TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሙሉ_መግለጫ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት፣ ታሪካዊትና ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ከደረሰችበት የሥልጣኔና የእድገት ደረጃ ከመድረሷ በፊት ብራና ዳምጣ፣ ቀለም በጥብጣና ፊደል ቀርጻ ትምህርትና ሥልጣኔን ያስጀመረች፣ የመጀመሪያው ዩኒቨርሲቲና የትምህርት ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሥርዓቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ መዋቅራዊ አደረጃጀት ገና ሳይኖረው ፍርድ እንዳይጓደልና ደሃ እንዳይበደል በማሰብ የፍትሐ-ነገሥት መምህራኖቿን በዳኝነት መድባ የፍትሕ ሥርዓትን የመሠረተች፣ ዜጎችን በሥነ-ምግባርና በግብረ-ገብነት ትምህርት ኮትኩታ በማሳደግ ሀገር ወዳድ ትውልድ በማፍራት መሠረት የጣለች፣ በውጭ ወራሪ ኃይል የሀገር ሉዓላዊነት በተደፈረ ወቅት የእምነቱ ተከታይ ምእመናኖቿና አገልጋይ ካህናቶቿ እንዲሁም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የእምነታችን መገለጫ የሆነውን የቃልኪዳኑን ታቦት ይዘው በየጦር ግንባሩ በመሰለፍና በመሰዋት እንኳንስ ሕዝቦቿ ምድሪቱም ለወራሪ ጠላት እንዳትገዛ በማውገዝ የሀገር ሉዓላዊነት ያስከበረችና ኢትዮጵያ ሀገራችን ከሌሎች አፍሪካ አገራት በብቸኝነት ቅኝ ገዥዎች ያልደፈሯት አገር ተብላ በታሪክ ድርሳናት እንድትመዘገብ ግንባር ቀደም ሚና የተጫወተች የሀገር ባለውለታ እናት ቤተ ክርስቲያን መሆኗን እንኳንስ እኛ ልጆቿ ይቅርና የታሪክ ምሁራን ዘወትር በየአደባባዩ የሚመሰክሩት በብዕር ሳይሆን ለነጻነት በተከፈለ በአበው አባቶቻችን ደም የተጻፈ አኲሪ ታሪካችን ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-07-3
#ቢላል_ቅርንጫፍ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ልዩ ቅርንጫፍ "ቢላል ቅርንጫፍ" በሚል ስያሜ በዛሬው ዕለት ጳጉሜ 2, 2011 ዓ.ም ከፈተ፡፡ ቦሌ ሚካኤል ዳረሰላም ሆቴል የሚገኘው ይህ ቅርንጫፍ በተመረቀበት ወቅት የባንኩ ፕሬዝደንትና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና፣ የባንኩ የሸርዓ አማካሪ ኮሚቴ አባላትና ደንበኞች ተገኝተዋል፡፡

Via #CBE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀዋሳ ከተማ አተት መከሰቱ ተሰማ!

በሀዋሳ ከተማ አጣዳፊ ትውከትና ተቅማጥ/አተት መከሰቱን የሃዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ አስታወቀ። በሽታው የታየው በጥልቴ ቀበሌ ሲሆን በበሽታዉ የተጠቁ 2 ግለሰቦች የህክምና አግልግሎት እያገኙ መሆኑን የገለፁት የሐዋሳ ከተማ ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ #ቡሪሶ_ቡላሾ በሽታውን ወደ ሌሎች የከተማው ክፍሎች ሳይዛመት ከወዲሁ ለመግታት ሁሉም የህብረተሰቡ ክፍል መረባረብ እንዳለበት አሳስበዋል። በሽታው ቶሎ ካልተገታ ከከተማው አልፎ ወደ ሲዳማ ዞን ሊዛመት እንደሚችል የጠቆሙት ሀላፊው ይህ እንዳይሆን ለማድረግ ከዘርፉ ባለሙያወች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በወንዶ ገነት ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

Via #SMN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #ጌትነት_ይርሳው ቦጋለ ከጷግሜ 1/2011 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት አስታወቀ።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላጆች ልጆቻችሁን አስመዝግቡ!

በ2012 የትምህርት ዘመን ከ 7 ሚሊየን በላይ ተማሪዎችን መዝግቤ ለማስተማር እየሰራሁ ነው አለ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ፡፡ በመላው የክልሉ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ እስከ መስከረም ሁለት ብቻ መሆኑን ወላጆች አውቀው ልጆቻቸውን ከወዲሁ እንዲያስመዘግቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ተሰማ ዲማ እንዳሉት በ2012 የትምህርት ዘመን በቅድመ መደበኛ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን፤ ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል 4 ነጥብ 7 ሚሊየን፤ ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ደግም 6 መቶ 81 ሺህ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

Via #SRTA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አልነጃሺ_መስጊድ

1ሺህ 441ኛ የአሹራ በዓል ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎችና ከውጭ የሚመጡ ምዕመናን በተገኙበት ከነገ በስቲያ በትግራይ አልነጃሺ መስጊድ በድምቀት ይከበራል። የአሹራ በዓል በእስልምና ሃይማኖት ወር በገባ በአስረኛ ቀን ጳጉሜን 4 ለፈጣሪያቸው ፀሎት በማድረግ የሚያከብሩት ነው። የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤትና የኢትዮ-ነጃሽ የማልማትና የማስተዋወቅ ፕሮጀክት ትናንት በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአሹራ በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ተደርጓል ብሏል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ በቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ጋብሬል ሙጋቤ ሕልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህምድ ሮበርት ጋብሬል ሙጋቤ ሕልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን ለዚምባብዌ መንግስት እና ህዝብ ገልጸዋል፡፡

ፎቶ📸#TheSun
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ወላይታሶዶ

ከፍተኛ የዞን አመራሮች የተሳተፉበት የደብተር ማሰባሰብ ዘመቻ!

ባለፈው ሳምንት "አለን ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ" ከተለያዩ የበጎ አድራጎት ማህበራት ጋር በመሆን ለ800 ተማሪዎች የሚውል ጠንካራ የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ ዘመቻ አካሂዶ ነበር። በዚህም የደፍተርና የ እስኪብርቶ ማሰባሰብ ፕሮግራም፦

•የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ
•የየዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ፍሬው
•የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ፀጋ
•የከተማዉ ካንቲባ አቶ ሀንጃላ
•የዞኑ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት
•የዞኑ የወጣቶች ሊግ ፕሬዝዳንት አቶ ሚካኤል
•የከተማው የወጣቶች አደረጃጀት አመራሮች እንዲሁም ሌሎች ባለሥልጣናት ተገኝተው ደብተርና እስኪብርቶ በመለገስ የወጣቶቹን መልካም ተግባር በመደገፍና ሀገራዊ ግዴታን በመፈፀም በ "አለን ኢትዮጵያ የሰው ልጆች የለውጥ ማዕከል" ጎን በመቆም የላለሳለሰ ድጋፍ አድርገዋል።

Via አለን ኢትዮጵያ ከወላይታ ሶዶ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ማዕከላዊ እስር ቤት አድራሻ፡- ከጊዮርጊስ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር መካከል ላይ ይገኛል፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መግለጫ

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ርዕሰ-መስተዳድሩ በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢ ስለሚንቀሳቀው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የኦሮሚያ ቤተ-ክሕነት ለማቋቋም ከቀረበው ጥያቄ በኋላ ከቤተ-ክርስቲያኗ ጋር ስላደረጉት ውይይት ንግግር አድርገዋል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጫማዎን አስጠርገው ለአንድ ልጅ ሙሉ የትምህርት ቁሳቁስ ያበርክቱ!

ፎቶ📸ቲክቫህ-ቦሌ ማፊ ሞል ፊትለፊት
👉ፎቶ በስሞ ይላኩ

Join TIKVAH MAGAZINE👇
https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEcez-UrldBjOpa-qQ

#ቲክቫህ_ጥቆማ
@tikvahethmagazine
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ህክምና ኮሌጅ!

"አዲስ የሕክምና ተማሪዎች ምዝገባ በቅርቡ ይጀመራል። መመዝገቢያ ነጥብም ይፋ እናደርጋለን። በሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ የድሕረ ምረቃ ምዝገባም በሚቀጥሉት ሣምንታት ይጀመራል።" t.iss.one/spmmc

#TIKVAH_ETHIOPIA

#share #ሼር

@tsegabwolde @tikvahethipia
ይህ ሀሰተኛ ገፅ ነው⬆️

የሀገር አቀፍ ትምህት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2011 ዓ/ም የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል በሚል እየተሰራስጨ የሚገስኘው መረጃ ሀሰተኛ ነው። 12,380 Like ያለው ገፅ ሀሰተኛ ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማዕከላዊ እስር ቤት⬆️

"ዛሬ ጠዋት ጀምሮ እስከ ረፋድ ድረስ በርካታ ሰዎች ማዕከላዊ እስር ቤትን እየጎበኙ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህም መካከል አቶ #ጃዋር_መሀመድ የተገኙ ሲሆን ኦቦ #በቀለ_ገርባ ለOMN ሚዲያ ሠዎች እና በቦታው ለተገኙ ጎብኚዎች ስለ ቦታውና በዚያ ስላሳለፉአቸው አስከፊ ጊዜያት ገለፃ ሲያደርጉና ሲያስጎበኙ ነበር።"

📸በርካታ የTIKVAH-ETH የቤተሰብ አባላት ማዕከላዊን በመጎብኘት የሚያዩትን ነገር በፎቶ እያስቀሩ እየላኩን ይገኛሉ!


Via #Fasil/TIKVAH-ETH/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
2954 አሽከርካሪዎች ጉቦ ለመስጠት ሲሞክሩ ተይዘዋል!

በ2011 በጀት ዓመት ለትራፊክ ፖሊሶች ጉቦ ለመስጠት የሞከሩ 2954 አሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት ፣አሽከርካሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ህግ በመተላለፍ ወንጀል ሲጠየቁ ለትራፊክ ፖሊስ አባላት የመማለጃ ገንዘብ ለመስጠት በመሞከራቸው ነው። እንደ ኮማንደር ፋሲካ አባባል ግለሰቦቹ ከሃምሳ እስከ ሁለት መቶ ብር ጉቦ ለመስጠት የሞከሩ ናቸው። ድርጊታቸው በበቂ ማስረጃ በመረጋገጡም ጉዳያቸው ለዓቃቤ ህግ ተላልፎ በክስ ሂደት ላይ ይገኛል። እስካሁን ከአሽከርካሪዎች ገንዘብ ሲቀበሉ የተያዙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት ያለመኖራቸውን ያረጋገጡት ኮማንደር ፋሲካ ድርጊቱ ካለፈው ተመሳሳይ ሁኔታ ጋር ሲነጻጸርም ቁጥሩ በ 5 በመቶ ያህል መጨመሩን ተናግረዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia