TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62K photos
1.58K videos
216 files
4.31K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ጠዋት ከ80 በላይ፤ እስከ ቀጣዩ ሳምንት አርብ ድረስ ከ500 በላይ ልጆች ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ” - የወላጆች ኮሚቴ በማይናማር በእገታ ከነበሩ በርካታ ዜጎች መካከል፣ “ ጠዋት (ማለትም አርብ) ከ80 በላይ ልጆች ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ ” ሲል የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። “ ትኬታቸው ጊዜው ስላለፈ 15ዐ ዶላር ሊቀጡ ነበር፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጣቱን አንስቶላቸው…
#Update

“ ልጆቻችን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ቤተሰብን ሲያዩ በጣም ደስተኞች ነበሩ ” - የወላጆች ኮሚቴ

በማይናማር በችግር ላይ የቆዩና ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩ 85 ልጆችን ዛሬ ጠዋት ቦሌ ኤርፓርት ሂዶ እንደተቀበለ የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

መጡ የተባሉት 85 ኢትዮጵያውያን ቢጂኤፍ እና ዲኬቢኤ ከሚባሉ ካምፓች የነበሩ እንደሆኑ፣ ኤርፓርት ሲደርሱም ዝግጅት አድርጎ እንደተቀበላቸው ኮሚቴው ነግሮናል።

ኮሚቴው በሰጠን ቃል፣ “ ልጆቻችን ዛሬ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ተኩል ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ቤተሰብን ሲያዩ በጣም ደስተኞች ነበሩ ” ብሏል።

“ ከመጡት ውስጥ የአዲስ አበባ ልጆች ጥቂት ናቸው። አምስት፣ ስድስትም አይሆኑም። አብዛኛዎቹ የክፍለ ሀገር ልጆች ናቸው ” ሲልም ተናግሯል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸው ተመላሾቹም፤ 85 ልጆች ወደ ኢትዮጵያ ዛሬ መግባታቸውን ገልጸው፣ ለሀገራቸው እንዲበቁ የተባበሯቸውን ሁሉ አመስግነዋል።

ወጣቶች ወደየትኛውም አገር ከመሄዳቸው በፊት፣ የሥራውን አይነት ቀድመው ማውቅ፣ የሚወስዷቸውን ሰዎች ህጋዊነት በሕጋዊ ተቋም ማረጋገጥ እንዳለባቸው በአጽንኦት አሳስበዋል።

ለቀሩት ልጆች ትኩረት እንዲሰጥ ተመላሾቹ የጠየቁ ሲሆን፣ እስከ ቀጣዩ ሳምንት ድረስ ከ500 በላይ ልጆች ይመጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ፣ የቀሪዎቹ ፕሮሰስም ከዚያ በኋላ እንደሚጀመር ኮሚቴው ትላንት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ መግለጹ ይታወሳል።

(ጉዳዩን እየተከታተልን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ 
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከጅቡቲ ለመውጣት የሶስት ወራት ጊዜ እንዲሰጣቸው ጥያቄ ቀረበ።

በጅቡቲ የሚኖሩ ሰነድ አልባ ኢትዮጵውያን፣ ሀገሪቱን ለቀው ለመውጣት የሶስት ወረ ጊዜ እንዲሰጣቸው ይፋዊ ጥያቄ መቅረቡን፣ በጅቡቲ ያለው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እና የሀይማኖት አባቶች ህብረት በጋራ ጠየቁ፡፡

አንድ የህብረቱ አባል የሆኑ አባት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ በነዚህ አካላት እየተደረገ ያለው ሽምግልና በዜጎች ላይ እንግልትና የመብት ጥሰት እንዳይፈፀም አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል፡፡

የህብረቱ አባል በዝርዝር ምን አሉ ?

" ሰነድ አልባ ዜጎች ከሀገሪቱ ለቀው ይውጡ የሚለው ነገር በሽምግልና ተይዞ ዜጎቻችንን ህጋዊ ነዋሪዎች ለማድረግ፣ ፓስፖርት እንዲያገኙ ለማስቻል፣ ቪዛም እንዲሰጣቸው፣ ቀደም ሲል የተሰጠው የአንድ ወር ቀነገደብ ወደ ሶስት ወራት እንዲራዘም ነው የጠየቅነው፡፡

ይህን ጥያቄ ለሀገሪቱ ፕረዝደንት ፅ/ቤት፣ ለሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ እና ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደብዳቤ አቅርበናል፡፡ ዜጎቻችን በቂ ዝግጅት አድርገው ከሀገር እንዲወጡ አለያም ህጋዊ እንዲሆኑ ቀኑ ይራዘምላቸው ብለናል፡፡

እኛ ወንድሞቻችሁ ነን፣ እናንተም ወንድሞቻችን ናችሁ፣ የሁለት ሀገር አንድ ህዝብ ነን እኛ፣ ልዩነት የለንም፡፡ ይህን ከግምት አስገብታችሁ፣ የትናንቱን ታሪክ የነገውንም ጉዞዋችንን ተመልክታችሁ መፍትሔ ስጡን፡፡ ጅቡቲ እና ኢትዮጵያ የሚለያዩ ሀገራት አይደሉም፡፡ የእኛ ዜጎች እዚህ ጫና እንደሚፈጥሩ ፤ አብዛኛው ዜጋችንም ህገወጥ ነዋሪ እንደሆነ እናውቃለን ብለናቸዋል፡፡

የጅቡቲ ባለስልጣናትም ጥያቄያችንን ተገንዝበው፣ ምላሽ እንደሚሰጡን ነግረውናል፡፡ ነገር ግን በምክር ቤት የተላለፈ ውሳኔ ስለሆነ አሁንም ውሳኔውን መለወጥ የሚችለው ምክር ቤቱ ነው ብለውናል፡፡ ነገር ግን ተረድተናችኋል ብለዋል፡፡

በዚህ የሽምግልና ስራችን የተረጋጋ ነገር እንዲኖር አድርገናል፡፡ ፖሊሶች ቤት ለቤት እየገቡ ሁከት እንዳይፈጥሩ፣ በቤት ውስጥ ሰው እንዳይዙ አድርገናል፣ ከዚህ ተግባር እንዲታቀቡ አስችለናል፡፡

መንገድ ላይ የሚያገኙትን ሰው ካልሆነ በስተቀር፣ ስራ ላይ ያለውን ሰው እንዳይነኩብን ጠይቀን ሰምተውናል፡፡ በልመና ነው ይህን ያስረዳናቸው፡፡ እኛ የሀይማኖት አባቶች ነን፣ መሸምገል ነው የምንችለው፡፡

ማክሰኞ ዕለት ደግሞ ኡጋዞችን ለማነጋገር ወደ ድሬዳዋ እንመጣለን፡፡ በዚህ ሽምግልና መሳተፍ ያለባቸውና የጅቡቲን መንግስት ማሳመን የሚችሉ ኡጋዞችን/የሀገር ሽማግሌዎችን በድረዳዋ እናነጋግራለን፡፡ እነዚህ ኡጋዞች እንደዚህ አይነት ሁኔታ ሲያጋጥም በራሳቸው ህግ ያስተካክሉታል፡፡ ኡጋዞቹን ወደ ሀገሪቱ መንግስት በሽምግልና ለመላክ ነው እየሰራን ያለነው፡፡

የእኛ ሽምግልና ከየትኛውም መንገድ የተሻለ ሆኗል፣ ተሳክቶልናልም፡፡ ሰነድ አልባ ዜጎቻችን ህገወጦች ናቸው ሲሉን፣ ህገወጥ ሰውነት የለም፣ ህገወጥ አካሔድ እንጂ ብለን ተከራክረናል፡፡ ሰውነት ህጋዊ ነው፣ ጉዞው ነው ህገወጡ፡፡ በደስታቸው ጊዜ፣ ከትኛውንም እምነት ተከታይ ጋር አብረን ነበርን፣ አሁን ሲያዝኑ ሲያለቅሱ ቆመን ማየት አንችልም፣ እኛ የሀይማኖት አባቶች ነን ብለናቸዋል፡፡ በካቢኔው ውስጥ ያሉት የመንግስት ሐላፊዎች በሀሳቦቻችን ተስማምተዋል፡፡ "

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

“ የዲኤችኤል/DHL ሰራተኞች ነገ ወደ ስራ ይመለሳሉ፡፡ ለሰራተኞቹ የ 35 በመቶ የደመወዝ ጭማሪ ይደረጋል ” - አቶ አባትይሁን ታከለ 

ባለፈው ሐሙስ ከአሰሪው ድርጅት ጋር ባለመግባባታቸው ስራ ያቆሙት የዲኤችኤል/DHL ሰራተኞች ከዛ በኋላ በተደረገ ድርድር የሰራተኛ ማህበሩና ድርጅቱ ስምምነት ላይ በመድረሳቸው በነገው ዕለት ወደ ስራ እንደሚመለሱ ተገለፀ፡፡

የትራንስፖርትና መገናኛ ሰራተኛ ማህበራት ኢንዱስትሪ ፈደሬሽን ፕረዝደንት አቶ አባትይሁን ታከለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል በቦሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ፅ/ቤት አሸማጋይነት ሲደረግ የሰነበተው የሁለቱ አካላት ድርድር በዛሬው ዕለት በስምምነት መቋጨቱን ተናግረዋል፡፡

አቶ አባትይሁን ታከለ በዝርዝር ምን አሉ ?

“ ባለፈው አርብ የቦሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ፅ/ቤት በአደራዳሪነት ገብቶበት፣ ሁለቱንም አካላት በማቀራረብ ረገድ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ የሰራተኛ ማህበሩ 50 ፐርሰንት የደመወዝ ጭማሪ ሲጠይቅ፣ ድርጅቱ ደግሞ 24 ፐርሰንት ብቻ ነው የምጨምረው የሚል አቋም ነበራቸው፡፡

በዚህም ሁለቱም ተደራዳሪዎች መስማማት ስላልቻሉ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ የስራና ክህሎት ፅ/ቤት በአሸማጋይነት ጣልቃ ሊገባ ችሏል፡፡ ይኸው መንግስታዊ አካል ያቀረበው የማስማሚያ ሀሳብ ደግሞ የደመወዝ ጭማሪው 35 ፐርሰንት ይሁን የሚል ነው፡፡

የቦሌ ክፍለከተማ ይህን ሀሳብ ያቀረበው ሰራተኞችንም በማወያየት ነው፡፡ በመጨረሻም የሰራተኛ ማህበሩ እና ድርጅቱ በዚህ ሀሳብ መስማማታቸውን አረጋግጠዋል፡፡ በዚህ መሰረት፣ የድርጅቱ ሰራተኞች በነገው ዕለት ማለትም ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ስራ እንደሚመለሱ ተስማምተዋል፡፡

ይኸው አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆን በሰራተኛ ማህበሩ በኩል የተጠየቀ ቢሆንም ድርጅቱ ባለመስማማቱ፣ የ 35 ከመቶ ጭማሪው ከግንቦት ወር ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ነው የተገለፀው፡፡ በሚያዝያ ወር ደመወዝ ላይ ግን የ 24 በመቶ ጭማሪ እንደሚያደርግ ድርጅቱ ተስማምቷል፡ ” ብለዋል።

እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ አስቸጋሪ የድርድር ሒደቶች መታለፋቸውን የገለፁት አቶ አባትይሁን የቦሌ ክፍለ ከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት በአሸማጋይነት ጣልቃ በመግባቱ ችግሩ ሊፈታ እንደቻለ ተናግረዋል።

ለዚህም የቦሌ ክፍለከተማ ስራና ክህሎት ፅ/ቤት ምስጋና እንደሚገባው ጠቅሰዋል፡፡

ድርጅቱና የሰራተኛ ማህበሩ ችግራቸውን በመግባባትና በመደራደር መፍታት ሲችሉ ነገሩ የከፋ ደረጃ ላይ (የስራ ማቆም እርምጃ ድረስ) መድረሱ አግባብ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል።

የዲኤችኤል/DHL ሰራተኞች፣ ባለፈው ሐሙስ፣ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ነበር በአሰሪና ሰራተኛ አዋጁ መሰረት የ10 ቀን ማስጠንቀቂያ ከሰጡ በኋላ ወደ ስራ ማቆም እርምጃ የገቡት፡፡

ለዚህ እርምጃ ምክንያት የሆኑዋቸው ጥያቄዎችም የቆዩና ብዙ ናቸው። አንደኛው በአዋጅ የተሰጠው የህብረት ስምምነት ድርድር ጥያቄ ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ የደመወዝ ጭማሪን የሚመለከት ነበር፡፡

አቶ አባትይሁን ታከለ ባለፈው ሳምንት እንደገለጹልን ድርጅቱ በየአመቱ ደመወዝ ይጨምር የነበረ ቢሆንም የዘንድሮን ግን ዘሎታል።

" ከማህበሩ ጋር የማደርገውን ድርድር ሳልጨርስ የደመወዝ ጭማሪ አላደርግም " በሚል ነው ደመወዝ ጭማሪውን የዘለለው። የማናጅመንት አባላት ለሆኑ ሰራተኞች ግም ደመወዝ ጨምሯል፣ ለሰራተኛው ግን አልጨመረም፡፡ ሰራተኞቹም " የገንዘብ የመግዛት አቅምም እየደከመ በመምጣቱ የደመወዝ ጭማሪ መደረግ አለበት " በማለት ነበር የስራ ማቆም እርምጃ የወሰዱት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update “ ልጆቻችን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ቤተሰብን ሲያዩ በጣም ደስተኞች ነበሩ ” - የወላጆች ኮሚቴ በማይናማር በችግር ላይ የቆዩና ወደ ኢትዮጵያ ይመጣሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩ 85 ልጆችን ዛሬ ጠዋት ቦሌ ኤርፓርት ሂዶ እንደተቀበለ የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል። መጡ የተባሉት 85 ኢትዮጵያውያን ቢጂኤፍ እና ዲኬቢኤ ከሚባሉ ካምፓች የነበሩ እንደሆኑ፣ ኤርፓርት ሲደርሱም ዝግጅት…
#Update

“ ትላንት 89 ልጆች፣ ዛሬ 85 ልጆች መጥተዋል፤ ነገ 90፣ ቅዳሜ 90 ልጆች ይመጣሉ ” - የወላጆች ኮሚቴ

በማይናማር በችግር ከነበሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን መካከል ከ70 በላይ የሚሆኑት በሁለት ቀናት ውስጥ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የወላጆች ኮሚቴ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

ኮሚቴው በሰጠው ቃል፣ ትላንት 89 ኢትዮጵያውያን መምጣታቸውንና የወላጆች ኮሚቴ ተቀብሏቸው ወደየቤታቸው መግባታቸውን አመልክቷል።

ዛሬ ደግሞ 85 ልጆች እንደመጡ ነገ 90፣ ቅዳሜ 90 ልጆች እንደሚመጡ ገልጿል።

ልጆቻችን በተከታታይ ጥሩ እየመጡልን ነው ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ሌሎች ያልመጡት ኢትዮጵያውያን የሚመለሱበትን ሁኔታ ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እያሳሰበ መሆኑን ኮሚቴው አስረድቷል።

“ አንዳንድ ውዥምብሮች ነበሩ፤ ልጆች ይወነባበዳሉ፤ ደላሎች ይመስሉኛል ሆን ብለው ልጆች እንዳይረጋጉ የሚያደርጓቸው ” ሲልም ገልጿል።

“ ‘ኤንጂኦ ጥቂት ሰው ብቻ ነው መውሰድ የሚችለው፤ እዚሁ ልንቀር ነው፤ ከቀን 18 በኋላ ደሊጌሽን ይመለሳል፤ ጨንቀት ላይ ነን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠይቁልን ’ እያሉ ስለነበር ሄደን አነጋግረንላቸውዋል” በማለትም ተናግሯል።

“ ሚኒስቴሩም ፓስፓርትና ትኬት ያላቸው መጀመሪያ፣ ሁለተኛ ትኬታቸው ኤክስፓየርድ ቢያደርግም ፓስፓርት ያላቸው፣ በሦስተኛ ትኬትም ፓስፓርትም የሌላቸውን ልጆትን ወጪ 20% የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ 80% ኤንጂኦ ችለውላቸው ይመጣሉ ተብሎ ከተቀመጠው ውጪ አዲስ የተለየ ነገር የለም የሚል ምላሽ ሰጥቶናል ” ነው ያለው።

ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው እስከሚመለሱ ተረጋግተው እንዲጠብቁ በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ኮሚቴው መልዕክት አስተላልፏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ዛሬ ቅዳሜ በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን በሚገኙ 6 ወረዳዎች ካለፈው የቀጠለ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመሩትን ህወሓት የሚቃወም የተቋውሞ ሰልፍ ተካሂደዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ " ራሳችን በራሳችን የማስተዳደር መብት ተጎናፅፈናል የህወሓት ቡድን በሚመድብልን ምስሌነ አንተዳደርም አያም በል ! " ብለዋል።

" የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት እናከብራለን ፤ ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ የትግራይ ሉአላዊ ግዛት እንዲከበር ሰላማዊ ትግላች አጠናክረን እንቀጥላለን " ሲሉም ተደምጠዋል።

" የአገርና የህዝብ ህልው አደጋ የሚከት ከውጭ ሃይል የሚደረግ ህገ-ወጥ ግንኑነት እንቃወማለን " ሲሉም አክለዋል።

ጊዚያዊ አስተዳደሩ አቃፊና አሳታፊ እንዲሆን የጠየቁት ዋና አስተዳዳሪው ህዝቡ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ተቆጥረው የተሰጡት ሃላፊነቶች እንዲሳኩ ከጎኑ ሆኖ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

በሰልፉ ላይ ተሳታፊዎች " የሃይል አስተዳደር አንቀበልም ፣ የምስሌነ አስተዳደር ይወገድ ፣ ህዝቡ ለህግና ስርዓት መከበር ፅኑ አቋም አለው ፣ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ይከበር " የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

" በክልሉ አድማ ብተናና መደበኛ ፖሊስ እየተወሰደ ያለዉ የሃይል እርምጃዉ ቀጥሎ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ 2 ንፁሃን አርሶአደሮች ተገድለዋል " - ነዋሪዎች

➡️ " ' የሃይል እርምጃ ተወስዶ ሁለት አርሶአደሮች ተገድለዋል ' የሚባለው ፍፁም የዉሸት መረጃ ነዉ። ሽፍቶችን ለመያዝ እየተደረገ ባለዉ ኦፕሬሽን እስካሁን የሞተ ሰዉ የለም " - የጋሞ ዞን ፖሊስ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የዘይሴ ነዋሪዎች " ካሳለፍነዉ እሁድ ጀምሮ በአከባቢው በአድማ ብተናና የጋሞ ዞን ፖሊስ እየተወሰደ ያለው ተገቢ ያልሆነ የሃይል እርምጃ በርካታ ምስቅልቅሎችን ሲፈጥር ቆይቷል ከትላንት በስቲያ ደግሞ ከብት በመጠበቅ ላይ የነበሩ 2 አርሶአደሮች በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች ተገድለዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

በአከባቢዉ እየተንቀሳቀሱ ባሉ የታጠቁ የፀጥታ አካላት እየተወሰደ ባለዉ ድብደባና እስር ምክንያት የህብረተሰቡ እቅስቃሴ ተገድቦ መቆየቱን የገለፁት ነዋሪዎቹ " ' ቢቀሳ 'ተብሎ በሚጠራዉ አከባቢ ከብት በረሃብ እንዳይጎዳ አሰማርተዉ የነበሩ 2 አርሶ አደሮችን በጥይት ተመተው ተገድለዋል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገርናቸው የአከባቢው የሃይማኖት መሪዎች እና ሽማግሌዎች " እርምጃው ፍፁም ትክክል ያልሆነ " ሲሉ ገልጸዋል።

ከሰሞኑን የሃይማኖት ተቋማትን ነፃነት የጣሰ ተግባር መፈጸሙን ጠቁመዋል።

" በኤልጎ ሙሉ ወንጌል እና ወዘቄ መካነ ኢየሱስ ቤተክርቲያናት አገልጋዮች ከመድረክ ተጎትተው ተወስደዉ የታሰሩበትና የተደበደቡበት ሁኔታ ነበር። በዚህም ምክንያት በእሁድ ዕለተ የአምልኮ ቀን ምዕመናን ወደ ቤተክርስቲያን አልመጡም " ሲሉ ተናግረዋል።

" የሃይማኖት ተቋማት ነፃነት ተጥሷል ፣ የጤና ተቀማት የወታደር ከምፕ ሆነዋል፣ ትምህርትና የእርሻ ስራን ጨምሮ አጠቃላይ ሰላማዊ እንቅስቃሴ በዘይሴ ኤሊጎ፣ ዘይሴ ዳቢሌ እና ዘይሴ ወዘቄ አከባቢዎች ወዳልተፈለ አቅጣጫ እያመራ ስለሆነ ከዚህ በላይ ቀዉስና ሞት እንዳይከሰት የክልሉ መንግስትና የፌደራል ገለልተኛ አካላት ጣልቃ ገብተዉ ያረጋጉ " ሲሉ የሃይማኖት መሪዎች እና ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

የጋሞ ዞን ፖሊስ ምን አለ ?

የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ደበበ ኦንቶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ ከሳምንት በፊት በግዳጅ ላይ ለነበሩ የፀጥታ አባላት ስንቅ ሲወስዱ በነበሩ የአድማ ብተናና ፖሊስ አባላት ላይ በተፈፀመ ድንገተኛ ጥቃት አንድ የአድማ ብተና ፖሊስ ተሰውቷል ሲሉ አስታውሰዋል።

" ይህን ጥቃት ያደረሱ ሽፍቶችን ለመያዝ የፀጥታ መዋቅር አካላት ተሰማርተዋል ነገርግን ' የሃይል እርምጃ ተወስዶ ሁለት አርሶአደሮች ተገድለዋል ' የሚባለው ፍፁም የዉሸት መረጃ ነዉ " ሲሉ ገልፀዋል።

" ለአከባቢው አለመረጋጋት ዋነኛ ምክንያት የሆኑት ተደብቀዉና በሰሩት ወንጀል የሚፈለጉ አንዳንዶች ደግሞ በሌሉበት የፍርድ ዉሳኔ ተላልፎባቸዉ የእስር ትዕዛዝ የወጣባቸው ናቸው " ያሉት አዛዡ " እነዚህ ግለሰቦች ሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የዉሸት መረጃ እያሰራጩ ነዉ " ብለዋል።

በአከባቢው የሚገኙት የፀጥታ አካላት በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዳይወርድ በሚፈልጉ ፀረ ሰላም ሃይሎች በሰላማዊ ዘጎች ላይ ጥቃት እንዳይፈጸም ከረጅም ጊዜ በፊት ጀምሮ በአከባቢው የሚገኙ ናቸዉ ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) የከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠባባቂ ፕሬዜዳንት ሹመት ሰጥተዋ።

አቶ መንግስቱ ተኽላይ ኪዳነ ከግንቦት 9/2017 ዓ.ም ጀምር የከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠባባቂ ፕሬዜዳንት ሆነው ተሹመዋል።

የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ተከተሎ ተቋቁሞ በአቶ ጌታቸው ረዳ ሲመራ በነበረው ጊዚያዊ አስተዳደር ተሾመው ላለፉት ሁለት አመታት ያገለገሉት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንትና ምክትላቸው በራሳቸው ፍቃድ  ከግንቦት 5/2017 ዓ.ም ጀምሮ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ ከሃላፊነት እንዳነሱዋቸው ይታወሳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ የተገደሉት ሰዎች ብዛት 17 ነው። ከሟቾች መካከል 12 ህፃናት ናቸው ” - የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባል በካማሺ ዞን ምዥጋ ወረዳ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለ ጥቃት ንጹሐን ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች እና የክልሉ ምክር ቤት አባል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። ነዋሪዎቹ፣ “የሸኔ ታጣቂዎች ጥቃት ፈጽመዋል” ብለው፤ ከ10 በላይ ንጹሐን እንደተገደሉ፣ አብዛኛዎቹ ሟቾች ህፃናት እንደሆኑ ተናግረዋል።…
#Update

“  ከተገደሉት ሰዎች በተጨማሪ 100 ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ንብረት ወድሟል፣ እንስሳትም ተዘርፈዋል ” - አስተያየት ሰጪ

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ ካማሺ ዞን ፤ ምዥጋ ወረዳ ያነጋገራቸው አንድ አስተያየት ሰጪ በሰጡት መረጃ በቀደም ሲል ' አንገርሜጢ ' በምትባል ቀበሌ፣ በአሁኑ አጠራር ደግሞ ' አይ ሻንጂድም ' በምትባል ታዳጊ ከተማ ውስጥ ባለፈው ዕሮብ ከጠዋቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ነው ጥቃት የተፈፀመው፡፡  ጥቃቱን " የሸኔ ታጣቂ ቡድን " መፈጸሙ ተገልጿል።

በጥቃቱ 12 ህፃናት የሚገኙባቸው 18 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ 12 ሰዎች ደግሞ ቆስለው በምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ነቀምቴ ከተማ በመከላከያ ድጋፍ የህክምና እርዳታ ተደርጎላቸዋል፡፡ አካባቢው በአብዛኛው የጉሙዝ ማህረሰብ የሚኖርበት እንደሆነ ተገልጿል።

ከተፈፀመው ግድያ በተጨማሪ ታጣቂዎቹ 500 ኩንታል እህል ዘርፈዋል፣ የቤት እንስሳትም ወስደዋል፣ ንብረት አውድመዋል፣ ከ100 በላይ ቤቶችን አቃጥለዋል፡፡ ታጣቂ ቡድኑ ጥቃቱን ከፈፀመ በኋላ፣ ወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ወለጋ ዞን አዋሳኝ ቀበሌዎች ሔዷል ፤ ሆኖም ብዙም አልራቀም ብለዋል አስተያየት ሰጪው፡፡

ከኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይሎች ጋር በመተባበር የአካባቢውን ሰላም ለማስጠበቅ እየተሰራ ቢሆንም፣ መንግስት በቋሚነት የፀጥታ ሀይሎችን በወረዳው ማስፈር አለበት ሲሉም ተናግረዋል፡፡ አካባቢው ከዚህ ሀይል ካልፀዳ ዘላቂ ሰላም አይኖርም ብለዋል፡፡   

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የአካባቢው ህዝብ ተወካይ የሆኑት መኮነን ጎሌሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በዚህኛው ጥቃት 18 ሰዎች ተገድለዋል፣ 12 ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል በማለት አረጋግጠዋል፡፡

“ ሸኔ ለምን በሰላማዊ ህዝብ ላይ ጥቃት እንደሚፈፅም አይገባኝም፡፡ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ካለ በሰላማዊ መንገድ መፍታት ይቻላል፡፡ እዛ ያለው ሀብት ለሁሉም የሚበቃ ነው፡፡ የፖለቲካ ፍላጎትን ለማሟላት ህፃናትንና ሴቶችን በአሰቃቁ ሑኔታ መግደል ትክክል አይደለም፡፡ ወደ ስልጣን መምጣት የሚፈልግ ሀይል ህፃናትን መስዋዕት በማድረግ አይደለም ” ብለዋል፡፡

በዚሁ ወረዳ ላይ ከሶስት ሳምንት በፊት ጉምቢ በሚባል አካባቢ 8 ሰዎች መገደላቸውንም ተናግረዋል፡፡ በወረዳው 13 የጉሙዝ ቀበሌዎች እንዳሉ የገለፁት የፓርላማ አባሉ አካባቢው ከምስራቅ ወለጋ ዞን ጋር የሚዋሰን እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የጉሙዝ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ፓርቲ አባል አቶ ተስፋዬ ንጉሴ ደግሞ ዛሬ ለቲካቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ " በጥቃቱ የሟቾች ቁጥር 19 ደርሷል ፤ ሟቾች የጉሙዝ፣ የኦሮሞና የአማራ ብሔር ተወላጆች ናቸው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በጥቃቱ የቆሰሉት ሰዎች ቁጥርም ወደ 14 አድጓል ያሉት አቶ ተስፋዬ ቁጥሩ የጨመረው ቀደም ሲል በጥይት ተመተው የሸሹ ሰዎች አሁን በመገኘታቸው ነው ብለዋል፡፡

ጥቃቱ በእጅጉ ዘግናኝ እንደሆነ አመልክተው እንዲህ አይነት በንፁሀን ዜጎች ላይ የሚከሰትን አሰቃቂ ድርጊት መንግስት ሊከላከል ይገባዋል ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

ከካማሺ ዞን እና ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለስልጣናት ተጨማሪ አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ ወደፊት መረጃ ካገኘን የምናቀርብ ይሆናል፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ያለፈቃዳችን ከደመወዛችን ተቆርጦብናል፤ ይመለስልን ” - መምህራን  ➡️ “ 'በእጃችን ይዘን በምንገባው ገንዘብ ራሳችንን ለማኖር እየተቸገርን ነው' እያሉ ባሉበት ወቅት ወርደው ሳያወያዩ ከደመወዛቸው መቆረጡ መምህራኑን አስቆጥቷል ” - የባስኬቶ ዞን መምህራን ማኀበር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባስኬቶ ዞን የላስካ ዙሪያ ወረዳ መምህራን፣ “ለህዳሴ ግድብ የቦንድ ግዥ” በሚል በአመራሮች ያለፈቃዳቸው እና…
#Update

" መንግስትን ጠይቀው ‘መምህራን በሀገራዊ ልማት መሳተፍ የለባቸውም’ ካለ ገንዘባቸው ሊመልስ ይችላል "  - የወረዳው ትምህርት ጽሕፈት ቤት

" እጅ በእጅ እስከ 380 ሺሕ ብር በዙሪያ ወረዳ ተሰብስቧል ! "

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ባስኬቶ ዞን ላስካ ዙሪያ ወረዳ ያሉ መምህራን ደመወዝ “ውይይት ሳይደረግ፤ ያለፈቃድ" መቆረጡ እንዳስቆጣቸው መምህራኑ፣ የክልሉና የዞኑ መምህራን ማኀበር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

የባስኬቶ ዞን መምህራን ማኅበር ፤ " ' በእጃችን ይዘን በምንገባው ገንዘብ ራሳችንን ለማኖር እየተቸገርን ነው' እያሉ ባሉበት ወቅት ወርደው ሳያወያዩ ከደመወዛቸው መቆረጡ መምህራኑን አስቆጥቷል " ብሎ ነበር።

ቅሬታ የተነሳበት የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?

የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አብርሃም ሽብልቶ፣ " ያላግባብ የሚባል ነገር የለም፤ ደመወዝ እንደሚቆረጥ ሀገራዊ አጀንዳ ነው " ብለዋል።

ለቦንድ መግዣ በተቀመጠው ስኬል መሠረት ከ750 እስከ 1500 ብር እንደሚቆረጥ ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ መምህራን ማህበሩ፣ የየትምህርት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን እንደተወያዩ ገልጸው፣ " ዛሬ የተፈጠረ አጀንዳም አይደለም፤ ከክልል የወረደ ነው፤ ተልኮ ከተሰጠ በኋላም በዙሪያ ወረዳ ምክትል አስተዳደርና በፋይናንስ ኃላፊው አማካኝነት በባንክ ነው የተሰበሰበው " ሲሉ አብራርተዋል።

"እጅ በእጅ እስከ 380 ሺሕ ብር በዙሪያ ወረዳ ተሰብስቧል ቀሪውን ግን በፋይናንስ ቆርጣችሁ ውሰዱ ጠዋት ማታ ብር አምጡ እያልን ሌላ አጀንዳ አንፈጥርም በሚል ተስማምተን እንጂ ዝም ብለን ያደረነው ነገር አይደለም " ነው ያሉት።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የመምህራኑ ደመወዝ የሚቆረጠው በአስገዳጅተነት ካልሆነ ታዲያ " ያለፈቃዳችን ተቆረጠብን ይመለስልን " ለሚሉት ገንዘቡን ለመመለስ ፈቃደኞች ናችሁ? የሚል ጥያቄ ለኃላፊው አቅርቧል።

ኃላፊው "
እኔ እንደ ዙሪያ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይህን መወሰን አልችልም፤ ሆኖም አጀንዳው የመንግስት ስለሆነ ለመንግስት ማቅረብ ይችላሉ " ብለዋል።

" ለምሳሌ ሁለት ዙር ከፍሎ የትቆረጠበት ሰው አለ፤ ተጨማሪ የተቆረጠባቸው ሰዎች ገንዘባቸውን እንዲወስዱ መልዕክት አስተላልፈናል። ስለዚህ መንግስትን ጠይቀው 'መምህራን በሀገራዊ ልማት መሳተፍ የለባቸውም' ካለ ሊመልስ ይችላል " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የዙሪያ ወረዳ እንጂ የከተማው መምህራን ደመወዛቸው አልተቆረጠም፤ ይህስ ለምን ሆነ ? ለምን ተመሳሳይ ተግባር አልተከተላችሁም ? ስንል ኃላፊውን ጠይቀናል።

ኃላፊው፣ " እኛም ጥያቄ አቅርበን (የከተማውም) ‘እጅ በእጅ ከፍለዋል’ ነው የተባልነው። በዚህ አግባብ ያልከፈሉ ደግሞ ከደመወቸው እንዲቆረጥ ደብዳቤ አስገብተናል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
“ ምን ያህል ተቃጥሎ ምን ያህል እንደቀረ አላወቅንም። እሳቱ ከባድ ነበር። ኮሚቴ ተልኳል ” - የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል ቡኖ በደሌ ዞን በበደሌ ከተማ የሚገኝ ከተሰራ አመት የሆነው መስጂድ ምክንያቱ እስካሁን ባልታወቀ ሁኔታ በእሳት መቃጠሉ ተሰምቷል። “ ቡልቲ አዳ” የተሰኘው መስጂድ “ሙሉ ለሙሉ በእሳት” መቃጠሉን የተመለከተ መረጃም በማህበራዊ ሚዲያ ተሰራጭቷል። …
#Update

“ መስጂዱ ሙሉ ለሙሉ ነው የተቃጠለው። ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተደረገ ነው ” - ኮሚቴው

በቡኖ በደሌ ዞን የበደሌ ከተማ “ቡልቲ አዳ” መስጂድ የእሳት ቃጠሎ እንደደረሰበት፣ የቃጠሎውን ምክንያትና መጠኑን ለማረጋገጥ ወደ ስፍራው ኮሚቴ ተልኮ እንደነበር የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጾ ነበር።

በዚህም ምክር ቤቱ በወቅቱ በሰጠን ቃል፣ ቃጠሎው መፈጸሙን ገልጾ፣ “ ምን ያህል ተቃጥሎ ምን ያህል እንደቀረ አላወቅንም። እሳቱ ከባድ ነበር። ኮሚቴ ተልኳል ” ነበር ያለው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ የመስጂዱ ቃጠሎ ምክንያት ታወቀ ? መስጂዱ ሙሉ በሙሉ ነው የተቃጠለው ? ሲል ዛሬ ወደ ስፍራው የተላከውን ኮሚቴ ጠይቋል።

ኮሚቴው ምን መለሰ ?

“ በቃጠሎው ተጠርጥረው በቀጥጥር ስር የዋሉ አሉ። እስካሁን ምርመራ ላይ ናቸው። ከቃጠሎው ጀርባ ያለው ምክንያት አልታወቀም። ምናልባት ግን ‘ሰዎቹ የአእምሮ ችግር ያለባቸው ናቸው’ እያሉ ነው።

‘እኔ ነኝ ጉዳዩን የፈጸምኩት’ ብሎ የተያዘ ሰው አለ። አንድ ሁለት ሰዎች ተይዘዋል። አሁን ተረጋግቷል። ተማሪዎቹም ወደ ትምህርታቸው ተመልሰዋል። ከክልልም ከዞንም ዛሬ መጥተው ልጆቹን አወያይተዋል።

መስጂዱ ሙሉ ለሙሉ ነው የተቃጠለው። ይህ መስጂድ ተትቶ ሌላ መስጂድ እንዲሰራ የመንግስት አካል ፈቅዷል። የተቃጠለው መስጂድ ተሰርቶ ያለቀ ነበር። አሁን ሌላ መስጂድ መስራት ሊጀመር ነው ” ብሏል።

የመስጂዱ የአዳሪ ትምህርት ቤት ከመስጂዱ ቅጥር ግቢ ውጪ ስለሆነ እንዳልተቃጠለ፣ በዚህም ወደ 300 የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሆነ ኮሚቴው ገልጿል።

መስጂዱ ከመሰራቱ በፊት የአሁኑን ጥቃት ሊያደርስ የሚችል የተፈጠረ አለመግባባት ተፈጥሮ ነበር ? ስንል ለኮሚቴው ጥያቄ አቅርበናል።

ኮሚቴው፣ “ አሁን እኛም ጠይቀን ነበር። ችግር እንዳልነበር ነው የተነገረን። እንደዛ የሆነ ነገር አልነበረም። ግን አሁን ሙሉ ለሙሉ እንደዚህ ነው ብለን ለማብራራት ምርመራው ገና እየቀጠለ በመሆኑ ማረጋጠጥ የቻልነው ነገር የለም ” ሲል መልሷል።

በወቅቱ ሲሰራ ከዞን አስተዳደር ተፈቅዶ እንደሆነ መረዳቱንም ገልጿል።

መስጂዱ ሲሰራ ምን ያህል ወጪ እንደጨረሰ ላቀረብነው ጥያቄ ኮሜቴው በሰጠን ምላሽ፣ የወጪውን መጠን እንዳልጠየቀ፣ ሆኖም በተማሪዎች መዋጭ ከተጀመረ በኋላ ህብረተሰቡ ተጨምሮበት ተውጣጥቶ የተሰራ እንደነበር ኮሚቴው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድቷል። 

ቲክቫህ ኢትዮጵያ 
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia