TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ⬆️በዛሬው ዕለት #ማዕከላዊ_እስር_ቤትን የጎበኙ የTIKVAH-ETHIOPIA የቤተሰብ አባላት ከላይ ያሉትን ፎቶዎች #አጋርተውናል!

እርሶስ ማዕከላዊን ጎብኝተው ነበር? ፎቶዎችን ያጋሩ!

ፎቶ©ABEBA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE በትምህርት ሚኒስቴር ስም እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰተኛ ነው!
5 በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸው ገፆች⬆️

ቴሌግራም፦

1. Walta TV -- ይህ የቴሌግራም ቻናል የዋልታ ቴሌቪዥን አይደለም። ዋልታ ሚዲያ እስካሁን በይፋ ያሳወቀው የቴሌግራም ቻናል የለም።

2. ትምህርት ሚኒስቴር --- የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርን ስም የሚጠቀመው ቻናል ሀሰተኛ ነው። ትምህርት ሚኒስቴር ቴሌግራም ቻናል የለውም።

3. NEAEA/የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ/ --- ኤጀንሲው ምንም አይነት የቴሌግራም ቻናል የለውም።

ፌስቡክ፦

1. አብን/የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ/--24,00 Like ያለው የፌስቡክ ገፅ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አይደለም። በዚህ ገፅ የመሰራጩ መረጃዎችም የአብን አይደሉም። ትክክለኛው የፌስቡክ ገፅ 153,422 like ያለው ነው።

2. OBN አማርኛ -- 20,236 ሺህ Like ያለው OBN አማርኛ በሚል የተከፈተው ገፅ #ሀሰተኛ ነው። የዋናው የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ 111 ሺህ Like ያለው ነው። ይህን የፌስቡክ ገፅ ተጠንቀቁት!

#Bonus

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ክቡር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በፌስቡክ #verify የተደረገ የፌስቡክ ገፅ አላቸው። ገፁ 97,017 Like ያለው ነው!

#TIKVAH_ETHIOPIA

በየዕለቱ 5 ሀሰተኛና በባለቤቶቻቸው እውቅና የሌላቸውን ገፆች እናቀርባለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

ዛሬ በተካሂደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ 95 በመቶ መግባባት ላይ መደረሱን ሊቀ አእላፍ ቀሲስ #በላይ_መኮንን ገለፁ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያ ተልኮ መመሪያ ዋና ኃላፊ መጋቤ ሰላም ቀሲስ #ሰለሞን_ቶልቻ በበኩላቸው፤ ውይይቱ በጥሩ መንፈስ መጠናቀቁን ገለፀው በነገው ዕለት መቋጫ እንደሚበጅለትና መግለጫ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ዛሬ ጠዋት መወያየታቸው ይታወቃል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Tikvah-eth
Tikvah-Eth 2
ደዋዮቹ እነማን ናቸው?

በተለያየ ሰው ስልክ ላይ እየደውሉ ከፋና ብሮድካስቲንግ ነው፤ እድለኛ ስለሆኑ ካርድ ይላኩልን የሚሉ አካላት እየበዙ መጥተዋል። እነዚህ አካላት ማንነታቸው #አይታወቅም። የሚደውሉትም በሞባይል መስመር ስልክ ነው። ስራቸውን በስልክ ነው የሚሰሩት በርካቶችን እያጭበረበረበሩ የሚገኙ አካላት ናቸው። በሚድሮክ ኢትዮጵያ ስም፣ በኢትዮ ቴሌኮም ስም፣ የማጭበርበር ስራ እየተሰራ ነው። ስልክ ከተደወለላቸው አካላት መካከል የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ይገኙበታል። ለመሆኑ ፋና ብሮድካስቲንግ ይህን ጉዳይ ያውቀዋል?? ሚድሮክ ኢትዮጵያ ያውቀዋል?? ኢትዮ ቴሌኮምስ?? ምን እየተሰራ ነው ያለው??

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ይሄ ስልክ +251 97 397 0261 የሚድሮክ ነው? የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው?? የኢትዮ ቴሌኮም ነው?? በዚህ ቁጥር እና በሌሎችም ነው እየደወሉ እስከ 800 ብር ድረስ ካርድ ለማስሞላት የሚሞክሩት። የሚመለከተው አካል ይህን ድርጊት በአስቸኳይ ያጣራ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬ በዚህ ቁጥር +251 97 397 0261 የተደወለለት የቻናላችን ቤተሰብ ይህን ብሏል፦

"እነዚህ ሰዎች ብዙ ሰው እያታለሉ ነው። መጀመሪያ ላይ እኔም አምኛቸው ነበር። በባህሪየ ተጠራጣሪ ነኝ ግን ለማሳመን የተጠቀሙበት መንገድ ከባድ ነው እንደሰማኸው በጣም ነው የሚያጣድፍህ ደቂቃዎች ብቻ ነው የሚሰጡህ። የገንዘብ ሽልማቱን በተመለከተ ለኔ እንኳን የጠቀሰልኝ ብር 42 ሺ ብር ነው። ይሄን ሰማ ነው መጠራጠር የጀመርኩት። እንደሚታወቀው ለበአል ሽልማት በአብዛኛው ሲዘጋጅ የበግ መግዣ ወይም ሌላ የቤት ቁሳቁስ እንጂ በዚህ ደረጃ የገንዘብ ሽልማት ሰምቼ አላውቅም። ብቻ ሁሉም ሰው ይወቀው። በተለይ ራንደምሊ ስለሚደውሉ ብዙ የገጠር አካባቢ ሰዎችን እንደሚያታልሉ መገመት ይቻላል። አመሰግናለሁ!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ📸ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ ከአውሮፓውያኑ የ2019 የሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት ማእከል ግንባታ አበርክተዋል።

የዛሬን ውሎ የተመለከተ ዘገባ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-06-5
TIKVAH-ETHIOPIA
የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ሰራተኞች ስራ አቁመዋል! ከቦነስ ይከፈለን ጥያቄ ጋር በተያያዘ የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ሰራተኞች በዛሬው ዕለት የስራ እንዳቆሙ እዛው የሚሰሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የምስራቅ ኢትዮዺያ ኢሰማኮ ዋና ሀላፊ እና የናሽናል ሲምንቶ ሊቀመንበርን በስልክ ለማግኘት ያደርግነው ጥረት ስልካቸው ባለመነሳቱ አልተሳካም። ኃላፊውን እንዳገኘናቸው ተጨማሪ…
የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ የዛሬ ውሎ!

የድሬደዋ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ሠራተኞች «ጥቅማ ጥቅም/ቦነስ» ያሉት ክፍያ እንዲሰጣቸዉ በመጠየቅ ዛሬ የሥራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን የቤተሰባችንን አባላት እንደነገሩን አይዘነጋም።

ማምሻውን DW አንድ ሰራተኛን አነጋግሮ ነበር፦

ከአድመኞቹ አንዱ ለDW እንደነገሩት ሠራተኛው ከዚህ ቀደም የሚያገኘዉ የማነቃቂያ ጉርሻ ወይም ቦነስ እንዲሰጠዉ ከረጅም ጊዜ በፊት ጥያቄ ቢያቀርብም የፋብሪካዉ ኃላፊዎች ተገቢዉን መልስ አልሰጡም ብለዋል። ሠራተኞቹ ዛሬ ጠዋት አድማ መምታታቸዉ እንደተሰማ የድሬዳዋ ፀጥታ አስከባሪዎች ወደ ፋብሪካዉ ቅጥር ግቢ መግባታቸዉን ሠራተኞቹ አስታዉቀዋል። ይሁንና ዛሬ ዉሎዉን ግጭትም ሆነ የፀጥታ መታጎል አልረፈጠረም። የDW ዘጋቢ የፋብሪካዉን ኃላፊዎች በስልክ ለማነጋገር ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ራድዮ ጣቢያው ገልጿል።

Via #DW

በድጋሚ በዚህ ጉዳይ ላይ የምስራቅ ኢትዮጵያ ኢሰማኮ ዋና ሀላፊ እና የናሽናል ሲምንቶ ሊቀመንበርን በስልክ ለማግኘት ያደርግነው ጥረት አልተሳካም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ቦርድ የ2011 ዓ/ም የሰራተኞች የበዓል ጉርሻ ክፍያ እንዲከፈል ውሳኔ አሳልፏል። #TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነገ ጳጉሜ 2 በስራ ገበታው ላይ ያልተገኘ ሰራተኛ ስራውን በገዛ ፈቃዱ እንደለቀቀ ተቆጥሮ ድርጅቱ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ገልጿል። #DIREDAWA

#ድሬዳዋ_ናሽናል_ሲሚንቶ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
አዳምጡ⬆️

ዛሬ በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምላዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ 95 በመቶ መግባባት ላይ መሰረደረሱን #ሁለቱም ወገኖች አስታውቀዋል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ ባልተቋጩ ጉዳዮች ነገ ጥዋት ይመክራል! ዝርዝር መግለጫም ይሰጣል!

Via VOA AMAHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለሚመለከተው አካል‼️ የአምና ወይም 2010 #የወርቅ_ሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች እስካሁን ስኮላርሺፕ እንዳላገኙ ለTIKVAH-ETHIOPIA በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። የወርቅ ሜዳሚያ ተሸላሚ ተመራቂዎቹ እንዳሉት፦ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ ቃል በገቡልን መሰረት ውጪ ሀገር scholarship እንደ ሚሰጠን በሁሉም የሚዲያ የተነገረ ነበር። ፕሬዘዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ በበኩላቸዉ የውጪ ሐገር…
የ2010 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች!

የ2010 የውርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች የውጭ የትምህርት እድል እንደምናገኝ ተገልፆ ህዝቡም ስምቶት የነበረ ቢሆንም ምንም የትምህርት እድል አላገኘንም አሁንም እዚሁ ነው ያለነው አንዳንዶች በስራ ፍለጋ፡ አንዳንዶችም ተቀጥረን እየሰራን ነው ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የሰጠው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል እና የዓምና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ይህን ብሏል፦

"መቅረቱ ምንም አይደለም ሄዶ የለፋው ተማሪ ፓስፖርት ብሎ ብዙ ነገር ብሎ፤ ያንን ፕሮሰስ ለመጨረስ ብሎ ከስራውም የተባረረ እና የተስተጓጎለ ሰው እንዳለ ነው የሰማሁት። ያንን ፕሮሰስ ለማድረግ በሌክቸርነት የተቀጠሩ 20 እና 30 ቀን አ/አ ተቀምጠው ብዙ ከተለፋ በኃላ #የለም ማለት ያሳዝናል። አዳንዶች የሚሰሩበትም ዩኒቨርሲቲ አላውቃችሁም ብሎ አባሯቸዋል። ሙሉ በሙሉ ስኮላርሺፕ ጠብቆም አልነበረም ሰዉ፤ ያው የፖለቲካ ጉዳይ ነው ብሎ ተማሪውም አስቦበት ነበር፤ ማለቅ ከነበረበት አምና ነው ማለቅ የነበረበት እንኳን 400 ተማሪ ሌላም መውሰድ ይቻላል። ተማሪውን ያሳዘነው መቅረቱ አይደለም መንከራተቱ ነው። ቢያንስ እውነተኛ መረጃ ሊሰጥ ይገባ ነበር። ተስፋ መስጠቱም ተገቢ አይደለም። ቀጣይም እንዲህ ያሉነገሮች መደረግ የለባቸውም።"

የነበረው ሁኔታ ያብራራላችሁ አካል አልነበረም?

"አንድም ይሄ ነገር ሆኗል ፣ እንደዚህ ነገር ሆኗል ያለን አካል የለም። ለትምህርት የተላከ የሄደ አንድም ሰው የለም። አዲስ አበባ ሄዶ ለተንገላታው ተማሪ መልስ የሰጠ የለም። አንድም የመንግስት አካል ያናገረን የለም።"

ይህ ጉዳይ እስካሁን ተዳፍኖ መቅረቱ እንዳሳዘናቸው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆኑ የ2010 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆኑ ተማሪዎች ተናግረዋል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአራዳ ልጅ ደም ይለግሳል!

በትዊተር የተሰባሰብን 100 የምንጠጋ ሰዎች ዛሬ ከጠዋት 4 ሰዓት ጀምሮ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ የደም መለገስ ፕሮግራም አሰናድተናል። ይህ ፕሮግራም የግሪን ሲቲስ (#ግሪንግ_አዲስ) የትዊተር እንቅስቃሴ አንዱ አካል ሲሆን ከወር በፊት በዚህ ግቢ ውስጥ 400 ችግኞች ተክለናል። አራዳነት ወይም ማወቅ ለሌሎችም መትረፍ ነው በሚል አላማ ነገ የመጀመርያ ዙር ደም ልገሳ ፕሮግራማችን ይካሄድል።

ሳሙኤል
ከግሪን ሲቲስ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ልገሳ!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ “ኑ በጋራ የልጆቻችንን ተስፋ ብሩህ እናድርግ” በሚል መሪህ ቃል ከነሃሴ 6 እስከ 10/2011 ዓ.ም. ባደረገዉ የልገሳ ሳምንት የተለገሰዉን የትምህርት ቁሳቁስ ለ13 ትምህርት ቤቶች በዛሬዉ እለት (ጳጉሜ 1/2011 ዓ.ም) አስረክቧል፡፡

በልገሳዉ ዝግጅት ላይ የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ የከተማ አስተዳደር አካላት፣ የከተማዉ ትምህርት ቢሮ፣ የ13 ትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች፣ የወላጅ ኮሚቴ አባላት እና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ለ1014 ተማሪዎች ለእያንዳንዱ 1ደርዘን ደብተር እና 10 እስክሪፐቶ በትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች በኩል የተለገሰ ሲሆን ለ300 ተማሪዎች ደግሞ ዩኒፎርም ማሰፊያ ተበርክቷል፡፡ በዚህ የልገሳ ሳምንት ከዩኒቨርሲቲዉ፣ ከዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ እና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ በገንዘብ ሲተመን ግማሽ ሚሊዮን እንደሚደርስ በዝግጅቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

የልገሳ ዝግጅቱን የከፈቱት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ፣ የለገሱትን እና ያስተባበሩትን አካላት አመስግነዉ፣ በቀጣይ ዩኒቨርሲቲዉ የበጎ አድራጎት ማዕከል በመክፈት የበጎ አድራጎት ስራን በተሳለጠ መልኩ እንደሚያካሂድ ገልጸዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የታደሙት አባገዳዎች፣ የከተማዉ ት/ት ቢሮ እና የትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች ለዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Via #JimmaUniversity

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጋምቤላ ሆስፒታል የተሰረቀች የአንድ ቀን ተኩል ዕድሜ ያላት ህፃን ከሁለት ቀናት ክትትል በኋላ ከነሙሉ ጤንነቷ ተገኘች። የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡቲያንግ ኡቻን እንደገለፁት በጋምቤላ ሆስፒታል ነሀሴ 28 ቀን 2011 ዓም አንዲት ህፃን በሰላም ወደ ዓለማችን ተቀላቅላለች።
ከምጥ ጋር ታግላ ጤናማ ህፃን በሰላም የተገላገለችው እናት ድካሙ አልለቀቃትም ነበርና በማግስቱ አገር አማን ነው ብላ ጨቅላዋን አጠገቧ እንዳስቀመጠች እንቅልፍ ሸለብ ያደርጋታል። ከእንቅልፏ ስትነሳ ግን የአንድ ቀን ተኩል እድሜ ያላት የአብራኳን ክፋይ እንዳስቀመጠቻት ከጎኗ የለችም። እናት በድንጋጤ ተውጣ የድረሱልኝ ጥሪ በማሰማቷ የሆስፒታሉ ማህበረሰብ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ስለ ጉዳዩ ማውረድ ማውጣት ይጀምራል። ዋነኛው መፍትሔ ሆኖ የተገኘው ግን ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቅ ነበር። የክልሉ ፖሊስም ነሀሴ 29 ቀን 2011 ዓም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ጠፋች የተባለችውን ጨቅላ ህፃን ለማግኘት ፍለጋውን ይጀምራል።

ይህን ተጭነው ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-07

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጋምቤላ የዓለም ሰብዓዊ አገልግሎት ተቋረጠ!

ሁሉም የሰብዓዊ ዕርዳታ ተቋማት በጋምቤላ ክልል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለጊዜው #ማቋረጣቸውን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ አስታወቁ፡፡ እዚሁ ውሳኔ ላይ የተደረሰውም በጋምቤላ ክልል በተፈፀመው ጥቃት ሁለት የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞች መገደላቸውን ተከትሎ፣ መሆኑን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ተጠባባቂ የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ ስቲቨን ዌር ኦማሞ ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia