TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለመከላከያ ሰራዊት አባላት እውቅና ተሰጠ!

በሶማልያ የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል (አሚሶም) ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ዕውቅና ሰጠ። እውቅናው የተሰጠው በአሚሶም ስር በሰላም ማስከበር ላይ የተሰማራው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት በግዳጅ ላይ ላሳዩት ቁርጠኝነት፣ ለከፈሉት መስዋዕትነት እና ሙያዊ ተጋድሎ መሆኑንም አሚሶም በድረ ገጹ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከትላንት በስቲያ ምሽት 1:30 የቤተሰባችን TIKVAH-ETH አንድ አባል የሆነ ሰው የሰንሻይን እና ኒውብሪጅ የስራ ፍቃድ እንዲሁም የኤች ቲ፣ ኦሲሚክስ፣ ሰንሻይን እና ኒውብሪጅ ማህተም ቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ተርሚናል 2 አካባቢ ጠፍቶበታል። እነዚህን ወሳኝ ሰነዶች ካገኛችሁ በዚህ ስልክ አሳውቁን 0911927941
#update ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ያለበትን 151 ሚሊዮን ብር እዳ ባለመክፈሉ ምክንያት የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎት አቋረጠ። ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የላብራቶሪ መመርመሪያና ሌሎች የህክምና ግብዓት የሚቀርቡለት የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ ነበር። ኤጀንሲው ከዚህ በፊት ለዚህ ሆስፒታል ያቀረበለትን ገንዘብ ባለመከፈሉ ምክንያት ግብዓት አላቀርብም በማለቱ ሆስፒታሉ ለጊዜው የላብራቶሪ ምርመራ አገልግሎትን እያካሄደ አይደለም። በዚህ ምክንያት ደግሞ ታካሚዎች ህክምና በላብራቶሪ ግብዓት እጥረት ምክንያት ለሳምንታት እየተንገላቱ መሆኑን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የቀድሞው ማዕከላዊ እስር ቤት ለጉብኝት ክፍት እንደሚደረግ ተገለጸ!

ጳጉሜን 5 ቀን 2011 ዓ.ም የሚከበረውን የፍትህ ቀን ምክንያት በማድረግ የቀድሞው ማዕከላዊ እስር ቤት ለጉብኝት ለህዝብ ክፍት እንደሚደረግ የበአሉ የኮሚዩኒኬሽን፣ሚድያና መድረክ ዝግጅት ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ዝናቡ ቱኑ ገለጹ፡፡

እስር ቤቱ ከዚህ ቀደም በዜጎች ላይ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ይፈጸምበት እንደነበር የሚታወስ ሆኖ ለውጡን ምክንያት በማድረግ መንግስት እንዲዘጋና ወደ ሙዚምነት እንዲቀር መወሰኑ ይታወቃል፡፡ በማእከላዊ እስር ቤት በፖለቲካ ነክ የህግ ተጠያቂ እስረኞች ላይ የማይሻር የስነ-ልቦና ቅጣት እስከ አካል ማጉደል የሚያደርስ የስቃይ ዘዴዎች ይፈጸሙ ነበር፡፡

በተጨማሪም በተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ ሂደት ሲከናወን በጨለማ ቤቶች ተዘግተው ከፍተኛ የሆነ ጫናና በደል ሲደርስባቸው አንዳንዶችም ህወታቸው ያልፍ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ሆኖ የእናቶች እንባ ከታበሰና የለውጡ ምህዳር ከሰፋ ጊዜ ጀምሮ እስር ቤቱ ዝግ ተደርጎ በዚህ ቦታ ላይ ይፈጸም የነበረው የተጠርጣሪዎች የሰብአዊ መብት ጥሰት ቆሟል፡፡

ኮሚቴው እንዳስታወቀው የፍትህ ቀንን ምክኒያት በማድረግ እስርቤቱ ለጉብኝት ከጳጉሜን 1 እስከ 4 ቀን 2011 ዓ.ም ለሁሉም ሰው ክፍት ሆኖ እንደሚቆይና በህብረተሰቡ ጉብኝት እንደሚደረግ በተጨማሪም በየፍትህ አካላት ማለትም በጠቅላይ ፍርድ ቤት፣በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን የተለያዩ የስዕል አውደ ርዕዮች እና በፍትህ ላይ የሚያጠነጥኑ የኤግዚቢሽን መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።

https://telegra.ph/ETH-09-03

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በቀጣዩ ምርጫ አንሳተፍም!

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በቅርቡ የፀደቀው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ አሁን ባለበት ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ በቀጣዩ ምርጫ የማይሳተፍ መሆኑን አስታውቋል።

ምክር ቤቱ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጸደቀው የምርጫ አዋጅ በአስቸኳይ ተመልሶ እንዲታይ ጠይቋል፡፡ ይህ አቋምም ከ107 ፓርቲዎች ከ75 በመቶ በላይ የሚሆኑትን ፓርቲዎች የጋራ አቋም የሚያካትት መሆኑ ተነግሯል፡፡

መንግስት አዋጁን በዚህ መልኩ ተግባራዊ ካደረገ የሚካሄደው ምርጫ ተዓማኒነት የሌለውና ሀገሪቷንም ወደ ችግር የሚዳርግ ይሆናል ብሏል ምክር ቤቱ፡፡ የጋራ ምክር ቤቱ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጁ ምርጫው ከመካሄዱ በፊት መልሶ እንዲታይ የጠየቀ ሲሆን፤ ጊዜው ካጠረም የምርጫ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቋል፡፡ እንደ ዋልታ ኢንፎ ዘገባ ጥያቄያቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጀምሮ እስከ ምርጫ ቦርድ ያሉ ተቋማትና ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው ምላሽ እንዲሰጡም ነው የጠየቁት።

Via waltainfo.com
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜዲስን መማር ለምትፈልጉ በሙሉ!

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ለ2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም መግቢያ መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
ማስፈንጠሪያው: https://197.156.83.153/admission/ መመዝገብ ትችላላችሁ።

Via https://www.facebook.com/sphmmc/
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሜዲስን ማመልከቻ መስፈርት!

ልዩ ትኩረት ከሚሹ ክልሎች እና ዞኖች፦ ጋምቤላ፣ ሶማሌ፣ አፋር፣ ቤኒሻንጉል፣ ደቡብ ኦሞ ዞን፣ ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ቦረና ዞን፣ ዋግምራ ዞን፦

•ለወንዶች 466 እና ከዚያ በላይ
•ለሴቶች 441 እና ከዚያ በላይ

ለአዲስ አበባ እና ሌሎች ክልሎች፦

•ለወንዶች 516 እና ከዚያ በላይ
•ለሴቶች 491 እና ከዚያ በላይ

ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ!

#ሼር #share
#ADDISABEBA

አንደኛው ሀገር አቀፍ የሆቴል እና ቱሪዝም ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ የኢፌዲሪ ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሆቴል እና መሰል አገልግሎት ሰጪ አሰሪዎች ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የአንደኛው የሀገር አቀፍ የሆቴል እና ቱሪዝም ኮንፍረንስ ዛሬ ሸራተን አዲስ ሲጀመር ተገኝተው መልዕክት ያስተላፉት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ደመቀ መኮንን መንግስት በጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ውስጥ የቱሪዝም ዘርፉ አንዱመሆኑን ተናግረው በተለይም የቱሪዝም ዘርፍ የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ችግሮችን ለመቅረፍ ትልቅ አቅም እንደሆነ መንግስት በፅኑ እንደሚምን ገልጸዋል፡፡

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምርጫ2012 -- የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ አሁን ባለበት ተግባራዊ የሚደረግ ከሆነ በቀጣዩ ምርጫ የማይሳተፍ መሆኑን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኬቨን ኃርት ባጋጠመው የመኪና አደጋ ጀርባው ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደረሰበት!

ኮሜዲያን እና ተዋናይ ኬቨን ኃርት በሎስ አንጀለስ ከተማ ባጋጠመው የመኪና አደጋ ጀርባው ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተነገረ። የኬቨን ባለቤት ኤኒኮ ፓሪሽ፤ ባለቤቷ መንቃቱን እና በሆስፒታል ህክምናውን እየተከታተለ እንደሚገኝ ለቲኤምዜድ የዜና ወኪል ተናግራለች።

ኬቨን ኃርት አደጋው ያጋጠመው ከ1970ው ሞዴል ፕለይማውዝ ባራኩዳ ጋር ተመሳስላ የተሠራችው ቅንጡ መኪናው ውስጥ ከሌሎች ሁለት ሰዎች ጋር ሲጓዝ ነበር። አደጋው የደረሰው ከእኩለ ለሊት በኋላ ሲሆን፤ መኪናዋን ሲያሽከረክር የነበረው ጃሬድ ብላክ መኪናውን መቆጣጠር ተስኖት መንገድ ዳር ከሚገኝ ግዑዝ ነገር ጋር መጋጨቱን ሪፖርቶች ጠቁመዋል።

አሽከርካሪው ጀርባው ላይ ከባድ ጉዳት እንዳጋጠመው የታወቀ ሲሆን፤ በመኪናው ውስጥ የነበረችው የጃሬድ ብላክ እጮኛ ሬቤካ ብሮክስተርማን ግን ያለ ምንም ጉዳት ከአደጋው መትረፏ ታውቋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን መደ ወላቡ ወረዳ አዲስ የዋሻ ቅርስ ተገኘ፡፡ ዋሻው በሊቂምሳ ቦኮሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ዋጫራ ሀይቅ በመባል በሚጠራ አካባቢ ነው የተገኝው፡፡

አዲስ የተገኘው ዋሻ “መነ ዋቃ (የእግዜር ቤት)” በመባል እንደሚታወቅ የመደ ወላቡ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ዋሻው 47 የመግቢያ በሮች እንዳሉት ጽ/ቤቱ ገልጿል፡፡

ዋሻው በድሮ ዘመን ሙዴ ገልቹ በተባሉ ሰው የአምልኮ ስርዓት ይፈፀምበት እንደበረም ከአካባቢው አዛውንቶች መረጃ መገኝቱ ታውቋል፡፡ ዋሻው “መነ ዋቃ (የእግዜር ቤት)” የሚል ስያሜ የተሰጠውም ከዚሁ ተነስቶ እንደሆነም ነው የአካባቢው አዛውንቶች የሚናገሩት።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በወሊሶና አሶሳ ከተሞች እንዲሁም በአገሎ ወረዳ ለሚገኙ ችግረኛ ተማሪዎች ግምታቸው ከ650 ሺህ ብር በላይ የሆኑ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ። በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የወሊሶ ከተማ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገው በከተማው ለሚገኙ 370 ችግረኛ ተማሪዎች ነው። ለተማሪዎቹ የተበረከተው ድጋፍ ከ300 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው መሆኑንም ጠቁመዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሮፖዛል ማቅረብ ትችላላችሁ!

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በሀገሪቱ ያለውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግ በሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ የልማት ድርጅቶች ፕሮፖዛሎቻቸውን እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።

የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ “በቀን አንድ ብር ለወገን ክብር ” በሚል መርህ በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ዳያስፖራዎች ያዋጡትን 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በአስከፊ ድህነት ውስጥ ያሉ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የሚያስችሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ለመተግበር ያስችል ዘንድ የመጀመሪያ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል
ጥሪ ይፋ አድርጓል።

ስለሆነም ህጋዊ እውቅና ያላቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ሀገር በቀል የልማት ድርጅቶች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት፣የፌዴራልና የክልል ተቋማት እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ድርጅቶች የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎቻቸውን በማቅረብ የገንዘብ ድጋፍ መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል።

ድርጅቶች የሚያቀርቡት የፕሮጀክት ፕሮፖዛልም በኢትዮጵያ ያለውን የትምህርት ጥራት፣የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ፣የንፁህ ውሃ አቅርቦትና ንጽህ አጠባበቅ እንዲሁም የግብርና ምርትን ማሻሻል የሚያስችል መሆን አለበት ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም የአካል ጉዳተኞችን አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ፣ምርታማነትን ማሻሻል የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ፣ለወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕል ፈጠራ፣የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም የሚያስችሉ ፕሮጀክቶች ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑ ተመላክቷል።

ዝርዝር መረጃውን ለማግኘት ፦https://www.ethiopiatrustfund.org/call-for-project-proposa…/
#update በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጡሎ ወረዳ ሂርና ከተማ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን በመጠቀም ለመገበያየት ሞክሯል የተባለው ግለሰብ አንድ ዓመት ከስድስት ወር በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።

አብረሀም ገብረ መድን ተንሳይ የተባለው ይሄው ግለሰብ ነሐሴ 20/2011ዓ.ም በሂርና ከተማ 15 ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖቶች በመያዝ  ለመገበያየት ሲሞክር እጅ ከፍንጅ ተደርሶበታል።

የጡሎ ወረዳ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል እና ቁጥጥር የስራ ሂደት መሪ ሳጅን በላይ አስራት ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቡ የአካባቢው ህብረተሰብ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ሊይዝ ችሏል።

በተጠርጣሪነት ተይዞ የቆየው ግለሰቡ በአቃቢ ህግ ከሳሽነት ጉዳዩን ሲከታተለው የነበረው የወረዳው የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነሐሴ 27/2011ዓ.ም  በዋለው ችሎት ጥፋተኝነቱን አረጋግጦ የቅጣት ውሳኔውን አስተላልፎበታል። ህብረተሰቡ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ለፖሊስ በመጠቆም እያደረገ ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል ሳጅን በላይ አሳስበዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FAKE የ2012 ዓ/ም የተማሪዎች ቅበላ ቀናት በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ የሚገኘው ይህ መረጀ ሀሰተኛ ነው።

💫እንደ TIKVAH-ETH የሚደርሱንን የጥሪ ቀናት እናቀርባለን!! የሚመለከታችሁ የዩኒቨርሲቲ ክፍሎች እና የተማሪ ህብረቶች ጥሪዎቻችሁን @tsegabwolde ማድረስ እንደምትችሉ በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ እንወዳለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመግቢያ ቀናት ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች!

©#Habtish
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአፍሪካ ህብረት በደቡብ አፍሪካ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት አወገዘ፡፡ የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ የሌላ ሀገራት ዜጎች ላይ እየተወሰደ ያለውን የሀይል እርምጃ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው ሲሉ አውግዘዋል።

የዜጎችን ንብረት መዝረፍም ሆነ የማጥፋት አካሄድ በህብረቱ የሚወገዝ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ሊቀ-መንበሩ እንደተናገሩት ቀደም ሲል በታሰሩት የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንዲህ አይነቱ ተግባር ይበረታታ እንደነበር ገልፀዋል፡፡

የሰዎችን ሕይወትና ንብረት ለመጠበቅ ተጨማሪ አፋጣኝ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው ያሉት ሊቀመንበሩ የደቡብ አፍሪካ መንግስት ወንጀለኞች ለፈፀሙት ድርጊት ተጠያቂ መሆናቸውን እንዲያረጋግጭ አሳስበዋል። እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ሌሎች ተጨማሪ ውድመት ላጋጠማቸው ሰዎች ትክክለኛ ፍትህ መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡

የህብረቱ ሊቀ-መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት እነዚህን ወንጀለኞች ለመያዝ በሚደረገው ጥረት ህብረቱ ለደቡብ አፍሪካ መንግስት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

Via #EthioFM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሁለት ዜጎቻችን ደ/አፍሪካ ውስጥ ሞቱ!

በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ንብረታቸውን ከዘራፊዎች ለማትረፍ በመሸሽ ላይ እያሉ ባጋጠማቸው የመኪና አደጋ መሞታቸው ተነግሯል። ኢትዮጵያዊያኑ የመኪና አደጋው የገጠማቸው ደቡብ አፍሪካ ዋና ከተማ ጆሃንስበርግ አቅራብያ በሚትገኝ ጁሊየስ የምትባል መንደር ውስጥ ወደሚገኝ ንብረታቸው እየነዱ በነበሩበት ወቅት መሆኑ ታውቋል።

ኢትዮጵያዊያኑ ወደ ሱቆቻቸው ለመሄድ የተነሱት የአካባቢው ነዋሪዎች የስደተኞች ሱቆችን እየዘረፉ ነበር በተባለበት ወቅት እንደነበረ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ ምክትል ሰብሳቢ ናህሊ ሙሳ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አደንዛዥ ዕፅ ሲያዘዋውሩ የነበሩ 4 ግለሰቦች በፖሊስ ተያዙ!

በኢሉአባቦር ዞን የአሌ ወረዳ ፖሊስ ዘጠኝ ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ ዕፅ ሲያጓጉዙ ደርሼባቸዋል ያላቸውን አራት ግለሰቦች መያዙን አስታወቀ። ግለሰቦቹ አደንዛዥ ዕጹን በተሽከርካሪ ጭነው ከአዲስ አበባ ወደ ጋምቤላ በማጓጓዝ ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነው ትናንት ከረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ የተያዙት።

የወረዳው ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ተወካይ ሳጅን ኦላና መንግስቱ እንደገለጹት ግለሰቦቹ እስከ ጎሬ ከተማ ከመጡበት ተሽከርካሪ በመውረድ የፍተሻ ኬላ በእግራቸው ለማቋረጥ ሲሞክሩ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መያዝ ተችሏል። በአሁኑ ወቅት በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ያመለከቱት ሳጅን ኦላና በእጃቸው የተያዘው አደንዛዥ ዕፅም ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ እንደሚላክ አስታውቀዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia