላንት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን #ምዕመናን ፣ ዋሺንግተ ዲሲ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊትለፊት ተገኝተው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ይታወቃል። በሰልፉ ላይ የተገኙት ሰዎች በቤተክርስቲያኗ እና በምዕመናን ላይ ደረሰ ያሉትን በደል አሰምተዋል፡፡ መንግስት አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስድም ጠይቀዋል፡፡

ከሰልፉ በኃላ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ክቡር አቶ ፍፁም አረጋ በትዊተር ገፃቸውን ይህን ፅፈው አሰራስችተዋል፦

"በዋሽንግተን ዲ.ሲ. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን አማኞች ማህበራት አስተባባሪነት ሰላማዊ የሆነ ሰልፍ ተካሄደ፡፡ ከአስተባባሪዎቹም ጋር በኤንባሲው አዳራሽ ውይይት አድርገናል፡፡ ለመንግስት ጥያቄዎችን በጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ በአገራችን በቤተ-ክርስቲያን ዙሪያ የሚታየው ጥቃት እንዲቆም፣ አጥፊዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ ተማጽነዋል፡፡ ጥያቄዎቹንም ለመንግስት እንደምናደርስ ቃል-የገባን ሲሆን፣ ላሳዩት ሥነ-ሥርዓት የተሞለበት ሰልፍ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡"

ቪድዮ📹VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የኢሬቻ በዓል ከግል ፍላጎታችን በላይ ነው!" አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኢሬቻ በዓልን ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በጋራ ማክበር ለኦሮሞ ህዝብ ክብር እና ድል ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ #ሽመልስ_አብዲሳ በዛሬው እለት የ2012 የኢሬቻ በዓል ዝግጅትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-20-5

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መስከረም 21 በሚከበረው ግሸን ደብረ ከርቤ ንግስ በዓል ለመታደም የሚመጡ እንግዶችን ለማስተናገድ ቅደመ ዝግጅት መደረጉን የደቡብ ወሎ ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Irreechaa2019

የኢሬቻ በዓል #በሰላም እንዲጠናቀቅ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ፅህፈት ቤት ሃላፊ ኮማንደር ታዬ ግርማ ኮሚሽኑ በቅርቡ ለሚከበረው የኢሬቻ በዓል እና ከዚያ በፊት ለሚከበሩት ፌስቲቫሎች ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

#ኢሬቻ2012
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሰዓታት በፊት ቅዱስ እስጢፋኖስ አካባቢ በደረሰው የመኪና መገልበጥ አደጋ 41 ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል። አንበሳ አውቶብሱ ከሽሮ ሜዳ ወደ ስቴዲየም ይጓዝ ነበር። አደጋው የደረሰበትን አውቶብስ ለማውጣት የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው።

Via ዋልታ ቴሌቪዥን
ፎቶ: TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሙገር ከተማ 1 የፖሊስ አባል ሲገደል ሌላ 1 ሰው ቆስሏል!

በትላንትናው ዕለት ምሽት አንድ ሰዓት ገደማ በሙገር ከተማ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰ ጥይት ሳጅን አለማየሁ የተባሉ የፖሊስ አባል ሲገደሉ ሌላ አንድ ሰው ቆስሏል። ግድያውን የፈፀመው አካል ማን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም። ለTIKVAH-ETH ጉዳዩን ያስረዱት የከተማው ፖሊስ አባል በማህበራዊ ሚዲያ ቦምብ ተወርውሮ ነው ሰው የተገደለው እየተባለ የሚወራው መረጃ ሀሰተኛ ነው ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba "ማምሻውን ከፈረንሳይ ሌጋሲዮን የተነሳው የአንበሳ አውቶቢስ በደረሰበት አደጋ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን። እስጢፋኖስ አካባቢ በሚገኘው ድልድይ ውስጥ በገባው አውቶብስ ለተጎዱት አስፈላጊው እርዳታ እየተደረገለቸው ይገኛል። በአደጋው እስከአሁን የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ በአደጋው ለተጎዱ ሁሉ የተሰማውን ልባዊ ሃዘን ይገልፃል፡፡"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አውቶብሱ የተገለበጠው የሰሌዳ ቁጥሩ ይፋ ያልተደረገ ኮድ 3 አ/አ መኪና ለመሸሽ ሲሞክር ነው!

እስጢፋኖስ ቤተክርስትያን ጀርባ በሚገኝው ድልድይ ውስጥ የመውደቅ አደጋ የገጠመው የከተማ አውቶብሱ ምክንያት ለጊዜው የሰሌዳ ቁጥር ይፋ ያልተደረገ ኮድ 3 አ.አ መኪና ለመሸሽ ሲል እንደሆነ የእሳት እና ድንገተኛ አደጋዎች የኮምንኬሽን ባለሙያ አቶ ስለሺ ተስፋዬ ለሽገር ራድዮ አስረድተዋል።

አውቶብሱ የተለመደ የመስመር ቁጥር ያልተሰጠው አዲስ ስምሪት እንደሆነም ታውቋል። መነሻውንም ከሽሮሜዳ አድርጎ ወደ ካዛንችስ እየሄደ እንደነበርም ነው ባለሙያው የተናገሩት። አደጋው ያጋጠመው አንበሳ የከተማ አውቶብስ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- አ/አ 68377 እንደሆነ ታውቋል። በዚሁ አደጋም 31 ሰዎች ብርቱ ጉዳት እንደገጠማቸው ተሰምቷል።

ካሰቡበት ለመድረስ #በአውቶብሱ ተሳፍረው አደጋው ያገኛቸው ኢትዮጵያውያንም ወደ ጥቁር አንበሳ ዘውዲቱ እና አቤት ሆስፒታል መወሰዳቸውን ባለሙያው ተናግረዋል። በደረሰው አደጋ እስካሁን የ2 ሰው ህይወት አልፏል ተብሏል። የሟቾች ቁጥርም ሊጨምር ይችላል ያሉት የኮምንኬሽን ባለሙያው ናቸው።

Via #ShegerFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህሌን እጠብቃለሁ ስለ ያሆዴ እሮጣለው!

የያሆዴ ክብረ በዓል ፌስቲቫልን ምክንያት በማድረግ ታላቅ የጎዳና ላይ ሩጫ በሆሳዕና ከተማ እና በሁሉም ወረዳዎች ባህሌን እጠብቃለሁ ስለ ያሆዴ እሮጣለው በሚል መሪ ቃል ለሁለተኛ ዙር መስከረም 11/2012 ዓ/ም በሆሳዕና ከተማ እንደሚደረግ የሀዲያ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሲሳይ እውነቱ ገልፀዋል። ሁሉም ሰው ቲሸርቱን በመግዛት ኢትዮጵያዊነቱን በሚያንፀባርቅ መልኩ የሀዲያን ባህል ለሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ለማስተዋወቅ ስለ ያሆዴ እንዲሮጥ ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦ Hossana Sport ሆሳዕና ስፖርት
@tsegabwolde @tikvahethiopia