የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለ10 ቀናት ሥራ ማቆሙ ተገለጸ!
የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክ ባጋጠመው የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት አስር ቀናት ያህል ሥራ የተቋረጠ ሲሆን አንድ ድርጅት የጄነሬተር ኃይል በመጠቀም ሥራውን በማከናወን ላይ ይገኛል።
የፓርኩ የቴክኒክ ክፍል ኃላፊ መሐመድ ሃጂ ለአዲስ ማለዳ ጋዜጣ እንደገለጹት፣ ፓርኩ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገኘው ከአዋሽ መልካሳ የኃይል ማመንጫ ሲሆን፣ ለፓርኩ ኃይል የሚያቀብለው ትራንስፎርመር በመቃጠሉ ምክንያት ሥራቸው መስተጓጎሉን ተናግረዋል። ባሳለፍነው ሰኞ ነሐሴ 20/2011 አዲስ ትራንስፎርመር ተገዝቶ ወደ አዋሽ መልካሳ መላኩን የነገሩን መሐመድ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ጥገናው ተጠናቆ የኃይሉ ችግር እንደሚቀረፍ ተናግረዋል።
በኃይል መቆራረጥ ምክንያት ለችግር የተጋለጠው የአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ብቻ አለመሆኑን በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ መኮንን ኃይሉ ገልጸዋል። ብዙዎቹ ፓርኮች ሥራቸውን ባቀዱት መጠን እንዳይሠሩ የኃይል መቆራረጡ እቅፋት እንደሆነባቸውም ኃላፊው ተናግረዋል።
#AddisMaleda
https://telegra.ph/ETH-09-02

ከበዓል በፊት ደሞዛችን ይከፈለን!
ከአደረጃጀት ጋር በተያያዘ የኛ #የዶክተሮች ክፍያ አልተፈፀመም ሲሉ በቀድሞው የሰገን አካባቢ ህዝቦች ዞን "ሰገን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል" የሚሰሩ ዶክተሮች ቅሬታ አቅርበዋል። የህክምና ባለሞያዎች ለሰሩበት እና ላገለገሉበት ክፍያ ካልተፈፀመላቸው ለምን መጥተው ያገለግላሉ ሲሉም ይጠይቃሉ? ከአደረጃጀት ጋር በሚያያዙ ጥያቄዎች የኛ ለሁለት ወር የደሞዝ አለመከፈል እጅጉን ቅሬታ ፈጥሮብናል፤ ይህ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ጤና መግባት የለበትም ያሉት ዶክተሮቹ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ከላይ ያሉት አመራሮች ትኩረት ሰጥተውበት እንዲሰሩ ጠይቀዋል አዲሱ ዐመት ከመግባቱም በፊት ተገቢው ክፍያ እንዲከፈላቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ተጨማሪ...
የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ የሆኑት ዶክተሮቹ በአሁን ሰዓት የሚገኙት በጉማይደ/ሰገን/ ከተማ ሲሆን አከባቢው #በወታደር ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ገልፀዋል።
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ኢዜማ በደሴ ከተማ ውይይት አደረገ!
ለኢትዮጰያ ጠንካራ አንድነት፣ሰላምና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበት አበክሮ እንደሚሰራ የኢትዮጰያ ዜጎች ማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ገለፀ ። ኢዜማ ከደሴና አካባቢዋ ነዋሪዎች ጋር በለውጡና በቀጣይ የሰራ እቅዶቹ ዙሪያ ትናንት መክሯል፡፡
የኢዜማ ምክትል መሪ አቶ አንዷለም አራጌ በምክክር መድረኩ ላይ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ህዝብ በጋራ የአገሩን ዳር ድንበር አስከብሮ፣ ተከባብሮና ተቻችሉ ክፉ ደጉን አሳልፏል፡፡ ይህን ከአባቶች የተገኘውን የረጅም ዘመን አንድነት፣ ሰላምና የመቻቻል ባህልና እሴት ለማጎልበት ኢዜማ አበክሮ እንደሚሰራ ገልፀዋል።
ኢትዮጵያ አሁን ከተደቀነባት አደጋ ለማውጣት በየደረጃው ጠንካራ መሪና ህዝብ ያስፈልጋታል ያሉት አቶ አንዷለም ከዚህ ችግር እንድትወጣ ከመንግስትና ከሌሎች ተፎካካሪ ፓሪቲዎች ጋር ተቀናጅተን እንሰራለን ብለዋል፡፡ እንደ አቶ አንዷለም ገለጻ ከማንኛዉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በፊት አገር፣አንድነትና ሰላም መቅደም እንዳለበትም አብራርተዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-02-2

እንኳን ደህና መጣችሁ!
በሞሮኮ አስናጋጅነት በተካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ13 የስፖርት አይነቶች የተሳተፈው የኢትዮጵያ የስፖርት ልኡካን ትናንት ሌሊት አዲስ አበባ ገብቷል።

#አዲስ_አበባ
በሞሮኮ አስናጋጅነት በተካሄደው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች በ13 የስፖርት አይነቶች የተሳተፈው የኢትዮጵያ የስፖርት ልኡካን ትናንት ሌሊት አዲስ አበባ የገባ ሲሆን በአዲስ አበባ ስታዲየም ይፋዊ አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል፡፡
በአቀባበል ስነ-ስርአቱ ላይ የኢትዮጵያ ስፖር ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እና ከኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን የተውጣጡ አካላት ተሳታፊ ናቸው፡፡
የስፖርት ልኡካን ቡድኑ አዲስ አበባ የገባበት ሰአት ለአቀባበል ምቹ ስላልነበረ የአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ለዛሬ መተላለፉ ተገልጿል፡፡ 250 አባላትን የያዘው የስፖርት ልኡካን ቡድኑ በሞሮው መድረክ 6 የወርቅ፣ 5 የብር እና 12 የነሃስ ሜዳሊያዎች በማስመዝብ ከአፍሪካ 9ኛ ደረጃ ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡
Via ኢቢሲ

ዶ/ር አብይ🛬አዲስ አበባ!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የውጭ ሃገራት ጉብኝታቸውን አጠናቀው አዲስ አበባ ገቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን እና እስራኤል ይፋዊ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

የድቬንቱስ ሰራተኞች የ3 ወር ደሞዝ አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል!
"ሰላም ጤና ይስጥልኝ! የdVentus Technologies (www.dventus.com) ሰራተኛ ነኝ፤ ደሞዝ በፈረንጆቹ በ27 ነበር ሚገባልን 3 ወር ሙሉ ሳይከፈለን ይኸው ዛሬ የአራተኛው ወር 6 ቀን ሆኖታል። የድርጅቱ ሼር ሆልደሮች አቶ ዳንኤል ግዛው እና ጥረት ኮርፖሬሽን ሲሆኑ፣ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ እና ትልቁን ሼር የያዘው አቶ ዳንኤል ግዛው ማረሚያ ቤት ይገኛል። ሌሎች ይመለከታቸዋል ያልናቸውን የድርጅቱ አመራሮች ብንጠይቅም መፍትሔ ሚሰጠን አጣን። ወዴት አቤት እንበል?"
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሰላም ጤና ይስጥልኝ! የdVentus Technologies (www.dventus.com) ሰራተኛ ነኝ፤ ደሞዝ በፈረንጆቹ በ27 ነበር ሚገባልን 3 ወር ሙሉ ሳይከፈለን ይኸው ዛሬ የአራተኛው ወር 6 ቀን ሆኖታል። የድርጅቱ ሼር ሆልደሮች አቶ ዳንኤል ግዛው እና ጥረት ኮርፖሬሽን ሲሆኑ፣ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ እና ትልቁን ሼር የያዘው አቶ ዳንኤል ግዛው ማረሚያ ቤት ይገኛል። ሌሎች ይመለከታቸዋል ያልናቸውን የድርጅቱ አመራሮች ብንጠይቅም መፍትሔ ሚሰጠን አጣን። ወዴት አቤት እንበል?"
#TIKVAH_ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ
"በትላንትናው ዕለት የአምባ ፋርማሲዩቲካልና አኳርየስ አቪየሽን በመተባበር ለ2ኛ ጊዜ በቢሾፍቱ ሀይቅ ዳርቻ ከአካባቢው ሕብረተሰብ ጋር ዝናቡ ሳያመልጠን ችግኞች ስንተክል፤ የዛሬ ወር ገደማ የተከልናቸውንም ስንንከባከብ ዉለናል።"

በየመን በሶስት ዓመታት ብቻ ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል!
በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ኃይል በየመን በፈጸመው የአየር ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቀ።
ቀይ መስቀል እንዳለው ከሆነ በተደጋጋሚ በተፈጸመው የአየር ጥቃት የተገደሉት በእስር ቤት ውስጥ ታጉረው የነበሩ ሰዎች ናቸው።
ከአየር ጥቃቱ በህይወት መትረፍ የቻሉ 40 ሰዎች ህክምና እየተደረገላቸው በመሆኑም ተነግሯል። የአየር ጥቃቱ ቢያንስ ስድስት ጊዜ መፈጸሙን ከአየር ጥቃቱ የተረፉት እና በአከባቢው የሚኖሩ ሰዎች ተናግረዋል።
#BBC
ተጨማሪ👇
https://telegra.ph/ETH-09-02-3

#update ቱርክ ለዓለም ገበያ ምታቀርባቸውን ምርቶች በተመረጡ 17 አገራት ላይ በአምስት ዘርፍ የምትልካቸውን ምርቶች እጥፍ ለማድረግ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች ይፋ አድርጋለች። ከተመረጡት አገራት ኢትዮጵያ አንዷ ስትሆን ከአፍሪካ ውስጥ ደቡብ አፍሪካን እና ኬንያን ጨምሮ ሦስት አገራት መሆናቸው ታውቋል።
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዳቦ ቤቶች የ1 ብር ከ30 ሳንቲም ዳቦን በ3 ብር፤ የ550 ብር ስንዴን በ2 ሺህ ብር በህገወጥ መንገድ እስከ መሸጥ መድረሳቸው ተነገረ!
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከንግዱ ማህበራት ጋር እያካሄደው ባለው የውይይት መድረክ ላይ በከተማዋ ያሉ ዳቦ ቤቶች በህገወጥ መንገድ የ1 ብር ከ30 ሳንቲም ዳቦን በ3 ብር፤ የ550 ብር ስንዴን በ2 ሺህ ብር በመሸጥ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ ለውይይት በወቀረበው ሰነድ ላይ እንደተገለፀው መንግስት ለህዝብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርቡ ሲል የአንድ ዳቦ ዋጋ በ1 ብር 30 ሳንቲም ተምኖ ለዚህ የሚውል ስንዴን በድጎማ በ550 ብር እያቀረበ ይገኛል፡፡
ሆኖም ዳቦ ቤቶች ስንዴውን ገበያ በማውጣትና ‘ልዩ ስንዴ’ በማለት በ2 ሺህ ብር እየሸጡ 1 ብር 30 ሳንቲም የነበረ የዳቦ ዋጋ 3 ብር ድረስ ሲሸጥ እንደተደረሰበት በሰነዱ ላይ ቀርቧል፡፡
ከዚህ ባለፈ ዳቦ ቤቶች የተፈቀደላቸው ዳቦ እንዲያቀርቡ ቢሆንም ኩኪስ፣ዶናት፣ ኬክና መሰል ምርቶችን በድጎማው ስንዴ አምርተው በመሸጥ ላይ እንደሚገኙም በመድረኩ ላይ ተገልጿል፡፡
በዚህ መሰረት ቁጥጥር ሲደረግ በተቀመጠላቸው ዋጋ መሰረት ሲሰሩ የነበሩ ዳቦ ቤቶች አርበኞች፤ ሮዛ፤አፍሪካ እና ምስራቅ ዳቦ ቤቶች ብቻ መሆናቸውም ተያይዞ ተገልጿል፡፡
Via #EPA

#update ከሰኔ 15 የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጋር በተያያዘ የብ/ጀ አሳምነው ፅጌ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ ደስታ አሰፋ እና ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በተጠረጠሩበት የሽብር ወንጀል መዝገብ ችሎቱ ተጨማሪ 28 ቀን ለፖሊስ ምርመራ ፈቅዷል፡፡
ዛሬ ፖሊስ በዚህ መዝገብ የተካተቱ 7 ተጠርጣሪዎችን ከዚህ በፊት ጠርጥሪያለው ብሎ ከነበረበት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተሳትፎ ባለፈ በቤንሻንጉል መተከል ከተፈጠረው ግድያ ጋር በተያያዘም እጃቸው እንዳለበት ጠርጥሪያለው ሲል ለችሎቱ አስረድቷል።
የብ/ጀ አሳምነው ፅጌ ሚስት የታሰሩት የእሱ ሚስት በመሆናቸው ብቻ መሆኑን ጠበቃቸው ለችሎቱ ያስረዱ ቢሆንም ፖሊስ ከመኖርያ ቤታቸው ያገኘው 60 ጥይት እንዳገኘ በመግለፅ ለምርመራ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሏል።
ጠበቃቸው ግን ሟች መንግስት ያስታጠቃቸውን መሳሪያ በመኖሪያ ቤታቸው ማስቀመጣቸው ባለቤታቸውን ከመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ ጋር ያገናኛቸዋል ማለት አይደለም ሲሉ ተቃውመዋል።
Via ሳምራዊት

አሳዛኝ ዜና!
በትግራይ ክልል ላዕላይ ማይጨው ወረዳ ዱራ በተባለው አከባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ሕይወት አለፈ። በትራፊክ አደጋው ሕይወታቸው ካለፈው ሶስት ሰዎች በተጨማሪ ስምንት ሰዎች ላይም ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ነው የተገለጸው።
አደጋው ከሽረ ወደ መቐለ ከተማ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ሃይሩፍ ተሸከርካሪ ከሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ መሆኑን የላዕላይ ማይጨው ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። አደጋው ከሚጠበቀው ፍጥነት በላይ በማሽከርከር የተከሰተ እንደሆነም የፖሊስ መረጃ ያመላክታል።
አሽካርካሪዎች ከዚህ አደጋ ትምህርት በመውሰድ ፍጥነት በመቀነስ በሰው ህይወት እና ንብራት ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንዲቀነሱ የላዕላይ ማይጨው ወረዳ ትራፊክ ፖሊስ ጽህፈት ቤት መልዕክቱን አስተላልፏል።
Via #FBC

በቺክቭ የተጠቁ ሰዎች 20 ሺህ ደርሷል!
በድሬዳዋ በችኩንጉኒያ ወረርሽኝ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ወደ 20 ሺህ ማሻቀቡ ተገለጸ፡፡ ችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ኤደስ በምትባል ትንኝ ንክሻ ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን ችኩንጉኒያ በሚባል ቫይረስ የሚመጣ ህመም ነው፡፡
የችኩንጉኒያ ወረርሽኝ ከሀምሌ ወር ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ የተከሰቱ ሲሆን የተጠቂዎች ቁጥር ባሳለፍነው ሳምንት ከደረሰበት 15 ሺህ አሁን ላይ ወደ 20 ሺህ ከፍ ማለቱን የኢትዮጵያ ህብረትሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡ በወረሽኙ እስከ አሁን ድረስ የሞተ ሰው አለመኖሩንም ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።
እስካሁን በተደረገ የቤት ለቤት አሰሳ 86 በመቶ የሚሆኑት ቤቶች ወረርሽኙን የሚያስተላልፈው ትንኝ እጭ እንደተገኝባቸው ኢንስቲትዩቱ አስታውቃል፡፡ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከድሬዳዋ አስተዳደር፣ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች የተውጣጣ ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን በቦታው በመገኘት የተቀናጀ ምላሽ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ነው የተገለጸው፡፡
ወረርሽኙን ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር በከንቲባ ፅ/ቤት የሚመራ ግብረሃል ተቋቁሞ በቅንጅት እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህም ዉስጥ የቤት ለቤት ርጭት፣ የቅኝት እና አሰሳ ስራዎች፣ የማህበረሰብ ንቅናቄ፣ የህክምና አገልግሎት በሁሉም ጤና ተቋማቶች እየተከናወኑ እንደሆነ ተገልጿል።
Via #EthioFM

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ቺኩንጉንያ ቫይረስ ምንድነው? ቺኩንጉንያ ቫይረስ (ቺክቭ) በትንኞች አማካኝነት ወደ ሰዎች ይተላለፋል። ቺክቭ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳትና ድንገት የሚከሰት የመገጣጠሚያ ህምምን ያስከትላል። ቺክቭ አብዛኛው ጊዜ ሞትን አያስከትልም፣ ነገር ግን የሚወልዳቸው የጤና እክሎች ነገሮችን ከመስራት እስከማገድ የሚደርሱ ሆነው በተወሰኑ ሰዎች ላይ ደግሞ ለከባድ ተጨማሪ በሽታ ሊዳርጉ ይችላሉ። ቫይረሱን እና ኢንፈክሽኑ የምንከላከልባቸው መንገዶችን የተመለከተ እውቀት መጨበጥ ወሳኝ ነው። የሚወስዷቸው ጥንቃቄዎች ከሌሎች በትንኞች የሚመጡ በሽታዎችም ይከላከልልዎታል።
#DCSSH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DCSSH
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
የቺክቭ ምልክቶች ምንድናቸው? አንድ ሰው በተለከፈ ትንኝ ከተነከሰ በኋላ ከ 3 እስከ 7 ቀናቶች ውስጥ ምልክቶች ይታዩበታል። የቺክቭ ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው የሚለያዩ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦
በድንገት የሚከሰት ከፍተኛ ትኩሳት (>102°F)
ከባድ የሆነ የመገጣጠሚያ ህመም በተለይ በክንዶች ወይም እግሮች ላይ
ራስ ምታት
የጡንቻ ህመም
የጀርባ ህመም
ሽፍታ (~50% ተጠቂዎች ላይ የሚያጋጥም)
በብዛት በሚከተሉት ሰዎች ላይ ይስተዋላሉ፦
ህጻናት (<1 ዓመት)
አረጋውያን (>65 ዓመት)
እንደ ስኳር በሽታ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ወዘተ በመሳሰሉ ስር የሰደዱ በሽታዎች የተጠቁ ሰዎች።
*ከላይ የተጠቀሱት ሰዎች በትንኝ እንዳይነከሱ ከሌሎች የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል።*
ቺክቭ እንዴት ነው የሚታከመው? ቺክቭ ለማከም የሚውል ተለይቶ የታወቀ መድሀኒትም ይሁን ክትባት #የለም።
#DCSSH
#share #ሼር

በቺክቭ ተጠቂቻለሁ የሚል ጥርጣሬ ካደረብኝ ምን ማድረግ አለብኝ? ትኩሳት እና የመገጣጠሚያ ህመም ለመቀነስ መድሀኒቶችን መጠቀም ጥቅም ሊኖረው ይችላል። ሐኪም ያማክሩ።
ቺክቭ ይዞኝ ሉሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ካደረብዎ፦
የታይብዎ ምልክቶችን መዝግበው በመያዝ ወደ ሐኪም ይሂዱ።
ራስዎን ተጨማሪ በትንኝ ከመነከስ ይከላከሉ።
በቺክቭ ከተያዙ በሽታው ወደ ሌሎች ሰዎች ላለማስተላለፍ እራስዎን ከትንኝ ንክሻ መከላከል ይኖርብዎታል።
ምን ማድረግ አለብኝ?
#ይልበሱ
ረዥም፣ ቀለል ያለ እና ቀላል ቀለም ያለው ልብስ ይልበሱ።
#ፈሳሽ_ማድረቅ
እቤት ውስጥም ከቤት ውጪም ያለ ማንኛውም ያቆረ ውሃ ያስወግዱ።
#ማታ እና #ጠዋት
ማታና ጠዋት ትንኞች በብዛት የሚንቀሳቅሱበት ጊዜ በመሆኑ በተቻለ መጠን ከቤት አይውጡ።
#DCSSH
#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቺክቭ ይዞኝ ሉሆን ይችላል የሚል ጥርጣሬ ካደረብዎ፦
የታይብዎ ምልክቶችን መዝግበው በመያዝ ወደ ሐኪም ይሂዱ።
ራስዎን ተጨማሪ በትንኝ ከመነከስ ይከላከሉ።
በቺክቭ ከተያዙ በሽታው ወደ ሌሎች ሰዎች ላለማስተላለፍ እራስዎን ከትንኝ ንክሻ መከላከል ይኖርብዎታል።
ምን ማድረግ አለብኝ?
#ይልበሱ
ረዥም፣ ቀለል ያለ እና ቀላል ቀለም ያለው ልብስ ይልበሱ።
#ፈሳሽ_ማድረቅ
እቤት ውስጥም ከቤት ውጪም ያለ ማንኛውም ያቆረ ውሃ ያስወግዱ።
#ማታ እና #ጠዋት
ማታና ጠዋት ትንኞች በብዛት የሚንቀሳቅሱበት ጊዜ በመሆኑ በተቻለ መጠን ከቤት አይውጡ።
#DCSSH
#share #ሼር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ስለ ፓልም ዘይት በሚዲያ የተሰራጨው መረጃ ተገቢ አይደለም ተባለ!
የፓልም ዘይት በህብረተሰቡ ላይ ጤና ላይ ጉዳት ያመጣል በሚል በሚዲያዎች የተሰራጨው መረጃ ተገቢ ያልሆነና በህዝቡ ዘንድ ውዥንብር እየፈጠረ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከንግዱ ማህበራት ጋር እያካሄደው ባለው የውይይት መድረክ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄር እንደተናገሩት የፓልም ዘይት በተገቢው ደረጃ እየተፈተሸ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገባ የሚደረግ፤ ህብረተሰቡም እንደ ልቡ ገዝቶ እንዲጠቀም የሚደረግ ነው ብለዋል፡፡
ሚኒስተሯ እንዳሉት ዘይቱ ወደ ሀገር ውስጥ ሲገባ ተገቢው ቁጥጥር ስለሚደረግበት እንደተባለው በሰው ላይ ጉዳት አያደርስም፡፡ እንደ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገለፃ የትኛውም ዘይት እኩል ደረጃ የለውም፤እኩል ለጤናም ጠቃሚም አይደለም፡፡
የፓልም ዘይትም የራሱ ደረጃዎች ያሉትና ህብረተሰቡም እንደ አቅሙ ገዝቶ ሊጠቀመው የሚችል ነው፡፡በመሆኑም የተሰራጨው መረጃ ተገቢ ያልሆነና ህብረተሰቡን ውዥንብር ውስጥ የከተተና ወደ አላስፈላጊ ነገር ውስጥ የሚያስገባም ነው ሲሉ ሚኒስትሯ ተናግረዋል፡፡
ምንጭ፦ ኢፕድ

የኮሌራ በሽታ በሶስት ክልሎች ላይ በድጋሚ ተከስቷል ተባለ!
በሀገሪቱ ተከስቶ የነበረውን የኮሌራ ወረርሽኝ በአብዛኛው ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የተቻለ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት በሶስት ክልሎች ላይ በሽታው ተከስቷል ተባለ፡፡ በአሁን ወቅት ወረርሽኙ በኦሮሚያ ክልል በሻሸመኔ ወረዳ 15 ሰዎች በፈዲስ ወረዳ 20 ሰዎች፣ ሀረሪ ክልል በ6 ወረዳዎች 15 ሰዎች ተይዘዋል ተብሏል።
እንዲሁም በደቡብ ክልል በሃዋሳ ከተማ 14 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተገልጿል። በወረርሽኙ የተያዙ ሰዎች የህክምና አገልግሎት እያገኙ እንደሆነ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ከወራት በፊት በተከሰተው የኮሌራ ወረርሽኝ 19 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። የበሽታው ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ የቀነሰ ቢሆንም ማህበረሰቡ በዚህ ሳይዘናጋ አሁንም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አስጠንቅቋል፡፡
ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም

በፋሲል ከነማ ደጋፊዎች እና በነቂያ የበጎ አድራጎት ማህበር ትብብር የተዘጋጀት የበጎት ዘመቻ እየተካሄደ ይገኛል። "ህፃናት ይማሩ፤ ሀገር ይረከቡ!" በሚል መሪቃል በዛሬው ዕለት 40 ደርዘን ደብተር ለህፃናት አበርክተዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia