TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በHERQA ወጣው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ⬆️

ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ጋር የትብብር ስልጠና የሚሰጥ የግል ድርጅት አለመኖሩን አሁንም ለመግለጽ እንወዳለን፦

ከዚህ በፊት ሲገለጽ በነበረው መሰረት ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከግል ተቋማት ጋር በመሆን የሚሰጥ ምንም አይነት የትብብር ስልጠና አለመኖሩን እየገለጽን ተማሪዎች፣ ወላጆች እና መላው ህብረተሰብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ኤጀንሲው ጥብቅ መልዕክቱን ማስተላለፍ ይወዳል፡፡

በኤጀንሲው ላይ የቀረበው ክስን በተመለከተ መስከረም 02/2012 ዓ.ም. የወጣውን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሙሉ ለሙሉ ህዝቡና የመገናኛ ብዙሃን እንዲያውቁት አቅርበነዋል፤ ከዚህ ውጭ በሚለቀቁ ቅንጭብ መረጃዎች ህብረተሰቡን እንዳይሳስቱ ጥንቃቄ እንዲደረግ እናሳስባለን፡፡

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

ሙሉውን ከዚህ ማግኘት ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/ETH-09-17-4
ኢ/ር ታከለ ኡማ...

"የቴክኖሎጂ ፈጠራ መከልከል ወይም ማፈን ሥራችን አይደለም። ልናደርግም አንችልም ደግሞም አይገባም። በዘንድሮ ዓመት ብቻ ከ10,000 ወጣቶች በላይ የሥራ ዕድል በዚህ ዘርፍ ይፈጥርላቸዋል። የመመርያው ፍሬ ሀሳብ በዚህ አውድ የተቃኘ ነው። ተግባቦት ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካላ ይስተካከላል። የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታት የታሰበ አሰራር ነው። ለኮድ 3 እንዲሁም ለኮድ 1 ቴክኖሎጂው ይሠራል። የተገልጋዩን ደንነት መጠበቅም የጋራ ሥራ ይሆናል። ኮድ 3 የንግድ ፈቃድ ሲያስፈልግ ኮድ 1 ግን የንግድ ፈቃድ ሳያስፈልጋቸው በቴክኖሎጂው ተጠቃሚ ይሆናሉ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ📸ይሄ ደግሞ ሀዋሳ መግቢያ #ቶጋ አካባቢ የደረሰ የመኪና አደጋ ነው። በአደጋ ስለደረሰው ጉዳት ወደበኃላ መረጃዎችን ሰብስበን እናሳውቃለን። @tsegabwolde @tikvahethiopia
የሁለት ሰው ህይወት አልፏል!

ከቢሻንጉራቻ ከፍ ብሎ ልዩ ቦታ ውሻሎ ምርጥ ዘር አካባቢ በዛሬ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ8 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን በምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ቁጥጥርና ክትትል ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ጉሳ ዴኮ ገልፀዋል፡፡

በዛሬው ዕለት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-03954 አይሱዙ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ከሻሸመኔ ወደ ሀዋሳ ሲመጣ ባልታወቀ ምክንያት የቀኙን መስመር ለቆ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚመጣው ኮድ 3-0739 በተለምዶ ዶልፊን ተብሎ በሚጠራው ሚኒ ባስ መኪና ጋር ተጋጭተው ዶልፊን ሚኒ ባስ መኪና ውስጥ ከነበሩት ሰዎች አስሩ ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡

በዚህም ለህክምና አቅራቢያ ወደሚገኘው ሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደው እየተረዱ የሚገኙ ሲሆን በአደጋው የ2 ሰዎች ህይወት ሊያልፍ ችሏል፡፡ ቀሪዎቹ 6 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳትና በ2 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ተመዝግቧል፡፡ በተጨማሪም በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል፡፡ ጊዜው ክረምት በመሆኑም አሽከርካሪዎች ሲያሽከረክሩ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና የፍጥነታቸውን ወሰን እንዲጠብቁ ኢንስፔክተሩ አሳስበዋል፡፡

Via #SRTA
ፎቶ: TIKVAH-ETH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተባበሩን!

በመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻው ከአ/አ ብቻ እስካሁን ከ700 በላይ መፅሃፍት ማግኘት ተችሏል። በተለያዩ ቦታዎችም ቃል የተገቡልን መፅሃፍት አሉ፤ እንዚህን መፅሃፍት ለመቀበል እና ወደተለያየ ቦታ ለመውሰድ የናተው የቤተሰቦቻችን እገዛ ስለሚያስፈልገን ተባበሩን።

መኪና ያላችሁ በዚህ ቁጥር ደውሉልን +251912178520

#TIKVAH_ETHIOPIA
ፕሬዘዳንት አሽራፍ ከሞት ተረፉ!

የአፍጋኒስታን ፕሬዚዳንት አሽራፍ ጋኒ ፓርዋን በተባለው ክፍለ ሀገር የምረጡኝ ዘመቻ ያካሄዱ በነበረበት ወቅት ከተከፈተው ጥቃት ለመትረፍ ችለዋል። ዛሬ በደረሰው ጥቃት 24 ሰዎች ተገድለው ከ30 በላይ ቆስለዋል። አንድ ሞተር ቢስክሌት የሚነዳ አጥፍቶ ጠፊ፣ ሰው በተሰበሰበበት ወታደራዊ ቦታ አጠገብ ፈንጂውን ሲያፈነዳ ፕሬዚዳንቱ ንግግር ለማደረግ ቀርበው እንደነበር ተዘግቧል። ህንፃው ውስጥ ከነበሩት ሰዎች ጉዳት የደረሰበት የለም። የምርጫ ዘመቻውም ከጥቃቱ በኋላ ቀጥሏል ሲሉ የአፍጋኒስታን የሀገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስራት ራሂሚ በትዊተር ጠቁመዋል።

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መከባባር የሰላም ምንጭ ነው!

ሰው በሰውነቱ #ሊከበር ይገባል። በዘመናችን በሀብት፣ በስልጣን፣ ወይም ደግሞ ታዋቂ ስለሆነ ሰውን እናከብራለን ያንን እንከተላለን ግን ትክክለኛው ሰውን በሰውነቱ ማክበር ነው። ሰውን የሚንቁ ሰዎች ዙሪያቸው ጤናማ ግንኙነት አይፈጥሩም። ሰውን እየናቁ ጤናማ ግንኙነት መፍጠር አይቻልም። ስለዚህ የሰውን ዋጋ እውቅና መስጠት ያስፈልጋል።

ሰውን ደግሞ እኛ ባሰብነው መንገድ ብቻ ወይም የኛን imagination ብቻ አይተን የምናከብረው መሆን የለበትም፤ ሁሉም ሰው #የተለያየ ነው። በተለያየ ቤተሰብ ያደገ፣ በተለያየ ሀገር፣ በተለያየ ሁኔታ እንዳንዶቻችን በትምህርት፣ በተለያየ መንገድ ያለፍን ስለሆነ ሁሉ ሰው አንድ አይነት አይደለም፤ የተለያየ ነው። ሰዎች እኔን ካልመሰሉ እኔን አይነት ካልሆኑ አላከብራቸውም የምንል ከሆነ ሙሉ በሙሉ ስህተት ነን! ሁሉ ሰው በተለያየ መንገድ ነው ያለው ሊከበር ይገባል። ...አለመከባበር የግንኙነት ዋስትናን ያበላሻል። ሰውን ዋጋ እያሳጣን ከዛ ሰው ጋር መኖር አንችልም።

ሰውን ማክበር ጥቅሙ ለራሳችን ነው ለሰውየው አይደለም፤ ምክንያቱም አንድን ሰው ባታከብረው ምን ይጎለዋል? ውስጡ ያለውን ማንም አይወስድበትም ግን እኛ ነን ሰውየውን የምናጣው። ካከበርነው ወዳጅ እናደርገዋለን ለኛ የሚጠቅመን ሰው እናደርገዋለን፤ ካላከበርነው ሰውየው ዋጋውን አያጣም ምክንያቱም ሌሎች የሚያከብሩት ሰዎች አሉ።

ሰውን ማክበር ለፈቀድነው ሰው የምንከፍለው ዋጋ ሳይሆን ለሁላችንም በነፃ የተሰጠን ስጦታ ነው!

Via Dr. GIRMA LULU

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በባሕር ዳር ከተማ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ የጦር መሳሪያዎቹ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ በገባ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ውስጥ ተደብቀው ሲጓጓዙ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት ተብሏል፡፡ አሽከርካሪው ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የአማራ ክልል አድማ ብተና 2ኛ ሻለቃ 1ኛ ሻምበል ምክትል ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ታለማ ዳኛ ተነናግረዋል፡፡

ምንጭ - አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#RIDE

"ይህንን ደንብ አንቀበለውም፣ ከፍርድ ቤት እገዳ ለማስወጣት ሂደት ላይ ነን" የራይድ መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊት

/ልዩ መረጃ-- ከኤልያስ ጋር/

የራይድ መስራች እና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊትን የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ ይፋ ስላደረገው አዲሱ መመሪያ፦

"ሲጀመር የትራንስፖርት ቢሮው ይህን መመሪያ ማውጣት ይችላል ወይ የሚለው ላይ ጥያቄ አለ፣ ምክንያቱም እኛ የቴክኖሎጂ ድርጅት ስለሆንን የሚመለከተው የቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስትር ነው። በእኛ እምነት የትራንስፖርት ቢሮው ይህ ስልጣን የለውም። ሲቀጥል በRide ስር ከ 6,000 በላይ አባላት አሉ፣ የሚጎዱት እነዚህ ሰዎች ጭምር ናቸው። ይህ መመሪያ ሲወጣ እኛን ማሳተፍ ነበረበት። ሌላው ቀርቶ ረቂቁን እንኳን አላየነውም። በአጠቃላይ ይህንን ደንብ አንቀበለውም፣ ከፍርድ ቤት እገዳ ለማስወጣት ሂደት ላይ ነን። በሌለ infrastructure አንድን ድርጅት እዚህ ማድረስ ቀላል አልነበረም። ይህንን ሁሉ ስራ ሰርተን እዚህ ስንደርስ appreciate መደረግ ነበረብን። በትራንስፖርት ቢሮ የተደረገው ግን እኛን የሚቃረን ነው። እንደዚህ አይደረግም! ይህ ፈፅሞ መቆም ያለበት ነገር ነው። ይብቃ! ወጣቱ ይስራ! ሀገሪቱንም ያሳድግ! በዚህ አጋጣሚ ኢንጅነር ታከለ እና አቶ እንዳወቅ እየደገፉን ነው ያሉት። (የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮው) ዶ/ር ሰለሞን ግን ትንሽ ቆም ብለው አስበው ከእኛ ጋር ቢሰሩ ጥሩ ነው። ብዙ ልምድ አለን። ምን አልባት ልምድ የላቸውም ብለው አስበው ከሆነ ተሳስተዋል።"

Via #ELIAS_MESERET
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪን ለመቆጣጠር እንዲቻል መመሪያ ተዘጋጀ!

በግል ትምህርት ቤቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ እየተደረገ ያለውን የተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪን ለመቆጣጠር እንዲቻል መመሪያ መዘጋጀቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊ እና የመማር ማስተማር እና ምዘና ዘርፍ ኃለፊው አቶ ተሰማ ዲማ ለደ.ሬ.ቴ.ድ እንዳስታወቁት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በተለይም በከተሞች የግል ትምህርት ቤቶች በየጊዜው ምክንያታዊ ያልሆነ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ቢሮው ጥቆማ ይደርሰዋል፡፡ ሆኖም ግን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የግል ትምህርት ቤቶችን የመማር ማስተማር ሥራ የሚከታተልበት አሠራር ያለው ቢሆንም ክፍያን በተመለከተ መቁረጥ ስለማይችል ትምህርት ቤቶቹ ሊመሩበት የሚገባውን መመሪያ ማዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ቢሮው ከግል ትምህርት ቤቶች ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት የግል ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን የትምህርት ቤት ክፍያ ላይ ጭማሪ ከማድረጋቸው አስቀድሞ በዓመቱ ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ ባሉት ወራት ከተማሪ ወላጆች ጋር በጥልቀት በመነጋገርና ምክንያቶችን ዘርዝረው የማስቀመጥ ኃላፊነት እንዳለባቸውም በመመሪያው ላይ በግልጽ መቀመጡን አብራርተዋል፡፡

የተማሪ ወላጆችና ማህበረሰቡ ያላመነባቸው የትምህርት ቤት ክፍያ ጭማሪ በአሠራሩ መሠረት ተቀባይነት እንደሌለው አውቆ በየአካባቢውና ችግሩ በስፋት በሚስተዋልባቸው ቦታዎች ህዝቡ መብቱን እንዲያስከብርም አቶ ተሰማ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በቀጣይም የክልሉ ትምህርት ቢሮ የችግሩን አሳሳቢነት በመገንዘብ ጥብቅ ክትትል እንደሚያደርግና ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር አብይ የዴሞክራሲ ሽልማት አሸነፉ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የአፍሪካ ዴሞክራሲ ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ለሽልማቱ የበቁት ዴሞክራሲን እና መልካም አስተዳደርን በአፍሪካ ለማረጋገጥ ባደረጉት ጥረት ምክንያት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሽልማቱ በአዲስ አበባ በተካሄደው በአራተኛው የአፍሪካ የፖለቲካ የምክክር መድረክ ላይ ነው የተበረከተላቸው፡፡ ከመላው አፍሪካ የተውጣጡ ከፍተኛ የፖለቲካ አማካሪዎች የሽልማቱ አዘጋጆች መሆናቸውን መረጃው አመልክቷል፡፡

የአዘጋጅ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት ኪንዴ ባሚግበታን ሽልማቱ በአህጉሪቱ ዴሞክራሲንና መልካም አስተዳደርን በማስፋፋት ተምሳሌታዊ ተግባር ላከናወኑ ሰዎች እውቅናን የሚቸርና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ የሚሰጥ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በተጨማሪ ናይጄሪያዊው ቦላ ቲኒቡ የዚህ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል፡፡

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE የአማራ ብሄራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥተዋል።

በዚህ መሰረት ፦

• አቶ ሙሉቀን አየሁ - የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኃላፊ
• ዶክተር መልካሙ አብቴ - የክለሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ
• ዶክተር ደስታ ተስፋው - የክልሉ የበይነ መንግስታት ኃላፊ
• አቶ ጎሹ እንዳላማው - የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ
• አቶ ቀለሙ ሙሉነህ እምሩ - የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ
• አቶ ማሩ ቸኮል መንግስቱ - የክልሉ የሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር
• አቶ ፈንታው አዋየሁ - የክለሉ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ምክትል ሥራ አስኪያጅ
• አቶ ዘላለም ልየው - የክልሉ የጣና ሐይቅና ሌሎች የውሃ አካላት ጥበቃና ልማት ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ
• ወይዘሮ ባንቺአምላክ ገብረማርያም - የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር
• አቶ ሞላ ትእዛዙ - የክልሉ ወሳኝ ኩነቶች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር
• አቶ ሀብታሙ መላክ - የርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ምክትል የጽህፈት ቤት ኃላፊ
• ወይዘሮ ውባለም እስከዚያው - የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሃውልት ጽህፈት ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ
• አቶ አዲስ በየነ - የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሃውልት ጽህፈት ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ
• አቶ በለጠ ጌታነህ - የዕፅዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብአቶች ጥራት ቁጥጥር ኳራንታይን ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለስልጣናቱ በ“ቪ8” መኪኖች ላለመጠቀም ያወጡትን መመሪያ ተግባራዊ አላደረጉም!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2009 ዓ.ም በ38ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል መንግሥትና ሌሎች ተቋማት ኃላፊዎች ወጪ ቆጣቢ፣ ውጤታማና ቀጣይነት ያለው የትራንስፖርት ሥርዓት እንዲኖራቸው ያወጣው መመሪያ በባለሥልጣናት ተግባራዊ አለመደረጉን በተለያዩ ተቋማት በሹፌርነት ሥራ የተሰማሩ ባለሙያዎች ገለጹ።

ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ በተለያዩ ተቋማት የተሰማሩ ሹፌሮችና ሠራተኞች መንግሥት ወጪ ለመቆጠብ በከተማ ሲነዱ ዝቅተኛ የነዳጅ ፍጆታ ያላቸውን አውቶሞቢሎች በከፍተኛ ወጪ ገዝቶ ለኃላፊዎች ቢሰጥም ኃላፊዎቹ በአዲስ አበባ ከተማ ‹‹ቪ8›› እና ፕራዶ ፓጃሮ መኪኖችን መንዳት ባለማቆማቸው ራሳቸው ላወጡት ህግ ተገዥ እንዳልሆኑ ተናግረዋል። እንደ ሹፌሮቹ ገለፃ፤ መንግስት ‹‹ወጪ ለመቆጠብ›› በሚል ባለስልጣናቱ ካሉዋቸው ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ለአንድ ኃላፊ ሁለትና ከዚያ በላይ መኪና በከፍተኛ
ወጪ ገዝቶ አድሏል ብለዋል።

Via አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የትምህርት ሚኒስቴር እኛ ለእኛ በጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር ከፓይለቶች ማህበር ጋር በመሆን ደቡብ ክልል ሀዋሳ ከተማ በሚገኘው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ተገኝተው የመማሪያ ቁሳቁሶችን አስረክበዋል፡፡ የአሶሳ እና የጅጅጋ መኪኖቻችንም ወደ ሥፍራው በመጓዝ ላይ ናቸው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ክልል በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን አመነ!

‹‹ፓርቲዎችን ኢላማ ያደረገ እስር የለም፣ ሁሉም እየተነሳ የፓርቲዬ አባል ታስሯል እያለ የሚያወራው ለፖለቲካ ጥቅም ነው›› አቶ ታዬ ደንደአ

አገርን ለማረጋጋት በሚደረጉ ጥረቶች #ተጠርጣሪዎች ተይዘው ለምርመራ መቅረባቸው እንደ አዲስ ነገር መታየት የለበትም ያሉት አቶ ታዬ ደንደአ፣ የክልሉ መንግሥስት ፓርቲዎቹን ለማጥቃት ያደረገው ዘመቻ ቢሆን ኖሮ የራሱን ከፍተኛ አመራሮች ባላሰረ ነበር ብለዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

ተጨማሪ ያንብቡ
https://telegra.ph/ETH-09-18
ተባበሩን!

በመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻው ከአ/አ ብቻ እስካሁን ከ700 በላይ መፅሃፍት ማግኘት ተችሏል። በተለያዩ ቦታዎችም ቃል የተገቡልን መፅሃፍት አሉ፤ እንዚህን መፅሃፍት ለመቀበል እና ወደተለያየ ቦታ ለመውሰድ የናተው የቤተሰቦቻችን እገዛ ስለሚያስፈልገን ተባበሩን።

መኪና ያላችሁ በዚህ ቁጥር ደውሉልን +251912178520

#TIKVAH_ETHIOPIA
#NEW

📝የአዲስ አበባ እና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ቀን እና ሰዓት ተገልጿል። ሌላው ደግሞ ምዝገባው የሚጠናቀቀው፡- ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ነው።

📝የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የፈተና ቀን እና ቦታ ተገልጿል።

📝ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን መቅጠር ይፈልጋል።

ሁሉንም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በTIKVAH-MAGAZNIE ማግኘት ትችላላችሁ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#update በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ 3 ሺህ 555 ህገ-ወጥ የብሬን ጥይት መያዙን የሳንጃ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ አስታወቀ።

የመቆጣጠሪያ ጣቢያው አስተባባሪ ኮማንደር ሞላ ተሾመ ለኢዜአ እንዳስታወቁት ጥይቱ የተያዘው ከዳንሻ ወደ ጎንደር ሲጓዝ በነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አአ 84556 በሆነ ፒካፕ መኪና ላይ ትናንት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት በተደረገ ፍተሻ ነው፡፡

አሽከርካሪው መቆጣጠሪያ ጣቢያውን ጥሶ ለማለፍ ሙከራ ቢያደርግም በፀጥታ ሃይሉ ጥረት በማስቆም በተካሄደ ፍተሻ በመቀመጫ ወንበሩ ስር ደብቆት የነበረውን ጥይት መያዝ መቻሉንም አስታውቀዋል።

አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ጉዳዩ በህግ እየታየ መሆኑን ገልጸው፤ ህዝቡ የሚጠራጠረው እንቅስቃሴ ካለ ለሚመለከተው አካል ጥቆማ በመስጠት ለሰላምና መረጋጋት የድርሻውን እንዲወጣም አሳስበዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEW

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናቸውን አሳውቋል!

ሁሉንም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በTIKVAH-MAGAZNIE ማግኘት ትችላላችሁ👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ
#Irreechaa2019

ታላቁ “የሆራ ፊንፊኔ” የኢሬቻ ሩጫ መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። ሩጫው መስከረም 24 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄደውን የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚካሄድ ሲሆን፤ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዘም ቢሮ ከ’ዲሲቲ ኢንተርቴይመንት’ ጋር በመሆን እንደሚያዘጋጁ ተገልጿል።

በዚህ የሩጫ ውድድር ላይም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አድማሱ ዋቅጋሪ ተናግረዋል። እንደ አቶ አድማሱ ገለጻ የሩጫው ቲ-ሸርት በፌዴራልና በክልሉ በመሰራጨት ላይ ያለ ሲሆን ሽያጩም እየተካሄደ ይገኛል።

የአንድ ቲ-ሸርት ዋጋ 250 ብር ሲሆን የመሸጫ ቦታዎች በፌዴራልና በክልሉ መስሪያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች እንዲሁም በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞንና በአዲስ አበባ የሚገኙ ነዋሪዎች ከኦሮሞ ባህል ማዕከል ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል። በክልሉ ሌሎች ዞኖች የሚገኙ ነዋሪዎች ደግሞ በዞን እና በወረዳ እንዲሁም በሁሉም ከተሞች ባሉት የባህልና ቱሪዝም ቢሮዎች ማግኘት ይችላሉ ብለዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቀኑ በመስከረም 7/2012 ይስተካከል⬆️

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካዮችና ከኢትዮጵያ እስልምና መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ጋር ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2012 ጠዋት ተገናኝተው ተወያይተዋል። አባላቱ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞቻቸውን ለማክበር ከመስቀል በዓል በፊት በሚደረግ ጽዳት ላይ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሦስተኛው ጣና ማህበራዊ ሚዲያ አዋርድ!

የዘንድሮው የጣና ሽልማት ወደ 21 ዘርፍ ከፍ ማለቱ ታውቋል፡፡ የሽልማቱ ዓላማ ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር ለሚጠቀሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅና መስጠት ነው፡፡ ባለፈው ዓመት በ16 ዘርፎች ነበር ሽልማት የሰጠው፡፡

ዘንድሮ ዘርፉን አስፍቶ በ21 መስኮች ሽልማት እንደሚሰጥ የዘመራ ማስታወቂያ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ እና የሽልማት ሥነ ስርዓቱ አስተባባሪ አቶ ደምስ አያሌው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡ ሽልማቱ ጥቅምት 1/2012 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ተገልጧል፡፡

ለተሸላሚዎች ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነፃ የትምህርት እድል እንደሚሰጥም ተናግረዋል፡፡ በዚህ ዓመት ለሚከናወነው የሽልማት ሥነ ስርዓት በየዘርፉ ለመጨረሻ ዙር የተመረጡት እጩዎች 68 መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በቀጣይ ዓመት መርሀ ግብሩን ወደ ትልቅ ደረጃ ለማሸጋገር መታሰቡን አቶ ደምስ ተናግረዋል፡፡ የጣና ሽልማት በ2009 ዓ.ም ነው መሰጠት የተጀመረው፡፡

Via #AMMA

የ3ኛው የጣና ሽልማት እጩዎችን ይህን በመጫን ማየት ትችላላችሁ👇
https://telegra.ph/TANA-AWRD-09-18