TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
39℅👍ድምፅ መስጠታችሁን ቀጥሉ!!

The link for the vote is⬇️
https://www.letsdothis.com/challengeawards/best-international/run-international
41%👍GREAT ETHIOPIAN RUN⬆️

The link for the vote is⬇️
https://www.letsdothis.com/challengeawards/best-international/run-international
43%👍GREAT ETHIOPIAN RUN⬆️

The link for the vote is⬇️
https://www.letsdothis.com/challengeawards/best-international/run-international
መብረቅ ጉዳት አደረሰ!

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ትናንት ሌሊቱን የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በወረደ መብረቅ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የወረዳው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ገለፀ።

የፅህፈት ቤቱ ሃላፊ ወይዘሮ ኮከቤ ማንበግሮ እንደገለፁት የመብረቅ አደጋው የደረሰው በቂልኝ ቀበሌ ልዩ ስሙ የሞኝ በር በሚባል ስፍራ ነው። በአደጋው አቶ ሃይሉ ሚንዳ የሚባሉ ግለሰብ በመኖሪያ ቤታቸው በመብረቁ ተመተው ህይወታቸው ሲያልፍ የሟቹ ንብረት የሆኑ ሶስት የቀንድ ከብቶችም መሞታቸውን ገልፀዋል፡፡

ከዚህም ሌላ በአካባቢው በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ከባድ ዝናብ በ22 ሄክታር መሬት ላይ የሚገኝ የባቄላ፣ አተርና ገብስ ሰብል ላይም ጉዳት ማድረሱን ገልፀዋል፡፡ በዚህም 37 አርሶ አደሮች ለችግሩ መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም አንጋዳ በተባለ ቀበሌ የመሬት መንሸራተት እንደደረሳና የጉዳት መጠኑን ለማወቅ ባለሙያዎች ወደ ስፍራው መላካቸውን ገልጠዋል።

የዝናብ ስርጭቱ ከፍተኛ በመሆኑ ነዋሪዎች አምሽተው ወንዝ እንዳይሻገሩ ፣ ከብቶቻቸውንና ልጆቻቸውን በጊዜ ወደ ቤት እንዲያስገቡ በአካባቢያው በሚኙ የግብርናና የጤና ባለሙያዎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ቅስቀሳ እየተደረ መሆኑን ወይዘሮ ኮከቤ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
17 የምግብ ዘይት ምርት አይነቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማሰሰቢያ ተሰጠ!

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች ባደረገው የገበያ ጥናት በ17 የምግብ ዘይት ምርቶች ላይ መሰረታዊ ችግር ስላለባቸው ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው አሳስቧል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባደረገው የገበያ ጥናት የዘይት ምርቶቹ የሚመረቱበት ቦታና የተመረተበት ሃገር፣ የምርት መለያ ቁጥር፣ የአምራች አድራሻ የሌላቸው፣ የገላጭ ጽሁፍ ችግርና ለጤና ጠቀሜታ እንዳለው ተደርጎ የተቀመጠ፣ የመጠቀሚያ ጊዜና ማብቂያ ቀን የሌላቸው እንዲሁም የሀገሪቱን የደረጃ ምልክት ያለጠፉና ደረጃውንም የማያሟሉ መሆናቸው በተደረገው ጥናት መረጋገጥ መቻሉን ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

ህብረተሰቡ የትኛውም የምግብ ምርት ከገበያ ሲገዛ የተመረተበትና የመጠቀሚያ የአገልግሎት ጊዜው ትክክለኛነት፣ ያልተፋቀና ያልተሰረዘ መሆኑን፤ የአምረች ድርጅቱ ስምና ሙሉ አድረሻ፣ የምርት መለያ ቁጥር ያለው መሆኑን በማረጋገጥ እንዲገዛ የተጠየቀ ሲሆን፤ የምርት ገላጭ ጹሁፍ ይዘቶች ያላሟላ ምርት ህብተሰቡ መግዛት እንደሌለበት ተገልጿል፡፡

በገበያ ጥናቱ ችግር የተገኘባቸው የምግብ ዘይቶች ዝርዝር፦

1. ሉሉ ዘይት
2. አርሲ ዘይት
3. አሃዱ ዘይት
4. ድሬ ንጹህ የምግብ ዘይት
5. አሚን ንጹህ የምግብ ዘይት
6. ሮያል የምግብ ዘይት
7. ዳግም የተጣራ የኑግ ዘይት 8. ጄጃን የምግብ ዘይት
9. ዉብ የተጣራ የኑግ ዘይት
10. ለማ የኑግ ዘይት
11. ኑድ ንጹህ የምግብ ዘይት
12. ገበታ የምግብ ዘይት
13. ዘመን ዘይት
14. አጋር ዘይት
15. አናጅና ዘይት
16. ሳባ ዘይት
17. ጃሎ ዘይት ናቸው፡፡

Via #EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Dr.ABIY

"...እንድገደል የሚፈለግባቸው ጊዜዎች #በርካታ ናቸው!" የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ

"...መስቀል አደባባይማ #የቅርብ ነው። ብዙ ጊዜ ሞት እንደዚሁ ዝም ብሎ እያየሁት አላየሁም እያለ ይሄዳል ለዚህ ነው #ሞት የማልፈራው እኔም። ብዙ ጊዜ እድገደለ የሚፈለግባቸው ጊዜዎች በጣም በርካታ ናቸው። ባለፉት 7 እና 8 ዓመታት ብዙ ሙከራዎች ተደርገዋል። ለምሳሌ ባለቤቴ ከመሄዷ በፊት ኢንሳን ለቅቄ እንደወጣሁ በየጊዜው ማታ ማታ በግቢያችን ድንጋይ ይወረወርብናል ስንወጣ ለመምታት፤ ሌላም ብዙ ሙከራዎች ተደርገውብን ያውቃሉ ግን ሞት #አልፈለገኝም እስካሁን እንግዲ አንድ ቀን ሲመጣ..." ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በሸገር ቅዳሜ ጨዋታ!

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከሁለት ሺ በላይ ምሁራንን የሚያሳትፈው የመጀመሪያው የአማራ ክልል የምሁራን መማክርት ጉባኤ በባህር ዳር ከመስከረም 9 እስከ 10 እንደሚካሄድ ተገለፀ፡፡ የመማክርት ጉባኤው በክልሉ እና በአገሪቷ በሚታዩ #ማህበራዊ#ፖለቲካዊና #የኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ሳይንሳዊ ጥናቶችን በማቅረብ ተወያይቶ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞዉ የዚምባቡዌ መሪ #ሮበርት_ሙጋቤ ዛሬ በዝምባቡዌ መዲና ሀራሬ በሚገኝ ግዙፍ ስቴዲዮም ውስጥ ሽኝት ተደርጎላቸዋል። የቀብር ስነ ስርዓታቸው ግን ከአንድ ወር በኋላ ነው የሚፈፀመው ተብሏል።

Via #DW
ፎቶ📸BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወቂያ!

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ለ2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) ለማስተማር ይፈልጋል፡፡

የማመልከቻ መስፈርት፦

1. በ2011ዓ.ም በመደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው ትምህርት ሚ/ር በወሰነው መሰረት በአራቱ የትምህርት አይነቶች (እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ እና አፕቲቲውድ)

• ልዩ ትኩረት ከሚሹ ክልሎች እና ዞኖች /ጋምቤላ ፣ሶማሌ፣አፋር፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ደቡብ ኦሞ ዞን፣ምዕራብ ኦሞ ዞን ፣ቦረና ዞን እና ዋግምራ ዞን/
 ለወንዶች 245 እና ከዚያ በላይ
 ለሴቶች 225 እና ከዚያ በላይ

• ለአዲስ አበባ እና ሌሎች ክልሎች
 ለወንዶች 265 እና ከዚያ በላይ
 ለሴቶች 245 እና ከዚያ በላይ, ውጤት ያለው/ያላት

2. ከ9-12ተኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ውጤት 80% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው/ያላት
የማመልከቻ ጊዜና ቦታ ፦
• ማስታወቂያው በሚዲያ (በቴሌቪዥን) ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በኮሌጁ ድረ ገፅ https://197.156.83.153/admission/ መመዝገብ ትችላላችሁ::
• በተጨማሪ የማመልከቻውን ሊንክ (Link) ከኮሌጁ ድረ ገፅ https://www.facebook.com/sphmmcc/ ማግኘት ይቻላል፡፡
• የጹሐፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን መስከረም 11/ 2012 ዓ.ም
• ፈተና የሚሰጥበት ቦታ አዲስ አበባ ብቻ ሲሆን የመፈተኛ ጣቢያ በኮሌጅ ድረ ገፅ እና Facebook ይገለፃል፡፡

ማሳሰቢያ፦
• ቀጥሎ የተገለፁትን ለማመልከት የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችን ስካን በማድረግ ማያያዝ ይጠበቅባችኋል
o የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤቶች
o ከ9-12 ክፍል ትራንስክሪፕት እና
o የመመዝገቢያ ክፍያ 50 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር -1000208431068 ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ
o ከዚህ ቀደም የተመዘገባችሁ አዲሱን መስፈረት የምታሟሉ ከሆነ በደጋሚ እንደ አዲስ ክፍያ ሳይከፍሉ ማመልከት ይቻላል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ሪጅስተራር
ጽሕፈት ቤት


@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግብፅ🤔

የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፋታኅ አል-ሲሲ ከስምንት አመታት በፊት በአገራቸው #የጸደይ_አብዮት ባይነሳ ኖሮ ኢትዮጵያ በአባይ ላይ ታላቁን የኅዳሴ ግድብ ባልሰራች ነበር ሲሉ ተናገሩ።

ተጨማሪ ያንብቡ AhramOnline👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-7

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ለግብፅ ጫና ትንበረከክ እንደሁ ይለያል!

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሀ አሞላል ላይ ከነገ እሁድ መስከረም 4 2012 አ.ም ጀምሮ እስከ ሰኞ ድረስ የግብጽ ; የሱዳንና የኢትዮጵያ ውሀ ሚኒስትሮች በካይሮ ይወያያሉ።የኢትዮጵያ የውሀ መስኖና ኤነርጂ ሚኒስትር ስለሺ በቀለም ለዚሁ ጉዳይ ወደ ካይሮ የሚያቀኑ ይሆናል። ሱዳንም አዲስ ባገኘችው የውሀ ሚኒስትር ያሲር አባስ መሀመድ ተወክላ የኢትዮጵያን ጨምሮ ከግብጹ የውሀ እና መስኖ ሚኒስትር መሀመድ አብደል አቲ ጋር ነው ውይይቱ የሚደረገው።

የካይሮው ስብሰባ ምናልባትም በህዳሴው ግድብ የውሀ አሞላል ላይ የስምምነት ፊርማ ሊካተትበት እንደሚችል ምንጮቻችን ነግረውናል።ሆኖም ኢትዮጵያን የወከሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ቢቻል በግድቡ ውሀ አሞላል ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብር አዲስ ሀሳብ ቢያቀርቡ ካልሆነ ደግሞ አሁን ለውይይት የተያዘው አጀንዳ ላይ በፍጹም ከስምምነት መድረስ የለባቸውምም ብለውናል።

ነገ በካይሮ በህዳሴው ግድብ ውሀ አሞላል ላይ ውይይት የሚደረገው የግብጹ የውሀ ሚኒስትር መሀመድ አብደል አቲ ከወር በፊት የሀገራቸውን እቅድ ካቀረቡ በሁዋላ ነው። አብደል አቲ በዚህ ባቀረቡት ሰነድ ውስጥ ኢትዮጵያ ግድቡን በሰባት አመት እንድትሞላ የሚጠይቅና ሌሎች ሀሳቦችም የተነሱበት ነው። በኢትዮጵያ በኩልም እነዚህ የካይሮ ፍላጎቶች ተቀባይነት የሌላቸው መሆኑን የሚያሳዩ ምላሾች ተሰጥቷቸዋል። እነዚህ በእንዲህ እያሉ ነው የነገው የሶስትዮሽ ውይይት የሚካሄደው።

#ዋዜማ_ሬድዮ

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-14-8
ነፃነት ወርቅነህና EBS TV ተለያዩ!

ለ3 ዐመት ያህል በEBS ቴሌቪዥን ሲተላለፍ በነበረው "የቤተሰብ ጨዋታ" የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅነት የሚታወቀው አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ከEBS ቴሌቪዥን ጋር መለያየቱ ተሰምቷል። አርቲስቱ በኢትዮ ኤፍ ኤም ራድዮ ጣቢያ በሚተላለፈው ታዲያስ አዲስ ፕሮግራም ላይ በያዝነው አዲስ አመት በአዲስ የፕሮግራምና በአዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያ ብቅ እንደሚል ተናግሯል። መስከረም ወር አጋማሽ ይጀምራል የተባለው ይኸው አዲስ ፕሮግራሙ በናሁ ቴሌቪዥን እንደሚተላለፍ ከታዲያስ አዲስ ለመስማት ተችሏል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም/ታዲያስ አዲስ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተስፋ አለን!

እርስ በእርስ #ከተከባበርን#ከተዋደድን፣ ካልተናናቅን፣ ከተፈቃቀርን፣ ከተሳሰብን፣ ያንዱ ህመም የኔም ነው ካልን፣ ያንዱ መጠቃት የኔም ነው ካልን፣ ካለፈው ታሪካችን መልካሙን ብቻ ማየት ከቻልን፣ ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚገባውን ክብር ከሰጠን፣ ጥላቻን ከተፀየፍን፣ ግጭት የሚቀሰቅሱ ኃይሎችን ጆሮ ካልሰጠናቸው እውነት ተስፋ አለን! ከዛሬው የድህነት ኑሯችን፣ የችግር ታሪካችን ወጥተን የሌሎች ሀገራት ዜጎች የሚኖሩትን ኑሮ የመኖር ተስፋ አለን!!

እኛ የቲክቫህ-ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ይህ ጊዜ አልፈን ለሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች ምን ለኢትዮጵያ ዜጎች ብቻ ለሰው ልጆች ሁሉ የምትስማማ ሀገር እንደምንገነባ #እናምናለን! ያ ሚሆነው ግን ስንዋደድ፣ ስንከባበር፣ አንዱ የሌላውን ባህል፣ እምነት፣ አመለካከት፣ ሲያከብር ብቻ ነው!! ስንት መከራን ያለፈ ህዝብ ይህን ማድረግ አይከብደውም።

በኢትዮጵያ ተስፋ አንቆርጥም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰሜን ወሎ ዞን - መቄት - አሁን⬆️

በሰሜን ወሎ ዞን መቄት ወረዳ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታይ ምዕመናን በቤተ ክርስቲያን እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለውን በደልና ጣልቃ ገብነት በሰላማዊ ሰልፍ እየተቃወሙ ነው፡፡ ምዕመናኑ “በቤተ ክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት እና ግድያ ሊቆም ይገባል!፤ ቤተ ክርስቲያኗ ለጠየቀችው ጥያቄም አፋጣኝ መልስ ሊሰጥ ይገባል!” የሚሉ ጥያቄዎችን እያስተጋቡ ይገኛሉ፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር⬆️

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታይ ምዕመናን ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በቤተክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ፣ ግፍ እና መሰደድ በተመለከተ በሰልፉ ድምጽ እያሰሙ ነው፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደብረ ታቦር⬆️

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታይ ምዕመናን ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ #DEBRETABOR #ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጎንደር፣ ደብረ ታቦር እና ደሴ ከተሞች ላይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኃይማኖት ተከታይ ምዕመናን ሰላማዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በቤተክርስቲያኗ እና በምዕመኖቿ ላይ እየደረሰ ያለውን መከራ፣ ግፍ እና መሰደድ በተመለከተ በሰልፉ ድምጽ እያሰሙ ነው፡፡

እየተካሄደ በሚገኘው ሰላማዊ ሰልፍ ከተላለፉ መልዕክቶች መካከል፡-

•ቤተ ክርስቲያንን ያቃጠሉ፣ ምዕመኖቿንም የገደሉ፣ በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ!
•መንግስት ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ ይጠይቅ፤ የተቃጠሉትን አብያተ ክርስቲያናትም በአስቸኳይ ያሰራ!
•መንግስት የሰላም ምንጭ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያንን ሊያከብር ይገባል! የሚሉት ይገኙበታል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቦንጋ⬆️

"ዛሬ የ ኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዓቢይ አህመድ ከፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ገብተዋል አሁን በቦንጋ እስታዲየም ይገኛሉ ከጥቂት ደቂቃዎች ቦሀላም የፓናል ውይይት ከማህበረሰቡ የተወጣጡ ጉርማሾወች[ወጣቶች ] እና የሀይማኖት አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች ጋ ይወያያሉ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮምቦልቻ⬆️

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ተከታዮች ሰላማዊ ሰልፍ እያደረጉ ይገኛሉ። በሰልፉ ላይ የቤተክርስቲያን ጥቃት እንዲቆም ጠይቀዋል። #ETHIOPIA #KOMBOLCHA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እስቴ መካነ እየሱስ የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍ⬆️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦንጋ⬆️

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ቦንጋ ከተማ ከነዋሪዎች ጋር በመወያየት ላይ ይገኛሉ። ጠቅላይ ማኒስትሩ ከካፋ ዞን ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነው እየተወያዩ የሚገኙት።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣  የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እና የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ለማ መገርሳም በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅድሚያ ሊቀበሏቸው በከተማዋ ስታዲየም ለተሰበሰበው የከተማዋ ነዋሪዎች ንግግር አድረገዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia